The Pentateuch Numbers

Laws of Inheritance

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 27-28 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 88 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የዘኁልቁ መፅሀፍ ልንጨርስ ትንሽ ነው የቀረን ፤ ቢሆንም ዘኁ 26 አላወራንም በእርግጥ ይህ ምዕራፍ ስለ ቁጥራቸው በተለይም ስለ ሁለተኛው ህዝብ ቆጠራ ነው ፡፡ እስራኤላዊያን ከ20 አመት የሚበልጡ ሁሉም መቆጠር አስፈለጋቸው ፡፡

የምዕራፍ 26 መጨረሻ በነገደ የምድሪቱን ውርስ ሰየመ፡ “ እግዚአብሄርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው ፡፡ ለእነዚህ በየስማቸው ቁጥር ምድሪቱ ርስት ሆና ትከፈላለች ፡፡ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣቸዋለህ ፡፡ ለሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን ርስታቸው ይሰጣቸዋል ፡፡ ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች ፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ ፡፡ በብዙዎችና በጥቂቶች መካከል ርስታቸው በዕጣን ትከፈላለች “(ዘኁ 26፡ 52-56) ፡፡

የሌዋዊያን ውርስ ከቀሩት ከሌሎቹ ወገኖች የተለየ ነበር ፤ የሚበተኑ ያሆናሉ ምድርም አያገኙም፡ “ ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቆጠሩት እነዚህ ናቸው ፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን ፡፡ እነዚህ የሌዊ ወገን ናቸው ፤ የሊብናዊያን ወገን የኬብሮናዉያን ወገን የሞሖላውያን ወገን የሙሳውያን ወገን የቆሬያውያን ወገን ፡፡ ቀዓትም እንበረምን ወለደ “(ዘኁ 26፡ 57-58) ፡፡

ትምህርት

ዘኁልቁ(27፡ 1-2)፡ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ሙሴን ቀረቡት ፤ ስሞቻቸውም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ኤግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበሩ ፤ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር እና በመላው ማህበሩ ፊት በመገናኛው ድንካን በግቢያ ላይ ቆሙ ፡፡

ዘኁልቀ(27፡ 3)፡ ሙሴን አባተቻው ሰለጰዓድ በምድረበዳ እንደሞተ ነገሩት ነገር ግን ከቆሬ ተከታዮች መሀከል አልነበረም ፤ የአመፁ አካል አልነበረም ግን በራሱ ኃጢዓት ምክንያት ሞተ ፡፡

ሰለጰዓድ በተለያዩ መንገዶች ሞቶ ይሆናል፡

  • ዘኁ(11፡ 33)፡ “ስጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩት የእግዚአብሄር ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ ፤ እግዚአብሄርም ሕዝቡንም በታላቅ መቅሰፍት እጅግ መታ ፡፡”
  • ዘኁ(21፡ 6)፡ “እግዚአብሄርም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ሰደደ ሕዝቡንም ነደፉ ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ ፡፡”
  • ዘኁ(25፡ 1)፡ “ሕዝቡም ከሞዓብ ልጆች ጋር ያመነዝሩ ጀመር ፡፡”
  • ዘኁ(25፡ 9)፡ “ በመቅሰፍትም የሞተው 24,000 ነበር ፡፡” ሰለጰዓድ ወንድ ልጆች እንዳልነበሩት መገንዘብ አስፈላጊ ነው ፡፡

ዘኁልቁ(27፡ 4)፡ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ለምንድን መሬት እንደማያገኙ ጠየቁ ምክንያቱም አባታቸው ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት ፤ ከአባታቸው ወንድሞች መካከል መሬት ፈለጉ ፡፡ እነዚህ አምስት ሴቶች በእግዚአብሄር ተስፋ አምነዋል ፤ ደፋር ነበሩ ፡፡ ብሉይ ኪዳን ሌሎች ጥቂት ደፋር ሴቶችን ይገልፃል፡

ሲፓራም፡ “እንዲህም ሆነ ፤ በመንገድ ላይ ባደረበት ስፍራ እግዚአብሄር ተገናኘው ሊገድለውም ፈለገ ፡፡ ሲፓራም ሚስቱ ባልጩት ወሰደች የልጅዋዋንም ሸለፈት ገረዘች ወደ እግሩም ጣለችው ፡፡ አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ አለች “(ዘጸ 4፡ 24-25) ፡፡

ዲቦራ፡ “ልካም ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን ጠርታ ፡፡ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሄር ፡፡ ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ዉጣ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች አስር ሺህ ሰዎች ውሰድ ፡፡ እኔም የኢያቢስን ሰራዊት አለቃ ሲሳራን ሰረገሎቹንም ሕዝቡንም ሁሉ ወደ አንተ ወደ ቂሶን ወንዝ እስባለሁ በእጁህም አሳልፌ እሰጠዋለሁ ብሎ አላዘዘህምን ? አለችው “(መሳ 4፡ 6-7) ፡፡

ተጨማሪ ደፋር ሴቶች፡ ሩት፣ ሀና፣ አቢጋኤል እና አስቴር ፡፡

ዘኁልቁ(27፡ 5-6)፡ ሙሴ በዘሌ(24፡ 1-11) አድርጎት እንደ ነበረው በእግዚአብሄር ፊት ነገራቸውን አቀረበ ፤ ሙሴ አብዛኛውን በእያንዳንዱ ቀን ሁኔታዎቹን በእግዚአብሄር ፊት ያቀርባል ፡፡

ዘኁልቁ(27፡ 7-8)፡ እግዚአብሄር ሙሴን ለሰለጰዓድ ሴት ልጆች ከአባታቸው ወንድሞች መካከል ውርሳዊ ንብረት እንዲሰጣቸው ነገረው ፤ በተጨማሪም እግዚአብሄር አንድ ሰው ያለ ወንድ ልጆች ቢሞት ወደ ሴት ልጆቹ ውርሱን እንዲያስተላልፉ ተናገረ ፡፡ እስከዚህ ክስተት ድረስ ሴት ልጅ በውርስ አልተካተቱም ነበር ፡፡

ዘኁልቁ(27፡ 9-10)፡ ሰዉየው ሴት ልጅ ከሌለው(ካልነበረው) ውርሰ ወደ ወንድሙ ይሄዳል ፤ ሰውየው ወንድሞች ከሌሉት(ካልነበሩት) ውርሱ ወደ አባቱ ወንድሞች ይሄዳል ፡፡

ዘኁልቁ(27፡ 11)፡ የሰውየው አባት ወንድሞች ከሌሉት(ካልነበሩት) ውርሱ ከዘመዶቹ ወደ ቅርብ ወገኑ ይሄዳል ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ውርስ በብዙ ይናገራል፡

“ እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሰራ እንደ እርሱ አሳብ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስት ተቀበልን “(ኤፌ 1፡ 11) ፡፡

“ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና ፡፡ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነው “(ቆላ 3፡ 24) ፡፡

“…ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ እድፈትም ለሌለበት ርስት…ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኃል “(1ጴጥ 1፡ 4) ፡፡

“ የእስራኤልም ልጆች የሙሴን ፊት ቁርበት እንዳንፀባረቀ ያዩ ነበር ፤ እርሱም ከእርሱ ጋር ሊነጋገር እስኪገባ ድረስ እንደ ገና በፊቱ ያደርግ ነበር “ (ዘጸ 34፡ 35) ፡፡

የማያልቀው ውርስ በክርስቶስ አይጠፋም ፤ የተሰጠን ይህ የማያልቀው ውርስ ዘለዓለመዊ፣ የማይበላሽ እና የማይጠፋ ነው ፡፡

ዘኁልቁ(27፡ 12-14)፡ ሙሴ ወደ ተራራው እንዲወጣና ለእስራኤላዊያን የተሰጠችውን ምድር እንዲመለከት ተነገረው ፤ እግዚአብሄር ሙሴን ምድሪቱን ካየ ቦኃላ እንደሚሞት ነገረው ፤ እግዚአብሄር ሙሴን በጺን ምድረበዳ ማህበሩ በተጣሉ ጊዜ አንተና አሮን ሁለታችሁም በእግዚአብሄር ትዕዛዝ ላይ ማመፃቸውን አስታወሰው ፡፡ሙሴ ተስፋ ተስጥቶ የነበረችውን ምድር በፍፁም አይቀበልም ፡፡

ዘኁልቁ(27፡ 18-23)፡ እግዚአብሄር ሙሴን እርሱን ለመተካት ኢያሱ እንደ ተመረጠ ነገረው ፡፡ ሙሴ በኢያሱ ላይ እጆቹን አስቀመጠ አዘዘውም ፡፡

መዝጊያ

ተስፋ ወደ ተሰጠን ወደ ውርሳችን እንገባለን ፤ ምንም እንካን ሙሴ እዚህ በምድር ላይ ወደ ውርሱ ባይወርስም ቃል የምገባላችሁ በሰማይ ከእኛ ጋር ይሆናል ፡፡ ይህ ሁሉ ወደ ዘላለማዊ ስዕል ያመለክታል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. የሰለጰዓድ ሴት ልጆች በተመለከተ ሙሴ በእግዚአብሄር ፊት የወሰደው ነገር (ዘኁ 27፡ 1-7) እና የእግዚአብሄር ውሳኔ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሴቶችን እንዴት አይታችሁ ከምትቀበሉት ጋር የሚቀጥል ይመስላል ? በዚህ ባህል ሴቶችን በእሴት ያስተናግዱአቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሳባችሁም ?
  2. በዘኁ (27፡ 12) እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ዓባሪም ተራራ እንዲወጣ ለምን ነገረው ?
  3. ለሙሴ እግዚአብሄር በመሪባ ዉሃ ቃዴስ ላይ አመፁን ማስታወሱ አስቸጋሪ ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ (ዘኁ27፡ 14) ? ለእናንተ የቀድሞው ኃጢዓታችሁን ለማንፀባረቅ በሌሎች ወይም በመንፈስ ቅዱስ በአስታወሳችሁ ጊዜ ያስቸግራችኃል(የሚያስቸግራችሁ ነው) ?
  4. በፍጥነት “ወደ ወገኖቹ እንደሚከማች “(እንደ ሚሞት) በተነገረው ጊዜ የሙሴ ጭንቀት ምን ነበር (ዘኁ 27፡ 15-17) ? በዚህ ፅሁፍ ምላሽ የሙሴ መልስ የማንን ቃል ነው ? ( ዮሐ 10፡ 3-4, 9-11)
  5. ኢያሱ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ወይም ፍርድ በፈለገ ጊዜ እና ሙሴ ባየ ጊዜ የተለየ ምንድን ይሆናል (ዘኁ 27፡ 5-6, 21) ?
  6. በዘኁ 27-28 በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 27:4-7

“‘Why should our father’s name disappear from his clan because he had no son? Give us property among our father’s relatives.’ So Moses brought their case before the LORD, and the LORD said to him, ‘What Zelophehad’s daughters are saying is right. You must certainly give them property as an inheritance among their father’s relatives and give their father’s inheritance to them.’”

ኦሪት ዘኁልቁ 27-28

የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች በድፍረት በሙሴ ፊት ቀርበዉ፥ የአባታቸዉን ንብረት ጠየቁ። እነዚህ ሴቶች የመጡት በምድረበዳ ጉዙዉ አባታቸዉን በኃጥያቱ እግዚአብሔር ከገደለዉ ሰዉ ነዉ። የቤተሰባቸዉ ኃጥያት እንዳለ ሆኖ፥ እግዚአብሔር በድፍረት የጠየቁትን የዉርስ ንብረት በመስጠት መልሶላቸዋል።

ጌታ፥ ያለፍክበትን እና አሁን ያለህበታን ሁኔታ እያወቀ፥ ይወደሃል፥ ይጠነቀቅልሃልም። በክርስቶስ፥ ከአሁን በኃላ ወላጅ አልባ ሳትሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ተብለህ ተጠርተሃል! ተስፋህን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ስታኖር፥ በእርሱ የማይጠፋ፣ የማይደበዝዝ እና የማይበሰብስ ዉርስ ትቀበላለህ። ከኢየሱስ ጋራ ስትመላለስ ለዘላለም የአንተ ይሆናል! እንደ የነገስታት ንጉስ እና የጌቶች ጌታ ልጆች፥ ሴቶቹ እንዳደረጉት በውርስ ማግኘት የተስፋ ቃል በድፍረት በፊቱ እንመላለስ!

"ወንድ ልጅስ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን አሉ። ሙሴም ነገራቸውን በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የሰለጰዓድ ልጆች እውነት ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ለእነርሱ አሳልፈህ ስጥ።"

ኦሪት ዘኁልቁ 27:4-7

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የዮሐንስ ወንጌል 14:18፦ "ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።"
  • ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:11-12፦ "እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን። ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው።"
  • 1ኛ ጴጥሮስ መልዕክት 1:3-5፦ "ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስጥ የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 88