The Pentateuch Exodus

Plagues 5-9

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 32 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ባለፈው ክፍል ስለ አስሩ መዓቶች ማውራት ጀምረናል ውሃው ወደ ደም ተቀየረ፣ እንቁራሪቶች ምድሩን ሸፈኑት፣ የትንኝ መዓት( ግብፃዊያን አስማተኞች ማስመሰል ያልቻሉት) እና የዝንብ መዓት እስራኤላዊያንን ሳይሆን ግብፃዊያንን ያጠቁ ፡፡ ዋይሰርቤ ሲናገር “ በመዓቱ ጊዜ ተአምራቱን ያሳየበት ሌላው ምክንያት አይሁዶች ስለታላቅነታቸው ሊናገሩ የሚችሉት ስለመጡበት የእነርሱ ታላቅ አምላክ አስደናቁ ሀይል ነው “

ትምህርት

ዘጸዓት(9፡ 1-3); እግዚአብሄር ለፈርዖን እንዲነግረው ሙሴን ላከው “ የዕብራዊያን አምላክ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ያገለግሉኝ ዘንድ ህዝቤን ልቀቅ” ፤ እግዚአብሄር እንደገና ራሱን “ የዕብራዊያን አምላክ እግዚአብሄር” ብሎ በመጥቀስ አሳወቀው ፡፡ እግዚአብሄር ፈርዖን እስራኤላዊያንን ለመልቀቅ አምቢ የሚልከሆነ ክፉ እንደሚሆንበት አስጠነቀቀው ፤ “ እነሆ የእግዚአብሄር እጅ በሜዳ ውስጥ ባሉት በከብቶችህ፣ በፈረሶችህም፣ በአህዮችህም፣ በግመሎችህም፣ በበሬዎችህም፣ በበጎችህም ላይ ትሆናለች ፡፡”

ዘጸዓት(9፡ 4); እንደ ቀድሞው መቅሰፍት እግዚአብሄር በግብፃዊያን ከብቶችና በእስራኤላዊያን ከብቶች መሀከል ልዩነነት አደረገ ፤ ማክአርተር ሲናገር ይህ በግብፃዊያን ሀሰተኛ አመላኮች ላይ የተደረገ ቀጥተኛ ማጥቃት ነበር ፡፡ ግብፃዊያን አፒሰ በሬን እንደ እንሰሳት አምላክ ዋጋ ሰጥተዋል፣ እንደ ሀቶር አምላክ ወንድ ልጅ ለይተውታል እናም በእሳ አምልኮ ትልቅ ሚና እንዳለው ሰይመውት ነበር ፡፡ አፒስ በተጨማሪም በሰውና በሌላ ታላቅ አምላክ ምሳሌ ፒታህ( የጥበበኛና የሰዓሊ አምላክ)፣ ኦስሪ( ከህይወት በኃላ ያለ አምላክ) እና አቱም(የአለም ፈፃሚ) መሀከል እንደ አገናኝ ፤ መረጃዎች የሚነግሩን አፒስ የመጀመሪያው የግብፅ አምላክ እንደነበር ነው ፡፡ እግዚአብሄር ለእነርሱ በተጠነቀቀላቸው ቦታ በጌሳም እንዲቀመጡ እስራኤላዊያንን ነገራቸው (ዘፍ45፡ 9-11) ፤ እግዚአብሄር ወደ ጌሳም የወሰዳቸው ሰዎቹን ብቻ ሳይሆን ከብቶቻቸውንም ነበር ከዚያም ጠበቃቸው ፤ በተጨማሪም እግዚአብሄር በዘጸዓት ውስጥ ከግብፅ ከብቶቻቸውን አስወጣ(ዘጸ12፡ 37-38)፡፡

ዘጸዓት(9፡ 5-11); “ ነገ እግዚአብሄር ይህን ነገር በምድር ላይ ያደርጋል ብሎ ጊዜ ወሰነ”(ቁጥር 5) ፤ እግዚአብሄር ለፈርዖን የ24 ሰዓት ማስጠንቀቂያ ሰጠው ፡፡ “ እግዚአብሄርም ያንን ነገር በነጋው አደረገ የግብፅም ከብት ሁሉ ሞተ ከእስራኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንካን አልሞተም”(ቁጥር 6) ፤ የግብፃዊያን ገበሬ ብትሆኑ አስቡት በፈርዖንና በሙሴና በአሮን መሀከል ስለተደረገው ቃለ ምልልስ ምንም ግንዛቤው የላችሁም ወደ መስክ ተጉዛችሁ ስትወጡ ሁሉም ከብቶቻችሁ ሞተዋል (ቁጥር 3) ፡፡ ፈርዖን ሙሴና አሮን የተናገሩት እውነት እንደሆነ እንዲያዩ መልዕክተኞችን ላከ ፤ ፈርዖን እውነት መሆኑን ቢያይም አሁንም ልቡን አፀና ፤ ምንም አላስደነገጠውም ፤ ማናንም አልፈራም ! እግዚአብሄር ሙሴና አሮንን ነገራቸው “ እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ ሙሴም በፈርዖን ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው “(ቁጥር 8)፡፡ ጥቁር ጥቀርሻ በበሽታ የጠቆረን ቆዳ ይወወክላል ፤ ምናልባት አሁንም እስራኤላዊያን ጡብ ለመስራት ጥቀርሻውን መጥበሻው ላይ በማስቀመጥ ጡብ ይሰሩ ነበር ፡፡ ፍርድ በግብፃዊያን ላይ ለማምጣት ሙሴ የሆነ ነገር አደረገ የባርነታቸው አካል የነበረውን ወደ ሰማይ በመወርወር፡፡ አስታዉስ ከአንዳንዶቹ መዓቶች በፊት ማስጠንቀቂያ ሀሳብ እንደነበርና ከአንዳንዶቹ በፊት እናዳልነበር; (1) ዉሃው ወደ ደም- ማስጠንቀቂያ; (2) እንቁራሪቶች- ማስጠንቀቂያ; (3) ትንኝ- ማስጠንቀቂያ አልነበረውም; (4) የዝንቡ- ማስጠንቀቂያ; (5) የከብቶቹ- ማስጠንቀቂያ; (6) ቁስል- ማስጠንቀቂያ አልነበረውም ፡፡ “ ከምድጃውም አመድ ወስደው በፈርዖን ፊት ቆሙ ሙሴም ወደ ሰማይ በተነው በሰውና በእንስሳም ላይ ሻህኝ የሚያወጣ ቁስል ሆነ ፡፡ይህ ቁስል “በክረምት የሚፈጠር ሽፍታ በዋናነት አባይ ሞልቶ በሚፈስበት ተቀራራቢ ጊዜ የማቃጠልና የመውጋት ስሜት በቆዳ ላይ በማመንጨት ጠንካራ ማንቀጥቀጥና ማቃጠል ስሜት ይሰጣል እነዚህን ደማቅ ማንቀጥቀጥን የሚመስል” ነበር ፡፡ አስማተኞቹም ቁስል ነበረበቸው ስለዚህ ህመም ስለነበረው በሙሴ ፊት ሊቆሙ አልቻሉም (2ጢሞ 3፡8)፡፡

ዘጸዓት(9፡ 12-13); “ እግዚአብሄር የፈርዖንን ልብ አፀና አልሰማቸውምም” ፤ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈርዖን ልብ መደንደን(መፅናት) ለእግዚአብሄር አይነተኛ የነበረው ፡፡ ኮንስታብል ሲናገር “ ሰው ልቡን ማደንደን ሲቀጥል እግዚአብሄር ለፍርድ በበለጠ ያደነድነዋል “(ምሳ29፡ 1) ፡፡ እንደ ሰባተኛው መዓት ደግሞ በማሳወቀው ያቀረበው( የተሰመረበትን ሀረግ ተመልከቱ) “ እግዚአብሄር ሙሴን እንዲህ አለው ማልደህ ተነሳ በፈርዖንም ፊት ቆመህ በለው የዕብራዊያን አምላክ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል እንዲያገለግሉኝ ህዝቤን ልቀቅ ፡፡”

ዘጸዓት(9፡ 14-19); እግዚአብሄር ሁሉንም ቁጣውን ወደ ግብፅ እንደሚልክ ቃል ገባ ከአንድ አላማ ጋር በዚህም እግዚአብሄርን የሚመስል እንደለለ ያውቃሉ ፡፡ እግዚአብሄር ሙሉ ኀይሉን በፈርዖን ላይ ለማምጣት አቀደ ፤ “ሁሉም” የሚለው ቃል በዚህ ንግግር ውስጥ 12 ጊዜ ተጠቅሞበታል ፤ “ አሁን እጄን ዘርግቼ አንተን ህዝብህንም በቸነፈር በመታሁህ ነበር አንተም ከምድር በጠፋህ ነበር”(ቁጥር 15) ፡፡ በባለፈው ክፍል “መምታት” ስለሚለው ቃል ጥቅም አስታውሱ ፤ እግዚአብሄር እነሱን የመግደል ሀይል ቢኖረውም፣ ዋይሰርቤ የፃፈው “ እግዚአብሄር በምህረቱ አሁንም ሊያድናቸው ወሰነ “ ፡፡ የእግዚአብሄር የተለየ ጠቅላላ አላማው ፈርዖን እንዲፈቅድና ግብፃዊያን እንዲኖሩ; “ነገር ግን ሀይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ “(ቁጥር 16; ሮሜ9፡17) ፡፡ እግዚአብሄር ፈርዖን እስካሁን በእስራኤላዊያን ላይ በትዕቢት እንዲሄዱ አለቅም በማለት እያደረገ እንደነበረ ተናገረ ፤ ሀሚልተን ሲናገር እግዚአብሄር ለፈርዖን እቅድ ነበረው፤ (ኤር 29፡ 11)፡፡ “ እነሆ ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሰረተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግብፅ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ አዘንብብሃለሁ”(ቁጥር 18) ፡፡ እግዚአብሄር ከብቶቻቸውንም ወደ መጠለያቸው እንዲያስገቡ አስጠንቅቃቸውም ነገራቸውም ፤ፈርዖን ለእግዚአብሄር መለሰ ፤ ሀሚልተን ሲናገር “ ለማንኛውም ሰው ከእግዚአብሄር ቃል በመጣ ጊዜ ሁል ጊዜ ሁለት ምርጫ አላቸው; መታዘዝ/አለመታዘዝ፣ ማዳመጥ/አለማዳመጥ፣ መመለስ/ችላ ማለት፣ በእግሩ ስር በመውደቅ እሱን ማምለክ/ከዛውጭ አያለሁ አላምንም፣ ልባችሁን ማለስለስ/ ማጠንከር “

ዘጸዓት(9፡ 20-26); የፈርዖን ባለስልጣኖች እግዚአብሄር እውነት እነደሆነ አወቁ ከፈርዖን መመለስ ጀመሩ ፤ እግዚአብሄርን የምር ያልተቀበሉ አገልጋዮቻቸውንና ከብቶቻቸውን በሜዳ ተው ፡፡” ሙሴም በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ እግዚአብሄርም ነጎድጋአድና በረዶ ላከ እሳትም ወደ ምድር ወረደ ፤ እግዚአብሄርም በግብፅ አገር ላይ በረዶ አዘነበ “(ቁጥር 23) ፡፡ ዮሐንስ ማክአርተር “ ሀይለኛ ከኤሌክትሪክ ጋር የተገናኘ ጎርፍ የያዘ ያልተለመደ መብረቅ እና እነዚህ የእሳት ካሶች እየተጠማዘዙ ወደ መሬት በመውረድ በነኩት ሁሉም ነገር ላይ ጥፋት ያመጣሉ” ነበር ብሎ ተናግራል ፡፡ይህ መዓት ወደ ፊት ምን እንደሚሆን መልክ ነበር ይህ በመጨረሻው ምን እንደሚመጣ ሙከራ ነበር (ራዕ8፡7)፡፡ “ በረዶ ከመብርቅ ጋር በውሃ ውስጥ ሲያልፍ በግብፅ ምድር ህዝብ ከሆኑ ጀምሮ ይህን የሚመስል ሆኖ አያውቅም በጣም አደገኛ ነበር “ ፤ ተፈጥሮ የነበረው ሁሉም ነገር እንደገና ለሚመጣው ጥላ ነው (ራዕ16፡ 21) ፡፡ በረዶ በግብፅ ውስጥ መታ ሞትና ጥፋትም በሰዎች ላይ፣ በአውሬዎች ላይ፣ የመስክ እፅዋትና ሁሉም ዛፍ ላይ መጣ ፤ በጌሳም ብቻ እስራኤላዊያን ደህና ነበሩ( ቁጥር 26) ፡፡ እነዚህ ሁሉ መዓቶች ወደ እግዚአብሄር ሰዎች አልሆኑም፤ በዘጸ(10፡23) ውስጥ(የጨለማው መዓት) ሁሉም በጨለማ በነበሩ ጊዜ እስራኤላዊያን በብርሃን ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር በግልፅ የዕብራዊያን አምላክ ተብሎ እንዲጠራ ስሙን ሰርቶ ነበር፡፡

ዘጸዓት(9፡ 27-35); ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ላከባቸው ኃጢዓቱንም ተቀበለ ያህዌ ፃድቅ እንደሆነ ተናገረ ፤ ፈርዖን ትንሽ ከልቡ ጡሩ ቢሆንም ወደ ንስሀ ግን አላመጣውም ፡፡ ግሪንበርግ ሲናገር “ ጥፋቱን አረጋገጠ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ በጥፋቱ ሄደ ፡፡” ሙሴ ፈርዖን እንዲወጣ ጠራው እሱና ባለስልጣኖቹ ያህዌን እንዳልፈሩ አመለከተው ፤ ኮንስታብል ሲናገር “ እሱን መፍራት ማለት ለሱ በመማረክ በምድር ላይ ሁሉ ከፍ ያለ እንደሆነ መስገድ ማለት ነው” ፤ ፈርዖን ለእግዚአብሄር የከንፈር አገልግሎት ነበር የሰጠው ፡፡ የደረሰው ተልባና ገብስ ጠፋ ነገር ግን ስንዴውና አጃው አልጠፋም ምክንያቱም ያልደረሱ ምርት ናቸው ፡፡ሙሴ ፈርዖንንና ከተማዋን ወጣ እጁንም ወደ እግዚአብሄር ዘረጋ ሁሉም ነገር ቆመ ፤ ነገር ግን ፍርዖንና አገልጋዮቹ ልባቸውን አፀኑ ፤ ፍርዖንም እስራኤላዊያን እንዲሄዱ አልፈቀደም ፡፡

ዘጸዓት10; ይህ ምዕራፍ ስለ ስምንንተኛውና ዘጠነኛው መዓት ዝርዝር ይሰጠናል; ስለአንበጣው መዓትና ስለጨለማው ፡፡

መዝጊያ

እግዚአብሄር ብርሃን ሰጥቶናል ፤ መንፈስም ሰጥቶናል ፤ የእግዚአብሄርን ሙሉነት እንድንለምደው ይፈልጋል ፡፡ እንደ ግብፃዊያንና እንደ ፈርዖን “ እምቢ ይህን አልፈልግም” በማለት ለመምሰል ፈቃደኞች መሆን የለብንም ፡፡ ለእኛ ነፃ አውጪ ሰጥቶናል ፤ የተሰጠን ህይወት ስላለን በባርነት እንዳለ አክት(መስራት) ማድረግ አንችልም ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs: David C. Cook, 2001), p. 188.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 94.

  3. Tom Constable, Dr. Constable’s Notes on Exodus, p. 89; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf.

  4. Carl Friedrich Keil and Franz Delitzsch, Keil & Delitzsch Commentary on the Old Testament, p1:487, quoted in Constable, p. 90.

  5. Constable, p. 90.

  6. Wiersbe, p. 95.

  7. Victor P. Hamilton, Exodus: An Exegetical Commentary (Grand Rapids: Baker Publishing Group, 2011), p. 150.

  8. Hamilton, p. 151.

  9. MacArthur, p. 96.

  10. Moshe Greenberg, Understanding Exodus, 2nd ed. (Eugene, OR: Cascade Books, 2013), p. 129; quoted in Hamilton, p. 151.

  11. Constable, p. 92

ጥያቄዎች

  1. እንደ ዘጸ(9፡ 4) አገላለፅ በመቅሰፍቱ(መዓቱ) ምን ያክል የእስራኤላዊያን ከብቶች ሞቱ ? ምንድን የእግዚአብሄርን ባህሪይ ነበር የተገለጠው እስራኤላዊያንን እና ንብረታቸውን ሳያቃርጥ በመጠበቅ ?
  2. ሙሴን እንዲፀልይለት በጠየቀው ጊዜ የፈርዖን ፍላጎት ምንድን ነበር (ዘጸ 8፡8፣28; 9፡ 27-28) ? እስካሁን ክርስቲያን ያልሆነ ለፀሎት ጠይቃችሁ አያውቅም ? ይህ ስለዛ ሰው ምን ይገልጥላችኃል ?
  3. በዘጸ(9፡ 15-16) በሙሴ በኩል እግዚአብሄር ምንድን በማድረግ ለፈርዖን ገለጠለት ? ከዚህ ምንድን ልትማሩ ትችላላችሁ (ሮሜ 9፡17) ?
  4. እግዚአብሄር የፈርዖንን ልብ በማፅናቱ ለእስራኤላዊያን ዉጤቱ ምንድን ነበር ?
  5. በዘጸ(9፡ 27-28) የፈርዖን ንስሀ ምንድን ነበር ስህተቱ ? ንስሀ በአለማዊው እና በመፅሀፍ ቅዱስ መሀከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው (2ቆሮ 7፡ 10) ?
  6. በዘጸ(9-10) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 9:16

“However, I have let you live for this purpose: to show you My power and to make My name known in all the earth.”

የደነደነዉ የፈርዖን ልብ

ኦሪት ዘፀዓት 9-10 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

የፈርዖን ልብ ደንድኖ ነበረ፥ እናም እስራኤላዉያንን ለመልቀቅ ተገዳደረ። በዚህም ምክንያት እግዚዓብሔር ድንቅ እና ተዓምራቱን፥ በግብፅ ምድር ላይ አበዛ። በተለይ ደግሞ እነዚያ አስርቱ መቅሰፍቶች!

ልክ የፈሮዖንን የደነደነ ልብ እግዚዓብሔር እንዳየዉ ሁሉ፥ ያንተንም ያየዋል። ልብህን፥ ወደ እርሱ መንገድ አሳልፈህ እንክትሰጠዉ ድረስ በናፍቆት ይጠብቃል። እንዲህ ባይሆንም ግን እግዚዓብሔር ኃይሉን ያሳያል! ስሙንም በምድር ሁሉ እንዲታወቅ ያደርጋል! እርሱ ታላቁ እኔ ነኝ ነው!

"ነገር ግን ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ።"

ኦሪት ዘፀዓት 9:16

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘፀዓት 7:3፦ "እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።"
  • መዝሙረ ዳዊት 67:1-2፦ "እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ማዳንህን፥ መንገድህንም በምድር እናውቅ ዘንድ።"
  • የማቴዎስ ወንጌል 6:10፦ "ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፈት፡ ክፍል 32