The Pentateuch Numbers

March of Israel: The Bronze Snake

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 85 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና ስለ ዘሁ 20 እና ስለሞቱት ሁለቱ ሰዎች ማሪያም እና አሮን አውርተናል ፡፡ ሙሴ አብዶአል በእግዚአብሄር ታምኖ አለቱን በመናገር ፋንታ መታው ፤ አለቱን የመምታቱ ውጤት የነበረው ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት አልተፈቀደለትም ፡፡

ትምህርት

ዘኁልቁ(21፡ 1)፡ ዓርዳ በእስራኤል በደቡብ በኩል( በምድረ በዳ) እውነተኛ ከተማ ነው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ 60 ፐርሰንት የእስራኤል ምድር በደቡብ በኩል ነው ነገር ግን በዚያ ቦታ 7 ፐርሰንቱ ብቻ ይኖራል ፡፡ በነጌቭ የሚኖረው የአርዳ ከነዓናዊ ንጉስ በአታሪም መንገድ እስራኤላዊያን እንደ መጡ በሰማ ጊዜ አጠቃቸው ከእነርሱም ጥቂቶችን ያዘ ፡፡ አታሪም መንገድ ምናልባት ቦኃላ ኢያሱ ምድሪቱን እንዲሰልሉ የላካቸው ሁለቱ ሰላዮች የሄዱበት መንገድ ነበር ፡፡

ዘኁልቁ(21፡ 2)፡ “ ከዚያም እስራኤል ለእግዚአብሄር ስለት አደረገ ፡፡” እስራኤላዊያን ይህን ስለት በማድረግ እራሳቸውን ለእግዚአብሄር ለመስጠት ቃል ገብተው ነበር ፤ ከነዓናዊያንን እግዚአብሄር በእጃቸው ከሰጣቸው ሙሉ ከተሞቻቸውን ያጠፋሉ ፤ “ማጥፋት” የሚለው ቃል እንደ ዋይርስቤ “ የሆነን ነገር በሙሉ ለእግዚአብሄር ማዋል፣ ህዝቡን እና ከተሞቻቸውን መጥፋት እናም ሁሉንም የተሰረቅ እቃዎችን ለእግዚአብሄር መስጠት” ማለት ነው ፡፡

ዘኁልቁ(21፡ 3)፡ የእስራኤላዊያን ፀሎት ሰማ ከነዓናዊያንን አሳልፎ ሰጣቸው ፤ እስራኤላዊያን በሙሉ ከነዓናዊያንን አጠፉ ቦታውንም ሔርማ አሉት ፡፡

ዘኁልቁ(21፡ 4)፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ከሆር ተራራ ወጥተው በቀይባህር መንገድ በኤዶም ዞረው እንዲሄዱ በላካቸው ጊዜ ህዝቡ በመንገድ ላይ ዛሉ(ትዕግስት አጡ) ፡፡ ትዕግስት ማጣታቸው በሌሎች ከታየው ትዕግስት ጎልቶ ተለየ ፤ አብርሃም ለወንድ ልጁ 25 አመታት ጠበቀ ፤ ዮሴፍ ከጉድጎአድ ወደ ቤተ መንግስት ለመሄድ 13 አመታትን ጠበቀ ፤ ሙሴ 40 አመታትን ጠበቀ በምድረበዳም ከህዝቡ ጋር ተጎአዘ ፤ ዳዊት ንጉስ ለመሆን 15 አመታት ጠበቀ ፤ ኢየሱስ አገልግሎቱን ለመፈፀም 30 አመታት ጠበቀ ፡፡ የእስራኤላዊያን ይህ ትዉልድ ከነዓናዊያንን ሲይዝ የመጀመሪያው ጊዜ ነበር በጥሩ አልያዙዓትም ፡፡ እግዚአብሄር ሁልጊዜ የሚወስደን(የሚይዘን) በሂደት ነው ፤ በሚገጥመን ችግር ውስጥ ለማስተማር ብዙ አለው ፤ ለምን ብሎ ከመጠየቅ ወይም ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ እግዚአብሄር ምን እያስተማረን ነው ብሎ መጠየቅ አለብን ፡፡ ሮሜ(5፡ 3-4) በችግራችን እንድንደሰት ያበረታታናል ምክንያቱም ፅናት፣ የተረጋገጠ ባህሪይ እና ተስፋ ይፈጥራልና ፡፡ ዕብ(6፡ 11-12) የተግቶ መስራትን ጠቀሜታ ይገልፃል፡ “በእምነትና በትዕግስም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን ፡፡”

ዘኁልቁ(21፡ 5-6)፡ ህዝቡ ስለ እንጀራ እና ዉሃ እጥረት እና ስለ “ቀላሉ ምግብ(እንጀራ)” በማጉረምረም በእግዚአብሄር እና ሙሴ ላይ ተናገሩ ፡፡ እግዚአብሄርን ስለፈተኑት የሚነድፉዓቸውን መርዛማ እባቦች ላከባቸው ብዙ ሰዎች ሞቱ ፤ 1ቆሮ(10፡ 9) የሚለው “ ከእነርሱም አንዳንዶች ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦችም እንደ ጠፉ ጌታን አትፈታተኑ ፡፡” እግዚአብሄር ምድሪቱን ለእስራኤል እንደሚሰጥ ያለማቐረጥ ተስፋ ገብቶ ነበር (ዘኁ 15፡ 1-2) ነገር ግን ሁልጊዜ ተስፋዉን ረሱ ፡፡ በዘጸ 16 እግዚአብሄር ሁሉንም ቀን መና እና ጅግራ(ድርጭት) ላከ ፤ እግዚአብሄር ሁሉንም ቀን እየተነጫነጩ እና እያጉረመረሙም ቢሆን እንካን መመገቡን ቀጠለ ፡፡

መዝ (78፡ 25) የገለጠው “የመላክትንም እንጀራ ሰው በላ ስንቅንም እስኪተርፋቸው ላከላቸው ፡፡” ቢያጉረመርሙም እግዚአብሄር የምርጡን ምርጥ ሰጣቸው ፡ “ በመካከላቸውም የነበሩ ልዩ ልዩ ሕዝብ እጅግ ጎመጁ የእስራኤል ልጆች ደግሞ ያለቅሱ ነበር ፡፡ የምንበላውን ስጋ ማን ይሰጠናል ? “ (ዘኁ 11፡ 4) ኬይል እና ደሊትዝስች ማብራሪያዎች ያሉት እነዚህ እባቦች በአካላቸው ላይ ቀይ ነጠብጣቦች በኡሁኑ ጊዜ እንካን ያሉ በርኸኞችን ያጠቃሉ ፡፡

ዘኁልቁ(21፡ 7-8)፡ ህዝቡ ወደ ሙሴ መጡ በአንተ እና በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት አድርገናል አሉት ፤ ለእነርሱ ወደ እግዚአብሄር እንዲማልድላቸው ሙሴን ጠየቁት ስለዚህ ሙሴ ለህዝቡ ፀለየ ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን የእባብ ምስል ሰርቶ በፖል ላይ ከፍ እንዲያደርገው ነገረው በዚህም ተነድፎ የነበረው ማንኛውም ያን በመመልከት ይድናል ፡፡

ዘኁልቁ(21፡ 9)፡ ሙሴ የነሀስ እባብ ሰራ በፖልም ላይ አስቀመጠው በዚህም ምክንያት መቼም ቢሆን የተነደፈ አንድ ሰው የነሀሱን እባብን መመልከት ይችላሉ ከዚያም ይድናሉ ፡፡

መፅሀፍት የሚሉት ይህ የኢየሱስ ስዕል ነበር፡

  • ዮሐ(3፡ 14)፡ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደሰቀለ እንዲሁ.. የሰዉ ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል “ ፤ ሰዎች ሊድኑበት የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ የኢየሱስ መሰቀል ነው ፤ ኢየሱስ በኃጢዓት የተጠቃ ሆነ በእውነትም ይሞታል ፡፡
  • ዕብ(9፡ 27-28)፡ ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኃላም ፍርድ እንደ ተመደበላቸው ፤ እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ የብዙዎችን ኃጢዓት ሊሸከም አንድ ከተሰዋ ቦኃላ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢዓት ይታይላቸዋል ፡፡” አሁን ኢየሱስ የሞት ስዕል ነው ነገር ግን በሞቱ ውስጥ ስንመለከት ህይወት እናገኛለን ፡፡
  • ሮሜ(10፡ 13)፡ “ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል ፡፡“ እባብ ያለበት ፖል በሰፈር ውስጥ ይወጣል ልክ እንደ ኢየሱስ የአለም አካል ይሆናል ፡፡
  • ሐዋ(4፡ 12)፡ “ መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና ፡፡”
  • ዮሐ(14፡ 6)፡ “ ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡” ማንንም በብትሩ ላይ ወደ እባቡ እንዲመለከቱ ማንም ማስገደድ አይችል ፤ እያንዳንዱ ሰው በራሱ ያን ያደርጋል ፡፤
  • ኢሳ(45፡ 22)፡ “ እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ እኔ አምላክ ነኝና ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ ፡፡ “
  • ኤፌ(2፡ 8-9)፡ ይህም የእግዚአብሄር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም ፡፡”

መዝጊያ

ጎአደኞቼ ከወሱዋ፣ ዊስኮኒስ የሳሙና ማስቀመጫ ሰረልኝ ፤ ይህን ሳሙና ማስቀመጫ እወደዋለሁ ፤ ስለዚህ ለደቂቃ በሳሙና ማስቀመጫዬ ጋር እሄዳለሁ ፡፡ ሰዎችን ይህንን ማድረግ አለባችሁ በማለት በጣም ደክሞኛል ይህ እና ይህ ያድናል ፡፡ ኢየሱስ ሲደምር የለም ፤ ኢየሱስ ብቻውን ነው ! ከሚኖረው ይልቅ ጠንካራ አድርገነዋል ፤ በብትሩ ላይ እባቡን እንደ ታየ ፤ ኢየሱስን በመስቀሉ ላይ ታየ ፡፡

1ቆሮ(1፡ 18-25) የሚነግረን፡ “ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሄር ኃይል ነውና ፡፡ የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተፅፎዓልና ፡፡ ጥበበኛ የት አለ ? ጻፊስ የት አለ ? የዚችን አለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን ? በእግዚአብሄር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሄርን በጥበብዋ ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሄርን በጎ ፈቃድ ሆኖአልና፡፡ መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው ፡፡ ለተጠሩት ግን አይሁድ ቢሆን የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ የእግዚአብሄር ኃይልና የእግዚአብሄር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው ፡፡ ከሰው ይልቅ የእግዚአብሄር ሞኝነት ይጠብባልና የእግዚአብሄርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና ፡፡”

እስራኤላዊያን በጉዞ ላይ ነበሩ ፤ ማማረር ጀመሩ ፤ እግዚአብሄርን ፈተኑት ፤ በመጨረሻም እግዚአብሄር ቁጣውን አመጣ እባቦችንም ላከ ፡፡ አንዴ በመጨረሻ ኃጢዓታቸውን አመኑ ንስሀ ገቡ እንደሚያድናቸው እግዚአብሄር ተናገረ፡፡ የሚያደርጉት ሁሉ ወደ እርሱ እንዲመለከቱ ነበር ፤ “ ወደ እኔ ተመልከቱ አድናችኃለሁ “ ብሎናል ፡፡ ይህ ወደ መጣው መሲህ ያመለክታል ፡፡

ሁላችንም ኃጢዓተኞች ነን ኃጢዓታችን ወደ ሞት ይመራናል ፤ እባብ ተነደፈ ወደ ሞት ያመራል ፡፡ ኤፌ 2 የሚለው ሁላችንም ማድረግ ያለብን በኢየሱስ ማመን ነው ፤ አንዴ “ ኢየሱስ በአንተ ነኝ “ ስንል ህይወት ይኖረናል ፤ ሙሴ የሰጠው መልዕክት ያ ነው ፡፡ የዘኁ 21 መልዕክት ያ ነው ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 347.

  2. Carl Friedrich Keil & Franz Delitzsch, “Commentary on Numbers 21.” Available from https://www.studylight.org/commentaries/kdo/numbers-21.html

ጥያቄዎች

  1. ለማጉረምረማቸው እግዚአብሄር(“ አጥፊው/የሚያጠፋው መለዓክ “ 1ቆሮ 10፡ 9-10) እስራኤላዊያንን መግደል እንደቻለ ለማመን የሚከብደውን ይህ ትፈልጋላችሁ ? እግዚአብሄር መርዘኛ እባቦቹን ለምን እንደላከ ምን ታስባላችሁ ?
  2. እስራኤላዊያን ከሞት ለመዳን በፖሉ ላይ ያለውን የነሐስ እባብ መመልከት እንዴት ነበር የተቻለው (ዘኁ 21፡ 8-9) ? ይህ የነሐስ እባብ በመጨረሻም ወደ ክርስቶስ ዕንዴት አድርጎ ያመለክታል (ዮሐ 3፡ 14-15) ? በተለይም ለሞት ምልክት ስዕል የነበረው እባቡ በመጨረሻም እስራኤላዊያንን አድኖአል የዚህን አስደናቂነት ትፈልጋላችሁ ?
  3. በዘኁ(21፡ 14) የጀመረው “ የእግዚአብሄር ጦርነት መፅሀፍ” ምንድን ነበር ?
  4. 2ጴጥ(2፡ 15-16) እና ይሁ 11 አንብቡ ፡፡ በዘኁ 22፡ 20 እግዚአብሄር እንዲያደርገው ያዘዘውን እና ከእነዚህን ሁለት ፅሁፎች ጋር እንዴት አድርጋችሁ ታስታርቃላችሁ ? የበለዓም ከባላቅ የተሳሳተ ምርጫ ጋር ለመሄድ መውሰን ለምን ነበር ?
  5. የበለዓም አህያ የእግዚአብሄርን መለዓክ ባየች ጊዜ(ዘኁ 22፡ 23) ወደ ባላቅ በመንገዱ ወደ ፊት አልተጎአዘችም ነገር ግን እስከ ዘኁ(22፡ 31) በለዓም መለዓኩን ለማየት አልቻለም ፡፡ እግዚአብሄር በመንገዳችሁ “በአህያ” ጣልቃ ለመግባት የሞከረበት ነገር ግን በመጨረሻ በትክክል መንገድ እንድትደርሱ ያስፈለጋችሁ ጊዜ አላችሁ ? እግዚአብሄር በለዓምን ለምን እንዳስቆመው እናም በመጨረሻም እንዲሄድ ለምን እንደፈቀደለት ምን ታስባላችሁ ? (ዘኁ 22፡ 35)
  6. በዘኁ(21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 21:8

“Then the LORD said to Moses, ‘Make a snake image and mount it on a pole. When anyone who is bitten looks at it, he will recover.’”

የእስራኤል ሰልፍ እና የነሃሱ እባብ

ኦሪት ዘኁልቁ 21-22 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እስራኤላዉያን በጉዞዉ ምክንያት አለመታገሳቸዉ እያደገ ሄደ። እግዚአብሔርንም በመቃወም ተናገሩ። እርሱም በህዝቡ መካከል መርዛማ እባብ ላከባቸዉ፥ ንክሻቸዉም ብዙ እስራኤላዉያን እንዲሞቱ አድረጓል! ደግሞ እንደገና ህዝቡ እርዳታን ተማፀኑ፥ ሙሴም በእነርሱ ምትክ እግዚአብሔርን ለመነ። እግዚአብሔርም በምህረቱና ፀጋዉ እስራኤላዉያን ከእባቡ የሚድኑበትን መንገድ አበጀላቸዉ። እግዚአብሔርም የነሃስ እባብ ሠርቶ እንጨት ላይ እንዲሰቅለዉ ሙሴን አዘዘዉ። በእባቡ የተነከሱ ሰዎች እንጨት ላይ የተሰቀለዉን እባብ በሚመለከቱበት ጊዜ፥ እየዳኑ ከንክሻዉም ይፈወሱ ነበረ።

ይህ እንዴት ከኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ፀጋ ጋራ እንደሚመሳሰል አስቡ? የህይወት ፈተና በሚበዛበት ወቅት፥ ጉዞዉ ልንሸከመዉ ከምንችለዉ በላይ እንደሆነ ሲሰማን፥ በእግዚአብሔር ላይ የምናጉረመርም፥ የታማኝነት የተስፋ ቃሉን የምንዘነጋ ልንሆነ እንችላለን። እግዚአብሔር ግን ትልቅ የሆነ ዓላማ አለዉ! ኢየሱስን በመስቀል ላይ ከፍ እንዲል ልኮታል። በህይወት ጉዞ ዉስጥ ወደላይ ቀና ብሎ እርሱን የሚመለክት ሰዉ ሁሉ ከሞት ይድናል፣ ከኃጥያት ይፈወሳል፣ ከእስራትም ነፃ ይወጣል። ክርስቶስን በመመልከት እና በእርሱ በማመን የዘላለም ህይወት ይኖረሃል! ወደ ክርስቶስ ተመልሰህ እርሱን ተመለከተዉ! በህይወትህ ዉስጥ ስላሉ ብዙ የተስፋ ቃሎች አመስግን!

"ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው።"

ኦሪት ዘኁልቁ 21:8

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኢሳይያስ 45:22፦ "ናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።"
  • የዮሐንስ ወንጌል 3:14-15፦ "ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።"
  • የሐዋርያት ሥራ 4:12፦ "መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 85