The People Rebel
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዘኁልቁን ስንጀምር ስለ እስራኤላዊያን ወታደራዊ አወቃቀር አውርተናል ፤ ሁሉም ነገር የተቆጠረ እና ሁሉም ሰው የተቆጠሩ ነበሩ ፡፡ ትናትና ወደ ምድሪቱ ስለ ሄዱት 12 ሰላዮች ማየት ጀምረናል ፡፡
ትምህርት
ዋይርስቤ በዘኁ 13-14 ስለ አምስት የልፍለፋ ኃጢዓቶች ያወራል ፤ ከእስራኤል ኃጢዓት ብዙ መማር እንችላለን፡
- የእግዚአብሄርን ቃል መጠራጠር (ዘኁ 13፡ 1-25)
- አስራኤል የእግዚአብሄርን ቃል ተጠራጠረ
- በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዛሬ መሆን የቻለውን ተስፋችንን ምን ያክል ጊዜ ተጠራጥረነዋል ?
- ሌሎችን ሰዎች ተስፋ ማስቆረጥ (ዘኁ 13፡ 28-29, 31-33)
- የውሸት ሪፖርት
- የምድሪቱ ሰዎች በጣም ትልቅ ነበሩ
- የእግዚአብሄር ፍቃድ መጣስ (14፡ 1-10)
- ወደ ከንዓን ለመግባት የእስራኤል ተቃውሞ
- የእግዚአብሄር ፍርድ ተገቢነት (ዘኁ 14፡ 11-38)
- በእስራኤል ተቃውሞ ላይ ፍርድ
- የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ አለመታዘዝ (ዘኁ 14፡ 39-45)
- ለኃጢዓታቸው ለማካካስ ሞከሩ
ዘኁልቁ(14፡ 1-2)፡ ሰላዮቹ እስራኤላዊያን የምድሪቱን ንብረት መውሰድ እንደማይችሉ ሪፖርት አደረጉ ፤ ህዝቡ አለቀሱ ሌላም ማጉረምረም ነበር ፤ በምድረበዳ እንዲሞቱ ተመኝተው ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 3)፡ እስራኤላዊያን ከነበሩበት በግብፅ እንደሚሻ ማሰብ ጀመሩ ፤ በግብፅ ከነበራቸው ከማይታወቅ ለእነሱ ይጠብቁት ከነበረው ከተስፋይቱ ምድር የሚሻል መሰላቸው ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 4)፡ ወደ ኃላ እንዲመሩ መሪ ሊሾሙ አውርተው ነበር (1ቆሮ 10፡ 10; ፊል 2፡ 14) ፡፡ ሁል ጊዜ ምርጫ አለን፡ይህ ህይወትን መስጠት ወይስ መውሰድ ነው ? እስራኤላዊያን በእግዚአብሄር ለመታመን እና ከሀሳባቸው በላይ የመባረክ እድሉ ነበራቸው ነገር ግን በዚያ ፋንታ መጥፎ ሪፖርት አዳመጡ ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 5)፡ ሙሴና አሮን በሁሉም ጉባኤ በፊታቸው ወደቁ ፤ ሙሴና አሮን በትህትና መለሱ ፡፡ የእግዚአብሄር ሰው ከእግዚአብሄር የሆነ ነገር በመስማት ፣ መሬቱን በመምታት ሞደል መሆንን ይመስላሉ (ዘኁ 16፡ 4፣ 22፣ 45፣ 20፡ 6) ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 6-8)፡ ኢያሱ እና ካሌብ ልብሶቻቸውን ቀደዱ በትህትናም መሰሉ ፤ ታውቆ በነበረው ተጨነቅ ፤ እነዚህ ሁለት ወንዶች የህዝቡን ማማረር መቃዎም ጀመሩ ፡፡ ኢያሱ እና ካሌብ እግዚአብሄር ቃል የገባውን እንደሚያደርገው አመኑ ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 9)፡ ኢያሱ እና ካሌብ ተናግረው የነበረው “ አትፍሩ እንደ እንጀራ እንጎርሳቸዋለን ፡፡“ የዘፍጥረት(15፡ 16) ጊዜ መጣ ፡፡ ኢያሱ እና ካሌብ ራዲካሊይ ከፍ አሉ ፡፡ በአለም ውስጥ ለመሆን ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው ነገር ግን ከአለም አደለም ፡፡ በእግዚአብሄር እርግጠኝነትን ማድረግ የምንጀምረው ምንድን ላይ ነው ?
ዘኁልቁ(14፡ 10-16)፡ ሙሉ ማህበረሰቡ (ምናልባት 2ሚልዮን የሚሆን) ኢያሱን እና ካሌብን ለመውገር አስፈራሩዓቸው ነገር ግን የእግዚአብሄር ክብር ተገለጠ ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዎች ልክ እንደ እግዚአብሄር ሰዎች አክት ያደርጋሉ እግዚአብሄር ያሳያያቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር ጠየቀ “ ይህ ህዝብ መቼ ነው የሚያምኑብኝ ? አጠፋቸዋለሁ አንተንም ሙሴ ለሚጠነክር ህዝብ አደርግሀለሁ ፡፡” ለህዝቡ ሙሴ ልብ ነበረው ፤ መደምሰሳችንን ግብፅ እንደሚሰሙ እግዚአብሄርን አስታወሰው ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 17-19)፡ “ እግዚአብሄር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል…….” (ቁጥር 18) ነገር ግን ሳይቀጣ አይሄድም ፡፡ ይህ ከግብፅ እስከ አሁን በእግዚአብሄር ትክክለኛ ፍቅር የፀና ነበር ፡፡ ሙሴ ለእስራኤል ማለደ፣ ፀለየ፣ “ የእግዚአብሄርን ህዝብ እወዳቸዋለሁ ስለዚህ እግዚአብሄር እስራኤልን ከግብፅ ፍቅርህን በመጠበቅ ነፃ አወጣሀቸው እባክህን የዚህን ህዝብ ክፉ ስራ ይቅርበል !” ሙሴ ኢየሩሳሌምን እንዲያድን ለእግዚአብሄር እንደፀለየው እንደ ነህምያን ፀለየ ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 20-21)፡ እግዚአብሄር ሰማ ይቅርም አላቸው (መዝ 130፡ 4) ፤ ሁልጊዜ ምህረት እግዚአብሄርን ወደ መፍራት ይመራል ፡፡ እግዚአብሄር የተናገረው “ ይቅር እላቸዋለሁ ነገር ግን ፍርድ ይኖራል ፡፡“
ዘኁልቁ(14፡ 22)፡ የመዳን ጉዞውን ለምደውት የነበሩ ወይም የእግዚአብሄር ክብር አይተው የነበሩ ማንኛውም ሰው ወደ ተስፋይቱ ምድር አይገቡም ፡፡ እግዚአብሄርን አስር ጊዜ ፈተኑት ስጦታውን አልተቀበሉም፡
ዘጸ 14 ፡ ቀይ ባህርን ተሸገሩ
ዘጸ 15፡ ማራ መራራ ዉሃው
ዘጸ 16፡ በብዙ ተራቡ
ዘጸ 16፡ የሙሴን መምጣት ችላ አሉ
ዘጸ 16፡ እንደገና መና
ዘጸ 16፡ ለሰንበት መና ለመሰብሰብ አልፈለጉም
ዘጸ 17፡ እንደገና ስለ ዉሃ ቅሬታ አቀረቡ
ዘጸ 32፡ ሲና ተራራ የወርቅ ጥጃ
ዘኁ 11፡ ለስጋ በእግዚአብሄር ላይ ተቆጡ
ዘኁ 13፡ መልካሙን ሪፖርቱን ለማመን እምቢ አሉ
ዘኁልቁ(14፡ 23)፡ እግዚአብሄር የተናገረው “ የምትንቁኝ ከሆነ አትገቡም ፡፡” እስራኤላዊያን የኃጢዓታቸውን ውጤት ይደርስባቸዋል ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 26-38)፡ የ20 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሬሳቸው በምድረበዳ ይወድቃል ፡፡ የሞት ዘመቻ ነበር ፤ ልጆቹ ብቻ ከነዓን ይገባሉ (ይቀምሱታል) ፤ ኢያሱ እና ካሌብ ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚገቡ ወጣቶች ይሆናሉ ፡፡
ዘኁልቁ(14፡ 39-45)፡ ሀዘን ነበር ነገር ግን ንስሀ የለም ፡፡ እስራኤላዊያን ወደፊት ለመሄድ ወሰኑ እናም በራሳቸው ሄዱ ፤ ሙሴ እንደሚሸነፉ አስጠነቀቃቸው ነገር ግን እስራኤላዊያን ያም ሀኖ አደረጉት ፡፡ ሙሴ በሰፈር ተቀመጠ ፤ እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር አልሄደም ፡፡
መዝጊያ
የሚሄዱ ከሆነ ሙሴ እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር እንደማይሆን ህዝቡን አስጠነቀቀ ፡፡ ከእስራኤላዊያን ልንማር ያስፈልገናል ፤ የእግዚአብሄር ፈቃድ ካለበት መስመር በወጣን ጊዜ በራሳችን ፈቃድ እና ጥንካሬ ለማሳተካከል ይልቅ በፊታችን በእግዚአብሄር ፊት መውደቅ ይሻላል ፡፡ ለትህትና በክርስቶስ አካል ውስጥ ጊዜ አለ ፤ ለትህትና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጊዜ አለ ፡፡ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመስመር ዉጪ ያሉ ነገሮች እንዳሉ ለማመን ጊዜ አለ ፡፡ ወደኃላ መጎተትን እናስብ ፤ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር አይሆንም ፤ መሰራታዊ ትህትና ይወስዳል ፡፡ ኢያሱ እና ካሌብ ይህ ነበራቸው ፤ ሙሴና አሮን ይህ ነበራቸው ፡፡
ዋይርስቤ የፃፈው “ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ሚንስተር ኤፍ. ወ. ሮበርሰን (1816-1853) መታዘዝ የመንፈሳዊ እውቀት ኦርጋን ነበር ብሎ የተናገረው ትክክል ነበር ፡፡” ታዛዦች ከሆን በእውነቱ በመታዘዝ መሄድ እንችላለንም የእግዚአብሄር ፍቃድንም እናውቃለን ፡፡ ዋይርስቤ የፃፈው “ ለመታዘዝ ፍቃደኞች ካልሆንን እግዚአብሄር ለዕኛ ፍቃዱን ለመግለጥ አይገደድም ፡፡” በመንፈስ ከተጎአዛችሁ መንፈስ ነፃ ያወጣችኃል (ዮሐ 8፡ 32) ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Expository Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 331–335.
Wiersbe, p. 334.
Wiersbe, p. 334.
ጥያቄዎች
-
እስራኤላዊያን ከሰላዮቹ በሰሙት መጥፎ ሪፖርት በሙሴ እና በአሮን ላይ አማረሩ ፤ እንደ አማኝ ህይወት ፍርሃት እንዲሰማን ሲያደርገን በፍርሀት ምላሽ ከመስጠት እራሳችንን እንዴት ልንጠብቅ እንችላለን ?
-
የሙሴና የአሮን መልስ በዘኁ 14፡ 5 በግንባራቸው(በፊታቸው) መውደቅ ነበር ፤ በቁጥር(13-19) ሙሴ ስለ ጉባኤው ማለደ ፡፡ ከግብፅ በመውጣት ጉዞአችሁ ውስጥ ይህን ሞደል(ቅርፅ) አይታችኃል ? እናንተ የትኛውን ትመስላላችሁ፡ አማራሪዎቹን፣ ተስፋ ለመቁረጥ ፈጣን ወይስ ኃጢዓት ሰርተው ለነበሩት የማለደውን ሙሴን ?
-
ከእምነት ይልቅ ፍርሀትን መሰረት አድርገው መጥፎ ሪፖርት ባመጡት አስር ሰላዮች ላይ ምንድን ሆነ(ዘኁ 14፡ 36-37) ? ካሌብና ኢያሱ ለምን ነበር ያልተካተቱት ?
-
በዕብ(3፡ 19) መሰረት እስራኤላዊያን ወደ ተስፋይቱ ምድር መግባት ያልቻሉበት ምክንያት ምን ነበር ?
-
የኃጢዓታቸውን ዉጤት ከሰሙበት ቀን ቦኃላ የእስራኤላዊያ እቅድ ምንድን ነበር (ዘኁ 14፡ 40) ? የሙሴ መልስ ምን ነበር ?
-
በዘኁ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 14:24
“But since My servant Caleb has a different spirit and has followed me completely, I will bring him into the land where he has gone, and his descendants will inherit it.”
የህዝቡ አመፅ
ኦሪት ዘኁልቁ 14
የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ከነዓንን ሊሰልሉ ከተላኩት አስራ ሁለቱ ሰዎች መካከል የተስፋ ቃሉን በማመን በህይወት የተገኙት ካሌብ እና ኢያሱ ብቻ ናቸዉ። ካሌብ የተለየ መንፈስ እንዳለዉና ፈፅሞ እንደተከተልዉ እግዚአብሔር አየ። ካሌም በእምነት እና በትህትና ተመላለሰ። ስለእስራኤላዉያን ኃጥያት ካሌብ ከሙሴ፣ አሮን እና ኢያሱ ጋራ በመሆን አዝኗል! በአዲሱ ምድር እግዚአብሔር ከእርሱ እና ከሌሎች ጋራ እንደሚሆን አምኗል።
እግዚአብሔር ስለአንተ እነዚህን ቃላቶች ተናግሮ ቢሆን ብለህ ማሰብ ትችላለህ? "[ስምህን ሙላዉ] በፍፁም ተከትሎኛል።" እግዚአብሔር ወደ ሆነ ነገር ሲመራህ፥ በእርሱ ታምኝነት እና በእርሱ ትታመናለህ ወይስ በመወላወል ዉስጥ ሆነህ ትጠራጠራለህ? ዛሬ፥ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ መሆንን ለመታመን ምርጫህ አድረግ! ፍፁም በሆነ መንገድም ከትህትና ጋራ እርሱን ተከተለዉ! ጌታ በሚታመነዉ ፍቅሩ ባለጠጋ ነዉ! ፍቅሩም ፈፅሞ አይጥለህም!
"ባሪያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለተከተለኝ እርሱ ወደ ገባባት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።"
ኦሪት ዘኁልቁ 14:24
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘኁልቁ 14:17-18፦ "አሁንም፥ እባክህ፦ እግዚአብሔር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ፥ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ ኃጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው ብለህ እንደ ተናገርህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን።"
- መዝሙረ ዳዊት 119:133፦ "አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ።"
- የያዕቆብ መልዕክት 4:6፦ "ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕ በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 81
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።