The Pentateuch Exodus

God Promises Deliverance

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 30 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እግዚአብሄር ህዝቡን ወደ ትክክለኛው ነፃ አዉጪ ወደ ያህዌ ለማምጣት ሙሴን እንደ ነፃ አውጪ ተጠቀመበት ፤ አስታውሱ እግዚአብሄር የሰጣቸውን ምልክት በትራ ወደ እባብ ተቀየረች፣ ለምፅ የሆነችው እጁና ዉሃው ወደ ደም መቀየሩን ከዚያም እስራኤላዊያን ሙሴንና አሮንን አመናቸው ፡፡ ነገር ግን ወደ ፈርዖን በሄዱ ጊዜ እንዲሄዱ ሊለቃቸው አልፈቀደም ፡፡ ሙሴ ምዕራፍ አምስትን “ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ለምንድን እኔን ትልከኛለህ” በማለት ጨረሰ ፡፡

በጥሪህ ውስጥ ስትሆን ሁል ጊዜ ከሌላ ሰዉ ተቃርኖና አለመረዳትን ጠብቅ ፡፡ እንደ አገልጋይ መሪ ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ ልታሳልፍ ይገባሀል(ይገባችኃል) ፤ ሙሴ በምዕራፍ አምስት ውስጥ ይህንን ነው ያደረገው በእግዚአብሄር ያለውን ፍርሀት በመግለፅ ፡፡

ትምህርት

ዘጸዓት(6፡ 1-2); ለሙሴ መለሰለት “ በጸናች እጅ ይለቅቃችኃልና በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋልና አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታይለህ “ ፤ ለሙሴ በመለሰው ውስጥ እግዚአብሄር ሁለት ጊዜ ሲናገር “ በጸናች እጄ ምክንያት “ ፤ ለሙሴ በመለሰው ውስጥ ሰባት ጊዜ እግዚአብሄር ሲናገር “ የማደርገውን” (ቁጥር 1፣ 6፣ 7፣ 8) ፡፡ ከዚያም እግዚአብሄር ለሙሴ ተናገረው ፤ ሙሴ እግዚአብሄርን በሚሰማ መልኩ በሚመስል ሰማው ፡፡ ለሙሴ በሚሰጠው ምላሽ ውስጥ ብዙ ጊዜ እግዚአብሄር ሲናገር “ እኔ ያህዌ(እግዚአብሄር) ነኝ” (ቁጥር 2፣ 6፣ 7፣8) ፤ (ዘጸ33፡11; ዘዳ 34፡10) ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 3-8); እግዚአብሄር ከሙሴ ጋር ማውራቱን ቀጠለ ከዚያም ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሲገለጥ ያህዌ የሚለውን ስሙን(ለሙሴ የገለጠዉን) በፍፁም እንዳልገለጠላቸው ገለፀለት ፡፡ እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ያለውን ኪዳኑን ማስታወሱንና ከግብፅ የእስራኤልን ስቃይ መስማቱን ነገረው ፤ እግዚአብሄር እስራኤልን ከግብፅ ባርነት ነፃ እንደሚያወጣና ቃል የተገባችውን ምድር ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን እንደሚሰጣቸው ቃል ገባለት ፡፡ በመሰረቱ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ከአብርሃም ወደ ሙሴ እንሻገራለን ፡፡

ሳይልሀመር ሲናገር ዘጸዓት 6 የኦሪት ህግ መፅሀፍ( የመጀመሪያዎቹ አምስቱ የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ) ዋና ሀሳብን ይሰጠናል

  1. እግዚአብሄር ኪዳኑን ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር መሰረተ (ዘጸ 6፡4)
  • በዘፍ(12፡ 1-3) ውስጥ እግዚአብሄር ከአብራም ጋር ኪዳን አደረገ በዘፍ15፣ በዘፍ 17 እና በዘፍ22 ውስጥ አረጋገጠለት
  • በዘፍ 15 ውስጥ እግዚአብሄር አብራምን ዘሩ በሌላ ምድር እንደ ምፃተኛ እንደሚኖር ነገረው (ጳውሎስ ይህን በብዙ ተናግራል)
  • እግዚአብሄር ኪዳኑን አስታወሰ ( ዘጸ 6፡5)
  1. እግዚአብሄር ህዝቡን ነፃ እንደሚያወጣ ቃል ገባ (ዘጸ 6፡6)

እግዚአብሄር እንደ እራሱ ህዝብ እንደሚቀበላቸው ቃል ገባለቸው (ዘጸ 6፡7)

ይህ ንድፍ በአድሱ ኪዳን ውስጥ ይደገም ይሆናል ፡፡

በሉቃ (4፡ 18-19) ውስጥ ኢየሱስ ኢሳ(61፡ 1) በመጥቀስ “ የእግዚአብሄር መንፈስ በእኔ ላይ ነው…..ለተማረኩትም ነፃነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ “ ብሎ በመናገረ ፤ ኢየሱስ ነፃ አውጪው ሰዎችን ነፃ አውጥቶ ለማስቀመጥ መጣ ፡፡

በክርስቶስ ልጆች ሆነናል (ኤፌ 1፡5) ፡፡

እግዚአብሄር ቃል ወደ ተገባችው ምድር እስራኤልን እንደሚያስገባቸው ቃል ገባላቸው (ዘጸ6፡ 8)

ምድር በእስራኤል የምር ጠቃሚ ነው ምክንያቱም መሬት በምትሰጥ ጊዜ በህግ መፅሀፍ ከተመሰረተው ከእግዚአብሄር ኪዳን ተቃራኒ ስለምትሄድ ፡፡

ለዛ ነው እንደ አማኝ እስራኤል ምድሩን እንዲያገኝና እንዲጠብቅ መርዳት የምንፈልገው ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 9-12); ሙሴ እግዚአብሄር ምን እንደተናገረው ለእስራኤላዊያን በነገራቸው ጊዜ አለዳመጡትም ፤ ነገሩን አስታውሱ እስካሁን እስራኤላዊያን ነፃ አልወጡም ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ፈርዖን እንዲሄድና ከምድሩ እንዲወጡ እስራኤላዊያንን እንዲለቃቸው እንዲነገረው ባዘዘው ጊዜ ሙሴ የራሱ ሰዎች ያለሰሙትን ለምን ፈረዖን ይሰማኛል የሚለውን ለማወቅ ፈለገ ፡፡ ሙሴ አይነተኛ የተጠቂነትን ካርድ ሳበ “ እኔ ደካማ ተናጋሪ ስለሆንኩ” ፈርዖን አይሰማኝም፡፡

ዘጸዓት(6፡ 13); በሙሴ አለመብቃት ጥያቄ መከራከርን ከመቀጠል ይልቅ እግዚአብሄር ትዕዛዙን እንደገና አረጋገጠ ፡፡ መፅሀፉ የሙሴንና የአሮንን የዘር ግንደ ለመስጠት አዚህ ጋር ይቆማል ፤ ፍራንሲስ ስቻእፈር ሲናገር “ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የማይጠቅም ሰው የለም ” ሁሉም ጠቃሚ ናቸው ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 14-16); እነኚህ ጥቅሶች ያዕቆብ በልያ ያገኛቸውን ሰዎስት ልጆች የዘር መስመር ይሰጣሉ; ሮቤል፣ ስምዖንና ሌዊ ፤ ቁጥር 16 የሚጠቅስልን የሌዊ ወንድ ልጆች ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ፤ (በዚህ የዘር መስመር በመቀጠል ብንከተል ሙሴና አሮን ሌዋዊያን መሆናቸውን እናያለን) ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 17); ይህ ቁጥር የሚጠቅስልን የጌድሶን ወንድ ልጆች የሌዊ የልጅ ልጆችን ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 18); ይህ ቁጥር የሚጠቅስልን የቀዓትን ወንድ ልጆች የሌዊ የልጅ ልጆችን ፤ በቁጥር 20 ላይ እንበረምም የሙሴና የአሮን አባት እንደሆነ ተጠቅሳል ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 19); ይህ ቁጥር የሚጠቅስልን የሜራሪን ወንድ ልጆች የሌዊ የልጅ ልጆችን ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 20); እምበረምም የአጎቱን ልጅ ዮካብድን አገባ ፤ ሁለት ወንድ ልጆችም ወለደችለት አሮን (ትልቁ) እና ሙሴ (ትንሹ) ፤ ማሪያም ነበረቻቸው (የሙሴ እህት) በነፃ ማዉጣቱ ውስጥ ዋና ድርሻ የነበራት (ሚክ 6፡ 4) ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 21-22); እነዚህ ቁጥሮች የሚጠቅሱልን የይስዓር ልጆችና የዑዝኤል ልጆችን የሙሴ የአጎት ልጆችን ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 23); አሮን ኤልሳቤጥን አገባ (በይሁዳ ነገድ ውስጥ የሚታወቀዉን ቤተሰብ የአሚናዳብን ሴት ልጅ) ፤ አሮን የሌዋዊያን ዘር ነበር የእስራኤልም ካህን ሆነ ፡፡ ኤልሳቤጥ ከይሁዳ ነገድ ነበረች (ዘኁ 1፡7; 2፡3) ፡፡ ይሁዳ ቀስ በቀስ ወደ ዳዊት ከዚያም በመጨረሻ ወደ መሲሁ ይወስደናል ፡፡ በአሮን ቤተሰብ የሌዋዊያን ዘርና የይሁዳ ዘር በአንድ ላይ መጡ ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 24); ቆሬ (የይስዓር ልጅ ቁጥር 21 እዩ) ለሙሴ የአጎቱ ልጅ ነበር ፤ ቆሬ በሙሴ ላይ ተቃውሞ አስነሳ (ዘኁ16)፤ ዘኁ (26፡ 11) የሚገልጥልን ቆሬና ሁሉም ሰዎች ሙሴን የተቃወሙት መሞታቸውንና የቆሬ ልጆች መዳናቸውን ነው ፤ እነዚህ የቆሬ ልጆች መዝሙር 84፣ 85 እና 87 ፅፈዋል ፡፡ በአባታችን መጥፎ ውሳኔ የማንቀጥል ከሆነ የቆሬ ልጆች ለኛ ተስፋ ይሰጡናል ፤ አንዳንዶቻችሁ ጡሩ የሆነ ዘር የላችሁም ችግር የለውም ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 25); የአሮን ልጅ በዘኁ 25 ጀግና የነበረው የፊንሀሳ አባት ኤልአዛር ነበር ፤ እነኚህ ከሌዊ ቤተሰብ የመጡ ጀግኖች ናቸው ፡፡

ዘጸዓት(6፡ 26-27); አነዚህ አሮንና ሙሴ ከግብፅ እንዲያወጣቸው እግዚአብሄር ያዘዛቸው እራኤላዊያን ናቸው ስለዚህ አሮንና ሙሴ ለፈርዖን የሚናገሩ ነበሩ ፡፡ ዋይሰርቤ ሲናገር “ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ጠራ ማለት እግዚአብሄር ያስችላል ማለት ነው ፡፡“

ሀሚልተን በዘጸ(6፡ 14-24) ውስጥ የተዘረዘረውን የዘር ግንድ በዘፍ(15፡ 13-16) ያለውን ትንቢት መፈፀሙን ያገናኘዋል ፤ በዘጸ(6፡ 16) የሚገልፀው መጀመሪያውን ትውልድ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ በባርነት የኖሩ የሌዊ ወንድ ልጆች ናቸው ፤ በዘጸ(6፡ 18) የሚጠቅስልን ሁለተኛው ትውልድን ፤ የሙሴና የአሮንን አባት የቀዓትን ልጅ እንበረምን ነው ፤ ዘጸ(6፡ 20) የሚጠቅስልን ሰዎስተኛው ትውልድን ሙሴንና አርንን የእንበረምና ዮካብድን ልጆች ሲሆን ፤ ዘጸ(6፡ 23) የሚጠቅስልን አራተኛውን ትውልድ የአሮንን ልጆች ናዳብ፣ አብዮድ፣ አልአዛርና ኢታምር ቃል የተገባቸውን ምድር ከሚወርሱት ይሆናል ፡፡

መዝጊያ

ሁሉም ነገር የሚያመለክተን ወደ ነፃ አውጪ ነው ፤ ይህን ልታመን ትችላለህ ? በአንዲት በማትረባ ስም ኤልሳቤጥ (የአሮን ሚስት) የአሚናዳብ ሴት ልጅና የነአሶን እህት ነበረች የሌዋዊያን የዘር መስመር ወደ መሲሁ ያመለክተናል ! ሁለቱም በክርስቶስ የዘር መስመር ውስጥ ነበሩ (ሉቃ 3፡ 32-33) ፡፡

  1. John H. Sailhamer, The Pentateuch as Narrative (Grand Rapids: Zondervan Publishing House, 1992; ePub Edition 2017), n.p251.

  2. Francis Schaeffer, No Little People (Wheaton, IL: Crossway Books, 2003), p. 10.

  3. Wiersbe, p. 187.

  4. Victor P. Hamilton, Exodus: An Exegetical Commentary (Grand Rapids: Baker Publishing Group, 2011), p. 110.

ጥያቄዎች

  1. በዘጸ (6፡ 3) ላይ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ባልገለጠላቸው እግዚአብሄር ለሙሴ በምንድን ገለጠለት ? ይህ ስም ለምን ነበር አስፈላጊነቱ ?
  2. በዘጸ(6፡ 6-8) እግዚአብሄር በሙሴ በኩል ለእስራኤላዊያን ቃል የገባላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው ? እስራኤላዊያንን ለማዉጣት ሙሴ የላከው ምን ነበር ? ይህ እንዴት ነበር የክርስቶስ መልክ የነበረው ? (ሉቃ 4፡ 18; ሮሜ 11፡ 26; ቆላ 1፡ 13-14)
  3. የእስራኤላዊያን መልስ ለእግዚአብሄር ቃል ምን ነበር ዘጸ (6፡ 9) ? በዚህ መልኩ ለእግዚአብሄር የመለሳችሁበትን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ?
  4. አሮንና ሙሴ ከሌዋዊያን የዘር መስመር ውስጥ መምጣታቸው ለምን አስፈላጊ ነበር ?
  5. በሁለቱም ዘጸ(6፡ 12) እና 30 ሙሴ ያቀረበው ተመሳሳይ ሀሳብ በሱ ንግግር ምክንያት ፈርዖንእንደ ማይሰማው ነበር ፤ እግዚአብሄር ድክመቱን ሳይንቅ እስካሁን ተጠቀመበት ? ሌሎችን ለማበረታታት ይህን እንዴት ልትጠቀመው ትችላለህ ?
  6. በዘጸ6 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳየህ(አስረዳህ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 6:2-3

“Then God spoke to Moses, telling him, ‘I am Yahweh. I appeared to Abraham, Isaac, and Jacob as God Almighty, but I did not reveal My name Yahweh to them.’”

ነፃ የመዉጣት ተስፋ

ኦሪት ዘፀዓት 6 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

በመጀመሪያዉ ዙር እግዚዓብሔር እስራኤላዉያንን ከእስራታቸዉ አላወጣቸዉም። ሙሴም ብሶቱን አሰምቷል! እግዚዓብሔርም ማን እንደሆነ እና የተስፋ ቃሉን በማስረዳት፥ ለሙሴ በቀጥታ መለሰለት። ለአብርሃም፣ ለይስሓቅ እና ለያዕቆብ እግዚዓብሔር ራሱን እንደገለጠላቸዉ ለሙሴ አስታወቀዉ። ለእነሱ ሲገለጥ "ሁሉን የሚችል አምላክ" ሆኖ ሲገለጥ ለሙሴ ግን "ያለና የሚኖር" ሆኖ ነው"፥ ትርጓሜዉም "እኔ፥ እኔ ነኝ" ማለት ነው። ይህ ስም ሙሉዕነቱን፦ ለዘላለም ኗሪነቱን፥ ሉዓላዊነቱን፥ ኃይሉ ገደብ የሌለዉ እና በሁሉም ቦታ የሚገኝ መሆኑን የሚገልፅ ነው። ይህ የሙሴን ሰበብ መስጠት መቋጨት ነበረበት። እግዚዓብሔር አምላክ የሰጠዉን ተልዕኮ ለመፈፀም እምነት የሚሆነዉን መተማመን ይዞ መሄድ ነበረበት!

አንተስ ምን ይመስለኃል? ሁሉን የሚችለዉን አምላክ፥ "ጌታ ነኝ" የሚለዉ አብሮነት እና በምትጓዝበት መንገድ ሁሉ የሚባርክህን ማወቅ በቂ ነው? ወይስ እግዚዓብሔርን ለምን እንደማትከተልዉ ሰበብ መስጠትህን ትቀጥላለህ? አስታዉስ፥ ታላቁ "እኔ ነኝ" ነው!

"እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው አለውም፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር።"

ኦሪት ዘፀዓት 6:2-3

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኢሳይያስ 46:9-10፦ "እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም። በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ።"

የዮሐንስ ወንጌል 8:58፦ "ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።"

የዮሐንስ ራእይ 1:8፦ "ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፈት፡ ክፍል 30