The Pentateuch Exodus

Moses Given Powerful Signs

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 4-5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 29 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሙሴ በመፅሀፍ ውስጥ ከተመዘገቡት በጣም በተለየ ማግኘት ከእግዚአብሄር ጋር ተገናኘ ፤ እግዚአብሄር ሙሴን በመጠቀም ከግብፅ እስራኤላዊያንን ነፃ ለማውጣትና ነፃ አወጪ ወደ ሆነው ኢየሱስ እንዲያመለክት ነፃ አዉጭ አደረገው ፡፡

ትምህርት

ዘጸዓት(4፡ 1-5); ትናትና እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ፈርዖን እንዲሄድ በነገረው ጊዜ ከተጠቀማቸው አምስት ምክንያቶች ውስጥ ሁለቱን ተመልክተናል; 1) እኔ ማነኝ; 2) የአንትን(የእግዚአብሄርን) ስም አላውቀውም ፡፡ ዛሬ ሙሴ የሰጣቸውን ተጨማሪ ሰዎስቱን ምክንያቶች እንመለከታለን ; ሰዎስተኛው ምክንያት ሙሴ ያቀረበው ሽማግሌዎቹ እኔን አያምኑኝም ፤ አይሁዳዊያን ለማረጋገጥ ሁል ጊዜ ምልክት እንደሚሹ ሙሴ ያውቃል ፤ በተጨማሪም ማረጋገጫ እንደሚያስፈልጋቸው ያውቃል እግዚአብሄርም ሙሴን ተናገረው በትሩን መሬት ላይ እንዲወረውረው ፤ “መወርወር” ይህ ቃል ፈርዖን የእብራዊያን ወንድ ልጆች ወደ አባይ እንዲጣሉ ህዝቡን ለማዘዝ ከተጠቀመበት ቃል ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄር በታዘዘ ጊዜ በትሩ እባብ ሆነ ሙሴም ከእርሳ ሮጠ ፤ እግዚአብሄር ሙሴን ጅርታን እንዲይዛት ነገረው ባደረገውም ጊዜ ወዲያውኑ ተመልሳ ብትር ሆነች ፡፡ ምልክት 1; በትራ እባብ ሆነች ከዚያም እንደገና በትር ሆነች ፤ እግዚአብሄር ይህን አደረገ በዚህም እስራኤላዊያን ያምናሉ በተለይም ሽማግሌዎቹ ፡፡ እግዚአብሄር ምልክትን ስለሰጠ ሽማግሌዎች በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ አምላክ ቢያምኑም ሙሴ ምክንያት አቀረበ ፡፡

ዘጸዓት(4፡ 6-8); እንደታዘዘው ሙሴ እጁን በብብቱ ውስጥ አስቀመጣት ለምፅም ሆነች ፤ ከዚያም እግዚአብሄር ሙሴን እጁን ወደ ብብቱ እንዲመለሳት ነገረው እጁም ዳነች ፡፡ ምልክት 2; የሙሴ እጅ ለምፅ ሆነች ከዚያም ለመፁ ዳነ ፤ በመጀመሪያው ምልክት ካላመኑ እግዚአብሄር “የሁለተኛውን ምልክትማስረጃ” ሰጠው ፡፡

ዘጸዓት(4፡ 9);ምልክት 3; በመጀመሪያው ወይም በሁለተኛው ምልክት የማያምኑ ከሆነ ሙሴ ከአባይ ውሃን በመውሰድ ደረቅ መሬት ላይ እንዲያፈሰው ታዘዘ በዚህም ወደ ደምም ይቀየራል ፡፡ ለሁሉም ነገር አባይ የውሃ ምንጭ ነበር !

ዘጸዓት(4፡ 10); አራተኛው ሙሴ ጥሩ ተናጋሪ እንዳልሆነ ተናገረ ፤ ሙሴ ትኩረቱ በራስ ላይ እንጂ በእግዚአብሄር ላይ አልነበረም ፤ዋይርስቤ ሲናገር “ ትክክለኛ ትህትና በመጠኑም ቢሆን ለራስ ማሰብ አይደለም ባጭሩ ስለምንም አለማሰብ ነው ነገር ግን ሁሉንም እግዚአብሄር ይሰራዋል ፡፡”

ሀሚልተን አራት ምክንያቶች ይጠቅሳል ለምን የሙሴ ክርክር ልክ እንደሚሆን; ምናልባት ሙሴ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ለማስወገድ ስለፈለገ፣ ምናልባትም የእውነት ሙሴ የንግግር ችግር ስላለበት፣ ማናልባት ሙሴ ዕብራዊ ለመናገር ስለሚያስቸግረው (ግብፃዊ ሆኖ ስላደገ) እና ምናልባት ሙሴ ለህዝብ መናገር ስለሚጨንቀው ፡፡ ዋይርስቤ ሲናገር “ ሙሴ ኩራቱን እየሸፈነ ነበር ከዚያም በድክመቱን በጥርጣሬ ባዶ የሆነ ንስሀ ገባ “

ዘጸዓት(4፡ 11-12); እግዚአብሄር በሚገባ “ አፍ እሆንሀለሁ ! ይምትናገረውንም አስተምርሀለሁ” በማለት መለሰለት፤ የአባቴ መንፈስ በእኛ በኩል ይናገራል ! በምንጠይቅ ጊዜ በመንገድ ላይ ላሉት ሰዎች ምን እንደምንናገር አናውቅም ይህ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ በእኛ በኩል ለመናገር በቂ እንዳልሆነ ነው ፡፡

ዘጸዓት(4፡ 13-14); አምስተኛ ሙሴ ይህን የሚሰራ ሌላ ሰው እንዲልክ እግዚአብሄርን ጠየቀው ፤ ይህ እግዚአብሄር በእውነት ንደቱን የገለጠበት የመጀመሪያ ጊዜ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ምድርንና የሰራውን ሁሉ ለማጥፋት እንዳቀደ በተናገረ ጊዜ እንደተናደደ አልተናገረም የተናገረው “በልቡ እንዳዘነ” ነበር (ዘፍ 6፡6) ፡፡ ዳዊት ሲፅፍ “ የቁጣህን ፅናት ማን ያውቃል ? ከቁጣህ ግርማ የተነሳ አለቁ ”(መዝ 90፡11) ፡፡ በዘጸ(34፡ 6) እግዚአብሄር ሲናገር “ እግዚአብሄር- እግዚአብሄር መሀሪ ሞገስ ያለው ታጋሽም ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፡፡” እግዚአብሄርም በሙሴ ምክንያት ተናደደ ስለሆነም እግዚአብሄር ለሱ ለመናገር አሮንን መጠቀም እንደሚችል ተናገረው ፤ ዋይሰርቤ ሲናገር “ አንዱ በጣም የሚያመው ዳኝነት እግዚአብሄር መላክ የሚችለው የራሱን ሰዎች ለፍቃዳቸውለራሳቸው መንገድ መተው ነው፡፡ “

ዘጸዓት(4፡ 15-17); “ አንተም ትናገረዋለህ ቃሉንም በአፉ ታደርገዋለህ እኔ ከአፍህና ከአፉ ጋር እሆናለሁ የምታደርጉትንም አስተምራችኃለሁ፡፡ “ ሙሴ ስለችሎታው ለእግዚአብሄር ለመናገር ተጠራጠረ ነገር ግን እግዚአብሄር ምን እንደሚናገርና እንደሚያደርግ እንደሚነግረው ለሙሴ አረጋገጠለት ፤ “ እርሱ ስላንተ ከህዝቡ ጋር ይናገራል ፤ እንዲህም ይሆናል ፤ እርሱ አፍ ይሆንልሀል አንተም በእግዚአብሄር ፋንታ ትሆንለታለህ ፡፡ ይህችንም ተአምራት የምታደርግባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ ፡፡” ሙሴ እንደታዘዘ በትሩን ወንድሙን ይዞ እግዚአብሄር ወዳለው ቦታ ሄደ ፡፡

ዘጸዓት(4፡ 18-21); አሁን ሙሴ በምድያም 40 አመታት ኖረ ፤ በህግ አባቱ ለሆነው ለዮቶር ተመልሶ ወደ ግብፅ በመሄድ አሁንም ዘመዶቹ አሉ እንደሆን ለማየት መሄድ እንደሚፈልግ ገለፀለት ፤ የህግ አባቱም በሰላም እንዲሄድ ባረከው ፤ ( ከያዕቆብና ከላባ አንፃር ያዕቆብ ባመለጠ ጊዜ ላባ ከሱ በኃላ አሳደደው )፡፡ ሙሴ ሁሉንም ታሪክ አልነገረውም ፤ ሙሴን ለመግደል የሚፈልጉት ወንዶች ሁሉ አሁን ሞተዋል ፡፡ ይህ ክርስቶስ ከንጉስ ሄሮድስ ጋር ከነበረው ተመሳሳይ መልክ ነበረው ፤ ሄሮዶስ በሞተ ጊዜ ኢየሱስና ቤተሰቦቹ ግብፅን በመልቀቅ ወደ እስራኤል ተመለሱ ፡፡ ድራማው አልፋል ፤ እግዚአብሄር ሙሴን የፈለገው እንዲሰራለት የጠራውን እግዚአብሄር እንዲከተል እሱም የእግዚአብሄርን ህዝብ ነፃ ማውጣት ነበር ፡፡ በጥሪህ መሄድ የተለየ ውብ ነው ፤ ሙሴ 40 አመታትን ያሳለፈው እነዚህን ሁሉንም ነገሮች በመማር ነው ከዚያም አሁን እግዚአብሄር እንዲሄድ ነገረው ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን “ ወደ ግብፅ ስትመለስ በእጅህ ያደረገሁትን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት ታደርገው ዘንድ ተመልከት ፤ እኔ ግን ልቡን አፀናዋለሁ ህዝቡንም አይለቅቅም ፡፡” ሙሴ ወደ ግብፅ ጉዞ እንደ ጀመረ እግዚአብሄር ለስራ እንደማይሄድ ሙሴን ነገረው ፡፡

ዘጸዓት(4፡ 22-26); እግዚአብሄር ሙሴ ለፈርዖን የሚለውን ነገረው “ እስራኤል የኔ የበኩር ልጄ ነው” ፤ አሁን የምናወራው ስለሰዎች ስብስብ እንጂ ስለያዕቆብ አይደለም ፤ እስራኤል በእግዚአብሄር የተመረጠ ህዝብ ስለሆነ ፡፡ በኤር(31፡ 9) እግዚአብሄር ሲናገር “ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና ኤፍሬምም በኩሬ ነውና ፡፡” በሆሴ (11፡ 1) እግዚአብሄር እስራኤልን ሲጠራ “የኔ ልጅ” ፡፡ እግዚአብሄር የፈርዖንን የበኩር ልጅ እንደሚገድል ተናገረ ምክንያቱም ፈርዖን የበኩር ልጁ እስራኤል ከግብፅ እንዲወጡ አልፈቀደም ! የበኩር ልጅ ለመግደል የገባው ቃል ትልቅ ውል ነበር ፡፡ ከምድያም ወደ ግብፅ ሙሴና ቤተሰቡ ጉዞ እንደ ጀመሩ እግዚአብሄር ሙሴን ተገናኘው “ ሊገድለውም ተመለከተው” ፤ ሙሴ ከልጆቹ አንዱን ምናልባትም ሁለተኛ ልጁን ኤልኤዘርን መገረዙን ቸል ብሎት ነበርና ፡፡ ዘፍ(17፡ 1- 11) የተገለፀው ግርዛት እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ላደረገው ኪዳን ምልክት ነበር ፤ ያችን ቀን አዳነችው ሲፓራም ነበረች ፡፡ የመፅሀፍ ቅዱስ ምሁሩ ካሱቶ ሲናገር “ሲፓራም የሙሴን አለመታዘዝ በማስተካከል የእግዚአብሄርን ፍርድ ከሙሴ ላይና ከቤተሰቡ ላይ አስወገደች” ፤ ሚስቱ ሲፓራም ስለ ኪዳኑ ታውቃለች ፤ ነፃ አውጭውን አዳነችው ፡፡ 1ጢሞ(3፡ 4-5) የሚያመለክተው እግዚአብሄር በአደባባይ ላይ የሚጠቀምባቸው ቤቤታቸውም ታዛዥ የሆኑትን ነው ! ሙሴ ቤተሰቡን ባያነፃ ኖሮ የእግዚአብሄርን ህዝብ ለመምራት በቂ አይሆንም ነበር ፤ ቤታችሁን የማታስተዳድሩ ከሆነ በእናንተ ላይ ያለውን ጥሪ እግዚአብሄር እንደሚያዘገየው አምናለሁ ፡፡

ዘጸዓት(4፡ 27-31); እርስ በእርስ በመሳሳም ሰላም መባባል በጊዜው የተለመደ ነበር ፤ ሮሜ (16፡16) የተካተተው ትዕዛዝ “ በተቀደሰ አሳሳም እርስ በእርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ” ፡፡ ሙሴ ከአሮን ጋር ተገናኝ እግዚአብሄር እንዲነግር የላከውን ሁሉንም ነገር ለእሱ ነገረው ከዚያም እግዚአብሄር እንዲያደርግ ያዘዘውን ምልክት አሳየው ፡፡ ወንድማማቾቹም አብረው የእስራኤላዊያን ሽማግሌዎች ለመናገር ሄዱ ፤ ለህዝቡም አሮን ሙሴ የነገረውን ሁሉንም እንደ ነገር ደገመላቸውም ምልክቱንም አደረገላቸው ፡፡ ለእግዚአብሄር ስራ በቂ እንዳልሆንክ የሚሰማህ ከሆነ ሌላ ይፈልጋል ፡፡ እግዚአብሄር የሆነ ነገር እንድናደርግለት የሚጠራን ከሆነ በዛው ለመሄድ ፈቃደኞቹ መሆን አለብን፡፡ እስራኤላዊያን አመኑ ወደ መሬትም በመደፋት እግዚአብሄርን አመለኩት (አመሰገኑት) ፤ እምንት ሁልጊዜ የሚመራው ወደ ታች በመደፋት እግዚአብሄርን እንድናመልክ ነው ፡፡

መዝጊያ

በዘጸዓት 5 ውስጥ ሽማግሌዎቹም አመኑ ወደፈርዖንም በመቅረብ ከዚህ መውጣት ጀመሩ ፡፡ ዘጸዓት 5 የሚያጠቃልሉ ሶዎስት ጥያቄዎችን ዋይሰርቤ አስቀምጣል (ጠቅሳል); 1) ፈርዖን እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሄር ማነው?-ዘጸ(5፡2); 2) ፈርዖን ህዝቡን ስራቸውን ለምን ታስተዋላችሁ ?- ዘጸ(5፡ 4; 14); እና 3) ሙሴ እግዚአብሄርን ስለምንስ ላክኸኝ ? (ዘጸ5፡ 22-23) ፡፡

ነገ በዘጸዓት 6 ውስጥ የመፈለግ እድል እናገኛለን ፤ እኔ F0D5ጉቻለሁ ስለ ሙሴ እንዴት እንደ ነፃ አወጪ ወደ ነፃ አውጪው ያህዌ ማመልከቱን ለማወቅ ፡፡

  1. Wiersbe, p. 183.

  2. Victor P. Hamilton, Exodus: An Exegetical Commentary (Grand Rapids: Baker Publishing Group, 2011), p. 71.

  3. Wiersbe, p. 184.

  4. Hamilton, p. 73.

  5. Wiersbe, p. 184.

  6. Wiersbe, p. 184.

  7. Umberto Moshe David Cassuto, A Commentary on the Book of Exodus (Jerusalem, Israel: Varda Book, 2005), p. 59–61; quoted in Dr. Constable’s Expository (Study) Commentary, p. 56; available online athttps://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf.

  8. Wiersbe, pp. 186–187.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር በዘጸ(4፡ 1-9) ውስጥ ለሙሴ እንደ ምልክት ሰዎስቱን ምልክት ለምን እንደመረጠ ምን ታስባለህ ?
  2. የሆኑ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ከምልክት ዉጪ የማያምኑ ወይም የማይቀበሉ ገጥመውህ ያውቃሉ ? ያንተ መልስ ምን ነበር ? (ማር 16፡ 15-18; ዮሐ 4፡48; 6፡30; 20፡ 30-31)
  3. በዘጸ(3፡ 11-14 እና 4፡ 1-17) ውስጥሙሴ ለእግዚአብሄር የሰጣቸው አምስት ምክንያቶች ምንድን ነበሩ ? ለእግዚአብሄር ተመሳሳይ ምክንያት የሰጠህበትን ጊዜ ማሰብ ትችላለህ ?
  4. ዘጸ(4፡ 21) እግዚአብሄር የፈርዖንን ልብ ለምን እንዳጠነከረው ምን ታስባላችሁ ? ፈርዖን በውሳኔው ተጠያቂ ነበር ? ካልሆነ ማን ነበር ? በዚህ ትታገላላችሁ(ፍጭት ታደርጋላችሁ) ?
  5. በዘጸ(4፡ 24-26) ውስጥ እግዚአብሄር ሙሴን ሊገለው የነበረው ለምን ነበር ? ማን እና ምንድን ሙሴን ከመገደል አዳነው ?
  6. በዘጽ(4-5) ውስጥ ለነፃ አውጭዉ የሚያስፈልገውን እንዴት አያችሁት ?
  7. በዘጸ(4-5) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 4:15-16

“You will speak with him and tell him what to say. I will help both you and him to speak and will teach you both what to do. He will speak to the people for you. He will be your spokesman, and you will serve as God to him.”

ተዓምራትና ምልክት ለሙሴ መሰጠቱ

ኦሪት ዘጸዓት 4-5 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እስራኤላዉያንን ነጻ በማዉጣት፥ እጁን እንዲሰጥ እግዚዓብሐር ሙሴን ጠራዉ። ሙሴ ለዚህ ጥሪ የመለሰዉ ግን በጥርጣሬ፣ በብቁ አይደለሁም ስሜት እና እሱ ለምን መሆነ እንደሌለብት ሰበብ በማቅረብ ነበረ። የሙሴ ሰበቦች እንዳሉ ቢሆንም እግዚዓብሔር ግን ተጠቀመበት። እግዚዓብሔር እንዴት ከእርሱ ጋራ እንደሚሆን በዝርዝር ገለጠለት።

እግዚዓብሔር አንተን በሚጠራበት ስፍራ እንዳይጠቀምብህ ከሙሴ ጋራ የሚመሳሰል ሰበብ ሊኖርህ ይችላል። ሙሴ በሰዎች ፊት ቀርቦ መናገር እንደሚችል አላሰብም፥ እግዚዓብሔር ግን በሚደንቅ መንገድ ተጠቀመበት! እግዚዓብሔር ለሆነ ስራ ጠርቶህ ከሆነ እግዚዓብሔር የሚያስፈልግህን ሁሉ እንደሚያስታጥቅህ እመን!

"የእግዚአብሔርም ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ እንዲህም አለ፦ ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ደህና እንዲናገር አውቃለሁ፤ እነሆም ደግሞ ሊገናኝህ ይመጣል፤ ባየህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለዋል። አንተም ትናገረዋለህ ቃሉንም በአፉ ታደርገዋለህ፤ እኔ ከአፍህና ከአፉ ጋር እሆናለሁ፥ የምታደርጉትንም አስተምራችኋለሁ።"

ኦሪት ዘፀዓት 4: 15-16

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:5፦ "ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም"

ወደ ፊልጵስዩስ 2:13፦ "ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።"

ወደ ዕብራዉያን 13:20-21፦ "በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 29