Moses & the Burning Bush
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 2-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘጸዓት ውስጥ የኛ ቃል ነፃ አውጭ ነው ፤ እግዚአብሄር እኛን ነፃ የሚያወጣን በበግ ጠቦት፣ በዘንግ፣ በመራራ ቅጠልና ዘይት እና በሰማይ አማካኝነት ነው ፡፡ ሙሴ የመጀመሪያዎቹን አምስቱን የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍን ፃፈ የኦሪት(የህግ) መፅሀፍን -ዘፍጥረት-ዘጸዓት-ዘሌዋውያን-ዘኁልቁና ዘዳግም ፤ ስለዚህ አሁን ስለራሱ ህይወት ቀጥታ ከሙሴ መስማት ይሆንልናል ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(2፡ 1-11); እስራኤላዊያን መብዛታቸው ቀጠለ ስለሆነም ፈርዖን ሁሉም የዕብራዊያን ወንድ ልጆች በናይል(በአባይ) ወንዝ እንዲጣሉ አዘዘ ፤ በዚህም ጊዜ እንበረምና ዮካብድ ወንድ ልጅ ያላቸው የተጋቡ የዕብራዊያን ጥንዶች ነበሩ ፤ ዮኬቤድ እናቱ ለሰዎሰት ወር ህፃኑን ደበቀች ነገር ግን መደበቁን ለመቀጠል ትልቅ እየሆነ መጣ ስለዚህ በቅርጫት ውስጥ አስቀመጠችው ከዚያም በናይል ወንዝ ዉስጥ በቄጠማ መሀከል አኖረችው ፡፡ በጥቂቱ (በአንዳንድ መንገድ) ዮካብድ ንጉስ የተናገረውን ታዛለች ፣ ልጃንም በህይወት ለማቆየት ለመርዳት የሆነ ነገር ጨምራለች እንደ ቅርጫት መሸፈኛ አይነት “ዝፍትና ቅጥራን “(ቁጥር 3) ፡፡ የፈረዖን ሴት ልጅ ልትታጠብ ወደ ወንዝ ወረደች ፤ ህፃንም አየች ከዚያም በእሱ ላይ ሀዘንን ተመለከተች ፤ የህፃኑ እህት ከሩቅ የመትመለከታቸው ህፃኑን የሚንከባከብ እንዲረዳት ከዕብራዊያን ሴቶች በመፈለግ የህፃኑን እናት ይዛ አመጣችላት ፤ የፈርዖንም ሴት ልጅ ጥሩ ሀሳብ እንደሆነ ተናገረች ፡፡ በእርግጥም ለሀኪማ ልትከፍላት ተስማማች ፡፡ የእህቱም ስም ማሪያም ነበር ፤ በተጨማሪም ህፃኑ ታላቅ ወንድም አሮን የሚባል ነበረው ፡፡ የፈርዖን ሴት ልጅ ህፃኑን ሙሴ አለችው ትርጉሙም “ከዉሃ አውጥቸዋለሁ” ማለት ነው ፤ ትንቢታዊም ስም ነው የሙሴ ህይወት በዉሃ ዙሪያና በጫካ(በበርሃ) የሚያጠነጥን ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እደረጃ ላይ አስቀምጦት ነበር ፤ ከአመታት በኃላ የእሱን ሰዎች ለመመልከት ሄደ፤ ፈርዖንም ዕብራዉያንን ለባርነት አስገድዳቸው ነበር ፤ ሙሴ የእሱ ሰዎች እንደተጨነቁ አየ ፡፡ ስለ ጭካኔአቸው ከመሰከረ(ከተመለከተ) በኃላ ሙሴ ግብፃዊ አሰሪያቸውን ገደለው ፡፡
ዘጸዓት(2፡ 15-24); ፈርዖን ሰው ስለገደለው ስለ ሙሴ ሰማ ሊገድለውም ፈለገ ፤ ሙሴም ለመሸሽ ከውሃ ካወጡት ተለየ(ሄደ) ፡፡ በጉዞውም ሙሴ እጉድጋዱ ጋር የሆኑ ሴቶች መንጎቻቸውን ዉሃ ሲያጠጡ ረዳቸው ለእራትም ጋበዙት፡፡ ሙሴም እቤተሰቡጋር ተቀመጠ ሲፓራንም አገባ ፤ ወንድ ልጅም ወለዱ ስሙንም ጌርሳም ትርጉሙም “ በሌላ ምድር ምፃተኛ ነኝ” ማለት ነው ፡፡ ሙሴ በሩቅ ጉዞው ላይ እያለ ፈርዖን(ምናልባት ቱቶምሰ ሶስተኛ) ሞተ ፤ ለእስራኤላዊያንም አስቸጋሪ ስራ ከሚጭኑት አንዱ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(2፡ 24-25); በኃይለኛ ስራ ምክንያት እግዚአብሄር የህዝቡን ለቅሶ ሰማ ( ዘኁ 20፡16; ዘዳ 26፡7) ፤ ዋይስርቤ ሲፅፍ “ የእግዚአብሄር መዘግየት እንደማያስበን ማስረጃ አይደለም የእኛን ማቃሰት ይሰማል፣ አስቸጋሪ ሁኔታችንን ይመለከታል፣ ሀዘናችን ይሰማዋል ከዚያም ኪዳኑን ያስታውሳል ፤ ቃል የገባውን ይፈፅመዋል ከእሱ ህዝብ ጋር ያደረገውን ኪዳን በፍፁም አያፈርስም ፡፡ ትክክለኛው ጊዜ ሲመጣ ወዲያውኑ እግዚአብሄር ወደ ስራ ይገባል ፡፡” በ400 እና በተጨማሪው አመት ዉስጥ እግዚአብሄር ኪዳኑን 14 ጊዜ አስታውሳል ! ከህዝቡ ከእስራኤላዊያን ጋር ያለውን ኪዳን አሁንም ያስታውሳል (መዝ 105፡ 8) ፡፡ ቅዱስ ኪዳኑን አስታወሰ (ሉቃ 1፡72) ፤ እናንተና እኔ በእርጋታ እግዚአብሄርን ለእኛ የገባውን ቃል የማስታዎስ ሚና መጫዎት እንችላለን ፡፡
ዘጸዓት(3፡ 1-2); በህግ የሙሴን የአባቱን የዮቶርን በጎች ሙሴ ይጠብቅ ነበር ፤ አንዳንድ ሰዎች ዮቶር የቅስና ስሙ ነበር ብለው ያስባሉ ፤ ራጉኤል ተብሎ ነበር የሚጠራው ቁጥር 18 ይህ የአባትነት የቤት ስሙ ነበር ፡፡ ሙሴ ወደ ኮሬብ ሄደ ይህም የእግዚአብሄር ተራራ የሲና ተራራ ተብሎ ይታወቅ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ያለማቃረጥ ቤቴልን፣ ሴኬምንና ቤርሳቤህን ተጠቀመ ፤ እግዚአብሄር ያንኑ በሲና ተራራ በዘጸዓት ውስጥ ሲያደርግ ታያለህ ፡፡
እግዚአብሄር እኛን ለሆነ ነገር ሲጠራን አንዳንድ ጊዜ በመጠበቂያ ጊዜ ውስጥ እንሄዳለን ፤ እግዚአብሄር ሲገለጥ ሙሴ በዙሪያው ዝምብሎ በመጠበቅ አልተቀመጠም ነበር ፡፡ “ የእግዚአብሄርም መልዓክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቁጥቃዓጦ ታየው “ በዚህ ጊዜ ሙሴ መንጋውን በመጠበቅ ላይ ነበር ፡፡ ሙሴ ለ40 አመታት እረኛ ነበር -ልክ እንደ ዮሴፍ 13 አመታት ጠበቀ እናም ጳዉሎስ 3አመት ጠበቀ ፤ ዋይስርቤ ሲፅፍ “ እግዚአብሄር የጠራቸው ሰዎች በስራ ላይ ያሉ መሆናቸው አስፈላጊ ነው; ጌዲዎን የስንዴውን ዘር አየወቃ ነበር (መሳ 6)፣ ሳሙኤል በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያገለግን ነበር (1ሳሙ 3)፣ ዳዊት ለበጎቹ ይጠነቀቅ ነበር (1ሳሙ 17፡20)፣ ኤልሳ በእርሻ ላይ ነበር (1ነገ 19፡19-20)፣ አራቱ ሐዋሪያት አሳ የማጥመድ ስራቸውን ይቆጣጠሩ ነበር(ማር 1፡16-20) እና ማቴዎስ ቀረጥ ይሰበስብ ነበር (ማቴ9፡9) ፡፡”ሃሳቡ እነዚህ ሰዎች ለህይወታቸው እየሰሩ እግዚአብሄር ተገለጠላቸው ፤ እግዚአብሄር ለመጠቀም ፈቃደኛና ታዛዥ ሰዎች ይፈልጋል (ምሳ 24፡ 30-33) ፡፡ሙሴ በጎቹን በመጠበቅ ላይ እያለ የእግዚአብሄር መልዓክ ተገለጠለት ፤ በዚህ ጊዜ በቁጥቃጦ ላይ እሳት ማየት የተለመደ ነበር ያልተለመደው አካል ቁጥቃጦው አይቃጠልም ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር መላዓክ ለሁሉም አይነት ሰዋች ተገልጦላቸዋል; ለአብርሃም(ዘፍ 22)፣ ለያዕቆብ(ዘፍ 31)፣ ለሙሴ(ዘጸ 3)፣ ጌድዎን(መሳ 6)፣ ለሳምሶን አባት(መሳ 13)፣ ለአጋር(ዘፍ 16) ፡፡ ሙሴ ቁጥቃጦውን ሲያየው አልጠፋምም ችግር አላገኘውም ፡፡ እሳት ሁልጊዜ የሚያመጣው 1) ውድመት(ጥፋትን); ሰዶምና ገሞራን አስብ (ዘፍ 18፡ 16-19; 29); 2) ለማጥራት; የሚነደው ከሰል የኢሳያስን አፍ አነፃው (ኢሳ6፡ 6-7) ፤ በሚቃጠል መስዋዕትም መንፃት አለ; 3) መገኘት; እግዚአብሄር የሚያጠፋ እሳት ነው (ዕብ12፡ 28-29) ፡፡ መብራቱ በፍፁም አይወጣም ነበር የእግዚአብሄር መገኝት ምልክት ስለነበር (ዘጸ27፡ 20-21) ፡፡
ዘጸዓት(3፡ 3-6); የሙሴን ስም ሁለቴ ጠራው ለዚህም ሲመልስ “እነሆኛ” አለ ፤ እግዚአብሄር በጣም ግልፅ የሆነ አቅጣጭ ሰጠው ፡፡ “ በእኔ መገኘት ውስጥ ትሆናለህ” አለው ፤ እኔ የምፈልገው ይህ የተለመደ እንዳልሆነ እንድታቁ ነው ! እግዚአብሄር ከአብርሃም ፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ኪዳን አስታወሰ ! ያዕቆብ በዘፍጥረት መጨረሻ ላይ እስኪያገኘው ድረስ ይህ አልሆነም ፡፡ እግዚአብሄር ከበፊትም የእነርሱ እንደነበርና አሁንም እንዳለ ያሳስባቸው ነበር ፡፡ በአምልኮና በፍርሕት ሙሴ ፊቱን ሸፈነ ፤ አስታውሱ ሙሴ ግብፃዊዉን ከገደለ በኃላ ፈሪ ሆናል (ዘጸ 2፡ 12-14) ፤ ሙሴ ይህ የእግዚአብሄር መገኘትና የተለየ እንደሆነ ያውቅ ነበር ፡፡ የተለየ ነገር በህይወቱ እንደተለማመደ ያውቅ ነበር ፤ ሙሴ ለዮሴፋዊያን ፀለየ በሚቃጠለው ቁጥቃጦ ውስጥ የነበረው የእሱ ሞገስ እንዲወርድባቸው ለዮሴፍ ዘር እንዲገለጥላቸው ጠየቀ ፡፡
ዘጸዓት(3፡ 7-10); እግዚአብሄር መለሰ “ ነፃ የመውጣት እድል መጣ” የኔልሰን ማብራሪያ የሚያወራው “ የሰዎች ማዳመጥ የአንባቢን ሰዎስት ነገሮች ያሳስባል ; 1) ምድሪቱ የንግግር ቅርፅ ብቻ አልነበረችም; በራሳቸው ወሰን ትክክለኛ ሰዎች የሚኖሩባት እውነተኛ ቦታ ነበረች ፤ 2) ለመኖሪያነት; የእነርሱ ጊዜ በቅርቡ ያልቅ ነበር አሁን የእነሱ የኃጢዓት ፅዋ ሞልታልና የእግዚአብሄርም ፍርድ ሰለ እነሱ ወረደች (ዘፍ 15፡16) ፤ 3) ምድሪቱ የእግዚአብሄር ስጦታ ስለሆነች ባዶ ሀብት አልነበረችም; ምድሪቱ ከነዋሪዎቻ የተቀረፀች ነበረች ፤ ይህም በእግዚአብሄር ሀይል ሆነ ፡፡” የእግዚአብሄርን ህዝብ እስራኤላዊያንን ሙሴ እንዲሄድ ከዚያም እየመራ ከግብፅ እንዲያወጣቸው እግዚአብሄር ተናገረው ፡፡
ዘጸዓት(3፡ 11-15); ሙሴ ከአምስት ምክንያቶች ጋር መጣ ፤ ሁለቱን ብቻ ዛሬ እንመለከታለን ፡፡ የመጀመሪያው “እኔ ማነኝ “(ቁጥር 11) ፤ ዋይርስቤ ሲፅፍ “ ሙሴ ከእግዚአብሄር ጋር ተከራከረም እስራኤልን ከባርነት ለማዳን መለኮታዊ ጥሪን ለማምለጥ ሞከረ ፤ በግብፅ ውስጥ ከ40 አመት በፊት ሙሴ ያደርግ የነበረው እንደ ሀይለኛ ፈረስና በእግዚአብሄር ፊት ችኩል ነበር ነገር ግን አሁን የሚያደርገው እንደ መንቻክ በቅሎና እግዚአብሄርን መቃወም ነው (መዝ 32፡9) ፡፡” እግዚአብሄር ቃል በመግብት መለሰለት “ ከአንተ ጋር እሆናለሁ”(ቁጥር 12) ፡፡ የሙሴ ሁለተኛው ምክንያት የነበረው “ ስምህን አላውቀውም” (ቁጥር 13) ፤ እግዚአብሄርም መልሱን ሰጠው “ ያለና የሚኖር እኔ ነኝ” (ቁጥር 14) ከዚያም “ያለና የሚኖር ወደናንተ እኔን ላከኝ ትላለህ፡፡ “ እግዚአብሄር ከእኛ ግር ነበር ከእኛ ጋር አለም ሁልጊዜም ከእኛ ጋር ይሆናል ፤ “ የአብርሃም አምላክ(ዘፍ26፡24)፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ወደ እናንተ እኔን ላከኝ ፡፡ “ ከ400 አመታት ባርነት በኃላ እግዚአብሄር አሁንም ለእነሱ ያለውን ቃል አሰበ ፡፡
ዘጸዓት(3፡ 16-22); እግዚአብሄር ከዕብራዊያን ጋር ግንኙነት ይሰራ ነበር ፤ የወተትና የማር ምድሪቱ ተክከለኛ ቦታ ነች ነገር ግን እውነታው በእዛ በሚኖሩ ሰዎች ተይዛለች ፡፡ ቁጥር 18 የሚለው እስራኤላዊያን ገለልተኛ(በሌላ) በሆነ ስፍራ አምላካቸውን ማምለክ ፈለጉ ስለዚህ በንፅህና ማምለክ ይችላሉ ፡፡ እስራኤላዊያንን ነፃ ለማዉጣት ሙሴ እቅድን እንደተቀበለ እግዚአብሄር በባዶ እጃቸው እንዳይወጡ ተናገራቸው ! እስራኤላዊያን ወደ ግብፅ ሲመጡ በሰረገላ ከግብፅ ሲወጡ ከተዘረፈ (ከተቀማ) ሀብት ጋር(ቁጥር 21-22) ፡፡
መዝጊያ
እግዚአብሄር ሙሴን ወይም በዕብራዊ ሙሼን በመጠቀም እስራኤላዊያንን ከግብፅ ነፃ ሊያወጣቸው ነው፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁና አትጨነቅ አለው ፤ እኔ ያለሁነኝ ይህንን ሀረግ በምሰማ ጊዜ ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ እንዴት እንደተናገረ አስባለሁ ፡፡
በዮሐ(8፡52) ኢየሱስ ከአንድ አገር ሰዎች ጋር ተገናኝቶ ነበር በዚህም አይሁዶች ሰይጣን አለበት ብለዉ ከሰሱት ፤ ይህን ያሉበት ምክንያት ኢየሱስ በፍፁም እንደማይሞት ስለተናገረ ነበር ፤ ምንም እንካን አብርሃም ቢሞትም ፡፡ ኢየሱስም መለሰላቸው “ እኔ አዉቀዋለሁ ቃሉንም እጠብቃለሁ “(ቁጥር 55) ፤ አብርሃም ከኢየሱስ ጋር ተገናኝ (ቁጥር 56); “ ከአብርሃም በፊት እኔ ነበረኩ “(ቁጥር 58) ፡፡ እነዚህን ሁለት ቃላቶች በመጠቀም ኢየሱስ በሚነደው ቁጥቃጦ ውስጥ እንዳለው እግዚአብሄር ራሱን አስተካከለ ፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ስምንንት ጊዜ ኢየሱስ “ እኔ ያለሁነኝ” ብሎ ተናግራል (ዮሐ 6፡35; 8፡12፣ 58; 10፡7; 11; 11፡25; 14፡6; 15፡1) ፡፡ ሁሉም ነገር የሚያመለክቱን ኢየሱስ ነፃ አውጭ እንደሆነ ነው ፤ ነገር ግን በዘጸዓት የጀመረው በሙሴ ነው ፡፡
Warren W. Wiersbe, Be Delivered (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1998), p. 23-24.
Warren W. Wiersbe, Be Delivered (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1998), p. 23-24.
Wiersbe, p. 24.
Wiersbe, p. 24.
ጥያቄዎች
-
በዘጸ(2፡ 1-10) ውስጥ እግዚአብሄር ለአላማው አሳዛኝ ሁኔታን አጠቃቀሙን እንዴት ታዩታላችሁ ?(ሮሜ 8፡ 28)
-
ምንድን በረከት ሙሴ ከእግዚአብሄር ተደረገለት እናቱ ለመታዘዛ ተቀበለች (ዘጸ 2፡9) ?
-
ሙሴ ከግብፅ ድሎት(ኃጢዓት) ለምን ለመሸሽ እንደወሰነ ምን ታስባላችሁ (ዕብ 11፡ 24-27) ? በክርስቶስ ምክንያት ከዚህ አለም ብልፅግና ዉጭ የሄድክባቸውን ጊዜ ምሳሌ ስጥ ፡፡
-
በዘጸ 2 ውስጥ ስለ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄር ማዳመጥ፣ መጠንቀቅና ማድረግ ለምንድን ምሳሌ ነው ? በህይወታችሁ ውስጥ እግዚአብሄር ይህን ሲያደርግ ገጥሞአችሁ ያውቃል ? (ዘጸ 3፡7; 6፡5; 1ጴጥ 5፡ 6-7)
-
በዘጸ(3፡6) ላይ እግዚአብሄር ለኛ ከሞት በኃላ ህይወት እንደሰጠን የሚያሳይ ማስረጃ ምንድን ተሰጠን ? (ማቴ 22፡32; ማር 12፡26-27; ሉቃ 20፡ 37-38)
-
እግዚአብሄር ስለራሱ ባህርይ በዘጸ(3 ፡14) ላይ ምንድን ገለጠ ? ይህ እንዴት ወደ ኢየሱስ ያመለክተናል ? (ዮሐ 8፡24; 28; 58)
-
በዘጸ(2-3) ውስጥ በትምህርትና በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 2:23-25
“After a long time, the king of Egypt died. The Israelites groaned because of their difficult labor, and they cried out; and their cry for help ascended to God because of the difficult labor. So God heard their groaning, and He remembered His covenant with Abraham, Isaac, and Jacob. God saw the Israelites, and He took notice.”
ሙሴ እና የሚነድደዉ ቁጥቋት
ኦሪት ዘጸዓት 2-3 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እስራኤላዉያን፥ በግብፅ በባርነት እና እስራት ዉስጥ በነበሩበት ጊዜ ወደ እግዚዓብሔር ጮሁ። እግዚዓብሔርም የተስፋ ቃሉን በማሰብ፥ ስቃያቸዉን ሰማ! ነጻ የመዉጣቱ ታሪክ የጀምረዉ እግዚዓብሔር የልባቸዉን ጩኸት በሰማ ጊዜ ነዉ።
ወደ እግዚዓብሔር በምንጮህበት ጊዜ፥ ለእግዚዓብሔር ሓቀኛ እየሆንን ነው። ፊታችንን ወደ እርሱ መለስ የምናደርገዉ በሁሉም ነገር ነዉ። ዛሬ ባላችሁበት ሁናቴ ሓቀኛ ሁናቹህ ለእግዚዓብሔር ንገሩት። ካላችሁበት እስራት ነፃ በማዉጣት፥ የድል ብስራትን ያመጣላችኋል። በክርስቶስ ነፃነት አለ! በእግዚዓብሔር ፊት ዛሬ ሓቀኛ ሁን!
"ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ። እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ። እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አየ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ያለውን ነገር አወቀ።"
ኦሪት ዘፀዓት 2:23-25
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘፀዓት 3:7-8፦ "እግዚአብሔርም አለ፦ በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ፤ ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።"
መዝሙረ ዳዊት 107:13-14፦ "አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤ ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ።"
ወደ ገላትያ ሰዎች 5:1፦ "በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 28
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።