Scouting Out Canaan
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 12-13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 80 ቀናት ውስጥ ይህን አድርገናል !
ትምህርት
ዘኁልቁ(12፡ 1-3)፡ ማሪያም እና አሮን ሙሴን ከአገባው አንፃር ተናገሩት ፤ ይህ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው ማሪያም የተጣለችበት ብቸኛው ጊዜ ነው ፡፡ እግዚአብሄር በሙሴ በኩል ብቻ ለምን እንደሚናገር ጠየቁ፡፡ የሙሴን መሪነት ጠየቁ እናም እግዚአብሄር ሰማ ! ሙሴ በምድር ላይ ትሁት ሰው ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(12፡ 4-14)፡ እግዚአብሄር ሙሴን፣ አሮንና ማሪያምን ከመገናኛው ድንካን እንዲወጡ ጠራቸው ፤ ማሪያም ወዲያዉኑ ለምፃም ሆነች ፡፡ ሙሴ ስለ ማሪያም እግዚአብሄርን ለመነ ፤ ማሪያም ለሰባት ቀን ከሰፈር ዉጪ ተቀመጠች ፡፡
ዘኁልቁ(13፡ 1-15)፡ እግዚአብሄር ሙሴን ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሰው ከነዓንን ለመሰለል እንዲልክ አዘዘው ፤ 12 ሰላዮች ተላኩ ፤ ዘዳ (1፡ 12) ሰላዮቹ እንዳይፈሩ ወይም ተስፋ እንዳይቆርጡ መዝግቦ ነበር ፡፡ ሙሴ ሰላዮቹን መረጠ - አካላዊ ብቃት ያላቸው፣ የሚሮጥ ሰው፣ የባህር ሀይል ያላቸው(መዋኘት የሚችሉ)፡
- ከሮቤል ነገድ ሰሙኤል
- ከስምዖን ነገድ ሰፈጥ
- ከይሁዳ ነገድ ካሌብ
- ከይሳኮር ነገድ ይግአል
- ከኤፍሬም ነገድ አውሴ
- ከብንያም ነገድ ፈልጢ
- ከዛብሎን ነገድ ጉዲኤል
- ከምናሴ ነገድ ጋዲ
- ከዳን ነገድ ዓሚኤል
- ከአሴር ነገድ ሰቱር
- ከንፍታሌም ነገድ ናቢ
- ከጋድ ነገድ ጉድኤል
ዘኁልቁ(13፡ 16-20)፡ ሙሴ አውሴን “ኢያሱ” ብሎ ሰየመው ፤ አውሴ ማለት “ ለድነት የሚፈለግ “ ማለት ነው ፤ “ ኢያሱ “ ማለት እግዚአብሄር ያድናል ደህንነት ነው ፡፡” ኢያሱ እና ኢየሱስ የተመሳሳይ ስም ሁለት አይነት የሚሆኑ ናቸው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው ሙሴ የአውሴን ስም ወደ ኢያሱ የቀየረው የሀይማኖታዊ ለውጥ ድርጊት መቀበልን የሚያሳይ ምልክት ነው ፡፡
ሙሴ ሰላዮቹን የት እንደሚሄዱ ነገራቸው ፤ ምድሪቱን እና ህዝቡን እንዲያረጋግጡ ምንድን እንደ ሚመስል እንዲግልፁ ነበር ፤ ጥቂት ወይስ ብዙ ? ጠንካራ ወይስ ደካማ ? ምድሪቱ መልካም ናት ወይስ መጥፎ ? ከተሞቾአስ? ወታደራዊ መስፈሪያቸውን ወይም ምሽጎቻቸውን ? ወፍራም ዛፎች እንዳሉኣት እንደሌሉዕት ? ፍሬ እንዳለት እንደሌላት ? ጀግና እንዲሆኑ እና ጥቂት ፍሬ ይዘው እንዲመለሱ ፡፡
ዘኁልቁ(13፡ 21-22)፡ ከፂን እስከ ረአብ ምድረ በዳ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ጠቅላላ 87 ማይል ሰለሉ ፡፡ በደቡብ በኩል ወደ ኬብሮም (የምትሆንላቸው ቦታ !) በግብፅ ካለቸው ከጣኔ ሰባት አመት በፊት የተሰራች ነበረች ፤ አብርሃም እዚህ ጋር መሰዊያ ሰርቶ ነበር (ዘፍ 13፡ 18) ፡፡ አብርሃም እና ይስሐቅ በዚያ ተቀበሩ (ዘፍ 49፡ 31) ፤ የዳዊት ዋና ከተማ በዚያ ነበር (2 ሳሙ 2፡ 11) ፤ የካሌብ ዘር በዚያ ነበር (ኢያ 14፡ 13) ፡፡
ዘኁልቁ(13፡ 23-25)፡ ኤሽኮል ሸለቆ ላይ ሰላዮቹ አንድ ነጠላ የወይን ዘለላ ቆረጡ በእንጨትም ላይ አስቀመጡት ፤ በእውነት ይህ የእስራኤል አገልግሎት የቱሪዝም ምልክት ነው ፡፡ ሁለት ወንዶች ወይኖቹን በእንጨት ተሸከሙ ፡፡ ደግሞም ሮማኖችን እና የበለስ ፍሬዎችን ሰበሰቡ ፡፡ የወይን ፍሬዎች ስለ ተቆረጡበት ኤሽኮል ተብሎ ነበር ፡፡ ሰላዮቹ ከ40 ቀናት ቦኃላ ተመለሱ ፡፡
ዘኁልቁ(13፡ 26-27)፡ ተመልሰው ነገሩዓቸው፡ የፍሬ ሪፖርት፡ እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ፍሬውን አሳዩአቸው ፤ ወተትና ማር የምታፈስስ ምድር ነበረች ፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ ተነግሮአቸው ነበር ፡
ዘጸ (3፡ 8)፡ ስለ ፍሬ እና ጠላቶቻቸው
ዘጸ (3፡ 17)፡ ከመከራ ጊዜ እንደሚወጡ ወደ ወተት እና ማር ምድር
ዘጸ (13፡ 5)፡ ለእናንተ እሰጣችኃለሁ
ዘጸ (33፡ 3)፡ ወደ ወተትና ማር ምድር እንደሚሄዱ
ጠላቶቻቸው በእያንዳንዱ ጊዜ የተጠቀሱ ነበሩ ፤ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ከፊታችን ላለው ያዘጋጀናል ፡፡
ዘኁልቁ(13፡ 28-29)፡ የፍርሀት ሪፖርት፡ ከተማዎቻቸው ትልቅ እና የመሸጉ እና ህዝቦቹ ጠንካሮች ናቸው ፤ የኤናቅ ዘሮች በዚያ ነበሩ ! ትልቆች፣ ረጃጅም ተዋጊዎች ነበሩ ፡፡ ደግሞም አማሌቃዊያን፣ ኬጥያዊያን፣ ኢያቡሳዊያን፣ አሞራዊያን እናም አዎን ከነአናዊያንም በዚያ ነበሩ ፡፡
ዘኁልቁ(13፡ 30-33)፡ ካሌብ ተነሳ ህዝቡንም ዝም አሳባለ ፤ “ ማሸነፍ እንችላለንና እንውጣ እንውረስ” ብሎ ተናገረ፡፡ ካሌብ ይናገር የነበረው ይህ መሆን እንደሚችል እና ምድሪቱ የእነርሱ መሆን እንደምትችል አምኖ ነበር ፡፡ አስሩ ሰላዮች ይህን አላመኑም ምክንያቱም የከንዓን ወንዶች በጥንካሬ የሚታዩ ነበር ፤ እምነት አልነበራቸውም ፡፡
ጥሩ ያልሆነ ሪፖርት ሰጡ - የፍርሀት ሪፖርት ፤ ወንዶቹ ትልቅ እንደነበሩ ደገሙት ፡፡ ኤናቅ የኔፊሊም ዘሮች ነበር ፤ ኒፊሊሞችም እዚያ ነበሩ ! እንደገና ሪፖርታቸው የነበረው “ እንደ አንበጣዎች እንመስላለን(ነን) ፡፡“
መዝጊያ
እግዚአብሄር የሆነ ነገር ቃል ከገባልን ወደ ፍሬማነት እንድናመጣው ይፈቅዳል ! የእናንተን ስለላ በተመለከታችሁ ጊዜ በምን መንገድ ሪፖርት ታደርጋላችሁ ? 2ጢሞ (1፡ 7) የሚለው “ እግዚአብሄር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርኃት መንፈስ አልሰጠንምና ፡፡” ከእግዚአብሄር የኃይል፣ የፍቅር እና የጠንካራ አይምሮ ተስፋ አለን ፤ ከእኛ አንፃር ያለው ነገር ያሳስበናል ? ፍርሀትን የምንዋጋበት ይህ ነው ፡፡
ቃዴስ - ፉራን ለስለላ ሪፖርት የታወቀ ቦታ ነበር ፤ ወደ ምድሪቱ ለመሄድ ከመዘጋጀታቸው በፊት ለሰላዮቹ የመነሻ መስፈሪያ ነበር ፡፡ በተጨማሪም ቃዴስ በሙሴ ላይ የቆሬ አመፅ የነበረበት ቦታ ነበር (ዘኁ 16) ፡፡ ማሪያም የተቀበረችው እዚህ ነው (ዘኁ 20፡ 1) ፡፡ ሙሴ አለቱን በመምታት እግዚአብሄርን ያላከበረው (ዘኁ 20፡ 8-12) ፤ የአመፅና የተቃውሞ ቦታ ይመስላል ቢሆንም እግዚአብሄር ደግሞ ደግሞ ፍሬን(ማፍራትን) ቃል ገባ ፡፡
ዋይርስቤ የሚለው “ ሊፈተን ያልቻለ እምነት ሊታመን አይችልም ፡፡” በእውነተኛነቱ እርግጠኛ እንድንሆን ሊረዳን እግዚአብሄር እምነታችንን ይፈትናል ይህም እንድናድግ ይረዳናል (1ጴጥ 1፡ 1-9) ፤ የተፈተነ እምነት በብዙ እሱን እንድንመስል ያደርገናል ፡፡ እግዚአብሄር ባህሩን እንድንሻገር፣ ምድሪቱን እንድንወስድ ነግሮናል ምክንያቱም የእኛ ነው ነገር ግን መሰረታዊ የሆነ እምነት ያስፈልገዋል !
ሮሜ (4፡ 21)፡ “ የሰጠውን ተስፋ ሊፈፅም እንደሚችል አጥብቆ ተረዳ ፡፡”
ዕብ (11፡ 6)፡ “ ያለ እምነት ደስ ማሰኘት አይቻልም ፡፡”
እዚህ ላይ ቢያንስ ከወንዶቹ አስሩ የተናገሩት “ በምንም ሊሆን አይችልም ” ፤ ነገር ግን ካሌብ ተነስና እስራኤላዊያን ምድሪቱን መውሰድ እንደሚችሉ ተናገረ ፡፡ በስለላ ለመስራት የስለላ ሪፖርቱ ምንም አልነበረም ነገር ግን እግዚአብሄር ቃሉን እንደሚጠብቅ እስራኤላዊያን እምነት ነበራቸው ወይስ አልነበራቸውም በሚለው ለመስራት ሁሉንም ነገር ነበር ፡፡
Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., The Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishing, 1997) p. 252.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 333.
ጥያቄዎች
-
በዘኁ(12፡ 1-2) አሮን እና ማሪያም በወንድማቸው በሙሴ ላይ ተናገሩ ፡፡ (1ዜና 16፡ 22; መዝ 105፡ 15) እግዚአብሄር በዘኁ(12፡ 6-8) በሙሴና በሌሎች ነብያት መካከል ያደረገው ምን አይነት ንፅፅር አደረገ ?
-
በዘኁ(12፡ 7) እግዚአብሄር ሙሴ በሁሉም በእግዚአብሄር ቤት የታመነ ነበር አለ ፤ በዕብ (3፡ 2) ቆይቶ ይህ ተጠቅሶዓል ፡፡ በዕብ (3፡ 1-6) ሁለቱ ሰዎች በምንድን ተነፃፀሩ ? ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነታቸው ምንድን ነበር ? (ዕብ 3፡ 5-6)
-
ሙሴ ከእርሱ ወደ ሚበልጠው የሚያመለክት የክርስቶስ አይነት ነበር ፤ (ዘኁ 12፡ 7; ዘዳ 18፡ 15; ሐዋ 7፡ 37) ህዝቡ በሚገባ ሙሴን አላደመጡትም አንዳንዴ በእርሱ ላይ ተናገሩም አጉረመረሙም ፤ በዘዳ(18፡ 15) መሰረት ቃየ ተገባውን ነብይ እንዲያዳምጡ ታዘው ነበር ? ሐዋ (3፡ 22-23) አንብቡ ፡፡ የመጣውን መሲህ የክርስቶስ ቃል በማይሰሙት ላይ ወይም በማይቀበሉት ላይ ምንድን ይሆናል ?
-
በዘኁ(13፡ 2) ከእያንዳንዳቸው ነገድ መሪዎች ተመልሰው ሪፖርት ይዘው እንዲመጡ እንደ ሰላይ ወደ ተስፋይቱ ምድር ተላኩ ፤ አብዛኛዎቹ መጥፎ ሪፖርት ሰጡ (ዘኁ 13፡ 32) ዉጤቱም በህዝቡ ላይ ፍራት ነበር (ዘኁ 14፡ 1-3) ፡፡ እግዚአብሄር ሰጥቶአቸው ከነበረው ተስፋ ይልቅ እንደ አምበጣ እንደሆኑ ለማመን ለምን እንደመረጡ ምን ታስባላችሁ ? (ዘፍ 17፡ 8; 35፡ 12; ዘጸ 6፡ 8; ዘኁ 13፡ 2) በእግዚአብሄር ተስፋ እና ቃል ውስጥ ያዩትን እና የሰሙትን ለማጣርት በመሪወች ላይ ስላለው ኃላፊነት ይህ ምንድን ይነግራችኃል ? (2ቆሮ 1፡ 20; 5፡ 7) “ መጥፎ ሪፖርት ” የሰማችሁበትን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ? ለራሳችሁ ያን ስራ እንዴት አደረጋችሁት ?
-
የዮፎኒ ወንድ ልጀ ካሌብ በሌሎቹ ሰላዮች በተሰጠው የውሸት ሪፖርት ላይ በመነሳት እምነትንና አሸናፊነትን ተናገረ ፡፡ በሰው ፍርሀት ከመመለስ ይልቅ በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ በመደገፍ ለምታምኑበት በብዙኀኑ ላይ እስካሁን ተነስታችሁ ታውቃላችሁ ?
-
በዘኁ(12-13) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 13:30-31
“Then Caleb quieted the people in the presence of Moses and said, ‘We must go up and take possession of the land because we can certainly conquer it!’ But the men who had gone up with him responded, ‘We can’t go up against the people because they are stronger than we are!’”
ከነዓንን ሰለሉ
ኦሪት ዘኁልቁ 12-13 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚአብሔር ሙሴን 12 ሰዎች እንዲሰልሉ ወደ ከነዓን ምድር እንዲልክ አዘዘዉ። ከ40 ቀናትም በኃለ ሁለት የተለያዩ ዘገባዎች ይዘዉ ተመለሱ። አብዛኞቹ ሰላዮች የተመለሱት፥ እጅግ ፈርትዉ፣ ደንግጠዉ እና ምድሪቱን ለመዉረስ አሉታዊ የሆነ ምልከታ ይዘዉ ነዉ! ነገር ግን ካሌብ በእምነት ተሞልቶ ምድሪቱን መዉረስ እንደሚችሉ ተናግሮ አረጋገጠ!
እግዚአብሔር ወደ የህይወት አዲስ ሁኔታዎች ሲመራህ፥ በአዎንታዊ ወይ ደግሞ አሉታዊ መንገድ ምላሽ መስጠት ያንተ ምርጫ ነዉ! መፍራትን ወይንም ማመንን መምረጥ ትችላለህ። ከመጀመሩ በፊት እንደተሸነፍክ ማመን ወይም በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ አሸናፊ ሆነህ እንደምጥወጣ ማመን መምረጥ ትችላለህ። እግዚአብሔር ራሱ ከአንተ ጋር የሚሄድ ከሆነና፥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በዉስጥህ ካለ፥ የማይቻል በሚመስሉ ሁኔታዎች ዉስጥ ለማለፍ የሚያስፈልገዉ ነገር ሁሉ አለህ። አስታዉስ፥ ከእግዚአብሔር ጋራ ሁሉም ነገር ይቻላል! እግዚአብሔር የሰጠን የፍርሃትን መንፈስ ሳይሆን የኃይል፣ የፍቅር እና ርቱዕ አስተሳሰብን ነዉ። ጌታ አንተን ወደ አዲስ የህይወት ግኝቶች በሚመራህ ጊዜ፥ ዛሬ በነዚህ የተስፋ ቃሎች ተመላለስ።
"ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፦ ማሸነፍ እንችላለንንና እንውጣ፥ እንውረሰው አለ። ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም አሉ።"
ኦሪት ዘኁልቁ 13:30-31
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የሉቃስ ወንጌል 1:37፦ "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37፦ "በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።"
- 2ኛ ወደ ጢሞቲዎስ 1:7፦ "እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 80
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።