Korah’s Rebellion
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የትናትናው ክፍል ስለ 12 ሰላዮች የተመለከተ ነበር ፤ አስሩ የእግዚአብሄር ወንዶች የተናገሩት “እንጠብቅ !“ ሲሆን ኢያሱና ካሌብ “እንሂድ !” ብለው ተናገሩ ምክንያቱም አስሩ ሰላዮች “ አይሆንም” እግዚአብሄር እስራኤል በሙለ ሊቀጣ ወስኖአል አሉ ፡፡ እስራኤላዊያን እስከ ሞታቸው ድረስ በዙሪያው ይንከራተታሉ ፤ እድሜአቸው ከ20 አመት በታች የሆኑት ብቻ የተስፋይቱን ምድር ለማየት ይኖራሉ ፡፡ ኢያሱና ካሌ በእግዚአብሄር ተስፋ ተደገፉ ነገር ግን ቀሪዎቹ እስራኤላዊያን በእነዚያ ተስፋ አልተደገፉም ፡፡ ምን እንደሆነ ተመልከቱ ፤ ቀሪዎቹ እስራኤላዊያን ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲገቡ አላደረጉም ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(15፡ 1-29)፡ እስራኤላዊያን ወደ ተስፋይቱ ምድር አይገቡም ልጆቻቸው ግን ይገባሉ (ቁጥር 1-5) ፡፡ ወደ ምድሩቱ በሚገቡ ጊዜ ስለ መስዋዕት ህጎች ነበሩ (ቁጥር 6-16) ፤ የማንሳት መስዋዕት ያደርጋሉ (ቁጥር 17-21) ከዚያም በተጨማሪ ሳይታወቅ ስለ ሚደረግ ኃጢዓት ምን እንደሚያደርጉ ትዕዛዝ ነበር (ቁጥር 22-29) ፡፡
ዘኁልቁ(15፡ 37-41)፡ እግዚአብሄር ሙሴን እንዲታዘዙ ለማሳሰብ እና የእግዚአብሄርን ትዕዛዞች እንዲያስታውሱ ለልብሶቻቸው ዘርፍ እንዲኖራቸው እስራኤላዊያን እንዲሰሩ አዘዘው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ በአንገት ላይ ከሚለበስ ጌጥ፣ ከተለየ ሳንቲም ወይም በቤታችሁ ካላ ምልክት ጋር ተመሳሳይ ይሆናል ፡፡ ሳልሀመር የፃፈው “ ህጎች ሲጨምሩ ግዴታዎች ያድጋሉ ህዝቡም ፍቃደኝነቱ ወይም እነርሱን የመከተል ችሎታ ያነሰ ይመስላል ፡፡” ህጎች ስለጨመሩ እስራኤላዊያን ያምፃሉ በዘኁ 16 የምታዩት ለዚያ ነው ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 1-2)፡ ቆሬ፣ ዳታንና አቤሮን ከእነርሱም ጋር 250 እስራኤላዊያን ወንዶች ነበሩ፣ ዝናቸውም የታወቅ መሪዎች ነበሩ ባለጌዎችም ሆኑ በሙሴም ላይ ተነሱ ፡፡ በዋይርስቤ መሰረት ቀዓትዋዊያን የመቅደሱን እቃ ይሸከማሉ ፡፡ በበዱብ በኩል ሰፍረዋል ስለዚህ ከጋድያዊያን፣ ከሮቤላዊያን እና ከስምዖናዊያን ጋር የተያያዙ(የተጠጋጉ) ነበሩ ፡፡ የዘኁ 12 ማሪያምና አሮን ሁለቱም የሙሴን ስልጣን መጠየቃቸውን አስባለሁ (1ቆሮ 15፡ 33, ምሳ 13፡ 20)፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 3)፡ የ250ዉ ቡድን በአንድ ላይ በመምጣት ሙሴን እና አሮንን ጠየቅዓቸው፡ “ እናንተ ብቻ ቅዱስ እንደሆናችሁ ለምን ታስባላችሁ ? ማህበሩ በሙሉ ቅዱስ ነው ፤ አብዝታችሁታል”(ዘጸ 19፡ 5-6) ፡፡ እውነታው የነበረው በስልጣን አንድ ሰው ይሆናል ( 1ቆሮ 15፡ 33, ምሳ 13፡ 20) ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 4-7)፡ ሙሴ ቅሬታቸውን በሰማ ጊዜ በፊቱ ወደታች ተደፋ ፤ ሙሴም እግዚአብሄር ነገ ማን ቅዱስ እንደሆነ እና ወደ እርሱ ማን መቅረብ እንደሚችል ይመርጣል ብሎ ተናገረ ፡፡ ቆሬ እና ተከታዮቹ ማጠኛዎችን ወሰዱ ፤ በቀጣዩ ቀን በእግዚአብሄር ፊት በማጠኛዎቹ ላይ እሳት እና ዕጣን አስቀመጡ ፤ እግዚአብሄር የመረጠው ሰው ብቻ ቅዱስ ይሆናል ፡፡ “ ሌዋዊያን ይህ የእናንተ ነው አብዝታችሁታል !” (ቁጥር 6) ፡፡ ኢየሱስ በፅድቅ ይፈርዳል ፡፡ 1ጴጥ 2፡ 23 ፤ ሉቃ 22፡ 42 ሰዎች በጠየቁት ጊዜ ኢየሱስ እንዴት እንደመለሰላቸው ያሳያሉ ፡፡ እሱ አለት ነው ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 8-11)፡ ለሌዋዊያን ሙሴ የተናገረው “ የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማህበር የለያችሁ፣ የእግዚአብሄርንም ማደሪያ አገልግሎት ትሰሩ ዘንድ፣ እንድታገለግሉዓቸውም በማህበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁ አይበቃችሁምን ? ይህ ያደረጋችሁት በእግዚአብሄር ላይ አድርጋችኃል ፤ ለምን በአሮን ላይ አጉረመረማችሁ ?” የእግዚአብሄርን ስራ በሰራችሁ ጊዜ የተጠላችሁ እንደምትሆኑ በሙሉ መጠበቅ አለባችሁ (1ዮሐ 3፡ 12-13, ዘፍ 37፡ 4, ዮሐ 15፡ 18-19) ፡፡ ለማገልገል በምትመጡ ጊዜ ከፍ ያደርጋችኃል (ማር 10፡ 45) ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 12-15)፡ ሙሴ ለዳታንና ለአቤሮንን ላከባቸው ነገር ግን አልመጡም ፤ “ በምድረበዳ ትገድለን ዘንድ ወተትና ማር ከምታፈስሰው ምድር ያወጣኸን አይበቃህምን ? ደግመህ በእኛ ላይ ራስህን አለቃ ታደርጋለህን ? አንመጣም !” አሉት ፤ ሙሴ በጣም ተበሳጨ መስዋዕታቸውንም እንዳይቀበል እግዚአብሄርን ጠየቀ ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 16-19)፡ ሙሴ ቆሬን ከሀሉም ሰዎቹ ጋር እና ከአሮን ጋር በቀጣዩ ቀን በእግዚአብሄር ፊት እንዲቀርብ ነገረው ፤ እያንዳንዳቸው እጣን ያለበትን ማጠኛ አመጡ (250 ማጠኛዎች ይሆናሉ) ከዚያም በእግዚአብሄር ፊት አቅርቡ ፡፡ ስለዚህ ቆሬና ስዎቹ በተጨማሪም ሙሴና አሮን ማጥናቸውን ከእጣናቸው ጋር ወስደው መገናኛው ድንካን መግቢያ ላይ ቆሙ ፤ የእግዚአብሄር ክብር ለጠቅላላ ማህበሩ ተገለጠ ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 20-24)፡ እግዚአብሄር ለሙሴና ለአሮን ተናገረ ፤ ከአጠቃላይ ማህበሩ ራሳቸውን እንዲለዩ ነገራቸው ምክንያቱም በቅፅበት ሊያጠፋቸው ስለሆነ ፡፡ ነገር ግን ሙሴና አሮን በ250 ወንዶች ምክንያት ጠቅላላ መህበሩን እንዳያጠፋ እግዚአብሄርን በግንባራቸው ተደፍተው ጠየቁት ፤ እግዚአብሄር ሙሴን ማህበሩ ከቆሬ፣ ከዳታን እና ከአቤሮን ማደሪያ እንዲርቁ እንዲነግራቸው ነገረው ፤ ከእርጉሞቹ ሰዎች መራቅ ነበረባቸው ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 25-27)፡ ሙሴ ወደ ዳታንና አቤሮን ሄደ የእስራኤል ሽማግሌዎች ተከተሉት ፤ ከእነዚህ እርጉም ወንዶች ድንካኖች እንዲሩቅ ጠቅላላውን ማህበር አስጠነቀቃቸው - የእነርሱ ከሆነው ማንኛውም ነገር ራቁ ወይም በኃጢዓታቸው ምክንያት እንዳትጠፉ ራቁ ፡፡ ከዚያም ዳታንና አቤሮን፣ ከሚስቶቻቸው ጋር፣ ልጆቻቸው እና ህፃናቶቻቸው ከድንካናቸው ወጥተው በመግቢያው ላይ ቆሙ ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 28-30)፡ እግዚአብሄር እንደላከው ሙሴ ነገራቸው ፤ የእራሱ ፍቃድ አልነበረም ፡፡ እነዚህ ሰዎች ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ከሞቱ እግዚአብሄር አላከውም ፤ እግዚአብሄር አድስ ነገር ያመጣል ከዚያም ምድር እነርሱን የእነርሱ ከሆነው ጋር ትዉጣቸዋለች ወደ ታች ወደ ሲዖል በህይወት ይሄዳሉ እስራኤላዊያንም ቆሬና ተከታዮቹ እግዚአብሄርን እንደናቁ ያውቃሉ ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 31-34)፡ ሙሴ ንግግሩን እንደጨረሰ ምድር ተሰንጥቃ ተከፈተች (1ሳሙ 14፡ 15; 1ነገ 19፡ 11) ፤ እግዚአብሄር ማንኛውንም በአካላዊ መንገድ መጠቀም ይችላል፡ በደመናዎች፣ በእሳት፣ በመብረቅ ወይም በነጎድጎአድ ማድረግ የፈለገውን ያደርጋል ፡፡ ምድር እነርሱን እና ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ሁሉንም የቆሬ ሰዎች እና ንብረታቸውን ዋጠች (ይሁ 1፡ 11) ፡፡ በሁሉም በብሉያ ኪዳን ውስጥ ይህ እንደ አንድ ኃይለኛ የአመፅ ቡድን ይታወቅ ነበር ፡፡ ከዚያም ምድር በላያቸው ላይ ተዘጋች ከጉባኤውም ጠፉ ፡፡ በጩኸታቸው ደግሞ እንዳትዉጣቸው በመፍራት በዙሪያ ያሉት ሁሉም ህዝብ ሸሹ ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 35-38)፡ ከዚያም እሳት ከእግዚአብሄር መጣ 250 ወንዶቹን እና እጣናቸውን በላች (ዕብ 10፡ 31) ፡፡ እግዚአብሄር ለሙሴ አለው “ ለአልዓዛር እንዲህ ብለህ ንገረው ተቀድሰዋልና ጥናዎቹን ከተቃጠሉት ዘንድ ውሰድ እሳቱንም ወደ ውጭ ጣለው ፤ በኃጢዓታቸው ሰውነታቸውን ያጠፉትን የእነዚያን ሰዎች ጥናዎች ጠፍጥፈህ ለመሰዊያ መለበጫ አድርገው ፡፡” ጥናዎቹ ቅዱስ ነበሩ ምክንያቱም ለእግዚአብሄር ስለቀረቡ ፤ ለእስራኤላዊያን እንደ ምልክቶች ያገለግላሉ ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 39-41)፡ አልዓዛር የናስ ጥናዎቹን ወሰደ ለመሰዊያም ለመለበጫነት ቀጠቀጣቸው ፡፡ ይህ ከአሮን ዘር ዉጪ የሆነ ያልተገባው ሰው በእግዚአብሄር ፊት እጣን ለመሰዋት እንዳይቀርቡ መታሰቢያ ነበር ፡፡ በቀጣይ ቀን ጠቅላላ የእስራኤል ማህበር ሙሴና አሮን የእግዚአብሄርን ሰዎች ገድላችኃል ብለው አጉረመረሙ ፤ እግዚአብሄርን መፍራት አልነበረም ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 42-46)፡ ሙሴና አሮን እመገናኛው ድንካን ፊት ከእግዚአብሄር ጋር ሊነጋገሩ ሄዱ ፤ እንደገና እግዚአብሄር የእስራኤልን ማህበር በቅፅበት ማጥፋት ፈለገ ፡፡ ሙሴና አሮን አሁንም እንደገና ስለ ህዝቡ በግንባራቸው ተደፉ ፤ ሙሴ አሮንን ጥናዎቹን በመውሰድ እሳትና ዕጣን በላያቸው ላይ እንዲያስቀምጥ ነገረው ፡፡ ወደ ማህበሩ በመሄድ ለእነርሱ ስርይት እንዲያደርግ አዘዘው ምክንያቱም እግዚአብሄር መቅሰፍት ሊያመጣ ስለሆነ፡፡
ዘኁልቁ(16፡ 47-50)፡ አሮን ሙሴ እንደተናገረው አደረገ ፡፡ አሮን መቅሰፍቱ እንደጀመረ አየ ህዝቡም መሞት ጀምረው ነበር ፤ አሮን በሞቱት እና በኖሩት መሀከል ቆመ መቅሰፍቱም አቆመ ፡፡ አሮን አማላጅ ነበር ፡፡ ከቆሬ ግጭት የሞቱትን ጨምሮ 14,700 ሰዎች ሞቱ ፡፡ አሮን በዕጣን እንደ አማለጅ አክት ባያደርግ ብዙ ይሞቱ ነበር ፡፡ አሮን ወደ መገናኛው ድንካን መግቢያ ላይ ወደ ሙሴ ተመለሰ ፡፡
መዝጊያ
ይህ ስለ ኢየሱስ እንዳስብ ያደርገኛል ፤ ኢየሱስ ወደ ሰፈራችን መሀከል በትክክል ሮጠ(ሮሜ 5፡ 8; ሕዝ 22፡ 30; ዕብ 7፡ 25) ፡፡ እግዚአብሄር ብዙ ጊዜ ሊያጠፋቸው ፈለገ ፤ እብደትን ለማቆም አሮን እንዴት በሁሉም ነገር መሀከል እንደሮጡ ወድጀዋለሁ ፤ ለእኛ እግዚአብሄር ያደረገልን ያንን ነው ፡፡
John H. Sailhamer, The Pentateuch as Narrative (Grand Rapids, MI: Zondervan, 1992), p. 391.
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 249.
ጥያቄዎች
-
ለእግዚአብሄር እንደ ሚጣፍት ሽታ ህዝቡ ያቀረበው ደመና “ የተለየው ስጦታዎች/መስዋዕቶች” ምንድን ነበሩ ?
-
እግዚአብሄር ሙሴን የነገረው በሰንበት እንጨት የሰበሰበው ሰውዬ የተሸከመው ቅጣት ምንድን ነበር ? በማን ? (ዘኁ 15፡ 35-36)
-
በዘኁ 16 በሙሴ ላይ ያደመው ወይም ያመፀው ማነው (ስለሆነም በእግዚአብሄር) ? ለምን እንዳደረጉት ምን ታስባላችሁ ?
-
በዘኁ 16፡ 6-7 እንዲያደርጉት በመንገር ሙሴ ምንድን አደረገ ? ለእነዚህ ሰዎች በቁጥር (31-32) ምን ሆነ ?
-
በዘኁ (16፡ 36-38) በእጣን ማንደጃዎች እንዲሰራ ሙሴን በመንገር እግዚአብሄር ምን አደረገ ? ለምን ?
-
በማግስቱ በማለዳ እንደገና ህዝቡ ያጉረመርም ነበር ፤ እግዚአብሄር ለመስራት ምን አደረገ ? ለመከላከል እንዲሰራ ሙሴ አሮንን በመንገር ምንድን አደረገ ?
-
በዘኁ 15-16 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 16:22
“But Moses and Aaron fell facedown and said, ‘God, God of the spirits of all flesh, when one man sins, will You vent Your wrath on the whole community?’”
የቆሬ አመፅ
ኦሪት ዘኁልቁ 15-16 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
የእስራኤል ማህበረሰብ በእግዚአብሔር ላይ ማመፁን ቀጥሏል። ሌዋዊዉ ቆሬ፥ ከሌሎች ታዋቂ 250 እስራኤላዉያን እና የማህበሩ መሪዎች ጋራ በመሆን፥ ሙሴና አሮን ባላቸዉ የመሪነት እና የክህነት ሹመት ቦታ ላይ ጥያቄ አስነሱ! በሶስት በተላያየ ጊዜ የሙሴ እና የአሮን ምላሽ በእግዚአብሔር ፊት መዉደቅ ነዉ! በእስራኤል ህዝብ ምትክ፥ በፍፁም ትህትናና ራሳቸዉን አሳልፈዉ በመስጠት እግዚአብሔርን ፈለጉ! ህዝቡ ሙሴን እና አሮንን በሚወቅስበት ጊዜ እንኳን ህዝቡን ለማዳን የጌታን ምህረትና ህዝቡን እንዳይቀጣ ይጠይቁ ነበረ።
እግዚአብሔር የህይወትህን ጥያቄ እንዲመልስ አጥብቀህ በምትፈልግበት ጊዜ የምታደርገዉ ምንድን ነዉ? ራስህን ሙሉ በሙሉ በመስጠት፥ ፉቱ ትደፋለህ? ሙሴ እና አሮን የእግዚአብሔርን ኃይል እያወቁ ያላቸዉን ነገር ሁሉ ይዘዉ በፊቱ ቀረቡ! ዛሬ በምታልፍበት መንገድ ሁሉ፥ በአምልኮ እና ራስህን ለእርሱ አሳልፎ በመስጠት በፊቱ ዉደቅ! ባለህበት ሁኔታም በኃይል እንደሚንቀሳቀስ ጠብቀዉ!
"እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው፦ አምላክ ሆይ፥ አንተ የሰው ሁሉ ነፍስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን? አሉ።"
ኦሪት ዘኁልቁ 16:22
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ወደ ገላትያ ሰዎች 2:20፦ "ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።"
- ወደ ዕብራዉያን 11:6፦ "ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።"
- የያዕቆብ መልዕክት 4:10፦ "በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 82
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።