The Pentateuch Exodus

The Passover

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 12-13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 34 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ማለፍ (ፋሲካ) የግብፃዊያን የበኩር ልጅ መሞት ነበር ነገር ግን እግዚአብሄር በእስራኤላዊያን ላይ አለፈ ፡፡ ሙሴና አሮን እግዚአብሄር ነፃ ያወጣቸውን ህዝቦች ረዱ በመጨረሻ ወደ ነፃ አውጪው መሲሁ አመለከቱን ፡፡ እግዚአብሄ ያመጣቸው አስር መቅሰፍት ; 1) ውህውን ወደ ደም ቀየረው; 2) እንቁራሪቶች ; 3) ትንኞች; 4) የከብቶች መሞት; 5) ቁስል; 6) በረዶ; 7) አንበጣ; 8) ጨለማ; 9) የበኩር ልጅ መሞት ፡፡ ዘጸዓት 12 የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ለፋሲካ እና የበኩር ልጅ ሞት ተመዝግባል ፤ በፈርዖን ልብ መፅናት ምክንያት እግዚአብሄር ስሙ እንዲታወቅ አደረገ (ሮሜ 9፡17)፡፡

ትምህርት

ዘጸዓት(12፡ 1-2); እግዚአብሄር ለሙሴና ለአሮን አድስ የቀን መቁጠሪያ ለአስራኤላዊያን ባለፈበት ወራት በመጋቢት ወይም በግንቦት ጊዜ መዋቅር ውስጥ የሚጀመር እንዲመሰርቱ አዘዛቸው ፡፡ ይህ ወር አቢብ ተብሎ ይጠራል ትርጉሙም “ የጆሮ ወር” ፍሬ(ጥሬ) በጆሮ ነበር ማለት የመሰብሰቢያ ጊዜ ነበር ማለት ፡፡ የባቢሎናዊያን ምርኮኝነት መጨረሻ ላይ ይህ ወር ኒሳን ተብሎ እንደገና ተጠራ (ናሆ 2፡ 1; አስ 3፡ 7) ፡፡ ዛሬ እስራኤላዊያን የሚጠቀሙት ሲቪል አቆጣጠር በአይሁድ አድስ አመት መስከረም ወይም ጥቅምት የሚጀመር ነው ፤ እግዚአብሄር ለእስራኤል እድስነገር ጀምሮ ነበር ቀን አቆጣጠራቸውን በመቀየር ምልክት አደረገ ፡፡ ይህ እኔን እንዳስብ ያደረገኝ መሲሁን አዳኝ አድርጋችሁ ስትቀበሉ ጠቅላላ አድስ አቆጣጠር አግኝታችኃል፣ ሁሉም አድስ ጅማሬ ሆናል ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 3-5); እግዚአብሄር እያንዳንዱ የቤት ሰዎች እንከን የሌለበት አንድ ወንድ እንስሳት(የበግ ወይም የፍየል) በወሩ በአስረኛው ቀን እንዲመርጡ አዘዛቸው ፡፡ አነስተኛ ቤተሰቦች በጋራ እንዲቀላቀሉና “ እያናዳናዳቸው እንደሚበሉት መጠን” እንዲመርጡ አዘዛቸው ፡፡ እንከን የሌለበት ለመባል እንሰሳው ችግር የሌለበት፣ ጉድለት የሌለበትና ያልተጎዳ መሆን አለበት ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 6); ይህ እንስሳት በወሩ አስራ አራተኛው ቀን ድረስ ይጠበቃል ከዚያም ሁሉም ማህበር እንስሳቶቹን ፀሀይ ስትገባ ያርዳቸዋል ፤ እንስሳቶቹን ለአራት ቀን የሚጠበቁት በእርግጠኝነት ፍፁም እንደነበሩ ለመፍቀድ ነበር ፡፡ በመሻገር ውስጥ የእነዚህ እንስሳቶች መስዋዕት እስራኤላዊያንን ይከላከላቸዋል ፤ ጠቦቱ ትዝ የሚያስብለን ጊዜ እግዚአብሄር አብርሃምን ይስሐቅን እንዲሰዋለት በጠየቀው ጊዜና የይስሐቅን ጥያቄ ለአብርሃምን ዝግጅት እንዳደረጉ “ የመስዋዕቱ በግ ግን ወዴት ነው ?”(ዘፍ 22፡ 7)፡፡

ይህ የመስዋዕት በግ ለክርስቶስ እንደ መስዋዕት በግ ጥላ ሆነ ፤ መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ ለመጠመቅ ወደሱ እየቀረበ መምጣቱን ባየ ጊዜ የተናገረው “ እነሆ የአለምን ሁሉ ኃጢዓት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ”(ዮሐ1፡29) ፡፡ ኢትዮጲያዊው ጃንደረባ ከኢሳ 53 በሚያነብ ጊዜ ምን እንደነበረ ማወቅ ይፈልጋል “ አንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ”(ሐዋ 8፡ 32) ስለዚህ ፊልጶስ ስለ ኢየሱስ መልካም ዜና ነገረው ፡፡ በኢሳ(53፡ 7) ላይ እንደተገለፀው ኢየሱስ“ ተጨነቀም ተሰቃየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም” ፤ ጴጥሮስ ኢየሱስን እንከንና ነቀፋ እንዴሌለበት ጠቦት ገልፆታል (1ጴጥ 1፡ 18-20)፡፡ በራዕ(5፡ 5-6) ላይ ዮሐንስ “ አንድ እንደታረደ በግ አየሁ” በእግዚአብሄር ዙፍን ፊት ቆሞ ፡፡መፅሀፍት የሚነግሩን ኢየሱስ እንከን የሌለበት የሚለውን መመልመያ(መመዘኛ) አማልታል ፤ ኢየሱስ ኃጢዓት አላወቀዉም(2ቆሮ 5፡ 12)፤ “ እርሱም ኃጢዓት አላደረገም ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም”(1ጴጥ 2፡ 22) ፤ በእርሱ ኃጢአት አልነበረም (1ዮሐ 3፡5) ፤ ኢየሱስ የእግዚአብሄር በግ ነው ፡፡ እሱ ፍፁም ነው ፤ በሰው መልክ የሆነ እግዚአብሄር ነው ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 7); ከንፅሁ የበግ ደም ወስደው በመቃናቸው ላይና በዳርና ዳር የበሩ ቃሚዎች ላይ እንዲያደርጉት ነገራቸው ፤ ዋይሰርቤ ሲናገር “ ይህ የበግ ህይወት አልነበረም ከፍርድ ህዝቡን ለማዳን እንጂ ነገር ግን በግ ሞታአል”፡፡ በተመሳሳይ የኢየሱስ መሞት ለእኛ ህይወት ሊሰጥ ነው ፤ ኢየሱስ የመጣው “ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ”(ማቴ 20፡ 28) ፡፡ ኢየሱስ አድስ ኪዳን በመሰረተ ጊዜ የተናገረው “ ስለ ብዙዎች ለኃጢዓት ይቅርታ የሚፈስ የአድስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው”(ማቴ 26፡ 28) ፤ ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው “ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለበጎቹ ያኖራል”(ዮሐ 10፡ 11) ፡፡ በእርሱ ደም ተዋጅተናል ይቅር ተብለናል (ኤፌ 1፡ 7) ኢየሱስ ራሱን ለሁላችንም ቤዛ አድርጎ ሰጠ (1ጢሞ 2፡ 5-6) ፡፡” ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም “(ዕብ 9፡ 22-23) ስለዚህ ኢየሱስ በደሙ ሰዎችን ለእግዚአብሄር ዋጀ (ራዕ 5፡ 9) ፡፡ ዘጸዓት 12 ክርስቶስ ለእኛ ኃጢዓት ለከፈለው መስዋዕትነት ሙሉ ጥላ ነው ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 8-11); እግዚአብሄር አድስ ጅማሬ የሚያደርጉበትን ምግብ አወሳሰድ ትዕዛዝ ሰጣቸው ፡፡ በጉ መጠበሳ ያለበት እና የሚበላው ከአልቦካ ዳቦና ከሚማረር ቅጠል ጋር ማታ መሆን እንዳለበት ፤ የበጉ ሁሉም አካል ጭንቅላቱን፣ እግሮቹንና የሆድ እቃውን ጨምሮ እንድበሉት፤ ማንያውም የቀረው ይቃጠል ፡፡ የእግዚአብሄር አድስ ጅምሬ በፍጥነት ይብሉ ከዚያም እስራኤላዊያን ለጉዞአቸው የሚያደርጉት ጫማችሁን በእግራችሁና በትራችሁን በእጃችሁ ይሁን ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 12-13); በዚያች ሌሊት እግዚአብሄር በመላው በግብፅ ምድር የበኩር ወንድ የሁለቱንም የሰውንና የአውሬን በመምታት ፍርዱን በግብፅ አምላክ ላይ ፈፀመ ፡፡ እስራኤላዊን በሚለየው በበግ ደም በመቃናቸውና በበራቸው ቃሚ ምልክት በተደረገው ከዚህ መቅሰፍት የተሸፈኑ ሆኑ ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 14-20); እግዚአብሄር እስራኤልን ይችን ምሽት ለማስታወስ በየአመቱ አድስ ጅማሮውን እንዲያከብሩ አዘዛቸው ፤ ለሰባት ቀን ከቤታቸው እርሾን እንዲያስወግዱና ያልቦካ ቂጣ እንዲበሉ ታዘዙ ፡፡ እግዚአብሄር እንዴት ከግብፅ እንዳወጣቸው እንዲያስታውሱ በዚህ ሳምንት በጠቅላላ “ ያልቦካ ቂጣ በአል ያደርጋሉ ” ፡፡ ምግብ ከማዘጋጀት ዉጪ ሌላ ስራ መስራት አይችሉም ከዚያም በመጀመሪያውና በሰባተኛው ቀን “ቅዱስ ስብስበ” እንዲያደርጉ ታዘዙ ፡፡ ማንም ይህንን ትዕዛዝ የማያከብር ከእስራኤል ይወገዳል ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 21-23); ሙሴ እስራኤላዊያንን የፋሲካውን እንስሳት እንዲመርጡና እንዲያርዱ ከዚም የሂሶጵ ቅጠል ደሙ ውስጥ በመንከርና በበሮቻቸዉ ማቃንና ጉበን ላይ እንዲረጩት አዘዛቸው ፡፡ እግዚአብሄር በግብፅ ሲያልፍ ደሙን ባየ ጊዜ “ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ አይተወውም ፡፡” ዋይሰርቤ ሲናገር “ ምናልባት የእና እምነት ከሂሶጵ የደከመነው ግን በራሳችን ያለን እምነት አደለም እኛን የሚያድንን ነገር ግን በአዳኛችን ደም ያለ እምነት ነው “፡፡

በቁጥር 23 ላይ “አጥፊው” ቅድመ ክርስቶስ ሊሆን ይችላል ? በዘኁ(22፡ 31) “ እግዚአብሄርም የበለዓምን አይኖች ከፈተ የእግዚአብሄርን መልዓክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ ሰገደም በግንባሩም ወደቀ ፡፡”

በኢሳ( 37፡ 36) “ የእግዚአብሄር መልዓክ ወጣ ከአሶራዊያንም ሰፈር 185 000 ገደለ” ፡፡በዘጸ(23፡ 20-23) እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን የሚጠብቅና ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚያስገባቸውንና አሞራዊያንን፣ ኬጢያዊያንን፣ ፌርዛዊያንን፣ ከነዓንያዊንን፣ ኤዊያውያንንና ኢያቡሳዊያንን ከፊታቸው የሚጠርግ መልዓክ ከፊታቸው እንደ ሚልክላቸው ይናገራል ፡፡ ኢየሱስ አጥፊው ነበር ወደራሱ የሚያመጣውን መንገድ እያዘጋጅ ፤ በብሉይ ኪዳን ኢየሱስ ሁሉም አይነት ሚና ነበረው ፡፡ ሁል ጊዜ ተናጋሪ ብቻ አልነበረም; ምናልባት ታግሎ ነበር፣ በሚነድድ ቁጥቐጦ ውስጥ ራሱን ገልጣል፣ ለህዝቡ መንገድ ለማዘጋጀት ህዝቦችን ጠርጋአል ፡፡ ራዕ(19፡ 11-14) የሚገልጠው ኢየሱስ እንደ ኃይለኛ ተዋጊ “ በጽድቅ ይፈርዳልም ይዋጋልም”በውጊያው ላይ የሰማይ ሰራዊትን ይመራል ፡፡ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ እንዲህ ሰላማዊ ሰው አይደለም ህዝቡን ነፃ ለማውጣት የሚወስደውን(የሚያስፈልገውን) ያደርጋል ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 24-28); ሙሴ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በየአመቱ የፋሲካን በዓል እንዲያደርጉ በዚህም እግዚአብሄር እንዴት ግብፃዊያንን እንደመታና እኛን ከምርኮ እንዳወጣቸው ለልጆቻቸው እንዲያስተምሩ አሳያቸው ፡፡ እስራኤላዊያንም እግዚአብሄር እንዳዘዛቸው አደረጉ ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 29-36); ፋሲካ ሆነ ፤ እስራኤላዊያን ፍፁም በሆነ ትንሽ በግ ነፃ ሆኑ ፤ እግዚአብሄር በግብፅ በኩርን መታ ፈርዖንም ከግብፅ የእስራኤልን መንጋ አስወጣ ፡፡ እግዚአብሄር ቃል እንደገባው ግብፃዊያን ለእስራኤላዊያን የብርና የወርቅ ጌጣቸውን ሰጣአቸው እና አልብሰው ከግብፅ አስወጥተው ላካአቸው ፡፡ ያ በግ በመጨረሻም ኢየሱስ ሆነ ፡፡

ዘጸዓት(12፡ 37-42); እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ጉዞ ጀመሩ ፤ ጆሴፍስ ሲናገር ከመንጎቻቸው ጋር የተጋአዙት እስከ 2ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ (600000 ወንዶች ከቤተሰባቸው ጋር ተጨምሮ) ፤ “ ከጎሳ የተቀላቀለ ህዝብ “ አይሁድ ያገቡ ግብፃዊያንን ወይም እግዚአብሄርን የፈሩ ግብፃዊያን ሊኖሩ ይችላሉ ፤ ምንም እንካን ከሌላ ምድር ቢሆኑም እነዚህ ሰዎች በብዙ ጊዜ ቆይታ የእስራኤላዊያን ማህበረሰብ ሆነዋል ፡፡” ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም ፡፡ፈርተዋቸው ነበርና ግብፅ በመውጣታቸው ደስ አላት”(መዝ105፡37-38) ፡፡ በግብፅ ከ430 አመታት በኃላ እስራኤላዊያን ነፃ ወጡ ! ወደ ተስፋይቱም ምድር ሄዱ ፡፡

ይሁ (1፡ 5) የገለፀው “ ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ህዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኃላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ ፡፡” ስለዚህ ነው ህዝቡን ከግብፅ ያወጣው ? ጌታ ! ኢየሱስ ! እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ በየትኛውም በኃይለኛው ይሄዳል ህዝቡን ለማዳን ፡፡

ዘጸዓት(13); ይህ ምዕራፍ እንደገና የሚያወራው የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በኩር የእርሱ እንደሆነ (ቁጥር 2)፣ ከግብፅ ስለሚወጡበት መንገድ ይገልፃል (ቁጥር17-18)፣ ሙሴ የዮሴፍን አጥንት ከእነርሱ ጋር ይዞ እንደወጣ ይገልጣል (ቁጥር 19) እና አፅዕኖት የሚሠጠን እግዚአብሄር ከፊታቸው በደመና አምድ ወይም በእሳት አምድ ሊመራቸው መሄዱን ያሳየናል (ቁጥር 21-22) ፡፡ ነገር ግን ከበጉ ደም ውጪ ዋና(አምድ) የለም ፡፡

መዝጊያ

እግዚአብሄር ነፃ በማውጣት ስራ ላይ ነው በዚህም የእኔ ፀሎት እናንተ እያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ደም ከኃጢዓት ባርነትና ከሞት ነፃ እንድትወጡ ነው ፡፡

  1. Tom Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Exodus, p. 105; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 198.

  3. Wiersbe, p. 199.

  4. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 108.

ጥያቄዎች

  1. ዘጸ(12፡ 12) የሚለው “ በግብፅም አማልዕክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ ፤ እኔ እግዚአብሄር ነኝ ፡፡ “ ሀይል የሌላቸው የውሸት አምልክ እንደነበሩ እናውቃለን ስለዚህ ይህ ጥቅስ ሰለሚለው ምን ታስባላችሁ ?
  2. እንደ ዘጸ(12፡ 2) እግዚአብሄር ሙሴን ከግብፅ ነፅ በወጡበት ወራት አቆጣጠራቸውን እንደገና እንዲጀምር አዘዘው ፤ ለምን እግዚአብሄር ይህን እንደመሰረተ ምን ታስባላችሁ ?
  3. በዘጸ 12 ላይ የፋሲካው በግ ወደ እግዚአብሄር በግ ክርስቶስ የሚያመለክት አይነት ነበር (ዮሐ 1፡ 29) ፤ ስለ ፋሲካው በግ ዝርዝር ምን አለ ስለ ክርስቶስ በዝርዝር የሚያመለክት መፈለግ ትችላላችሁ ?(መዝ 34፡ 20; ዮሐ 19፡ 36; 2ቆሮ 5፡ 21; 1ጴጥ 1፡ 18-20; ራዕ 5)
  4. በፋሲካ ድግስ ሌላ ሰው(እስራኤላዊ ያልሆነ ሰው) እንዳይካፈል በትዕዛዝ ያለመፈቀዱ አስፈላጊነት ምንድን ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ዘጸ 12፡ 43; ዘኁ 9፡ 14; 1ቆሮ 11፡ 26-27)
  5. ሙሴ ህዝቡን በመጀመሪያው በፋሲካ ድግስ ቀን ሁሉንም እርሾ ከቤታቸው እንዲያስወግዱ አዘዛቸው (ዘጸ12፡ 14-15) ማንም ማናኛውንም የቦካ የበላ ከእስራኤል ይወገዳል ፡፡ እርሾን ማስወገድ ጥቅሙ ምንድን ነበር ? (ዘጸ 12፡15; 20; 13፡3; ዮሐ 6፡ 48; 51; 1ቆሮ 5፡ 7-8)
  6. እግዚአብሄር ለሙሴ የተናገረው “ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማህፀንን የሚከፍት በኩር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ የእኔ ነው ”(ዘጸ 13፡ 2) ምን ማለት እንደሆነ ግለፁ ፡፡
  7. ከፋሲካው በግ በተጨማሪ ሌላ ነፃ አውጪ በዘጸዓት ምዕራፍ 12 ምንድን አያችሁት ?(ዘጸ 12፡ 51; ሐዋ 7፡36; 13፡ 17)
  8. በዘጸ (12-13) ውስጥ በትምህርት ወይም በንባብ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያቸሁ ወይም አስረዳችሁ ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 13:17-18a

“When Pharaoh let the people go, God did not lead them along the road to the land of the Philistines, even though it was nearby; for God said, ‘The people will change their minds and return to Egypt if they face war.’ So He led the people around toward the Red Sea along the road of the wilderness.”

የፋሲካ በዓል መመሪያዎች

ኦሪት ዘፀዓት 12-13 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

ከአስረኛዉ መቅሰፍት በኋላ፥ ፈሮዖን እስራኤላዉያንን ለቋቸዋል። እስራኤላዉያን ከግብፅ በመዉጣት መንገዳቸዉን ከጀመሩ በኋላ እግዚዓብሔር ያዘጋጀዉ ዓላማ ነበረዉ። መጀመሪያ የመራቸዉ በአጭሩ መንገድ ሳይሆን ለየት ባለ መስመር ነው። ነገር ግን ይህ ለህዝቡ ጥቅም የተሻለ መንገድ ነው! ከዚያም እግዚዓብሔር ለህዝቡ እንደሚያስብ ተናገረ። የኋላ የኋላ እግዚዓብሔር ከህዝቡ ፊት ለፊት ቀድሞ በመሄድ ይመራቸዉ ጀመር።

አስታዉስ፥ እግዚዓብሔር ትናንትም፣ ዛሬም እስከ ለዘላአለምም ያዉ ነዉ። ስለዚህም የራስህ ጉዞም ልክ እንደዚሁ ነዉ። ቀላሉ እና አጭሩ መንገድ ባይሆንም የእግዚዓብሔር መንገድ ይሻልሃል። እግዚዓብሔር ስላንተ ይጠነቀቃል። በቀንም በማታም እግዚዓብሔር ይቀድምሃል፥ ከአንተ ጋራም ነው። ስለዚህም በአንድ ጊዜ አንድ እርምጃ እየተራመድክ የህይወት መንገድህን ቀጥል።

"እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብፅም እንዳይመለስ ብሎአልና። ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ምድር ተሰልፈው ወጡ።"

ኦሪት ዘፀዓት 13:17-18

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘፀዓት 13:21፦ "በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ።"
  • ወደ ዕብራዉያን 13:8፦ "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።"
  • መፅሓፈ ምሳሌ 3:5-6፦ "በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።"

የመሲሁ ሙሉ ምሳላካል ኦሪት: ትምህርት 34