Trumpets & Complaints
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 10-11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘኁ 9 ደመናው ሁልጊዜ እንዴት ህዝቡን እንደመራ አይተናል ፡፡ ምዕራፍ 10 ስለ ብር መለከቶችና እንዴት እንደሚጎአዙ በመታወጁ እንዴት ያስፈልጋቸው እንደነበር ነው ፡፡ በአሁን ጊዜ ከእግዚአብሄር የመንሰማበት የተለያዩ መንገዶች አሉ፡ በእግዚአብሄር ቃል በኩል፣ በመንፈስ ቅዱስ በኩል እና በፓስተሮች፣ በመምህሮች እና በሌሎች ክርስቲያኖች ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(10)፡ በአንድ ላይ እንደመጡ መለከቶች ለህዝቡ ይነገራል ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የብር መለከቶቹ ህዝቡ እንዲቀሳቀሱ እግዚአብሄር ሲፈልግ ለእስራኤል ይነገራል ፤ ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ የመለከት ድምፅ ይሰማል (1 ተሰ 4፡ 16-17) ፤ የሰማይ ድምፅ ይሆናል ተመልሶም ይመጣል !
ዘኁልቁ(11፡ 1)፡ የእስራኤል ሰዎች የእግዚአብሄርን ስጦታ ለማማን የተማሩ አልነበሩም ፡፡ በዘጸ (15፡ 22-24) ከሰዎስት ቀን በኃላ ከባርነት ነፃ ወጡ ማማረርም ጀመሩ ፡፡ እኛም ተመሳሳይ ነን ፤ ደግመን ደግመን እግዚአብሄር ሲንቀሳቀስ አይተናል እስካሁን እናማርራለን ፡፡ ህዝቡ በግልፅ ስለ ችግሩ አማረረ ፤ የእግዚአብሄር ንደት ነደደ እሳትም ላከ ወዲያውኑም አቃጠለቻቸው ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 2-5)፡ እሳቱም ትኩረታቸውን አገኘ ስለዚህ ቅሬታ ለማቅረብ ወደ ሙሴ ሄዱ ፡፡ ሙሴ ወደ እግዚአብሄር ፀለየ እሳቱም ጠፋ ፤ ይህ ቦታ “ ተቤራ “ ተብሎ ተጠራ ትርጉሙም “ በመካከላቸው እሳት ነዶ ነበር ” ማለት ነው ፡፡ ማስጠንቀቂያ ነበር የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው ማጥሪያ ነበር ፡፡ ከዚያም ስለ ምግብ አማረሩ “ ድብልቅ ህዝብ “ ለሌላ ምግብ ጠንካራ ጉጉት የነበራቸው ከእስራኤላዊያን ጋር የተቀላቀሉ መፃተኞች ነበሩ ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 6)፡ “ አሁን ግን ዕያናችን ከዚህ መና በቀር ምንም አታይም “አሉ ፤ “ ፍላጎታችን የለም ፡፡” ይህ ሀይለኝነት ! ከአስር ምዕራፍ ቦኃላ (ዘኁ 21፡ 5) እስራኤላዊያን አልተቀየሩም ነበር ፤ ያማርሩም ነበር ፡፡ ዋይርስቤ የፃፈው “ ኢየሱስ ያስተማረው የትም እግዚአብሄር እውነተኛ ልጆቹን ሲተክል ሰይጣን በጎን በመምጣት አስመስሎ ይተክላል ፡፡”
እግዚአብሄር ለእኛ እንደተጠነቀቀ ወዲያውኑ እንረሳለን ከዚያም ማማረር እንጀምራለን፣ መታመንም እናቆማለን ፡፡
- 2ጴጥ (2፡ 1-2)፡ የሰዎቹ ፍላጎት የተለያየ ምግብ ወይም ብዙ ምግብ እንፈልጋለን ነው ፡፡ ትንሽ ይመስላል ነገር ግን ይህን እንዴት ሊጀመር ነው ፤ ሁለተኛው ወደ ራሳችሁን ጥንካሬ መመልከት ስትጀምሩ የራሳችሁን ፍላጎት እና አጀንዳ መፈለግ ትቀጥላላችሁ ፡፡
- ገላ (2፡ 4)፡ ይህ ከአጥር ውጪ የሆነ ማጣት አይደለም ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጣ እንጂ ፡፡
- 2ቆሮ (11፡ 13-14)፡ ንቁ ሁኑ ! ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል ፡፡ ልክ እንደ ሰይጣን እንደ ብርሀን መለዓክ ለሚከሰቱ ያወቃችሁ ሁኑ ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ጠንቃቃ መሆን አለባት !
- ይሁ 4፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኖቻችን ሰዎች በስውር እየመጡ እውነትን ለመቀየር ቅሬታ እያቀረቡና ዘመቻ እያደረጉ የስህተትን ትምህርቶች እየተገበሩ ናቸው ፡፡
ተጠንቀቁ የማማረር ካርድ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ መካድ ሊመልስ ይችላል ፡፡ ሰዎችን ውደዱ ነገር ግን በመለመን አታመቻምቹ ፤ እውነቱን ንገሩዓቸው ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 7-10)፡ ሙሴ መናን ጥሩ እንደነበር በመናገር ገልፆታል ፡፡ እስራኤላዊያን የሚበቃቸውን ያክል ሰበሰቡም አዘጋጁም ፡፡ ዘጸ(16፡ 33) ለመናው የወርቅ ማድጋ ትዕዛዝ ሰጠ ስለዚህ እስራኤላዊያን እግዚአብሄር እንዴት እንደሰጣቸው አይረሱትም ፡፡ ማማረር ከቤተሰብ ወደ ቤተሰብ ተስፋፋ ብዙዎች በድንካናቸው ውስጥ አለቀሱ ፤ እግዚአብሄር ተበሳጨ ሙሴም ተናደደ ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 11-14)፡ ለዚህ የመሪነት ቦታ እግዚአብሄር እንደ ሾመው ሙሴ አመለከተ በተጨማሪም በእውነትም ሙሴ እስራኤላዊያንን አልወለዳቸውም ነበር ፡፡ ይህ አንዱ ጊዜ ነው በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር ለሰዎች እንደ ሴት በማስመሰል መውለድ የሰጠበት ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄርን “ የአንተ ልጆች እንጂ የኔ አይደሉም ፤ ተንከባከባቸው “ ብሎ ተናገረው ፤ ሙሴ ስጋ እንዲሰጣቸው ፈለገ ስለዚህ ዝም ይላሉ ፤ ሙሴ ከእነርሱ ጋር ጨርሶ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 15)፡ በመሰረቱ ሙሴ የተናገረው “ በዚህ ውስጥ የምቀምጥ ከሆነ ግደለኝ ጨርሻለሁ ወይም ስራዬን ከጨረስኩኝ ስቃይ አታሳየኝ ከእኔ አርቀህ ወሰደው ፡፡“ በ 1ነገ (19፡ 4) ኤልያስ ከባድ ነገር(ግድግዳ) ጋር ተጋጨ በክትክታም ዛፍ ስር ተቀመጠ ለመሞት ጠየቀ ፤ መሪዎች ከባድ ነገር ጋር በተጋጩ ጊዜ ለመሄድ ወይም ላለመሄድ ይወስናሉ ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 16-17)፡ ሙሴ እርዳታ ተቀበለ ፡፡ 70 ሰዎች ሙሴ ለእርዳት ተሰበሰቡ ፤ በሱ ላይ ያለው መንፈስ ከእርሱ ተወስዶ በእነዚህ ሰዎች ላይ በማስቀመጥ ይካፈላሉ ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን በእነዚህ 70 ሰዎች ላይ ስጦታቸውን በማሸከም(በማካፈል) ሙሴን እረዳው ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 18-20)፡ ሙሴ እስራኤላዊያንን ተናገራቸው፡ “ ተዘጋጁ ! ነገ ስጋ ይኖራችኃል ! ራሳችሁን ቀድሱ ፤ ትበላላችሁ ፡፡” ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለሙሉ ወር ስጋ ይኖራቸዋል ፤ ብዙ ስጋ ይኖራል በአፍንጫቸው ይወጣል ከዚያም ይሰለቹታል ፡፡ እግዚአብሄር ይል የነበረው “ ደግማችሁ እንዳትጠይቁኝ ፡፡”
ዘኁልቁ(11፡ 21-24)፡ ሙሴ ለ600,000 ወታደሮች ሴቶች እና ልጆች ሳይጠቅስ ስጋ መመገቡን ለመያዝ(ለማሳብ) ሞከረ ፤ ሙሴ ለስጋ የሚሆን በቂ እንስሳት የባህር አሳ እንካን ቢቆጠር እንደማይበቃ ያውቃል ፡፡ ተስፋ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄርን ኃይል አታሳንስ ግን ጠብቅም እይም ፤ ጨዋታው ተጀመረ ! ሙሴ ህዝቡን ነገራቸው ፤ እግዚአብሄር በ 70 ሰዎቸ ላይ መጣ ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 25)፡ እግዚአብሄር በደመና ወረደ ፤ ሽማግሌዎቹ በሙሴ ላይ ከነበረው መንፈስ ጥቂት ተቀበሉ ፤ በዚያን ጊዜ ብቻ ቃል አወጡ ትንቢትም መናገር ጀመሩ ፡፡ ኢገኔ መርሪል የፃፈው “ እዚህ መተንበያቸው ትንብያን የሚገልፅ አይደለም ወይም አዋጅ እንካን አይደለም ነገር ግን ምስጋና መስጠት(በዝማሬ ወይም በንግግር) እና ያለልምድ ተመሳሳይ ገለፃ ነው ፡፡“ በ 1ሳሙ(10፡ 9-10) ተመሳሳይ ነገር ሆኖአል ፤ ይህ በ 1ሳሙ(10፡ 9-10) ተመሳሳይ ነገር ሆኖአል ፤ ይህ ለ70 ዎቹ የሆነው ነው ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 26-29)፡ ኤልዳድ እና ሞዳድ በሰዎቹ መሀከል የተዘረዘሩ ነበሩ ነገር ግን አልመጡም ፤ ባይመጡም ተመሳሳይ መንፈስ በእነሱ ላይ ደግሞ መጣባቸው ፡፡ አንድ ወጣት ሰው ስለ ትንቢታቸው ሪፖርት አደረገ ፤ ኢያሱ እንዲያቆሙ ፈለገ ፤ ሙሴ ኢያሱን በስጦታው እንዳይቀና ነገረው - ሁሉም ህዝብ እግዚአብሄር እንዲናገሩ የነገራቸውን ነቢያት መሆን እና መናገር ያስፈልጋቸዋል (1ቆሮ 14፡ 1-5) ፡፡ በደንብ የሚያደርጉትን በመቀበል እነዚህን ስጦታዎች መፈለግ እና መባረክ አለብን ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 30-32)፡ ሙሴና ሽማግሌዎቹ ወደ ካንፕ ተመለሱ ፡፡ ንፋስ ከባህሩ በሁሉም አቅጣጫ ከመኖሪያቸው 20 ማይል ርቆ ከመሬት 3 ጫማ ከፍታ የሚበርሩ ድርጭቶችን አመጣ ፤ እስራኤላዊያን ይህን ስጋ ይዘው ገደሉ ፡፡ ለሁለት ቀንና ምሽት ድርጭት ሰበሰቡ ፤ አንድ ቤተሰብ የሰበሰበው ትንሹ መጠን 50 መስፈሪያ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(11፡ 33-35)፡ እግዚአብሄር ስጋ ላከላቸው ግን ደግሞ አደገኛ መቅሰፍት ነበር (መዝ 106፡ 15፣ 78፡ 31) ፡፡ እውነታው መቅሰፍቶቹ ከእግዚአብሄር ነው ፤ እግዚአብሄር የተመኙ ጥቂት ወንዶችን ገደለ ፡፡ እስራኤላዊያን የተጎመጁትን ወንዶች ቀበሩ ከዚያም ወደ ሐጼሮት ተጎአዙ በዚያም ተቀመጡ ፡፡
መዝጊያ
ዋይርስቤ የፃፈው “ ቃልን እንቢ ማለት፣ በግደለሽነት ማድረግ ወይም በፍቃድ አለመታዘዝ ለእግዚአብሄርን ደቀመዝሙር ለመጠየቅ ነው (ዕብ 12፡ 5-11) ፡፡” በአለም ቃል ሳይሆን በእግዚአብሄር ቃል መደገፍ አለብን (ኤር 15፡ 16) ፡፡ ይህ ትንቢት የሚያደርገው ነው ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ሰው የሚያደርገው በቂ ይሆናል !
Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson, 1999), p. 207.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 328.
Eugene Merrill, The Zondervan Pictorial Encyclopedia of the Bible (Grand Rapids. MI: Zondervan, 1957), p. 227.
Wiersbe, p. 329.
ጥያቄዎች
-
የብር መለከቶቹ የጠቀሙት ለምንድን ነበር ? (ዘኁ 10፡ 1-10)
-
ሙሴ ኦባብን ወደ ቀድሞ ምድሩ እና ህዝቦቹ ተመልሶ ለመሄድ በፈለገ ጊዜ ጉዞ እንዲቀጥል አሳመነው (ዘኁ10፡ 31) ፡፡ እግዚአብሄር ለእናንተ በላው ጉዞ ላይ እንድትቆዩ ሌሎች በምንድን መንገዶች አበረቱዓችሁ? መልሳችሁ ምንድን ነበር ?
-
በዘኁ (11፡ 14) ሙሴ እግዚአብሄርን በወቅቱ የነበረበት ሚና በራሱ ለመሸከም ብዙ ሽክም እንደ ነበር ነገረው ፤ እንደ ሚና ለእናንተ ይዛችሁት የነበረው ብዙ ጫና እንደነበር ተሰምቶአችኃል ?
-
እግዚአብሄር ሙሴን 70 ሽማግሌዎችን እንዲሰበስብ እና ሙሴ ከተሸከመው ጥቂት መንፈስ እንደ ሚያስቀምጥባቸው እንዲገልፅ ነገረው (ዘኁ 11፡ 17) ፡፡ ማከፋፈል ብቸኛው አማራጭ እንደ ነበር የተሰማችሁ ሁኔታ ውስጥ ሆናችሁ ታዉቃላችሁ ? ስትጠይቁት በምንድን ተግባራዊ መንገዶች እግዚአብሄር ሸክማችሁን ያቀልላችኃል ?
-
ሙሴ ከተሸከመው ጥቂት መንፈስ ሽማግሌዎቹ በተቀበሉ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ ነገር ግን አንድ ጊዜ ብቻ ነበር ፡፡ (ዘኁ 11፡ 25) ለምን ነበር አንድ ጊዜ ብቻ ትንቢት መናገር የቻሉት ? በዘኁ (11፡ 29) የሙሴ ቃል በመጨረሻ እንዴት በሐዋ 2 ተፈፀመ ? በአድስ ሚናቸው 70 ሽማግሌዎችን ለመርዳት የመንፈሱ አስፈላጊነት ለምን ነበር ?
-
በዘኁ 10-11 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 11:23
“The Lord answered Moses, ‘Is the Lord’s power limited? You will see whether or not what I have promised will happen to you.’”
መለከቶች እና ማጉረምረሞች
ኦሪት ዘኁልቁ 10-11 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እስራኤላዉያን ከሚያልፉበት ስቃይ የተነሳ አጉረመረሙ። የሰፈሩን አንድ ክፍል እስኪያቃጥል ድረስ፥ የእግዚአብሔር ቁጣ በመካከላቸዉ ነደደ። ከዚያም አንዳንዶች እግዚአብሔር አምላክ ባዘጋጀላቸዉ መና ደስተኞች አልነበሩም። ከወትሮዉ የተለየ ምግብ ፈለጉ፥ ስጋ ፈለጉ! እግዚአብሔርም በጠየቁት ፋንታ ድርጭት ሰጣቸዉ። ሌላ ምግብ እንደሰጣቸዉ ሲያጉረመርሙ የነበሩቱ ድርጭቱን እየበሉ ሳለ ሞቱ! እዚህ ጋ ተመሳሳይ ንድፍ እየተመለከታችሁ ነዉ? ህዝቡ ደስተኛ አይደለም፥ እግዚአብሔር ይመልሳል፥ ህዝቡ አሁንም ደስተኛ አይደለም። እንዴት አድካሚ ነዉ!
ጌታ፥ በእርሱ ብቻ ደስታህን እንድታገኝ ይናፍቃል! የእግዚአብሔርን ህልዉና ከምንም ነገር በላይ መራብ በህይወትህ መራብ አለብህ። ይህንን ልብ ካላልክ የጠላት ዉሸት ሌላ ነገር ይነግርሃል። እስኪ ዛሬ ልብህን መርምር፥ እግዚአብሔርን ከእርሱ ይልቅ ለደስታህና እርካታህ የዚህ ዓለምን ነገሮች ለማግኘት የምትጓጓ እንደሆንክ በሚገባ ለማወቅ ጠይቀዉ። አስታዉስ፥ በጌታ መገኘት የደስታ ሙላት አለ!
"እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በውኑ የእግዚአብሔር እጅ አጭር ሆነ? አሁን ቃሌ ይፈጸም ወይስ አይፈጸም እንደ ሆነ አንተ ታያለህ አለው።"
ኦሪት ዘኁልቁ 11:23
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 16:11፦ "የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።"
- ትንቢተ ኤርሚያስ 15:16፦ "ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።"
- ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:13-15፦ "ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 79
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።