Years of Wandering: Purification Rituals
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሰላዮቹ ስለ ሰጡት መጥፎ ሪፖርት በተጨማሪም የእስራኤላዊያንን ማጉረምረም እና ተጨማሪ ማጉረምረሞቹን አውርተናል ፡፡ ሪቫይቭ ት/ቤት ይህን አላደረገምን አላዉቅም በመገናኛው ድንካን ውስጥ የአሮንን በትር ዋጋ አያለሁ፡፡ የሪቫይቭ ት/ቤት ሙሉ አላማው በአድስ እና በታደሰ መነንገድ በጠቅላላ ማህበረሰብ ውስጥ ተፅዕኖ በማምጣት እግዚአብሄርን ለመልመድ(ለመቅመስ) ነው ፡፡ በዚህ ነገር መጎአዝ ይኖርባችኃል፣ በዚህ ነገር መኖር ይኖርባችኃል ፡፡ በዘኁ 19 ስለ ቀይ ጊደር ኃይማኖታዊ ማንፃት እናወራለን ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ 19፡ እስራኤላዊያን አንድ ቀይ ጊደር ከገደሉ አመድ በመጠቀም ውሃውን ያነፃሉ ፡፡ ርኩስ እና ንፁህ ነበር ፤ ሬሳ ከነኩ ስለ ንፅህና ለማግኘት በውሀ ይህን አመድ ይጠቀማሉ ፡፡ እስራኤላዊያን እንዴት እንደሚሄዱ ትእዛዝ አስፈለጋቸው ፤ ሙሉ የዘኁልቁ መፅሀፍ እግዚአብሄር እንዲያደርጉ የነገራቸውን እንዴት እንደሚያደርጉ እና በዚህ ነገር ውስጥ እንዴት እንደሚጎአዙ ሳያቆአርጥ ህዝቡን የሚያስተምር ነው ፡፡ ዘርፎቹ፣ መናው፣ በትሩ - እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር እንደነበር መታሰቢያ ነበሩ ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 1)፡ ይህ ምዕራፍ የተካሄደው በእስራኤላዊያን የምድረበዳ ጉዞ መጨረሻ ላይ ነው ፤ ይህ 40 አመት ነበር ፡፡ ሁሉም የእስራኤላዊ ማህበር በመጀመሪያው ወር የፂን በርሀ ላይ ደረሱ በቃዴስም ተቀመጡ ፡፡ ማሪያም በዚያ ሞተች ተቀበረችም ፡፡ ማሪያም ታዋቂ እህት ነበረች ፤ ከፍርዖን ሴት ልጅ ጋር ተሳሰረች ሙሴ ሊሞት አገኙት ከዚያም ህይወቱን አዳነችው ፡፡ በዘጸ(15፡ 21) በቀይ ባህር ላይ የሴቶችን ምስጋና መራች ፤ በዘጸ 12 ሙሴ ከማሪያም ጋር ብቻ የነበረውን ጉዳይ እናያለን የወንድምና የእህት ፀብ ነበር ፤ የእግዚአብሄር እጅ በግልፅ በማሪያም ላይ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 2-5)፡ በፂን በርሀ ው አልነበረም ፤ እስራኤላዊያን በሙሴና በአሮን ላይ ተሰበሰቡ ፡፡ “ ወንድሞቻችን በእግዚአብሄር ፊት በሞቱ ጊዜ እኛም ምነው በሞትን ኖሮ !” ብለው ሙሴን ተጣሉት ፤ እንደገና ይህ የእምነት እጥረት ነበር ፤ ከዚያም ቦታውን ከፉ ብለው ጠሩት ፡፡ እስራኤላዊያን በግብፅ የነበራቸውን ሁሉንም ነገር ማንሳት ጀመሩ፡ ዘር፣ በለስ፣ ወይን እና ሮማን ፤ “ የሚጠጣ ዉሃ እንካን የለም !” ብለው አዘኑ አሁንም ልባቸው በግብፅ ነበር፡፡ ልባቸው በአለም ነበር (1ዮሐ 2፡ 15-16) ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 6-10)፡ ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንካን መግቢያ ላይ ሄዱ በግንባራቸውም ተደፉ ፤ የእግዚአብሄር ክብር ተገለጠላቸው ፡፡ ዋይርስቤ እንደ ገለፀው እግዚአብሄር የጨዋታውን እቅድ እንደሚገልጥ ተናገረ ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን በትሩን እንዲወስድ ፣ እሱ እና አሮን ጉባኤውን እንዲሰበስቡ አዘዘው ፡፡ ሙሴ አለቱን ይናገረዋል በአይኖቻቸው ፊትም ውሃም ያፈስሳል ፤ ዉሃው ለማህበሩ እና ለከብቶቻቸው ይሆናል ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄር እንዳዘዘው በትሩን ወሰደ ፤ ሙሴና አሮን በአለቱ ፊት ጉባኤውን ባንድ ላይ ሰበሰቡ ፡፡ ሙሴ በእስራኤላዊያን ተበሳጨ “ በውኑ ከዚህ ድንጋይ ዉኃን እናወጣላችኃለንን ?” አላቸው ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 11)፡ ሙሴ እጁን አነሳ በብትሩም ሁለት ጊዜም አለቱን መታው ፤ ዉሃ ፈለቀ ማህበሩ እና ከብቶቹ ጠጡ ፡፡ እግዚአብሄር ለአለቱ እንዲናገረው ነገረው እንጂ እንዲመታው አይደለም ፤ የሚሰራው ስራው የሙሴ አልነበረም የእግዚአብሄር እንጂ ፡፡ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳይገባ የከለከለው የችኮላ ኃጢዓት ነበር (ዘጸ 17፡ 6)፡፡ ምናልባት በደመነፍስ ውስጥ ሙሴ ወደ ኃላ ወደ ዘጸ 17 ሞደል ጣለ ፡፡ በዘኁ 20 ለዚህ ታሪክ አለቱ አስፈላጊ የሆነ ይመስለኛል(ዘዳ 32፡ 4, 15, 18; መዝ 18፡ 2; 31፡3; 42፡ 9; 106፡ 32-33; ዕብ 9፡ 26-28; 1ቆሮ 10፡ 4) ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 12-13)፡ አሁን ዋይስርቤ እንደፃፈው የሚያም ቅጣት እየመጣ ነበር ፤ ቅዱስነቱን ይገልጥ ዘንድ አላመኑትም እና ይህ ማህበር ወደ ምድሪቱ አይገባም ፡፡ እነዚህ የመሪባ ዉሃዎች ነበሩ እስራኤላዊያን ከእግዚአብሄር ጋር የተጣሉበት እናም እግዚአብሄር ቅዱስነቱን የገለጠላቸው ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 14-17)፡ አሁን እስራኤላዊያን ወደ ቃዴስ እየተጎአዙ ነበር ፤ ሙሴ እነሱን እንደ ቤተሰብ በመጥቀስ እና እንደ ወንድም በማድረስ ለኤዶምያስ ንጉስ መልዕክት ላከ ፡፡ ሙሴ ንጉሱን በግብፃዊያን በኩል የሆኑትን ሁሉ ነገረው በምድራቸውም ውስጥ እንዲሄዱ ፍቃድ ጠየቀው ፤ ሙሴ እስራኤላዊያን በየትኛውም ማሳ ወይም የወይን ቦታ እንደማይሄዱ ወይም ከጉድጎአዶቻቸው ዉሃ እንደማይጠጡ ቃል ገባ ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 18-20)፡ ኤዶምያስ በምድራቸው ውስጥ እንዳያልፉ ወይም በሰይፍ እንደሚገጥሙዓቸው መለሰ ፡፡ እስራኤላዊያን ከከብቶቻቸው ጋር በዋናው መንገድ እንደሚቀመጡ እና የእነርሱን ማንኛውንም ዉሃ ከጠጡ አንደሚከፍሉ መለሱ ፤ በእግራቸው ብቻ ያልፉ ዘንድ ፈለጉ ፡፡ ኤዶምያስ አታልፉም ብሎ ፀና በዚህም በትልቅ የጦር ኃይል ሊገጥማቸው ወጣ ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 21-24)፡ ኤዶምያስ እስራኤላዊያን እንዲያልፉ ለመፍቀድ እምቢ አለ ስለዚህ እስራኤላዊያን ከእነርሱ ተመለሱ ፡፡ እስራኤላዊያን ወደ ሆራ ተራራ መጡ ፤ እግዚአብሄር ለሙሴን እና አሮንን በኤዶምያስ ድንበር በሆራ ተራራ ተናገራቸው ፡፡ አሮን ወደ ህዝቡ(ወገኑ) ይሰብሰብ ፤ ወደ ምድሪቱ እንዲገባ አልተፈቀደለትም ምክንያቱም እሱና ሙሴ ሁለቱም በመሪባ ዉሃ በእግዚአብሄር ትዕዛዝ ላይ አመፅዋል ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 25-27)፡ አሮን ከልጁ ከአልዓዛር ጋር ወደ ሆራ ተራራ ወጣ ፤ አሮን ልብሶቹን ያውልቅ በአላዓዛርም ላይ ያስቀምጣቸው ፡፡ አሮን ወደ ወገኖቹ ይከማች በዚህም ይሞታል ፡፡ ሙሴ ማህበሩ ሁሉ እያዩ ሆራ ተራራ ላይ ወጣ ፡፡ ይህ የአብርሃምን እና የይስሐቅን ያስታውሳችኃል ፡፡ እስራኤላዊያን ከአሮጌው ትውልድ ወደ አድሱ ትውልድ እየተጎአዙ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(20፡ 28-29)፡ ወዲያውኑ በአልዓዛር ላይ የአሮንን ልብሶች አስቀመጡ አሮን ሞተ ፤ ከዚያም ሙሴና አልዓዛር ከተራራው ወረዱ ፡፡ መፅሀፍ የአሮንን አካል አወረዱት አይልም ፡፡ ሙሴና አልዓዛር የሞተውን የአሮንን አካል መንካት አልቻሉም ምክንያቱም ታላቅ ካህናት ነበሩ ፡፡ ሁሉም ማህበር በአሮን ማለፍ ለ30 ቀናት አዘኑ ፡፡ ዮሐንስዌስሌይ የፃፈው “ እግዚአብሄር ሰራተኞቹን ቀበረ ነገር ግን ስራው ሁልጊዜ እንዳለ ይሄዳል ፡፡”
መዝጊያ
ሙሴ ህዝቡ በእግዚአብሄር ስንት ጊዜ እንደነገራቸው ታዉቃላችሁ ? በዚህ አንድ ጊዜ ግራ ተጋባ ምን እንደተፈጠረ ተመልከቱ ፡፡ ሙሴ የእምነት ሰው ነበር ፡፡
ዕብ (11፡ 23)፡ “ ሙሴ ከተወለደ ቦኃላ በእምነት ቤተሰቦቹ ሸሸጉት…..”
ዕብ (11፡ 24)፡ “ ባደገ ጊዜ ሙሴ በእምነት……”
ዕብ (11፡ 27)፡ “ የግብፅን አገር በእምነት ተወ…..”
ዕብ (11፡ 29)፡ “ ቀይ ባህርን በእምነት ተሸገሩ ….”
ሙሴ እስራኤላዊያንን ውርሳቸውን ሊሰጣቸው አልቸለም በእምነት ይቀጥላሉ (ገላ 3፡ 18) ፤ አውቃለሁ ይህ የተዘረጋ ነው ፡፡ ከኢያሱ ምንድን ይመጣል ? ሙሴ ወደ ምድሪቱ መሻገር አይችልም ኢያሱ ግን ይችላል ፡፡ ኢያሱ እንደ መሸጋገሪያ መሳሪያ አገለገለ ፡፡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ሊያስገባን የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው ፤ የእኛ አለት ነው ፡፡ በዘኁ 20 ማሪያም ሞተች፣ አሮን ሞተ እናም ሙሴ በመንፈስ ሞተ ምክንያቱም ተስፋውን አጣ ፡፡ በቀረው(ባለው) ትምህርት ጊዜ ኢያሱ እንዴት ወደ መሲሁ እንደሚያመለክት እናገኛለን ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 344.
Wiersbe, p. 344.
John Wesley; quoted in Wiersbe, p. 345.
ጥያቄዎች
-
ለማረድ አልዓዛር ቀይ ኪደር ከከተማው ዉጪ በወሰደ ጊዜ ከቀረው ጋር ወደ እሳቱ የሚወረወር ምንድን ያስፈልጋል ? (ዘኁ 19፡ 6)
-
ቀዮአ ጊደር የክርስቶስ አይነት ነው ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላመናችሁም ? ለኃጢዓት እንዴት ደም ያስተሰረያል ? (ዕብ 9፡ 13-14)
-
በዘኁ(20፡ 8) ላይ እግዚአብሄር ሙሴን እና አሮንን ምንድን እንዲያደርጉ አዘዛቸው ? አድርገውታል ? ምንድን ቅጣት ተቀበሉ ? እግዚአብሄር ያለውን ትክክለኛውን ከማድረግ ይልቅ በራሳችሁ መንገድ ያደረጋችሁበትን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ?
-
ሙሴና አሮን ወደ ሆራ ተራራ በሄዱ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ማንን ወሰዱ ? ለምን ?
-
በዘኁ(19-20) በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 20:11-12
“Then Moses raised his hand and struck the rock twice with his staff, so that a great amount of water gushed out, and the community and their livestock drank. But the Lord said to Moses and Aaron, ‘Because you did not trust Me to show My holiness in the sight of the Israelites, you will not bring this assembly into the land I have given them.”
አሁንም እንደገና፥ እስራኤላዉያን በቂ ዉሃ ስላልነበረ በሙሴ እና በአሮን ላይ በማማረር አጉረመረሙ። ሙሴ እና አሮንም እንደገና በእግዚአብሔር ፊት በመዉደቅ የእርሱን እርዳታ ፈለጉ። እናም እንደገና እግዚአብሔር በድንቅ መንገድ አቅርቦቱን እንደያሳይ መለሰላቸዉ። እግዚአብሔር ህዝቡ እየተመለከቱ ዓለቱ ዉሃ እንዲያፈልቅ፥ ሙሴን እንዲናገረዉ አዘዘዉ። ነገር ግን ሙሴ እጁን አንስቶ በያዘዉ በትር ዓለቱን ሁለት ጊዜ መታዉ። ይህ ግልፅ በሆነ መንገድ ሙሴ እግዚአብሔርን አለመታዘዙን ያሳየናል። ቢሆንም ጌታ ግን ምህረቱን በማሳየት ዓለቱ ዉሃ እንዲያፈልቅ አደረገ! የሙሴ ድርጊት የቁጣና የትዕግስት የማጣት ነዉ። በዚህም ያለመታዘዝ ድርጊት ምክንያት እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ተስፋይቱ ምድር መግባትን እንዲከለከል አደረገዉ!
እግዚአብሔር ምንም እንኳን ይቅር ባይ አምላክ ቢሆን የምናሳየዉ ባህርይ ግን ፍሬ አለዉ። ድርጊቶቻችንን በጌታ ታማኝነት ላይ ያለን እምነት ነፀብራቅ ናቸዉ። በመንፈስ ስትመላለስ፥ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ፦ ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛትን ትሞላለህ። በህይወትህ ከእነዚህ ዉስጥ አንዱ ወይም ከዚያ በላይ የሚጎልህ ከሆነ፥ ዛሬ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ የተወሰኑ ደቂቃዎችን ዉሰድ! በህልዉናዉ ዉስጥ የተወሰነ ጊዜ አጥፋ! ቃሉን እያነበብክ፥ ወደ አዕምሮህ የሚመጡ ኃጥያቶችን ሁሉ ተናዘዝ፥ እናም በመንፈሱ እና በቃሉ እንዲሞላህ ፍቀድለት። በመንፈስ በምትታደስበት ጊዜ፥ ለቀጥይ ጉዞህ የሚሆንህን ጉልበት ታገኛለህ!
"ሙሴም እጁን ዘርግቶ ድንጋዩን ሁለት ጊዜ በበትሩ መታው፤ ብዙም ውኃ ወጣ፥ ማኅበሩም ከብቶቻቸውም ጠጡ። እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፦ በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም አላቸው።"
ኦሪት ዘኁልቁ 20:11-12
ተጨማሪ ጥቅሶች
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:9-10፦ "እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።"
- ወደ ገላትያ ሰዎች 5:22-23፦ "የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።"
- ወደ ኤፌሶን 5:18፦ "መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 84
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።