Plagues 1-4
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እነዚህ በዘጸዓት ውስጥ አይነተኛ ምዕራፎች ናቸው ፤ የምናወራው ስለ ወረርሽኝ ነው ፡፡ የእነዚህ ወረርሽኝ አላማ (ሀሳብ) የራሱን ህዝብ ነፃ ለማውጣት ብቁ እንዳልሆነ የተሰማውን ይህን ሰው እግዚአብሄር ለመጠቀም ነበር ፤ ዘጸ(6፡ 30) የሚለዉ “ ሙሴም በእግዚአብሄር ፊት እነሆ እኔ ከንፈረ ቆላፋ ነኝ ፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል ?”
ትምህርት
ዘጸዓት(7፡ 1-3); “እግዚአብሄርም ሙሴን አለው እይ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሀለሁ ፤ ወንድምህም አሮን ነብይ ይሆንልሀል ” (ቁጥር 1) ፡፡ ይህ አስቀያሚ ንግግር ነበር ! ጥርጣሬና ጥያቄ ቢኖረውም እግዚአብሄር በሙሴ ተማመነ፡፡ “ ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ” (ቁጥር 2) ፤ “ እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ታምራቴን አበዛለሁ “(ቁጥር 3) ፤ እግዚአብሄር የፈርዖንን ልብ እንደሚያፀና ወይም ድንቁንና ታምራቱን እንዴት እንደሚያበዛበዝርዝር አላቀረበም ፡፡ እነዚህ ምልክቶች የሚያስታውሱን በፈርዖን ፊት ሁል ጊዜ የእግዚአብሄር አስፈሪ መገኘት እንደሚሆን ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህን ድንቅና ታምራቱን የሚገላፀው እንደ “ የማይካድ ስራዎች” እግዚአብሄር ያደረገው “ ሀይሉን ለማሳየትና የወኪሎችን የሙሴንና የአሮንን ትክክለኛ ለማረጋገጥ፡፡ “
ዘጸዓት(7፡ 4); የእጆቹ ስዕሎች የወዳችነት አልነበረም የእግዚአብሄር የቁጣ ስዕል እንጂ ፤ በአድስ ኪዳን ውስጥ ፈሪሳዊያን እጃቸውን በኢየሱስ ላይ ለማንሳት መፈለጋቸውን ምክንያቱም ሊገድሉት ስለፈለጉ የሚለውን ለመግለፅ ተመሳሳይ ቐንቐ ተጠቅሞ ነበር (ሉቃ 20፡ 19; ማር 14፡ 46) ፡፡
ዘጸዓት(7፡ 5-8); “ ግብፃዊያን ኤ እግዚአብሄር እንደሆንኩ ያውቁኛል “(ቁጥር 5) ፤ ይህ ፍርድ ለምን በዘጸ(12፡12) ላይ እንዲደገር አስፈለገ ? እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ለማስወጣት ለምን ፈለገ ? የግብፃዊያንን አምላክ ማምለክ ጀምረው ነበር(ሕዝ 20፡ 7-9) ፡፡ “ስለዚህ ሙሴና አሮን እግዚአብሄር እንዳዘዣቸው አደረገ”(ቁጥር 6) ፤ እግዚአብሄር በሰጣቸው አቅጣጫ ላይ አልጨመሩም እግዚአብሄር የተናገራቸውን ብቻ አደረጉ ፤ ሙሉ በሙሉ አብርዉ ተF0D5ዙ ፡፡ በቁጥር 8 ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሄር ለሙሴና ለአሮንን ባንድ ላይ ተናገራቸው ፡፡
ዘጸዓት(7፡ 9-11); “ ፈርዖን ታምራትን አሳዩኝ ሲላችሁ አሮንን በትርህን ወስደህ እባብ እንድትሆን በፈርዖን ፊት ጣላት በለው ፤ እባብም ትሆናለች ፡፡“ ይህቺን ብትር የተጠቀሙባት ለህዝብ እንደ ነፃ ማዉጫ ነበር ፤ ሙሴ እረኛ ነበር ፤ ኢየሱስ መልካም እረኛ ነው ፤ ያልተለመደ ነገር ለማድረግ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ሰዎችን እንደሚጠቀም ስዕል ነበር ፤ “ ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን በመግባት እግዚአብሄር ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡ “ የምር በትራ እባብ ሆናለች? አንዳንድ ሀተታ ሰጪዎች ተሳቢ ፍጡረ፣ አዞ ወይም ጭራቅ ሊሆን ይችላል ብለው ያስባሉ ፡፡ ኮንስታብል የሚጠቅስል ይህ ታአምራት የተጀመረበት ጊዜ እንደነበር ነው ፤ በመፅሀፍ ውስጥ አራት የታዕምራትን ጊዜያት እናያለን; በሙሴና በኢያሱ አማካኝነት፣ በኤልያስና በኤልሳህ፣ በክርስቶስና በሐዋሪያቶቹ እና መጨረሻው ሁለቱ ምስክሮች በራዕይ ፡፡ ማር(16፡ 17) ድንቅና ተአምራት ይሆናሉ ነገር ግን እንዲሆኑ መስራት አንችልም ፡፡ “ ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ የግብፅም ጠንቐዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ “ ፤ ይህ የተአምራቱ ጨለማ ጎኑ ነበር ፤ የራሳቸው ትንሽ የማታለያ ቦርሳ ነበራቸው ፡፡ የአስማት እውቀት ተቆጣጥራቸዋል(አሳዩ) ፤መፅሀፍ የሚለው ሰይጣን ራሱን እንደ ብርሃን መልዓክ ማስመሰል ይችላል (2ቆሮ 11፡ 14) ፤ ሁል ጊዜ ሰይጣንን መጠበቅ የምንችለው እግዚአብሄር ማድረግ የሚችለውን ለመኮረጅ ሲሞክር ነው ፡፡ ዋይሰርቤ ሲናገር “ ሰይጣን ለራሱ ሰዎች የውሸት ድንቅ ማድረግ እንዲችሉ ስልጣን ይሰጣቸዋል “ (2ተሰ 2፡ 9-10) ፤ ዋይሰርቤ ሲናገር “ የፈርዖን አስተሳሰብ ማንኛውንም ጅሆቫ ከሚያደርገው የተሸለ ማድረግ እንደሚችሉ ነበር !” (ማቴ 24፡ 24; ራዕ 13፡ 11-16) ፡፡ ከሙሴ ጊዜ እስከ መጨረሻው በሁሉም መንገድ የጠላትን ማታለል እናያለን ፤ ይህን መጠበቅና መፈተን አለብን (1ዮሐ 4፡1)፡፡
ዘጸዓት(7፡ 12); “ እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ እባቦችም ሆኑ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች “ ፤ በትሮች ብዙ ነው የአሮን በትር ሁሉንም በላቻቸው ፡፡ የእግዚአብሄር በትር በአንዳፍታ የእነርሱን በትሮች የሰይጣንን አሸነፈች ፤ ለምን ? ዘሩ ነፃ መዉጣት ስለነበረበት እናም ህዝቡን የሚያነፃ መንገድ ላይ ማንም ስለሌለ ፡፡ በአድስ ኪዳንም ውስጥ እነዚህን የውሸት ሁኔታዎችን ሁል ጊዜ የውሸት ወንድሞችና ውሸቶች የትኛውም ቦታ ብትሄዱ በክርስቲያኑ ውስጥ ታያላችሁ (ሮሜ 10፡ 1-3); የውሸት ወንድም (2ቆሮ 11፡ 26); የውሽት ወንጌል (ገላ 1፡ 6-9) ፡፡ ወደ መጨረሻው ጊዜ ስንቀርብ ዛሬም ከሀሰት ወንጌል ልንጠነቀቅ ይገባናል ፤ የኛ አምላክ ሁል ጊዜ የውሸት እውነታቸውን ያሸንፋል ፡፡
ዘጸዓት(7፡ 13-16); “ እግዚአብሄር እንደተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና አልሰማቸውምም ፡፡“ ደግሞ ደግሞ የፈርዖን ልብ ሲፀና እናያለን ፤ሙሴና አሮን በማለደ በመሄድ ለፈርዖን ሰዎስት ጊዜ በመደጋገም በመዓቱ ትምህርት ነግረውት ነበር፡፡ “ እንዲህም ትለዋለህ የዕብራዊያን አምላክ እግዚአብሄር እንደነግርህ ወደ አንተ ላከኝ….” ከአስሩ መዓቶች ሰባቱ ፈርዖንን ያስጠነቀቁ ነበሩ ፤ ሰዎስቱ መዓቶች ህዝቡን ያለማስጠንቀቂያ የተመለከቱ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(7፡ 17); “ እነሆ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል ፡፡” የአባይ ወንዝ ለሁሉም ነገር የውሃ ምንጫቸው ነበር ፤ አንድ ሀተታ ሰጪ ይህን በተፈጥሮ በቀይ አፈርና በቀይ ዋቅላሚ መሀከል የተፈጠረ ሊሆን ይችላል ብሎ ገልፆታል ፤ መፅሀፍ የሚለዉ ግነ ደም ነው ስለዚህ እኔ የማምነው ደም እንደሆነ ነው ፡፡ “ መምታት” የሚለውን ቃል ሰዎስት በተለያዩ ጊዜ ተጠቅመዉታል ፤ በግብፃዊያን ላይ የዚህ የመምታት ስዕሎች በዘጸ(2፡ 12) ሙሴ በመታው ጊዜ ግብፃዊው ሞተ፣ በዘጸ(17፡ 6) ሙሴ አለቱን በመታው ጊዜና በዘጸ 12 እግዚአብሄር በኩራቸውን በመታ (በገደለ) ጊዜ ፡፡
ዘጸዓት(7፡ 18-19); አሳዎቹ ሞቱ፣ ውሃው ሸተተ፣ እና ግብፃዊያን ከአባይ ለሚጠጣ ውሃ ማግኝት አልቻሉም ፡፡ በዚህ መዓት ውስጥ እግዚአብሄር በምድር ላይ ያለውን ስልጣን ያሳየበት ነበር (ቁጥር 18) ፤ ከዚያም እግዚአብሄር በመላው ግብፅ ያለውን ውሃ ወደ ደም ቀየረው -“ በወንዞቻቸውም፣ በመስኖቻቸውም፣ በኩሬዎቻቸውምና በዉሃ ማከማቻቸው ሁሉ…….በእንጨት እና በድንጋይ እቃ ላይ ሁሉ፡፡ “አንድ ጥቂት አካባቢ ብቻ አልነበረም የተቀየረው ሁሉም ነገር ደም ሆነ ከዉሃው ምንጭ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ውሃ የያዙ እቃዎች እንካን ሳይቀሩ(ቁጥር 19) ፡፡ ዋይሰርቤ ሲናገር “ ይህ በአባይ ወንዝ በራሱ ላይ ያለ ፍርድ ነበር ያዩት የነበረው እንደ አምላክ የደስታ፣ የአባይ አምላክ ለለምነት፣ የአባይ አምላኮች ፡፡“
ዘጸዓት(7፡ 20-22); “ ሙሴና አሮንም እግዚአብሄር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ “ ፤ እግዚአብሄር ስላደረገው መዝሙረኛውም የፃፈው መዝ (78፡ 43-44 እና 105፡ 29) ፤ በአባያ ወንዝ ያሉ አሳዎች ሞቱ በመላው ግብፅ ምድር ውስጥ ደም ነበር ፡፡” የግብፅም ጠንቐዮች በአስማታቸውእንዲሁ አደረጉ እግዚአብሄርም እንደተናገረው የፈርዖን ልብ ጸና አልሰማቸውምም ፡፡”ቀድሞውኑ ውሃው ደም ከነበረ ግብፃዊያን ተመሳሳይ እንዴት ሊያደርጉ ቻሉ ? ምናልባት እግዚአብሄር እያወራ ያለው መሬት ላይ ስላለው ውሃ እንጂ ከመሬት በታች ስላለው ስላልነበር ስለዚህ ጥቂት ውሃ ቆፍረው ይሆናል 9ቁጥር 24) ፡፡ ግን እንደምናውቀው ይህ ውሸት ነበር ምክንያቱም የተጠቀሙት አስማታዊ ድርጊት ስለነበር ፤ የፈርዖን አስማተኞች ያደረጉት ሀይለኛ ካደረጋቸው በተቃራኒው ሙሴና አሮን ያደረጉት ነበር ፡፡
ዘጸዓት(7፡ 23-25); “ ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ ይህንም ደግሞ በልቡ አላኖረም “ በውሃ ማጣት ምክንያት ህዝቡ እየሞተ እንደሆነ ፈርዖን አላሳሰበውም ፡፡” ሁሉም ግብፃዊያን በወንዙ አጠገብ ውሃ ሊጠጡ ቆፈሩ “(ቁጥር24) ፤ እዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሄር ምድር ላይ ያለውን ውሃ ብቻ እንደቀየረ ፍንጭ እናገኛለን ፡፡” እግዚአብሄር ወንዙን ከመታ በኃላ ሰባት ቀን ተፈፀመ “ ፤ ይህ የነበረው ሰባት ቀን ውሃው ደም የሆነው ወይም ቀጣዩ መዓት እስኪመጣ ሰባት ቀን ነበር ፤ ይህ ብቸኛው ከዘጠነኛው መዓት የሰዎስት ቀን ጨለማዉ ውጭ ከአስሮቹ መዓቶች በጊዜ ገደብ የተገለፀ ነው (ዘጸ 10፡ 21-23) ፡፡
መዝጊያ
ዕብ(10፡ 31) የሚለው “ በህያው እግዚአብሄር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው !” ፈርዖን የተጋዘው በሰላም መንገድ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሄርን በመቃወምና ልቡን በማጽናት ፤ በተጨማሪም በህዝቡ ላይና በቤተሰቡ ላይ ጥፋትን አመጣ ፡፡ ሙሴም የዚህ አካል ነበር ፤ ሙሴና አሮን ህዝቡን ነፃ ለማዉጣት ረዱ ስለሆነም ነፃ ሊወጡ ቻሉ ፤ ለምን ? ነፃ መውጣት ያስፈልጋቸዋል በዚህም መሲሁ በመልኩ ውስጥ መምጣት ይችላል ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 98.
Victor P. Hamilton, Exodus: An Exegetical Commentary (Grand Rapids: Baker Publishing Group, 2011), pp. 95-96.
Tom Constable, Dr. Constable’s Notes on Exodus (available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf) pp. 74-75.
Nelson’s Commentary, p. 99.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 188.
Wiersbe, p. 188.
Nelson’s Commentary, p. 100.
Wiersbe, p. 189.
ጥያቄዎች
-
በዘጸ(7-8) ውስጥ የነበሪት የመጀመሪያዎቹ አራቱ ቁጣዎች (መዓቶች)(መቅሰፍቶች) ምንድን ነበሩ ?ለምን በእነዚህ በተለዩ መዓቶች እግዚአብሄር በመጀመሩ ምን ትምናለህ ? ፤ የመዓቶቹ ቅደም ተከተል አስፈላጊነት አለው ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በዘጸ(7፡ 1) እግዚአብሄር ከሙሴ ጋር ሲያወራ ስላለው ምን ታስባላችሁ ?
-
በዘጸ(7፡ 4) በፈርዖንና በግብፃዊያን ላይ ለመከወን ያሰበው “ፍርዶች” ምን ነበሩ ዘጸ(7፡ 1-5) ?
-
እግዚአብሄር ከላካቸው ምዓቶች ውስጥ የትኛው ነበር የመጀመሪያው አስማተኞቹን ያሳመነው ? ይህ ስለሱ ያላቸውን አመለካካት ቀይራል ? ለምንድነው አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሄር ሀይል ያዉቃሉ ነገር ግን አያመልኩትም ? (ሮሜ 1፡ 18-25)
-
በዘጸ(8፡ 20-30) በእስራኤላዊያን ላይ ሳይሆን በግብፃዊያን ላይ እግዚአብሄር የሰደዳቸው አራቱ መዓቶች ምንድን ነበር አስፈላጊነቱ ? ለፈርዖንና ለግብፃዊያን እና ለእስራኤል ልጆች ለሁለቱም ቡድን እግዚአብሄር ስለራሳቸው ምን ነበር የገለጠላቸው ?(ዘጸ 11፡7; ዮሐ 15፡ 19; ሮሜ 1፡ 1; 2 ቆሮ5፡ 17; 1ጴጥ 2፡ 9)
-
በዘጸ(7-8) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳየህ(አስረዳህ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 7:5
“The Egyptians will know that I am Yahweh when I stretch out My hand against Egypt, and bring out the Israelites from among them.”
ፈርዖን፥ በእግዚዓብሔር እጆች
ኦሪት ዘፀዓት 7-8 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚዓብሔር ግብፅን በከባድ መቅሰፍቶች እንዲመታ የፈቀደዉ ለምንድን ነዉ? ምክንያቱም፥ ግብጻዉያም እግዚዓብሔር አምላክ እንደሆነ እንዲያዉቁ እና እስራኤላዉያን ደግም እንደ ነፃ አዉጪያቸዉ እንዲያዉቁት ነው።
እግዚዓብሔር የአንተም ነፃ አዉጪ ነዉ። በኃጥያት ምክንያት ሁላችንም ሞት የተገባን ብንሆንም እግዚዓብሔር በልጁ በኢየሱስ ዓለምን ነፃ አዉጥቷል። አምላክ እሱ ብቻ እንደሆነ እንድታዉቅ ከምታልፍበት ከባድ ሁኔታ ዉስጥ ያወጣሃል! አሁን በዚህ ጊዜ፥ በህይወትህ ዉስጥ እግዚዓብሔር ነፃ አዉጪ መሆኑን ሊያሳይህ እንድታልፍበት የፈቀደዉ ነገር አለ? ወደ እርሱ ተመለስና ነፃ ያዉጣህ!
"ግብፃውያንም፥ እጄን በግብፅ ላይ በዘረጋሁ ጊዜ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው ባወጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆነሁ ያውቃሉ።"
ኦሪት ዘፀዓት 7:5
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 22:1-4፦ "ዳዊትም እግዚአብሔር ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ እጅ ሁሉ ባዳነው ቀን የዚህን ቅኔ ቃል ለእግዚአብሔር ተናገረ። እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፤ እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኃኒቴ ሆይ፥ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ።"
መዝሙረ ዳዊት 34:7-8፦ "የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል። እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።"
ወደ ገላትያ 5:1፦ "በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 31
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።