Balaam Blesses Israel
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘፍጥረት ዘሩን ክርስቶስን አይተናል ፤ በዘጸዓት ነፃ አዉጪ ሙሴ ወደ መጨረሻው ነፃ አውጪ አመለከተ እሱም ክርስቶስ ነው ፤ በዘሌዋዊያን አስተሰሪው መስዋዕትነትን እና በመቅደሱ መስዋዕት ያደረገ ነበር ፤ በዘኁልቁ ስለ አለት እያወራን ነው ፡፡ በ 1ቆሮ(10፡ 4) ጳዉሎስ የተናገረው “ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ አለት ጠጥተዋልና ያም አለት ክርስቶስ ነበር ፡፡” በዘኁ 21 ሰዎች በተነደፉ ጊዜ መጀመሪያ በትሩ ላይ ያለውን እባብ ማየት እንደቻሉ እና እንደሚድኑ ወደ ክርስቶስ አሳየን ፡፡ ወደ ዘኁልቁ 23 ከመግባታችን በፊት ዘኁልቁ 22 ዋይርስቤ እንዴት እንዳጠቃለለው እንመልከት፡
- ዘኁ 22፡ 1-20፡ የንጉሱ ጥያቄ፡ የሞዓብ ንጉስ የሴፎር ልጅ ባላቅ በእስራኤላዊያን ላይ እርግማን እንዲያስቀምጥለት በበለዓምን ጠየቀ ምክንያቱም እስራኤላዊያን በተመለከተ ኃይለኛ እንደነበሩ ቃል ተሰራጭቶ ስለነበር ፡፡
- ዘኁ 22፡ 21-30፡ የአህያዋ ተቃውሞ፡ አህያዋ መሄድ አልፈለገችም ምክንያቱም የእግዚአብሄር መልዓክ በመንገዱ ላይ ቆሞ ነበር ፤ ይህ መልዓክ የእግዚአብሄር ስለነበር በእውነት መልካም እድል ነው ፤ እንድትሄድ አህያዋን በለዓም ሰዎስት ጊዜ መታት ፤ ከዚያም አህያዋ በለዓምን አነጋገረችው ፡፡
- ዘኁ 22፡ 31-35፡ የመለዓኩ መገለጥ፡ የእግዚአብሄርን መለዓክ እንዲያ እግዚአብሄር የበለዓምን አይኖች ከፈተ ፤ መለዓኩም “ እነሆኖ መንገድህ ጠማማ ነውና እቐቐምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ አህያይቱም አይታኝ ከፊቴ ሰዎስት ጊዜ ፈቀቅ አለች ከፊቴስ ፈቀቅ ባላለች በእውነት አሁን አንተን በገደልሁህ “(ቁጥር 32-33)፡፡ በለዓምም ኃጢዓት እንዳደረገ አመነ ምክንያቱም መለዓኩ በዚያ እንደነበር አላወቀም (ቁጥር 34)፡፡ የእግዚአብሄር መለዓክ ከአህያው ጋር እንዲሄድ ነገረው ነገር ግን እንዲናገር የነገረውን ብቻ ይናገራል (ቁጥር 35) ፡፡
- ዘኁ 22፡ 36-41፡ ባላቅ እና በለዓም፡ ባላቅ በለዓምን ሊገናኘው ከተማዋ ጫፍ ላይ ወጣ(ቁጥር 36) ፡፡ በለዓም ከእግዚአብሄር የመጣውን ብቻ መናገር እንደሚችል ተናገረ (ቁጥር 38) ፤ በለዓም ከባላቅ ጋር ሄደ ባላቅም ከብት እና በግ ሰዋ(አረደ) (ቁትር 39-40) ፤ ይህ የአስማት ሂደት አካል ነበር ፡፡ በማግስቱ ማለደ ባላቅ በለዓምን ወደ እስራኤላዊያን ሰፈር እንዲመለከት ወደ በአል ኮረብታ ወሰደው ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(23፡ 1-12)፡ የመጀመሪያው ምላሽ፡ ምላሽ በአገናኝ የተላለፈ መልዕክት ነበር ፡፡ እዚህ ላይ ባላቅ እስራኤላዊያንን በተመለከተ መስማት ስለፈለገ አስማተኞች እንዲነግሩት ሰበሰበ ፡፡ በለዓም ባላቅን ሰባት መሰዊያዎች እና ለእያንዳንዳቸው መሰዊያ ሰባት የበግ ወጠጤዎች እንዲያዘጋጁ ነገረው ፤ በለዓም ባላቅን እግዚአብሄር ይናገረው እንደሆን ለማየት ሲሄድ በመሰዋት እንዲጠብቀው ነገረው ፡፡ እግዚአብሄር ከበለዓም ጋር ተገናኘ ለባላቅም መልዕክት ሰጠው ፤ በለዓም ወደ ባላቅ ተመለሰ ከዚያም ይህን የመጀመሪያ ግጥም ወይም ምላሽ ከእግዚአብሄር ነገረው፡
ባላቅ በእስራኤል ላይ ርግማን እንዳስቀምጥ ጠየቀኝ ነገር ግን እስራኤላዊያንን መርገም አልቻልኩም ምክንያቱም እግዚአብሄር አልረገማቸውም (ቁጥር 7-8) ፡፡
እስራኤላዊያን የተለዩ ናቸው(ቁጥር 9) ፡፡
የእስራኤላዊያንን ሰፊነት እንካን ሊገባኝ አይችልም ፤በእውነት እንደ እነርሱ መሆን እፈልጋለሁ(ቁጥር10) ፡፡
በለዓም እስራኤልን በመርገም ፈንታ ባርኮአቸው ስለነበር ባላቅ ቅሬታ አቀረበ በለዓምም እግዚአብሄር በአፉ ውስጥ ያስቀመጠውን ብቻ እንደሚናገር መለሰለት ፤ ይህ በአሁኑ ጊዜ በእስራኤል አገር እንደሚካሄድ ቀላል ምሳሌ ነው ፤ ኢራን እስራኤልን ከምድር ገፅ ለመደምሰስ፣ ለማጥፋት እና ለማስወገድ ትፈልጋለች ፤ በመሰረቱ ያ የባላቅ አላማ ነበር ፤ እግዚአብሄር ጣልቃ ገባ ምክንያቱም እጁ በእግዚአብሄር ህዝብ ላይ ነው ፤ ህዝቡን ምንም አይነካቸውም ፡፡
ዘኁልቁ(23፡ 13-26)፡ ሁለተኛው ምላሽ፡ ባላቅ በለዓምን ለእርሱ በለዓም እስራኤላዊያንን ይረግምልኛል በሚል ተስፋ እስራኤላዊያንን እንዲያ ወደ ሌላ ቦታ ወሰደው ፡፡ ባላቅ ወደ ሰፈሩበት እንዲመለከት ወሰደው ፤ እንደገና ሰባት መሰዊያ ሰሩ ለእያንዳንዱ መሰዊያ አንድ ሰባት ወጠጤዎች ሰዉ ፡፡ በለዓም ባላቅን ከእግዚአብሄር ጋር ከመስዋዕቱ ጋር እንዲቆይ ነገረው ፤ ማሳሰቢያ በዚህ ጊዜ “ምናልባት” አላለም ነገር ግን ከእርሱ ጋር እገናኛለሁ አለ ፡፡ እግዚአብሄር ከበለዓም ጋር ተገናኘ በአፉም ውስጥ መልዕክትን አስቀመጠ ፤ በለዓም ተመለሰ ሁለተኛውን ምላሽ ተናገረ፡
ለምናገረው ትኩረት ስጥ ! (ቁጥር 18) ፡፡
እግዚአብሄር ሀሳቡን አይቀይርም (ቁጥር 19) ፡፡
እንድባርክ ትዕዛዝ ተቀብያለሁ ልቀይረው አልችልም (ቁጥር 20) ፡፡
ለያዕቆብ ጥፋት አይሆንም ወይም ለእስራኤል አደጋ አይሆንም እግዚአብሄር በእነርሱ ይደሰታል (ቁጥር 21) ፡፡
በያዕቆብ ላይ የአስማት ርግማን አይሆንም (ቁጥር 23) ፡፡
ዘኁልቁ(23፡ 27- 24፡ 9)፡ ሰዎስተኛው ምላሽ፡ ባላቅ በለዓምን ከዚህ በለዓም በእነርሱ ላይ ይረግምልኛል ብሉ ተስፋ በማድረግ ጠፉ ምድሩ ከሚታይበት ወደ ፌጎር ጫፍ ላይ ወሰደው ፡፡ ባላቅ ሌላ ሰባት መሰዊያዎችን ሰራ በእያንዳንዳቸውም ላይ በሬ እና ወጠጤ ሰዋ (ቁጥር 27-30) ፤ እግዚአብሄር እስራኤልን እንዲባርክ በልዓም ስላየ እንደ በፊቱ ምልክቶች አልፈለገም ፡፡ በለዓም የእስራኤላዊያን መስፈሪያዎች ነገድ በነገድ ወደ ታች ሲመለከት የእግዚአብሄር መንፈስ መጣበት(ቁጥር 1-2) ፤ የእግዚአብሄር መንፈስ በክፉው ሰው ላይ መጣ ከእስራኤላዊያን ኃላ እየመጣ ነበር ፤ ይህ ሁሉም ሰው በእግዚአብሄር ሊነኩ እና ሊባረኩ እንደሚችሉ ያሳያል ፡፡ ከዚያም በለዓም ሰዎስተኛውን ምላሽ አወጀ(ተናገረ)፡
እግዚአብሄር “አይኖቹ የተከፈቱትን ሰው” በለዓምን በምጥራት ምላሹን ጀመረ ፤ ዮሐንስ ማክአርቱር እንደ ተናገረው የእግዚአብሄር መንፈስ መረዳት ሰጥቶት ነበር ፡፡
በለዓም የእግዚአብሄርን ቃል ሰማ ሁሉን ከሚችለው ራዕይ አየ በተከፈቱ አይኖቹ ራስን ወደ አለማዎቅ ወደቀ (ቁጥር 4) ፤ ራዕይ በነቃቹሁ ጊዜ ይከሰታል ፤ ህልም በተኛችሁ ጊዜ ህልም ይከሰታል ፡፡
“ ያዕቆብ ሆይ ድንካኖችን …..ምንኛ ያምራሉ ! እንደ ሸለቆች በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች እግዚአብሄር እንደ ተከለው እሬት በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል “(ቁጥር 5-6) ፡፡
ከማድጋዎቻቸው ዉሃ ይፈስሳል ፤ ዘራቸው የተትረፈረፈ ዉሃ ይኖረዋል (ቁጥር 7) ፡፡ ቶም ኮንስታብል የተናገረው ውሃ የማቴሪያል ብልፅግና እና በረከት ምንጭ ነበር ፤ ምሳ (5፡ 15-17) ይህን ያረጋግጣል፡ ባላቅ እና ሞአባዊያን ብዙ እስራኤላዊያን ሲያስቡ በለዓም ብዙ እየመጡ እንደነበር ይናገር ነበር ፡፡
የእስራኤላዊያን ንጉስ ከሌሎቹ ይበልጣል ፤ እነዚህን ህዝቦች ምንም ሊነካቸው አይችል(ቁጥር 7-8) ፡፡
“ የሚመርቅህ ሁሉ የተመረቀ ይሁን የሚረግምህም ሁሉ የተረገመ ይሁን “(ቁጥር 9) ፤ በዘፍ(12፡ 3) እግዚአብሄር አብርሃምን ነገረው፡ “ የሚባርኩህን እባርካለሁ የሚረግሙህን እረግማለሁ ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ ፡፡ “ ዘፍ(49፡ 9) በይሁዳ ላይ የእስራኤል በረከት ተመዝግቦአል፡ “ ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው ፤ ልጄ ሆይ ከአደንህ ወጣህ እንደ አንበሳ አሸመቀ እንደ ሴት አንበሳ አደባ ፤ ያስነሳው ዘንድ ማን ይችላል ? “ በእግዚአብሄር ሰዎች ግራ አትጋቡ ፡፡
እንደገና ባላቅ በበለዓም ፈርቶ ነበር ምክንያቱም በመርገም ፋንታ ሰዎስት ጊዜ እስራኤልን ስለ ባረከ ፤ ባላቅ ያለክፍያ ወደ ቤቱ በላከው ጊዜ ባላቅ መልዕክቶችን ልኬልሀለሁ አለ እናም ባላቅ ቤት የሞላውን ብር እና ወርቅ ቢሰጠው እንካን ከእግዚአብሄር ዉጪ መሄድ አይችልም ፤ በመቀጠል በለዓም አራተኛውን ምላሽ አወራ(ተናገረ) ፡፡
ዘኁልቁ(24፡ 15-19)፡ አራተኛው ምላሽ፡ በለዓም መሲሁን አመለከተ፡
ወደፊት ከያዕቆብ የሚመጣ ኮኮብ አየ ፤ ማቴ(2፡ 1-2) ሲናገር ከምስራቅ ጥበበኛ ወንዶች መጡ ምክንያቱም “ኮኮቡን በምስራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና ፡፡”
በኮኮብ ምስል ክፉው ሰው በለዓም ስለመጣው መሲህ ተንብዩአል ፡፡
በትረ መንግስት ከእስራኤል ይነሳ ነበር ፤ በትረ መንግስት የንጉስ ምልክት ነበር ፤ መዝ (89፡ 27) የሚለው “ እኔም ደግሞ በኩሬ አደርገዋለሁ ከምድር ነገስታትም ከፍ ይላል ፡፡”
መዝጊያ
እግዚአብሄር ለመሲሁ ከእስራኤል እንዲመጣ አቀደ ከዚያም በመጨረሻ አለምን ለማዳን ፡፡ ወደ አምስተኛው፣ ስድስተኛው እና ሰባተኝው መልስ ስንገባ የባላቅ ሙሉ አላማው እንደ ዳላስ የዩንቨርስቲይ ፕሮፌሰሩ ሮል አለን የነበረው፡ “ አንድ ህዝብን አንስቶ በሌላ በመተካት በራሱ ብቻ ለመፍረድ ፤ በአንፃሩ ይህ ማለት በእስራኤል ህዝብ ላይ የቀጠለ በረከት እና የተረጋገጠ ተስፋቸው የወደፊት ነፃ አዉጪ የመጨረሻ አሸናፊ የሚሆነው ፡፡”
በለዓም በመጨረሻም ወደ እውነት አመለከተ ያ ማሸነፍ በዚህ ነፃ አዉጪ በኩል እንደሚመጣ ፡፡ አህያዋ እንዲቆም በነገረችው ጊዜ ኢየሱስ( የእግዚአብሄር መለዓክ) ጣልቃ ገባና በለዓምን የነገረውን ሁሉንም ነገር እንዲነግራቸው ነገረው ፡፡ በለዓም እግዚአብሄር የተጠቀመበት ያልታወቀ አገልጋይ ነበር እንደዚህ እግዚአብሄር ሌሎች የማይታወቁን ተጠቅሞአል ፤ ዳዊት ትንሽ እረኛ ወንድ ነበር ፤ ነህምያ ጠጅ አሳለፊ ነበር ፤ ማሪያም በናዝሬት ወጣት ሴት ነበረች ፤ ጴጥሮስ አሳ አጥማጅ ነበር ፤ ጌዲዎን የታናሽ ታናሽ ነበር ፤ ሙሴ ነፍሰ ገዳይ ነበር ፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች የተለየ ጀግና ራስ ባይኖራቸውም እግዚአብሄር ተጠቀመባቸው ፤ ወደ ኮኮቡ ሰዎችን እንድታመለክቱ እግዚአብሄር ይጠቀምባችሁ ይችላል !
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 350.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 186.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Numbers, p. 145; available at http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/numbers.pdf.
Ronald B. Allen, The Expositor’s Bible Commentary: Numbers, rev. ed. (Grand Rapids: Zondervan, 2012), p. 336.
ጥያቄዎች
-
ባላቅ በለዓምን እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ላይ እንዲያደርግለት ምንድን እንዲጠይቅለት ፈለገ (ዘኁ 23፡ 7, 11) ? ባላቅ ያ እንዲሆን በጣም የፈለገው ለምን ነበር ?
-
ባላቅ በለዓምን የእግዚአብሄርን ሞገስ እንዲያገኝ ሊከፍለው ሞከረ ( ዘኁ 22፡ 17) ፡፡ ስለ እስራኤላዊያን ስኬት ከየት እንደመጣ ስላወቀ ባላቅ ምንድን አደረገ ?
-
በበለዓም የመጀመሪያ ምላሽ ከእግዚአብሄር እስራኤላዊያን ከሌላ ህዝብ እንደተለዩ ተናግሮአል (ዘኁ 23፡ 9) በአሁን ጊዜ እንደ ክርስቲያን እናንተ ተለይታችኃል ? የተለየ መሆን(መለየት) ማለት ምን ማለት ነው ? (መዝ 4፡ 3, ሮሜ 1፡ 1, 2ቆሮ 6፡ 17, 1ጴጥ 2፡ 9, 1ዮሐ 4፡ 4)
-
አንዳንድ ጊዜ የሰዎች ግንኙነት ይጥሉናል ሁኔታዎችም በቐሚነት ይቀየራሉ ፤ በዘኁ(23፡ 19) እንዴት ምቾት(መፅናናትን) መውሰድ እንችላለን ? (ኢሳ 40፡ 8, 55፡ 11, ኤር 1፡ 17)
-
በለዓም ከባላቅ ጋር ለመገናኘት እግዚአብሄርን በጠየቀው ጊዜ የእግዚአብሄር መልስ አይሆንም ነበር (ዘኁ 22፡ 12) ፤ ግን በለዓም ደግሞ በጠየቀው ጊዜ እግዚአብሄር እሺ አለው (ዘኁ 22፡ 20) ፤ ከዚያም የእግዚአብሄር መለዓክ መንገዱን ዘጋበት እናም ለመግደል ትንሽ ቀረው (22፡ 32-33) ፡፡ እግዚአብሄር ይን ለምን አደረገ ? በለዓም ታዛዥ ሆኖ ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታምኑም ? (ዘኁ 31፡ 16, ራዕ 2፡ 14)
-
በዘኁ(23-24) በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 23:15-17
“Balaam said to Balak, ‘Stay here by your burnt offering while I seek the LORD over there.’ The LORD met with Balaam and put a message in his mouth. Then He said, ‘Return to Balak and say what I tell you.’ So he returned to Balak, who was standing there by his burnt offering with the officials of Moab. Balak asked him, ‘What did the LORD say?’”
በለአም እስራኤልን ባረክ
ኦሪት ዘኁልቁ 23-24
እግዚአብሔር የበለአምን ልቦና ያገኘዉ፥ የአህያይቱን አፍ ከፍቶ በልአምን እንድትናገረዉ ያደረገ ጊዜ ነዉ። በመሃል መንገድ ላይ በልአም ከእግዚአብሔር መለዓክ ጋራ ከተገናኘ በኃላ እግዚአብሔር በአፉ ያስቀመጠለትን መልዕክት ብቻ ይናገር ነበር። ንጉስ ባላቅ እንኳ ለመስማት የሚፈልገዉ ባይሆንም፥ በላአም ይናገር ነበር። እግዚአብሔር በለአምን በመጠቀም፥ ንጉስ ባላቅ እና የእስራኤልን ህዝብ፥ ስለሚመጣዉ የንጋት ኮከብ፥ ስለ ንጉሱ መሲህ ክርስቶስ ያመላክታቸዉ ነበር!
እግዚአብሔር የእዉነትን መልዕክት በአህያ እና በቅጥረኛ አገንጋይ መናገር ከቻለ፥ አስታውስ፥ በማንኛዉም ሰዉ መናገር ይችላል። ከእርሱ ጋራ ህብረት በምታደርግበት ጊዜ፥ እግዚዓብሔር በልብህ መልዕክትን ከሰጠህ፥ ታዛዥ እና ደፋር በመሆን ለሌሎች ሰዎች አካፍለዉ። እግዚአብሔር ማንንም የሚናግርቡት አፉ ያደርጋል! ብቁነትህ ከእግዚአብሔር እንጂ ከአንተ ዘንድ አይመጣም!
"ባላቅንም፦ እኔ ወደዚያ ለመገናኘት ስሄድ በዚህ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ አለው። እግዚአብሔርም በለዓምን ተገናኘ፥ ቃልንም በአፉ አድርጎ፦ ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም በል አለው። ወደ እርሱም መጣ፥ እነሆም፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ምንድር ነው? አለው።"
ኦሪት ዘኁልቁ 23:15-17
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘኁልቁ 24:17፦ "አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል።"
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:5፦ "ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤"
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:5-6፦ "ከእነዚህ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በአንድ ነገር እንኳ እንደ ጎደልሁ ራሴን አልቆጥርም። በአነጋገሬ ያልተማርሁ ብሆን እንኳ፥ በእውቀት ግን እንዲህ አይደለሁም። ነገር ግን በሰው ሁሉ መካከል በነገር ሁሉ ተገልጠንላችኋል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፈል 86
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።