The Doctrine of Balaam
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 25-26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና ስለ አህያዋ; እግዚአብሄር ይጠቀምበታል ብሎ የማያስበውን ስለ በለዓም; እና በእግዚአብሄር ህዝብ ላይ ርግማን ለማምጣት ስለ ሞከረው ንጉስ ባላቅ አውርተናል ፡፡ የእግዚአብሄር እጅ በእስራኤላዊያን ላይ እንዴት እንደነበር እናያለን ፤ ከዚያም ወደ ዘኁልቁ 25 እንገባለን እስራኤላዊያንም እንደገና በአጠቃላይ ችግር ያገኛቸዋል ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(25፡ 1)፡ እስራኤላዊያን በሰጢም እንደነበሩ ወንዶቹ ከሞአባዊያን ሴቶች ጋር ፆታዊ ግንኙነት ጀመሩ ፡፡ ሰዎች ሲሰለቹ ችግር ውስጥ እንደሚገቡ ታዉቃላችሁ ?ዮሐንስ ማክአርቱር የተናገረው ሰጢም ከኢያሮኮ በመላው ዮርዳኖስ ወንዝ ክልል ነበር እስራኤል በመጨረሻ ከነዓንን ይዘውታል ፤ ኢያ (2፡ 1) ያረጋግጣል “ የነዌም ልጅ ኢያሱ ፡፡ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላካ ፡፡ “
ዘኁልቁ(25፡ 2-3)፡ “ ለአምላኮቻቸው ለመሰዋት ሴቶቹ ጋበዙዓቸው እስራኤላዊያን በሉም ለአምላኮቻቸውም በአምልኮ ተደፉ ፡፡” አሁን እስራኤላዊያን በሞዓባዊያን ሀይማኖት ተቀላቀሉ ፡፡ መፅሀፍ የሚለው ሁለቱ አንድ ስጋ ይሆናሉ (ዘፍ 2፡ 24) ፤ ከሴት ጋር ግንኙነት በሚኖራችሁ ጊዜ በሚገባ አሪፍ ነኝ የምትለው በምታምነው እና ህይወቶአን እንዴት በምትኖረው ነው ፡፡ እስራኤል ራሱን ከብኤልፌጎር በዓል ጋር ቀላቀለ (ቁጥር 3) ፤ ይህ ለእስራኤል የማያቆአርጥ አደናቃፊ መዝጊያ ሆነ ፡፡ መሳ(2፡ 13) የገለፀው “እግዚአብሄርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ“ ፤ በ 2ነገ(17፡ 16) “ የአምላካቸውንም የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ሁሉ ተው ቀልጠው የተሰሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ ለሰማይም ሰራዊት ሁሉ ሰገዱ በኣልንም አመለኩ ፡፡” ኤር(2፡ 8) የሚገልፀው “ ካህናቱም እግዚአብሄር ወዴት አለ ? አላሉም ባለ ኦሪቶችም አላወቁኝም ፤ ገዢዎችም ዐመፁብኝ ነቢያትም በባኣል ትንቢት ተናገሩ የማይረባም ነገር ተከተሉ ፡፡” በዚህም ምክንያት የእግዚአብሄር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ (ቁጥር 3) ፡፡
ዘኁልቁ(25፡ 4-5)፡ እግዚአብሄር ሙሴን ሁሉንም የእስራኤል መሪዎች እንዲወስድ እና በጠራራ ፀሀይ እንዲሰቅላቸው ነገረው (ቁጥር 4) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው “ እስራኤል ወደ በኣል አምልኮ ለመቀላቀል ተዳርቶ ነበር ፡፡“ ወንዶቹ ወደ ዝሙት ገቡ ይህም ለሀሰተኛ አምላኮች በር ከፈተ ፡፡ የአይኖቻችንን ዝሙት(ምኞት) በምንከታተል ጊዜ ወደ ህይወታችን እንዲመጣ ለሰይጣን የተከፈተ በር ነው ፡፡ አንድ ትንሽ ነገር ባስረከብን ጊዜ ኃጢዓት የሚቆም እና የሚሮጥ ነው ፡፡ በዚህ ጊዜ ሙሴ ዳኞቹን ከበኣል ጋር ራሳቸውን የቀላቀሉትን እያንዳንዱን ሰው እንዲገድሉ አዘዛቸው (ቁጥር 5) ፡፡ እነዚህን ወንዶች እንዲድኑ ተደፍቶ ለእግዚአብሄር አልፀለየም ፡፡
ዘኁልቁ(25፡ 6-9)፡ አንድ እስራኤላዊ ሰው አንዲት ምድያማዊ ሴት በሙሴ ፊት ወደ ዘመዶች ባመጣት ጊዜ እስራኤላዊያን ወደ መገናኛው ድንካን መግቢያ ላይ ያለቅሱ ነበር የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ተነስቶ በእጁ ጦር ወሰደ (ቁጥር 6-7) ፤ ይህ ሰው በህዝቡ እን በእግዚአብሄር ፊት ኃጢዓቱን አስመሰለ ፤ ፊንሐስ ወደ መገናኛው ድንካን ተከተላቸው ጦሩን ሰውየው እና ሰቲቱ ውስጥ በሴቲቱ ሆድ በኩል ወጋቸው (ቁጥር 8) ፡፡ በእግዚአብሄር ቤት ኃጢዓታቸውን አሳዩ ስለዚህ ፊንሐስ ወሲብ እያደረጉ እንደነበር ገደላቸው ፡፡ በዚህም በእስራኤላዊያን ላይ መቅሰፍቱ አቆመ ነገር ግን በዚህ መቅሰፍት 24,000 ሞቶአል (ቁጥር 8-9) ፡፡
ዘኁልቁ(25፡ 10-11)፡ እግዚአብሄር ሙሴን ቁጣዬን ከእስራኤል ልጆች ፊንሐስ አስቁሞታል ብሎ ነገረው ፤ ከዚያም እግዚአብሄር ፊንሐስን የሰላም ኪዳን ዋስትና አደረገው ፤ መዝ(106፡ 30-31) “ ፊንሐስም ተነስቶ ፈረደባቸው ቸነፈሩም ተወ ፤ ያም እስከ ዘላለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ፡፡” በዚህ መቅሰፍት የሞቱትን 24,000 በሰማችሁ ጊዜ ወደ ኃላ የወርቅ ጥጃ በማምለካቸው የገደላቸውን 23,000 ትከረታችሁ ላይ ይስለል ፡፡
ዘኁልቁ(25፡ 13)፡ ለእግዚአብሄር በፊንሐስ ቅንዓት ለእስራኤላዊያን ፊንሐስ ስርየት አደረገላቸው በዚህም የሰላም ኪዳኑም ለእርሱ የሚቀጥል ክህነት ይሆንለታል ፡፡ የፊንሐስ መግደል የእስራኤላዊያንን ኃጢዓት አስተሰረ፡፡
ዘኁልቁ(25፡ 14-15)፡ የተገደለው እስራኤላዊይ ሰው ስም ዘንበሪ ነበር ከሰምዖናዊያን ቤት መሪ ነበር ፤ የምድያማዊት ሴት የሱር ልጁ ከስቢ ነበረች ከነገዳቸው የአንዱ መሪ ነበር ፡፡ እነዚህ ሁለቱ እንደ ማይነኩ እና በተጨማሪም ማድረግ ከፈለጉት ከማንኛው ጋር መራቅ እንደሚችሉ ነበር ያሰበት ፡፡
ዘኁልቁ(25፡ 16-18)፡ እግዚአብሄር ሙሴን ምድያማዊያንን እንዲያጠቃ እና እንዲገድላቸው ነገረው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚናገረው “ እግዚአበሄር ሙሴን በበቀል በምድያም ላይ ቅዱስ ጦርነት እንዲያደርግ አዘዘው “ ፤ የሙሴ ሚስት ምድያማዊ እንደ ነበረች እናስታውሳለን ፤ አባቶአ ዮጦር የምድያም ካህን ነበር ፤ ቢሆንም እግዚአብሄር ሙሴን ምድያምን እንዲያጠቃ ነገረው ፡፡
መዝጊያ
የአይኖቻችሁ መውሰድ(ምልከታ) ምኞትን በምትፈቅዱበት ጊዜ ለብዙ በቀስታ በር ትከፍታላችሁ ፡፡ ሁል ጊዜ ያን በር ስትከፍቱ ከክርስቶስ ወደ ሀሰተኛ አምልኮ ትጠፋላችሁ ፤ መፀሀፍ ይህን ደግሞ እና ደግሞ የሚለው፡
- ምሳ(5፡ 3-8)፡ “ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና አፍዋም ከቅቤ የለሰለሰ ነውና ፤ ፍጻሜዋ ግን እንደ እሬት የመረረ ነው ሁለት አፍ እንዳለው ሰይፍም የተሳለ ነው ፡፡ እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ አረማመድዋም ወደ ሶኦል ነው ፤ የቀና የህይወት መንገድ አታገኝም ፤ በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት የሚታወቅም አይደለም ፡፡ አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ ከአፌም ቃል አትራቁ ፡፡ መንገድህን ከእርስዋ አርቅ ወደ ቤትዋም ደጅ አትቅረብ ፡፡ “ በአንድ ቦታ በእግዚአብሄር ላይ ለማታለል በራችሁን በከፈታችሁ ጊዜ ለብዙ በሩ ይከፈታል ፤ እንደ እግዚአብሄር ሰዎች ምኞትን ልንቐቐም እና ሌሎችን ምኞትን እንዲቐቐሙ ልንጠራ ይገባናል ፡፡
- ዕብ(13፡ 4)፡ “ መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹህ ይሁን ፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሄር ይፈርድባቸዋል ፡፡”
- 1ቆሮ(6፡ 18)፡ “ ከዝሙት ሽሹ ! ሰው የሚያደርገው ኃጢዓት ሁሉ ከስጋው ዉጪ ነው ፤ ዝሙት የሚሰራ ግን በገዛ ስጋው ላይ ኃጢዓትን ይሰራል ፡፡ “ ቢሊይ ግርሃም ሁል ጊዜ ወደ ሆቴሉ ክላስ የሚሄድ የነበረን የሆነ ሰው በሚጎአዝ ጊዜ ቸክ ያደርገዋል ፤ ሁል ጊዜ በማማ ላይ ልትሆኑ ይገባችኃል ፤ ለዚያ ነው ሁልጊዜ በጥንድ መጎአዝ የተጠበቀ የሚሆነው ፡፡
- 1ቆሮ(10፡ 13)፡ “ ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባቸውም ፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሄር የታመነ ነው ትታገሱም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኃል ፡፡ “
1ቆሮ(6፡ 19-20)፡ “ ወይስ ስጋችሁ ከእግዚአብሄር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን ? በዋጋ ተገዝታችኃል እና የራሳችሁ አይደላችሁም ፤ ስለዚህ በስጋችሁ እግዚአብሄርን አክብሩት ፡፡ “የሆነ ሰዎች ጉዳይ ከኖራቸው በእግዚአብሄር ላይ የሚያጭበረበሩ ናቸው ፡፡
1ዮሐ(1፡ 9)፡ “ በኃጢዓታችን ብንናዘዝ ኃጢዓታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው ፡፡” እዚህ ነገር ላይ ከሆናችሁ እንደገና መጀመር ትችላላችሁ ፤ እግዚአብሄር ይቅር ሊላችሁ ይቻለዋል ፡፡ ማንም ሰው ከአስተሳሰብ ነፃ ነው የማይበገር ነው ፡፡
ደህና አድራሻ ውስጥ የሚኖሩ ሴቶች ወደ ጉጉት ከመግባት እንዲረዱአችሁ የሚጠብቁ አስር ምክሮች ያቀርባሉ፡
ከቀድሞ ወንድ ጎአደኞቻችሁ እና ሴት ጎአደኞቻችሁ ተጠንቀቁ ፡፡
በምታወሩዓቸው እና ምንድን ነው ትክክል በሚለው ድንበር ስሩ ፡፡
ከሌላ ፆታ ትኩረት የሚያስገኙ አለባበስ አስወግዱ ፡፡
ከሌላ ፆታ ሰው ጋር በፍፁም ብቻችሁን አትሁኑ ፡፡
በኃይል ምኞታችሁን ለእግዚአብሄር ተናዘዙ ፡፡
ስለ ምኞታችሁ ለሆነ ሰው ንገሩ ፡፡
ከባለቤታችሁ ዉጪ ተቃራኒ ፆታ ከሆነ ሰው ጋር በስሜታዊነት የቀረባችሁ አትሁኑ ፡፡
በአሁኑ ስዓት ከሆነ ሰው ጋር በስሜታዊነት የተገናኝችሁ ከሆነ ግንኝነቱን አቁሙ ፡፡
የተደበቀ ስሜታችሁ እንደ ማይገኝ እንዳታስቡ ፤ ሁልጊዜ የተደበቀ ይገለጣል ፡፡
ሁልጊዜ ኃጢዓታችሁ ሌላን አካል ይጫናል(ተፅዕኖ ያደርጋል) ፡፡
ወደ ጉጉት(ሞኞት) ውስጥ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ ! እስራኤላዊያን አደረጉት ፡፡ የተለየ ምን አለ እንድናስብ የሚያደርገን ? ዘንበሪን ወይም ከሲብን አንሁን ፡፡ ዘኁ 25 እና ዘኁ 26 በማጥናት ውስጥ ፀሎቴ ይህን መልዕክት ለሚሰማ ሁሉም ሰው መንፈስ ቅዱስ እንዲናገር እና እንዲነካ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ነገሮችን እንዲገልጥላችሁ ጠይቁት ከዚያም መንፃት ይመጣል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 187.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 224.
Nelson’s Commentary, p. 224.
Courtney Joseph, “When You Are Tempted to Have an Affair”; available from https://womenlivingwell.org/2015/06/when-you-are-tempted-to-have-an-affair/.
ጥያቄዎች
-
ባላቅ እንደ ፈለገው በለዓም እስራኤላዊያን ላይ ርግማን ማስቀመጥ አልቻለም ፤ በዘኁ 25 የእግዚአብሄር ቁጣ በእነርሱ ላይ የተቀሰቀሰው ለምን ነበር ? ድርጊታቸውን እግዚአብሄር እንደማያፀድቀው ያውቃሉ ? (ዘጸ 34፡ 15-16)
-
በዘኁ 25፡ 4 እና 9 እግዚአብሄር ኃጢዓትን በጣም በትኩረት መውሰዱ የተለመደ ነበር ፤ እግዚአብሄር ለምንድን ነው ኃጢዓትን የማይታገሰው(የማይችለው) (ኢሳ 59፡ 2፣ ዕባ 1፡ 13፣ ማቴ 6፡ 2፣ 1ቆሮ 15፡ 34)? እግዚአብሄር እንዳደረገው ኃጢዓትን በትኩረት ትወስዳላች(ለኃጢዓት ትኩረት ትሰጣላችሁ) ?
-
ፊንሐስ “ ለአምላኩ የቀና” ተብሎ ተገልፆ ነበር ፤ (ዘኁ 25፡ 11፣ 13) “ ቀና “ የሚለው ቃል (1ነገ 19፡ 10፣ 14) አልያስን ለመግለፅ እና (ሐዋ 22፡ 3; ገላ 1፡ 14) ሳኦል ጳዉሎስ ከመሆኑ በፊት ለመግለፅ ተጠቅሞበት ነበር ፡፡ ቀናተኛ በመሆን እነዚህ ገለፃዎች እንዴት ተመሳሳይ ናቸው ? እንዴትስ የሚለያዩ ናቸው ?
-
በሁለቱም የህዝብ ቆጠራ የተካተቱት ሁለቱ ሰዎች ብቻ እነማን ነበሩ ? ሁለቱ ብቻ የዳኑት ለምን ነበር ? (ዘኁ 14፡ 29-32)
-
ለአብርሃም ያደረገውን ተስፋ የእግዚአብሄርን ታማኝነት ለማሳየት ሙሴን ሁለተኛውን የህዝብ ቁጥር እንዲወስድ በመጠየቅ እንዴት አደረገ ? (ዘፍ 12፡ 1-3)
-
በዘኁ (25-26) በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 25:10-11
“The LORD spoke to Moses, ‘Phinehas son of Eleazar, son of Aaron the priest, has turned back My wrath from the Israelites because he was zealous among them with My zeal, so that I did not destroy the Israelites in My zeal.’”
የበለዓም እምነት
ኦሪት ዘኁልቁ 25-26 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እስራኤላዉያን በዮርዳኖስ ወንዝ በረሃ አጠገብ፥ በሞአብ ተራራ ላይ ነበሩ። በሰፈሩበት አከባቢም ለፈተናቸዉ ራሳቸዉን አሳልፈዉ ሰጡ። በዚይ ወቅት የሰሩት ኃጥያት ስጋዊ ፍትወት ነበር። በምላሹም የእግዚአብሄር ቁጣ በእስራኤላዉያን ላይ ነደደ። እግዚአብሔር ራሳቸዉን ከብዔፌጎር ጣኦት ጋራ ያገናኙ ወንዶች ሁሉ ሙሉ በሙሉ እንደጠፉ ፈለገ። ፊንሃስ የሚባል አንድ ሰዉ ምን እየተደረገ እንዳለ በመረዳት፥ ለትክክለኛ ነገር ቆመ። ከቅንዓቱም የተነሳ፥ ለእግዚአብሔር ቅዱስ የሆኑ ስጦታዎች በሚቀርቡበት ስፋራ ላይ ማለትም ወደ መገናኛዉ ድንኳን መግቢያ አጠገብ ግብረ-ስጋ ግንኙነት ይፈፅሙ የነበሩ አንድ ወንድ እና ሴት ገደለ! ከፊንሃስም ይህ ነዉር ላይ ያሳየዉ ድፍረት እና ጅግንነት የተነሳ እግዚአብሔር መቅሰፉን አቆመ! ከዚያም በኃላ ሌላ የተገደለ የለም! በአሸዋዉ ላይ መስመር ተበጀና የእስራኤል አመፅ ላይም ትልቅ ለዉጥ መጣ!
በዚህ አስጨናቂ እዉነታ ዉስጥ የት ነህ? በኃጥያት የወድቅህ ወይስ ኃጥያት ልምምድ ዉስጥ እየዳከርክ የምትኖር ነህ? ወይስ በቅንዓት እየተቀጣጠልክ ጌታን ለመከተል እና ትክክለኛን ነገር ለማድረግ የወሰንክ ነህ? ሰይጣን እና ዓለም በዚህ ዓለም የኃጥያት መንገድ ሊያታልሉህ ይሻሉ! እነዚህም፦ ስሜታዊነት እና አመንዝራዊነት፣ ከትዳር በፊት ግብረ-ስጋ ግንኙነት ማድረግና ልቅ የሆነ የወሲብ ምስል ይገኙበታል። ከጌታ ዘንድ እንዳልሆነ ታዉቃለህ፥ ነገር ግን ስለኃጥያት ያለህ ስሜት ስለደነዘዘ፥ በሚሰጥህ ጊዜያዊ ደስታ ትረካለህ! ክርስቶስን እንደሚከተል፥ ዛሬ፥ በአሸዋዉ ላይ መስመርን አስምር! ከኃጥያት ጨለማ ተመልሰህ፥ በክርስቶስ ብርሃን ተመላለስ። በይቅርታ በተዘረጉ እጆች፥ ጌታ ሊቀበልህ ይጠብቃኃል! አንድ ወንድም ወይም እህት በዚህ ምልልስ እየተሰናከሉ ከሆነ ከናዔ በመሆን የሆነ ነገር ተናገር! በኃጥያት እየተመላለሱ እንደግኡዝ አካል ዝም አትበል! ዛሬ፥ ለክርስቶስ ብርሃን ሁን!
"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የካህኑ የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በቅንዓቴ በመካከላቸው ቀንቶአልና ቍጣዬን ከእስራኤል ልጆች መለሰ፤ እኔም የእስራኤልን ልጆች በቅንዓቴ አላጠፋሁም።"
ኦሪት ዘኁልቁ 25:10-11
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 106:30-31፦ "ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፤ ያም እስከ ዘላለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።"
- 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:13፦ "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።"
- ወደ ገላትያ ሰዎች 6:1፦ "ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 87
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።