Pharaoh Oppresses Israel
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትምህርት 27 የዘፀዓት የመጀመሪያው ትምህርት ነው ! የምንገልጥላችሁን የእኛን አድስ ስዕል አግኝተናል ! በዘፍጥረት ውስጥ ለክርስቶስ የነበረው ቃል ዘር ነበር ፤ ለዘፀዓት መፅህፍ የእኛ ቃል ነፃ አውጭ ነው ፡፡
ኡገኔ መሬል ስለ ዘፀዓት አላማ ሲፅፍ “ በእርሱ የተመረጡትን የእስራኤል ሰዎች ከግብፅ ባርነት ወደ ነፃነት ወዳለው ኪዳን ከእርሱ ጋር ግንኙነት ወዳለው በቸርነት ነፃ ያወጣቸው እግዚአብሄርን ማክበር ነው ፡፡” “ዘፀዓት” የሚለው ቃል ትርጉሙ “ መውጣት፣ መሄድ፣ ተለይቶ መራቅ” ማለት ነው ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት (1፡1-4); ይህ ቀለል ያለ የእስራኤልን ቤተሰብ መልክ ለኛ ይሰጠናል ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊና ይሁዳ የልያ ወንድ ልጆች ነበሩ ፤ በተጨማሪም ይሳኮርና ዛብሎንም የልያ ወንድ ልጆች ነበሩ ፡፡ ብንያም የረሄል ወንድ ልጅ ነበር ፤ ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር የቢላና የዘለፉ ወንድ ልጆች ነበሩ (ዘፍ 46፡ 8-27) ፡፡
ዘጸዓት (1፡5); በቀደመው ጥቅስ ውስጥ ዮሴፍን ከቤተሰቡ መልክ ትተነው ነበር ፤ ለምን ? ቀድሞውኑ በግብፅ ስለነበር ፡፡ አስታውሱ እግዚአብሄር ዮሴፍን መንገድ እንዲያዘጋጅ ከፊት ላከው ፡፡ 70 ቁጥር አስፈላጊ ነው ፡፡
- ዘፍ (10፡ 1-32)፡ 70 ህዝቦች
- ዘጸ (24፡ 9)፡ 70 የእስራኤል ሽማግሌዎች
- ዘኁ (11፡ 16)፡ 70 ሌሎች ሽማግሌዎች
- መሳ (1፡ 7)፡ 70 ትሁት(እሺ ባይ) ንጉሶች
- 1ሳሙ (6፡ 19)፡ 70 ሰዎች ወደ ታቦቱ የተመለከቱ
- መሳ (8፡ 30)፡ ጌዲዎን 70 ወንድ ልጆች ነበሩት ( ጌዲዎን ከምናሴ ወንድ ልጆች በጣም ታዋቂዉ ነው )
- 2ነገ (10፡ 1)፡ አክአብ 70 ልጆች ነበሩት
- ኢየሱስ በተለያ ክፍሎች 70 ወይም 72 ምስክሮችን ላከ ፡፡
እግዚአብሄር በ12 ነገዶችና በ12 ደቀመዛሙርት ጀመረ ፤ ወደ ግብፅ ምድር 70 አወረደ !
ዘጸዓት (1፡ 6-7); ዮሴፍና የእሱ ትውልድ ሞቱ ነገር ግን እስራኤላዊያን መብዛታቸውን ቀጠሉ ፤ በቁጥር 5 ሰባ ሰዎቹ ብዙ ሆኑ ምድርንም ሞላት ፡፡ በዘፍጥረት ውስጥ ያነበብነው ትንቢታዊ ቃል በዚህ በዘጸ(1፡7) ለሆነው ጅማሬ ነበር ፤ አሁን እንካን በትንቢት እንደሚጋዙ ያውቁ ነበር (ዘፍ 12፡ 1-3) ? በዘጸዓት ጊዜ ምሁራን ቁጥራቸውን 600000 ወንዶች እድሞዓቸው 20ዓመትና ከዚያ በላይ ሴቶችና ልጆች ከተቆጠሩ ከ2ሚሊዮን በላይ እንደሚሆኑ ያተነብያሉ (ይገምታሉ) ፡፡ የአብርሃም ዘር እንደ ምድር አሸዋ ትበዛላችሁ የሚለው ትንቢታዊ ቃል መፈፀም ጀመረ ፡፡
የእኛ ቃል ለዘጸዓት ነፃ አዉጪ ነው ፡፡ ከግብፅ የሚወጡ ከሆነ የሚመራቸው የሆነ ሰው ያስፈልጋቸው ነበር ፤ ጥያቄ የነበረው ማነው ? ዮሴፍና ሁሉም ወንድሞቹ ሞተዋል ፡፡
ዘጸዓት (1፡ 8-10); ምድሩን የሚያስተዳድር አድስ ፈርዖን ተነሳ ለእስራኤላዊያንም አያስብላቸውም ፤ ያስብ የነበረው ስለ እስራኤላዊያን ቁጥር መብዛትና ጥንካሬ ነበር ፡፡ የእባቡ ዘርና የሴቲቱ ዘር እንደገና በጦርነት ሆኑ ፡፡
ዘጸዓት (1፡ 11); ፈርዖን በጉልበት ስራ ጨቆናቸው ፤ ይህ የዘፍጥረት 15 መፈፀምና የ400 የጭቆና ዓመት ጅማሬ ነበር ፡፡ ይህንን ቁጥር በማነብ ጊዜ የማስበው ዘፍ(15፡13) “ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ ፡፡“ ያ ምድር ግብፅ ነበር !
አስታውሱ ዮሴፍ ወደ ግብፅ በገባ ጊዜ እግዚአብሄር አትፍራ ብሎ የነገረውን ? አሁን እስራኤላዊያን ለፈርዖን አጋዥ የሆነ ከተሞችን ይገነቡ ነበር ፤ ይህን በማይ ጊዜ እንዴት ስለ እውነተኛው እግዚአብሄር ለቃሉ እንደሆነ ደስታ ያገኘኛል፡፡
ዘጸዓት (1፡ 12-13); በብዙ እስራኤላዊያን ተጨቆኑ እነሱም በብዙ በዙም ሰፉም ፤ ተጨቆኑ ማለት ተጨፈለቁ ነዉ ፡፡ ግብፃዊያን በጉልበት (በኃይል) እንዲታዘዙዓቸው ያደርጉ ነበር ፤ እስራኤላዊያንም በጭንቅ ሰሩ ፡፡ ሕዝ(34፡4) የሚለው “ በኃይልና በጭቆናም ገዛችኃቸው ፡፡”
ዘጸዓት (1፡14); እስራኤላዊያን ከባድ ስራ ተሰጣቸው ከእነዚህም ጡብ መስራትና አርማታ ፤ በተጨማሪም ሁሉንም የመስክ ስራ አይነቶች ይሰራሉ ፡፡ ይህ በጣም አስቸጋሪ ልፋት(ትጋት) ነበር ! ባርነት ከእግዚአብሄር አይደለም! አስታውሱ ልፋት(ስራ) የተመሰረተው ከኃላ በዘፍ(3፡ 17-19) ከውድቀት በኃላ ነው ፡፡ አሁን ትክክል ያልሆነ ሀይለኛ ጥረት እንደ ባረነት እናያለን ፡፡
ዘጸዓት(1፡15-16); እስራኤላዊያን በመልሱ በመብዛት ይታገሉ ነበር ፤ ስለዚህ ፈርዖን የህዝቡን እድገት ለመቆጣጠር ወሰነ ፡፡ አዋላጆቹንም የእስራኤልን ወንድ ልጆች እንዲገድሉ ጠየቀ ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር የአብርሃም ዘር መብዛት እንደሚቀጥሉ ከተናገረው እነሱም ማደጋቸውን ይቀጥላሉ ፡፡
ዘጸዓት(1፡ 17); እነዚህ የግብፃዊያን አዋላጆች አይደሉም አነሱ እብራዊያን ነበሩ ፤ ታማኝነታቸው ለእግዚአብሄር እንጂ ለሰው አልነበረም ፤ ሲፋራህና ፉሀ (የእብራዊያን አዋላጆች) ጠንካራ(ጀግና) ነበሩ ምክንያቱም ያቀርቡ የነበረው ለእግዚአብሄር እንጂ ለሰው አይደለም ፡፡ ሮሜ 13 ውስጥ ለመንግስት እንድናቀርብ እናያለን ከእግዚአብሄር ተቃራኒ የሚሄድ እንድናደርግ ከሚጠይቁን ውጭ ፡፡
የንፁህ አለመታዘዝ በመፅህፍ ውስጥ ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ ታያለህ ፡፡ እስራኤላዊያን ህግ ማክበሩን ተቃወሙ ምክንያቱም የሚበልጥ መልካም ነገር ስለነበረ ፡፡
“ እግዚአብሄርን መፍራት” አስተሳሰብ ያለው፡
ዘፍ(20፡ 11); አብርሃምም ስለሳራ እህቴ ነች ብሎ ዋሸ ምክንያቱም ግብፃዊያን እግዚአብሄርን መፍራት እንዳላቸው ስለተናገረ ፡፡
ዘፍ(22፡ 12); አብርሃም ይስሐቅን ለመሰዋት ፍቃደኛ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሄርን ስለሚፈራ ፡፡
ዘፍ(42፡ 18); ዮሴፍ እግዚአብሄርን ስለሚፈራ ወንድሞቹ ቢኒያምን እንዲያገኙት ላካቸው ፡፡
እግዚአብሄርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው (ምሳ 9፡10) ፤ ቆላ (2፡ 2-3) የሚለው ኢየሱስ የእግዚአብሄር እውነተኛ ጥበብ ነው ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ከሆነ እግዚአብሄርን በምትፈራ ጊዜ መረዳትና መሲሁን መያዝ ትጀምራለህ ማለት ነው ፤ ስለዚህ እነዚህ ሁለት ሴቶች ይህን ነበር ያደረጉት ፡፡ የዕብራዊያን አዋላጆች የግብፅን ንጉስ እምቢ ማለት ከቻሉ ለምን እኔ ያለፍርሀት በእምነት መሄድ አልችልም ?
ዘጸዓት(1፡ 18-21); ፈርዖን ጠየቃቸው “ ይህን ለምንድን አደረጋችሁ” ? ዋሽተዋልን ? ርዓብ ዋሽታለች ፣ ራሄልም ዋሽታለች ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሄር አላማ ነበር ፡፡
ወደ እስራኤላዊያን ሰዎች የተስፋፋው ከእነዚህ ከሁለት ዕብራዊ ሴቶች ሞደል መሆን የጀመረው ምንድነ ነበር (ዘፀ 18፡21; ዘፀ 20፡ 20) ፡፡ እግዚአብሄር ለአዋላጆቹ መልካም ነበር ምክንያቱም አዋላጆቹ እግዚአብሄርን ስለፈሩ ፤ ለእነሱም ቤተሰባቸውን ሰጣቸው (ቁጥር 20-21) ፡፡ ስራቸውን ባረከላቸውከዚያም እነሱን ባረካቸው ፤ መዝ(127፡3)” እነሆ ልጆች የእግዚአብሄር ስጦታ ናቸው የሆድ ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው ፡፡” አይገድሉም ፤ ውርጃ የእግዚአብሄር አይደለም ! ልጆች የእግዚአብሄር ስጦታ ናው ፡፡
ፈርዖን እንዴት የእስራኤል ሴቶች እንደሚመልሱለት አልወደደውም ፤ በግብፅ አገር ያሉትን ሁሉንም የሱን ሰዎች የዕብራዊያንን ወንድ ልጆችን መግደል እንዲጀምሩ አዘዛ ፡፡
መዝጊያ
እንዴት ይህ ነፃ አዉጭ ለሚለው ይመጥናል(ይጣጣማል) ? መልካም ዜናን ለመረዳት መጥፎ ዜና ሊኖርህ ይገባል ፤ አድስ ህይወት ለመልመድ ኃጢዓትና ሞትን መረዳት ያስፈልግሀል ፡፡
በዘፀዓት 1 ውስጥ ባርነትን፣ ባርነትንና ጭቆናን ታያለህ ፤ የሆነ ቦታ ላይ ነፃ ይወጣሉ ፡፡ በ40 ምዕራፍ ትምህርት ላይ በዚህ አይነት ሂደት ውስጥ እንሄዳለን ፡፡ እንዴት እስራኤላዊያን ነፃ ወጡ ?
Eugene Merrell, Exodus Sermon Series (Copley, OH: Covenant of Grace Church, 2017); available online at http://cogc.org/exodus/.
ጥያቄዎች
-
የዘጸዓት ትርጉም ምንድን ነው ? እንዴት ዘጸዓት ለነፃ አዉጪው የሚያስፈልገውን ያሳያል ?
-
ህዝብን የመውለድ የእግዚአብሄር እቅድ በዘጸ(1፡ 7) ቅርፅ መያዝ ጀመረ ፤ አድሱ የግብፅ ንጉስ ለምን ነበር ስለ ዘጸ(1፡ 8-10) የተበሳጨው ?
-
የግብፅ ንጉስ በዘጸ(1፡ 11-14) እስራኤላዊያን እንዲሰሩ ምንድን አደረገ ? የእስራኤላዊያን መልስ ለግብፃዊያን ማስጨነቅ እንዴት አደረጉ ዘጸ(1፡12) ? ብትሰቃይ እንዴት ትመልሳለህ ?
-
የግብፅ ንጉስ ለእብራዊያን አዋላጆች ወንዶች ልጆችን እንዲገድሉ ግን ሴቶችን እንዳይገድሉ ለምን አደረገ ? (ዘጸ 1፡ 9-10; 15-16; ሐዋ 7፡ 18-19)
-
አዋላጆቹ ለንጉስ እሺ አሉ ? እግዚአብሄር እንዴት ነበር በድርጊታቸው ያከበራቸው ? ሌላ ምስሌ ልታስብ ትችላለህ በዛሬ ጊዜ የሆነ ሰው ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሄር የሚታዘዝ ? (ሐዋ 4፡ 19; 5፡29; ሮሜ 13፡ 1-5)
-
ለአዋላጆቹ መታዘዝ እንዴት ነበር እግዚአብሄር የባረካቸው ? (ዘጸ 1፡ 20-21)
-
በዘጸዓት 1 ውስጥ በትምህርትና በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳየህ(አስረዳህ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 1:20-21
“So God was good to the midwives, and the people multiplied and became very numerous. Since the midwives feared God, He gave them families.”
ኦሪት ዘፀዓት 1 የዕለቱ ቃል ከላዉራ ማርቲን
እግዚዓብሔር ዕብራዉያን እንዲበዙ የህፃናት አዋላጆቹን በሚደንቅ መንገድ ተጠቅሞባቸዋል! አዋላጆቹ፥ የሰዉን ፍርሃት በማሸነፍ፥ እግዚዓብሔርን መፍራት መረጡ!
እግዚዓብሔርን በምትፈራበት ጊዜ፥ አንተ በምትቆጣጠራቸዉ ነገሮች ወይም በራስህ ላይ የምትደገፍ አትሆንም። በዚያ ፋንታ ግን እግዚዓብሔር ሁሉን ነገር በልክ እንደሚያበጅ ተረድተህ በመደነቅ እና በአክብሮት ተዘልለህ ትኖራለህ! እግዚዓብሔር እንድትፈራዉ፥ እናም የምትፈልገዉን ነገር ሊፈፅምልህ ይጓጓል።
ዛሬ ይሄኛዉን ዓረፍተ-ነገር ለራስህ የምታሟላዉ እንዴት ነው? "እግዛዓብሔርን ስለፈራ (ስም)፤ እግዚዓብሔር ለእርሱ/ለእርሷ ................................ ሰጠዉ/ስጣት።
"እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፥ እጅግም ጸና። እንዲህም ሆነ አዋላጆች እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ ቤቶችን አደረገላቸው።"
ኦሪት ዘጸዓት 1:20-21
ተጬማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘጸዓት 1:17፦ "አዋላጆች ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፥ የግብፅ ንጉሥም እንዳዘዛቸው አላደረጉም፥ ወንዶቹን ሕፃናትንም አዳኑአቸው።"
መዝሙረ ዳዊት 145:19፦ "ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም።"
የሉቃስ ወንጌል 1:50፦ " ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።"
የመሲሁ ሙሉ ስ በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 27
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።