The Pentateuch Numbers

Aaron’s Staff That Budded

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 83 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ዘኁ 17 እና 18 እያጠናን ነው ፤ ከባለፈው ምዕራፍ ስንነሳ እንዴት ሙሴ እና አሮን ከአመፁ ቦኃላም እንካን ህዝቡ እንዲባረኩ ፈለጉ ነው ፡፡ በመፅሀፍ ውስጥ ከአመፆች ሁሉ አስከፊው የቆሬ አመፅ ነበር ፡፡ ሙሴን እና አሮንን አላመኑአቸውም ስለዚህ እግዚአብሄር እንድትዉጣቸው ምድርን ከፈተ ከዚያም 250 ተከታዮቻቸውን ለማቃተል እሳት አመጣ ፡፡ በዘኁ ምዕራፍ 17 እግዚአብሄር የተናገረው እስራኤላዊያን ከእነርሱ ጋር እንደ ነበር ተጨማሪ ማረጋገጫ ካስፈለጋቸው ተጨማሪ ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል ፡፡

ትምህርት

ዘኁልቁ(17፡ 1-3)፡ እግዚአብሄር ሙሴን አዘዘው ፤ እንደገና ይህ ቃለ ምልልስ እናያለን የሚመጣ ፈተና እንደ ነበር ፡፡ ሙሴ ለእስራኤላዊያንን ከእያንዳንዳቸው ከ12 ነገዶች መሪ አንድ በትር አንዲወስዱ ነገራቸው ፤ ከዘያም የእያንዳንዱ ስም በብትራቸው ላይ እና የአሮንን ስም በሌዋዊያን ብትር ላይ ይፅፈዋል ፡፡ ለሁሉም ለእስራኤል ቤት አንድ በትር ነበር ፡፡

ዘኁልቁ(17፡ 4-5)፡ ቀጣይ ሙሴ በመገናኛው ድንካን ላይ በምስክርነቱ(በቅድስተ ቅዱሱ) ፊት ለፊት 12 በትሮች ያስቀምጣል ፡፡ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያየ አሮን ብቻ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር “ የመረጠሁት ሰው በትር ታቆጠቁጣለች ፤ በእናንተም ላይ የሚያጉረመርሙባችሁን የእስራኤል ልጆች ማጉረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ ” ብሎ አዘዘ ፡፡

ዘኁልቁ (17፡ 6-7)፡ ሙሴ እስራኤላዊያንን ከ12 ነገድ ከእያንዳዳቸው መሪ በትር እንዲሰጡት ጠየቃቸው ፡፡ አሮን ጥቂት መጥፎ ነገሮችን አድርጎ ነበር ለምሳሌ ዘጸ(32፡ 4) የወርቅ ጥጃን ፡፡ ሚስት እና አራት ወንድ ልጆች ነበሩት ሁለቱ ሞተውበታል ፡፡ ይህ ሰው አሮን የመረጠው ደም ስር(ዋና) እንደ ነበር እግዚአብሄር ሁሉም እስራኤላዊያን ያሳያቸው ነበር ፡፡ ኬይል እና ደሊትዝስች የፃፉት“ የአንድ ሰው ረጅም በትር በቤት እና በጉባኤ እንደ ገዢ የስልጣን ምልክት ነበር ፡፡“ በአስቴር ታሪክ ውስጥ ንጉሱ በትረ መንግስቱን ለእርሳ ዝቅ ባያደርግላት ወደ ፊት ለመምጣት አይፈቀድላትም ነበር ፡፡ በትር የኃይል እና የስልጣን ምልክት ነበር ፡፡ ሙሴ በእግዚአብሄር ፊት በምስክርነቱ ድንካን ውስጥ በትሮቹን አስቀመጠ ፡፡

ዘኁልቁ(17፡ 8)፡ በቀጣይ ቀን ሙሴ ወደ ምስክርነቱ ድንካን ገባ የሌዊን ቤት የወከለችውን የአሮንን በትር ማቆጥቆጥ ብቻ ሳይሆን ለምልማለች፣ አብባለች እናም ለውዝ አፍርታ እንደነበር አያት ፡፡ በትሮአ ከሞት ወደ ማቆጥቆጥ ሄደች ፡፡ ዌንሀም የፃፈው “ ለዉዞች በነጭ አበባዎች ቶሉ ያብባሉ በተጨማሪም ፍሬው ከፍተኛ ዋጋ ያወጣ ነበር ፡፡”

  • ዘፍ (43፡ 11)፡ “ እስራኤልም አባታቸው እንዲህ አላቸው ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህንን አድርጉ፡ ከተመሰገነው ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ ፣ ጥቂት በላሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምር እና ለውዝ ውሰዱ ፡፡” ለዮሴፍ ይህን ወስደው ነበር ፡፡ ነጭ ቀለም ንፁህነትን፣ ቅዱስነትና እና ራሱን እግዚአብሄርን ያመለክታል ፡፡
  • ኢሳ (1፡ 18)፡ “ ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሄር ፤ ኃጢዓታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነፃለች ፡፡” በተመሳሳይ ጊዜ እግዚአብሄር መንፃት እና ፍሬን ያሳይ ነበር ፤ እጅ በእጅ ይሄዳሉ ፡፡

ዳን (7፡ 9)፡ “ ዙፋኖቹም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ በዘመናት የሸመገለውን ተቀመጠ ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ የራሱም ጠጉር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበሩ ፡፡” ሁልጊዜ ነጭ የእግዚአብሄርን መገኘት ይወክላል ፡፡

ራዕ (20፡ 11)፡ “ ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም ፡፡” ዌንሀም እንደ ፀፈው “ ነብዩ ኤርምያስ ለዉዝን ከመመልከት ጋር ያዛምደዋል ፡፡”

ኤር (1፡ 11-120፡ “ ደግሞ የእግዚአብሄር ቃል ፡፡ ኤርምያስ ሆይ ምን ታያለህ ? እኔም የለውዝ በትር አያለሁ አልሁ ፡፡ እግዚአብሄርም እፈፅመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና መልካም አይተሀል አለኝ ፡፡”

ዘኁልቁ(17፡ 9-12)፡ ሙሴ ለእያንዳንዱ ሰው በትሮቹን እንዲመለከቱዓቸው አወጣላቸው ፤ እግዚአብሄር ሙሴን የአሮንን በትር ለአመፀኛ እንደ ምልክት በምስክርነቱ ድንካን ፊት ለፊት መልሰህ አስቀምጠው ብሎ ነገረው ፡፡ ማጉረምረማቸው እንዲያበቃ ወይም እንዳይሞቱ ምልክት እንዲሆን ይጠበቀዋል ፡፡ ሁላችንም ወደ እግዚአብሄር የሚያመለክት አስታዋሽ ያስፈልገናል ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄር እንዳዘዘው አደረገ ፡፡ ማርሲንህ የፃፈው “ በግልፅ የሞተውን በትር በተዓምር ፍሬ እንዲሸከም ማድረግ ከቻለ ስለዚህ እንደሌሎች ዘራቸውን መምረጥ ይችላል በተጨማሪም በፍሬዓማነት የክህነትን አገልግሎት ለማገልገል ያስችላል ፡፡” ዋይርስቤ የፃፈው “ እንደተለመደው እስራኤላዊያን ዜናውን በሰሙ ጊዜ በኃይል ተበሳጩ ፡፡” እስራኤሌዊያን “ ልንሞት ነው ፤ ጠፋን” እያሉ አለቀሱ ፡፡

ዘኁልቁ(17፡ 13)፡ እስራኤላዊያን “ ወደ እግዚአብሄር ማደሪያ የሚቀርብ ሁሉ ይሞታል ፤ በውኑ ሁላችን እንሞታለን ? አሮን ሁሉም ህይወቱ ይህ በትር ነበረው ፡፡

ዘጸ (7፡ 8-10)፡ “ እግዚአብሄርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው ፈርዖን ተዓምራትን አሳዩኝ ሲላችሁ አሮንን በትርህን ወስደህ እባብ እንድትሆን በፈርዖን ፊት ጣላት በለው ፡፡ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ እግዚአብሄርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በባሪያዎቹ ፊት ጣለ እባብም ሆነች ፡፡”

ዘጸ (7፡ 19)፡ “ እግዚአብሄርም ሙሴን አለው አሮንን በትርህን ውሰድ ደምም እንዲሆኑ በግብፅ ዉኆች በወንዞቻቸውም በመስኖቻቸውም በኩሬዎቻቸውም በውኃ ማከማቻዎቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ በለው ፤ በግብፅም አገር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል ፡፡”

ዘጸ (8፡ 15-16)፡ “ ፈርዖንም ጸጥታ እንደሆነ ባየ ጊዜ ላቡን አደነደነ ፤ እግዚአብሄርም እንደተናገረ አልሰማቸውም ፡፡ እግዚአብሄርም ሙሴን አለው አሮንን በትርህን ዘርጋ በግብፅም አገር ሁሉ ቅማል እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ በለው ፡፡ “

በመጨረሻ እስራኤላዊያን የኑሮአቸውን ኃጢዓተኝነት እና መጥፎት አይተው ይሆን ?ዋይርስቤ እንደ ፃፈው “ እግዚአብሄር እስራኤልን ህጉን እንዲታዘዙ እና ለፍቃዱ እንዲገዙ እንዲያበረታቸው ሰዎስት መታሰቢያዎችን ሰጣቸው፡ በልብሶቻቸው ላይ ዘርፍ፣ በመሰዊያው ላይ የታሰረው ጥና እና በቅድስተ ቅዱሱ ውስጥ የአሮን በትር ፡፡”

መዝጊያ

እንደ ተመሳሳይ እግዚአብሄር ምንድን ይሰጣል ስለዚህ በእርሱ ታዛዦች ነን ? ዋይሰርቤ የፃፈው፡

የእግዚአብሄር ቃል(ዮሐ 17፡ 17)፡ “ በእውነትህ ቀድሳቸው ፤ ቃልህ እውነት ነው ፡፡”

መንፈስ ቅዱስ(1ቆሮ 6፡ 19-20)፡ “ ወይስ ስጋችሁ ከእግዚአብሄር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታዉቁምን ?በዋጋ ተገዝታችኃልና ለራሳችሁ አይደላችሁም ፤ ስለዚህ በስጋችሁ እግዚአብሄርን አክብሩ ፡፡”

የእግዚአብሄር እራት(1ቆሮ 11፡ 23-24)፡ “ ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና ፤ ….በዚያች ሌሊት እንጀራን አንስቶ አመሰገነ ቆርሶም ፡፡ እንካችሁ ብሉ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ስጋዬ ነው ፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ ፡፡”

የሚያማልደው አዳኝ(ዕብ 4፡ 14-16)፡ “ እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ ስላለን ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ ፡፡ ከኃጢዓት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም ፡፡ እንግዲህ ምህረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ ፡፡”

ስለዚህ ከሞት ወደ ህይወት መምጣት እንችላለን (ሮሜ 8፡ 11) ፡፡ ይህ ሁሉ የሚመጣው አሁን ፍሬ ካለው ከሞተችው በትር ቀላል ስዕል ነው ፡፡ ዘኁልቁ 18 ስለ ካህናት ቤተሰቦች ስጦታ ያወራል ከዚያም ወደ ካህናቶቹ እርዳታ ይገባል ፡፡

  1. C. F. Keil and Franz Delitzsch, The Pentateuch (Grand Rapids, MI: Wm. B. Eerdmans Publishing, n.d.), 3:114.

  2. Gordon J. Wenham, “Aaron’s Rod (Numbers 17:16–28)” (Zeitschrift für die Alttestamentliche Wissenschaft, 1981), p.140.

  3. Wenham, p. 280–281

  4. B. Maarsingh, Text and Interpretation Series, Numbers: A Practical Commentary, Tran. John Vriend (Grand Rapids, MI: Wm. B. Eerdmans Publishing, 1987), p. 63.

  5. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 340.

  6. Wiersbe, pp. 340–341.

  7. Wiersbe, pp. 341.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር ሙሴን ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ 12 የእንጨት በትር እንዲሰበስበ ተናገረው ይህን ለምን አደረገ?
  2. በዘኁ (18፡ 7) እግዚአብሄር አሮንንና ልጆቹን በመስጠት ምንድን አደረገ ? ወደ መቅደሱ በቀረበ ለማንኛውም ባልተፈቀደለት ሰው ላይ ምንድን ይሆናል ?
  3. በእሳት ያልተቃጠለውን የቅዱሱን መስዋዕት ድርሻ እግዚአብሄር አካፈለ ፤ ያን የሚይዘው የትኛው መስዋዕት አደረገ ?
  4. እግዚአብሄር አሮንን ካህናቶቹ የምድሪቱን ድርሻ እንደ ማይቀበሉ ተናገረው ይህን ለምን አደረገ ?
  5. በዘኁ 18፡ 29 የሚናገረው የስጦታችንን ምርጡን ድርሻ ለመስጠት እርግጠኞች እንድንሆን ነው ፤ ምርጡን ለእግዚአብሄር መስጠትን ለምን እናደርጋለን ?
  6. በዘኁ 17-18 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 17:8

“The next day Moses entered the tent of the testimony and saw that Aaron’s staff, representing the house of Levi, had sprouted, formed buds, blossomed and produced almonds!”

ዓለት

ያቆጠቆጠችዉ የአሮን በትር

ኦሪት ዘኁልቁ 17-18 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

በእያንዳንዱ የነገድ መሪ ስም ከተሰየሙ 12 በትሮች መካከል፥ እግዚአብሔር የአሮንን በትር መረጠ። በተዓምር ከአንድ ደረቅ እንጨትነት፥ በአንድ ምሽት ወደ ማቆጥቆጥ፣ እምቡጥ ወደማዉጣት፣ ማበብ እና መታደስ የጀመረችዉ የአሮን በትር ብቻ ነበረች። ከዚያም እግዚአብሔር ለክህነት አገልግሎት አሮንን እንደመረጠ እና በህዝቡ ዉስጥ ያሉ አጉረምረሚያዎች እንዲያቆሙ፥ እንደ ምልክት በትሩን በምስክርንት መስጫ ፊት ለፊት እንዲቆም እግዚዓብሔር አዘዘ።

እንደ አማኝ እግዚአብሔር በስምህ ጠርቶሃል። በክርስቶስ ከሞት ወደ ህይወት ተራምደሃል! በአሮን ክህነት ላይ በበትሩ ላይ የነበረዉ ነጭ እምቡጥ ንፅህናን እና ቅድስናን እንደሚወክል ሁሉ አንተም እንደ የተመረጥክ የክርስቶስ የንጉስ ካህን፥ ቅዱስ እና ህይወት የሚዘራ ንፁህ ልትሆን ይገባል። ከክርስቶስ ጋራ በምትራመድበት ጊዜ ብዙ ፍሬን ታፈራለህ። ዛሬ፥ በጥሪህ በምትመላለስበት ጊዜ፥ የእግዚአብሔር ህልዉና እና መንፈስ ቅዱስ በአንተ ዉስጥ እንደሚኖሩ አትርሳ። ብቻህን አይደለህም! በትሩ እና ምርኩዙ ያፅናኑሃል!

"እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፥ ለመለመችም፥ አበባም አወጣች፥ የበሰለ ለውዝም አፈራች።"

ኦሪት ዘኁልቁ 17:8

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 23:4፦ "በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።"
  • ወደ ሮሜ ሰዎች 8:11፦ "ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።"
  • 1ኛ የጴጥሮስ መልዕክት 2:9፦ "እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 83