The Final Plague Threatened
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ አስረኛውን መዓትና የመጨረሻውን መዓት እንሸፍናለን ፤ በዘጸ(7-10) የገለፅናቸውን መዓቶች እስኪ እንከልሳቸው; 1) ውሃው ወደ ደም ተቀየረ; 2) እንቁራሪቶች(ጋጉንቸር); 3) ትንኞች; 4) ዝንቦች; 5) የከብቶች መሞት; 6)ቁስል; 7) በረዶ; 8) አንበጣዎች; 9) ጨለማ ፡፡ የመፅሀፍ ቅዱስ ሀተታ ሰጪው ቺልዲስ ሲናገር በምዕራፍ 11 ያለው ድርጊት የመዕቱ(የመቅሰፍቱ) መደምደሚያና የመሻገር ባህል መጀመሪያ ነበር ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(11፡ 1); እግዚአብሄር ለሙሴ ምንያክል መቅሰፍት እንደሚያመጣ(እንደሚያደርግ) አልነገረውም ፤ አሁን እግዚአብሄር የመጨረሻው መቅሰፍት እንደሚሆንና ፈርዖን እንዲሄዱ እንደሚለቃቸው ገለጠ ፡፡ ሙሴ መጨረሻው እንደመጣ እንደነበር አየ ፤ እግዚአብሄር “ አባሮ ያስወጣችኃል” ብሎ በመናገር አሳወቀው ፤ ይህ ሀረግ የተተረጎመው ለመዓት፣ ለበሽታ፣ ለጉዳት ቃል መሰረት ከሆነው “ነጋ” ከሚለው ነው ፡፡ ይህ ስም ነው የሆነ ነገር በሚነካ ጊዜ የሚገልፀው ፤ አስታዉሱ እግዚአብሄር የያዕቆብን ጭን “በነካዉ” ጊዜ (ዘፍ 32፡25) ? አሁን እግዚአብሄር ጥብቅ በሚሆን መንገድ ግብፃዊያንን “ይነካል” ፤ ግብፃዊያን በሆነ መጠን ያክል ከእግዚአብሄር የሆነውን መነካት ለምደውት ነበር ፡፡ በዘፍ(12፡ 17) ውስጥ “ እግዚአብሄር በአብራም ሚስት በሶራ ምክንያት ፈርዖንንና የቤቱን ሰዎች በታላቅ መቅሰፍት መታ” ፡፡ እግዚአብሄር ይህን ፍርድ አመጣ ግብፃዊያን እሱ ሰዎች ላይ ባደረጉት ምክንያት ነበር ፡፡ ሀሚልተን ሲናገር በምሳ(6፡ 32-33) እንደተገለፀው ባልዋን ተገድዶ በምንዝርና “እንዲነካ” ፈቀደች ከሚለው ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(11፡ 2); እግዚአብሄር ሙሴ ነ ለእስራኤል ወንዶችና ሴቶች ጎረቤቶቻቸው የብርና የወርቅ ጌጣቸውን እንዲጠይቁ እንዲነግራቸው ነገረው ፡፡ ይህ ትንሽ ጥያቄ አልነበረም ፤ በ991 ከክርስቶስ ውልደት በፊት 42 በፓውንድ በላይ የሚመዝን የአንገት ጌጥ ተቀብሮ አግኝተዋል ፤ ይህ የዘረፉት ብዛት ነበር ! እግዚአብሄር ቀድሞ(በዘጸ3፡ 22) ለሙሴ ይህን ቃል ገብቶለት ነበር ፤ ከዚያም (ዘጸ 12፡ 36) የእውነት ሆናል ፡፡
ዘጸዓት(11፡ 3); “ እግዚአብሄርም በግብፃዊያን ፊት ለሕዝቡ ሞገስን ሰጠው ፡፡ ሙሴም በፈርዖን ባሪያዎችና በሕዝቡ ፊት በግብፅ አገር እጅግ የከበረ ሰው ነበር ፡፡” እስራዔላዊያን በብዙ ሀዘን ውስጥ ነበሩ እናም አሁን እግዚአብሄር በእነረሱ ላይ ሞገሱን አፈሰሰ ፡፡ አስታውሱ እግዚአብሄርን በመፍራትና ሙሴ የተናገረውን በማመን ምክንያት የፈርዖን አገልጋዮች በረዶም እንደሚመጣና በከብቶቻቸው ላይ የሚያመጣው ባወቁ ጊዜ ? እዚህም እንደገና ህዝቡ እግዚአብሄርን ፈሩ ምክንያቱም ያደረገውን ስላዩ ፤ ይህንን ያላየው ፈርዖን ብቻ ነበር ፡፡
ሙሴ በግብፅ “በጣም የተከበረ” ነበር ፤ ይህ በአስ( 9፡ 4) ላይ መርደክይዎስን ለመግለፅ ከተጠቀሙበት በፋሪስ ሰዎች “በጣም ከፍ ከፍ አለ(የተከበረ)”ከሚለው ቐንቐ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር ሞገስ በስራችሁ ወይም በአገልግሎታችሁ ወይም በቤተሰቦቻችሁ በሆነ ጊዜ ማየት ትችላላችሁ ፡፡ ይህ ለሙሴ ሆነለት ምክንያቱም ታዛዥ ስለነበርና በትምህርቱ ስለታገሰ ፡፡
ዘጸዓት(11፡ 4); ሙሴ ሲናገር “ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል በእኩለ ሌሊት እኔ በግብፅ መካከል እወጣለሁ “ የተለየ መጥፎ ነገር በእኩለ ሌሊት ላይ እንደሚሆን እናስባለን ፤ ይሁን እንጂ በእኩለ ሌሊት ላይ ጥቂት መልካም ነገሮችም ተፈጥረዋል በመፅሀፈ መዝ ( 119፡ 62) እኛን የሚያነሳሳን “ ስለ ፅድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት ላይ ላመሰግንህ እነሳለሁ” ፡፡ ሐዋ(16፡ 25) የሚገላፅልን ጳውሎስና ሲላስ በእስርቤት በእኩለ ሌሊት ላይ ሲፀልዩና መዝሙር ሲዘምሩ ለጌታ ሁሉም እስረኞች ያደምጣቸው ነበር ፡፡ “ እወጣለሁ “ የሚለውን ንግግር ስናስታውስ ትርጉሙ እግዚአብሄር በግብፅ መሀከል ይሄዳል የሚለው ይሆናል ፤ ይህ ስጋ ለማልበስ(እውነት ለማድረግ) ተዘጋጀ ወይም ስጋ ለማልበስ(እውነት የማድረግ) ጥላ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(11፡ 5); እግዚአብሄር ፍርዱን ማድረግ በሚጀምር ጊዜ ምናልባት፣ ግን ወይም በኃላ አይኖርም በግብፅ ምድር የሚኖር በኩር ወንድ ልጅ ሁሉ ይሞታል ፤ ፈርዖን ከዚህ ፍርድ አያመልጥም ፤ ከዚህ በኃላ የስልጣን ደረጃ አይኖርም ፡፡ የሚያጠቃው ሁሉንም ነው ከብቶችንም ያካትታል ፡፡ በዘፍጥረት ውስጥ የበኩርን ዋጋና ጠቀሜታ አውርተናል ፤ ስለ ቃየንና አቤል፣ ስለ ያዕቆብና ኤሳውና ስለ 12 የእስራኤል ነገዶች አስቡ ፡፡ ኮንስታብል ሲናገር የበኩር ወንድ ልጆች የህዝቡ የጥንካሬና ሀይለኝነት ምልክቶች ነበሩ ፤ የቤተሰብ መስመር የመጣው በበኩር ወንድ ልጅ ውስጥ ነበር ፤ አስታውሱ ሌዋዊያን እንደ በኩር ልጅ መደረጋቸውን ፡፡ ዶዘማን ይህንን ድርጊት ያጠቃለለው 1) ጊዜው; በእኩለ ለሊት; 2) ይዘቱ; የበኩር ወንዶችን በግብፅ; 3) ስፋቱ; በዚያው ዙሪያና 4) ውጤቱ; ታላቅ የለቅሶ ጭንቀት; ንፁህ ህፃናት ስለሚሞቱ(ቁጥር 6) ፡፡
ዘጸዓት(11፡ 6); “ በግብፅም አገር ሁሉ አስቀድሞ እንደ እርሱ ያልሆነ ኃላም ደግሞ የማይሆን ታላቅ ጩኸት ይሆናል“ ፤ ይህ እኔን ስለ ኖህና ስለ ቀስተ ዳመናው እንዳስብ አደረገኝ ፡፡ ብዙዎች እግዚአብሄር እንዴት የበኩር ልጅ ህፃናትን ሊገድል ቻለ ብለው ይጠይቃሉ ፤ ኮንስታብል አምስት የሚሆኑ ሀሳቦችን ሰጥቶናል; 1) ምንም ይሁን እግዚአብሄር ያደረገው ትክክል ነው ምክንያቱም እግዚአብሄር ስለሆነ; 2) እግዚአብሄር የሚያኖርና ህይወት ሰጪ ነው ስለሆነም ከማንኛውም ፍጥረት ላይ ህይወትን መውሰድ መብቱ ነው; 3) እግዚአብሄር ሂዎት መስጠትም መውሰድም ይችላል; 4) ሰዎች ኃጢዓተኞች ናቸው የኃጢዓት ውጤት ደግሞ ሞት ነው ስለዚህ እግዚአብሄር ሰዎችን አየቀጣ ነው እና 5) እግዚአብሄር ሁሉንም ህፃን አልገደለም ፡፡
ዘጸዓት(11፡ 7) “ እግዚአብሄር ግን በግብፃዊያንና በእስራኤል መካከል እንዲለይ እንድታውቁ በእስራኤል ልጆች መካከል ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ውሻ ምላሱን አያንቀሳቅስባቸውም ፡፡” እስራኤል ይድናል ፤ ነገር ግን የግብፅ በኩር ሁሉ ይሞታል ፡፡ እግዚአብሄር በዚህ ሂደት ውስጥ ዘሩን ያወጣል ፤እግዚአብሄር በእስራኤላዊያን የበኩር ወንዶች ሁሉ ላይ ያልፋል ፡፡
ዘጸዓት(11፡ 8); ሙሴ በኃይለኛ ቁጣ ከፈርዖን ፊት ወጣ፡፡ ስለ ቁጣ በማስብ ጊዜ የኢየሱስን ቁጣ በቤተ-መቅደስ አስባለሁ ፤መፅሀፍት የፅድቅ ቁጣ እንደነበር ይናገራሉ ፤ እኔም ይህ ቁጣ ሲሰማኝ እኔም ልክ ነበርኩ ፡፡ ሙሴ አድርገውት በነበረው በክፉው ታሞ(ደክሞ) ነበር ፤ ከዚህ ሁኔታ በተጨማሪ ሙሴ ብዙ በሌላ ጊዜዎች ቁጣውን ብግልፅ ፊት ለፊት አሳይታል ፡፡ በዘጸ(16፡ 20) ላይ እስራኤላዊያን ለአንድ ቀን ከሚገባቸው በላይ መና በሰበሰቡ ጊዜ ሙሴ ተቆጣ ፤ ዘሌ( 10፡ 16) ላይ መስዋዕቱን በስርአት ባለማድረጋቸው ሙሴ በፈርዖን ልጆች ተቆጣ ፡፡ዘዳ(16፡ 15) ላይ ቅሬታ ባቀረቡ ጊዜ ለእስራኤላዊያን ውሃ እንዲያፈልቅ ሙሴ በመሪባ አለቱን በቁጣ መታው ፤ በዚህ ምክንያት የሙሴ ቁጣ የእግዚአብሄር ቅዱስነት እንዳይታይ ከለከለው በዚህም ሙሴ እስራኤልን እየመራ ቃል ወደ ተገባችው ምድር ይዞ እንዲገባ አልተፈቀደለትም ፡፡
ኃጢአት ሲኖር አንዳንድ ጊዜ መቆጣት ችግር የለውም ፤ በእናንተ ውስጥ መገንባት ያለባችሁ የት ቦታ ላይ ነው ትክክል የሚሆነው ቁጣችሁ ? መቼ ነው ቸርች ይህን የምታገኘው ? የምናደርገው በፍጥነት እባህላችን ላይ ተፅኖ አያደርግም ብለን እናምናለን(እንቀበላለን) ? የእኛን ኑሮ ለእግዚአብሄር አልሰጠነውም ! አንዳንድ ጊዜ “ ቸርች ልቦቻን በጎ(ቅን/የሚመለስ) ታድርግ “ ብዬ መናገር እፈልጋለሁ! በአሜሪካ ባሉ ፈርዖኖች እበሳጫለሁ ፡፡ በእግዚአብሄ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ነኝ ፡፡ ታማኝ ከሆናችሁ ሁሉንም ለእርሱ አሰጠዋለሁ ማለት ትችላላችሁ ?
ዘጸዓት(9፡ 10-11); ሙሴና አሮን ባደረጋአቸው ድንቆች ፈርዖን ለእግዚአብሄር ኃይል ቢመሰክርም እስራኤላዊያን እንዲሄዱ አልፈቀደም ፡፡ ሰዎች ካላዳመጡኝ ለእኔ የሚሰጠኝ ተስፋ ምንድን ነው ታውቃላችሁ ? እግዚአብሄር ኃይሉን ለመግለጥ እድል አገኘ ከዚያም ክብርን ያገኛል ፡፡ እግዚአብሄር ኃይሉን ሲገልጥ ማየት እፈልጋለሁ ፡፡ ሙሴና አሮን ታዛዥ ነበሩ ፡፡
መዝጊያ
ሳይልሀመር ሲናገር “ በመጨረሻው መቅሰፍት ትርጉም ፀሀፊው በዘጸዓት ትረካው ወደትልቅ መዋቅር በሁሉም በአምስቱ የኦሪት ህግ መፅሀፍት በተለይም የመጀመሪያዎቹ ዘፍጥረትን ምዕራፎች ይዞልናል መምጣት ችላል ፤ በሞት ፍርድ መሀል ላይ እግዚአብሄር ቃል ለተሰጠው ዘር የሚድንበትን መንገድ ሰጠ (ዘፍ3፡15) ፡፡ ልክ እንደ ሄኖክ(ዘፍ 5፡ 22-23)፣ እንደ ኖህ(ዘፍ 6፡ 9) እና እንደ ሎጥ(ዘፍ 19፡ 16-19) እነዚህ በእግዚአብሄር መንገድ የሄዱ ከሞትና ከጥፋት ዳኑ ፡፡
እግዚአብሄር ዘሩን ለማውጣት ቃሉን አከበረ በተለየም መንገድ- በፋሲካ(ፋሲካ ሆነ) መጥቶ ነበር ፤ እግዚአብሄር በእስራኤላዊያን ላይ ያልፍ ነበር ህዝቡን ሊያድንና ግብፃዊያንን ሊገድል(ሊመታ) ፡፡
Brevard S. Childs, The Book of Exodus (Louisville, KY: Westminster John Knox Press, 1974, 2004), p. 161.
Victor P. Hamilton, Exodus: An Exegetical Commentary (Grand Rapids: Baker Publishing Group, 2011), pp. 165–166.
Hamilton, p. 167.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), pp. 105–106.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Exodus (available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf), p. 99.
Thomas B. Dozeman, The Eerdmans Critical Commentary: Exodus (Grand Rapids: Wm. B. Eerdmans Publishing Co., 2009), p. 249.
Constable, pp. 100-101.
Hamilton, p. 168.
John H. Sailhamer, The Pentateuch as Narrative (Grand Rapids: Zondervan Publishing House, 1992), p. 258.
ጥያቄዎች
-
በዘጸ(11፡ 7) ላይ እግዚአብሄር በእስራኤልና በግብፅ መሀከል ልዩነት እንዳደረገ እንዲያዉቁ ፈለገ ፤ በመጀመሪያዎቹ በዘጸዓት ምዕራፎች ውስጥ ያደረጋቸው የተለያዩ ልዩነቶች ምንድን ነበሩ ?
-
በዘጸ( 11፡ 1) ላይ እግዚአብሄር ለሙሴ “ከአንድ መቅሰፍት” በኃላ ፈርዖን እንዲሔዱ እንደሚለቃቸው ነገረው ፤ ይቺ የመጨረሻዋ መቅሰፍት ፈርዖን እንዲልካቸው ምክንያት ከነበረች እግዚአብሄር ሌሎቹን መቅሰፍቶች በግብፅ ላይ ለምን እንደላከ ምንድን ታስባላችሁ ? ወይስ የሁሉም መደምደሚያ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ (ሮሜ 9፡ 17) ?
-
ዘጸ(11፡ 2) እስራኤላዊያን ግብፃዊያን ጎረቤቶቻቸውን ለብርን ለወርቅ እቃ እንዲጠይቁ ለምን በእግዚአብሄር ስለመታዘዛቸው ምንድን ታስባላችሁ ?
-
ሁሉም ነፃ የማውጣቱ ሂደት በዘጸዓት 11 ውስጥ ያሳወቀን ወድያውኑ የሆነ ድርጊት እንዳልነበር ነው ፡፡ በሙከራችሁ መሀል ላይ እግዚአብሄርን የሰጣችሁን ነፃ ማውጣት እንዴት አያችሁት ?
-
ዘጸ(11፡ 7) መነሻ በማድረግ እግዚአብሄር አሁንም በእስራኤልና በገዳዮቻ መሀከል ልዩነት አድርጋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ማናኛውንም የተለየ ድርጊት መጥራት ትችላላችሁ ?
-
በዘጸ 11 ውስጥ በትምህርት ወይም በንባብ መንፈስ ቅዱስ ምንድን እጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 11:9
“The LORD had said to Moses, ‘Pharaoh will refuse to listen to you, so that My wonders may be multiplied in the land of Egypt.’”
የይሁዲ ፋሲካ መምጣት
ኦሪት ዘፀዓት 11 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ግብፅ በዘጠኝ መቅሰፍቶች ከተመታች በኋላ እንኳን የፈርዖን ልብ እንደ ደነደነ ነበረ። እስራኤላዉያንን መልቀቅ አልፈለገም። እግዚዓብሔርም ለሙሴ በግብፅ ምድር ያለ በኩር ሁሉ የሚገደልበት አስረኛዉ እና የመጨረሻዉ መቅሰፍት ለማምጥት ቅደም ተከተል ሰጠዉ። እግዚዓብሔር ኃይሉን መግለጡን ቀጥሏል። በዚህ ሁኔታም ዉስጥ ገዢዉ ራሱ እግዚዓብሔር ነው!
እንዲሁ በተመሳሳይ መንገድ፥ በህይወትህ ዉስጥ ፈተና እና ስቃይ እንደሚኖር እግዚዓብሔር እናገራል። ነገር ግን፥ እነዚህን ጊዜያቶች፦ ለመመልስ፣ ለማረጋገጥ፣ ለማበረታታት እና በማይናወጥ መሠረት ላይ እኛን ለማስቀመጥ እግዚዓብሔር ይጠቀምበታል። በጭንቅ ጊዜያቶች መካከል፥ እግዚዓብሔር ዓለምን እንዳሸነፈ በልቦናህ ተገንዘብ። ከዚህም ለሚልቅ ነገር ጉልበት ኖሮህ መቋቋም እንድትችል የሚያደግን ኃይል እንድታዳብር እግዚዓብሔር በአንተ ዉስጥ እየሰራ ነዉ!
"እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ተአምራቴ በግብፅ አገር ብዙ እንዲሆን ፈርዖን አይሰማችሁም አለው።"
ኦሪት ዘፍጥረት 11:9
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የዮሐንስ ወንጌል 16:33፦ "በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።"
- የያዕቆብ መልዕክት 1:2-3፦ "ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት"
- 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:10፦ "በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 33
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።