The Pentateuch Numbers

Calendar of Public Sacrifices

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 29-30 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 89 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና ሙሴ 120 አመቱ ላይ እስራኤልን የመምራት ስልጣኑን ወደ ኢያሱ ሲያስተላልፍ አየን ፡፡ ወደ ዘኁ 28 ስንሄድ ሙሉ ጦርነት እንደሚሆን እንጠብቃለን ፤ በዚያ ፋንታ ሙሴ ቁርባን እና መስዋዕት ተካፈለ ፡፡ እግዚአብሄር በህዝቡ አይምሮ ውስጥ የቀን አቆጣጠር ዋጋ(ትኩረት) ስር እንዲሰድ ደርግ ነበር ፤ ትኩረታቸውን እናዳያጡ እነዚህን ድግሶች እንዲያደርጉ አዘዛቸው ፤ እግዚአብሄር እንዲያውቁ የፈለገው በጠቅላላው ቀናቶቻቸው ልባቸው ያለው አምልኮው ላይ እንዲሆን ነበር ፡፡

በዘኁ 28 ቀን መቁጠሪያው ያጀምራል ( በክፍሉ መጨረሻ ላይ ቻርቱን ተመልከቱ) ፡፡ ከሌዋዊያን ወገን የነበሩት ካህናቱ የሚያገለግሉባቸው አመታት ቁጥር ነበራቸው ፤ ካህናቱ በ25 አመት ማገልገል ይጀማራሉ በ50 አመት ያቆማሉ ፤ 50 አመት ካለፋቸው ቦኃላ እንዲራዱ ተፈቅዶላቸዋል ነገር ግን በትክክል ስራውን አይሰሩም ፡፡

ትምህርት

ዘኁልቁ(29፡ 1-6)፡ መለከቶች በሚነፉበት ድግስ ጊዜ እስራኤላዊያን የሚያሰሩት ስራ የለም፣ የተቀደሰ ጉባኤ ያደርጋሉ እና የሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባሉ ፡፡ ትክክለኛው(ተቀባይ የሚሆነው) መስዋዕት እንከን የሌለበት እንስሳት ነበር - አንድ ወይፈን፣ አንድ ወጠጤ በግ እና አንድ አመት የሞላቸው ሰባት ወንድ ጠቦቶች - እና ለራስ እንደ ኃጢዓት መስዋዕት የሚቀርብ አንድ ፍየል ፡፡ መለከት በአይሁድ ቀን አቆጣጠር በአድሱ አመት(ሮሽ ሀሻናህ) መጀመሪያ ላይ ይነፋል ፡፡

በተጨማሪም ካህናቶቹ መለከት ህዝቡን በአንድ ላይ ለመሰብሰብ፣ ማስጠንቀቂያ ለማሰማት ወይም ጦርነትን ለማሳወቅ ይነፋሉ ፤ አጭር እና እረጅም ጩኸቶች የህዝቡን ትኩረት ለማግኘት ይጠቅሙ ነበር ፡፡ እስራኤል የተበታተነ ቢሆኑም መጨረሻ ጊዜ ላይ በመለከት ድምፅ በመጨረሻም በአንድ እንደ ገና ተሰበሰቡ ፡፡

  • “ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል ፤ እግዚአብሄር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ ፡፡ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል ፤ ታላቅ መለከት ይነፋል በአሶርም የጠፋ በግብፅ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሄር ይሰግዳሉ “(ኢሳ 27፡ 12-13) ፡፡
  • “ ከዚያች ወራትም መከራ ቦኃላ ወዲያውኑ….በዚያን ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል …. መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱም ነፋሳት ለእነርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ “(ማቴ 24፡ 29-31) ፡፡
  • የተመረጡት በአንድ ተጠርተዋል (1ተሰ 4) ፡፡

ዘኁልቁ(29፡ 7)፡ የስርየት ቀን(ዮም ኪፑር) ታላቅና የቅዱስ ቀናት ቅዱስ ነበር ፡፡ የህዝቡን ኃጢዓት ወስዳ ወደ ምድረበዳ የተለቀቀችውን ፍየል የተጠቀመ ስነ ስርዓትም ነበር (ዘሌ 16፡ 10) ፡፡ እስራኤላዊያን እንከን የሌለበት እንስሳት ወይ አንድ ወይፈን፣ ወይ አንድ የበግ ወጠጤ፣ አንድ አመት የሞላቸው ሰባት ወንድ ጠቦት እና አንድ ወንድ ፍየል የሚቃጠል መስዋዕት አቀረብ ፡፡

በዘኁ(28-29) እግዚአብሄር አብሮ ቅርፁን(መዋቅሩን) አስቀመጠ ስለዚህ አስተዳዳሪዎቹ ህዝቡ ወደ ምድሪቱ እንደ ገባ መፈፀም ይችላሉ ፤ ይህ በየጊዜው የሚቀርበውን የግለሰብን መስዋዕት አያካትትም ፡፡ በሌላ መልኩ ዘሌ(23) በእዚህ ምዕራፎች ከራሱ ከክስተቱ ይልቅ በይበልጥ ስለ መስዋዕቱ እንማራለን ፤ በዚህ ጊዜ በሙሉ ተግባር ላይ የዋለው ድግስ ፋሲካ ብቻ ነበር ፡፡

ዘኁልቁ(29፡ 12-39)፡ የድንካኑ ማደሪያ ድግስ(የዳስ በዓል) ዛሬም የሚከበር ነው ፤ የሰባት ቀን በዓል ነው ፡፡ አስተውሉ ከበሬዎች ውጪ ጉድለት የሌለባቸው እንስሳቶች የኃሳብ ፅናት(ቀጣነት) ቀርቦአል (በገፅ 2 ቻርቱን እዩ) ፡፡

ዘኁልቁ

በዓል

በተጨማሪም የሚታወቀው

በሬዎች

የበግ ወጠጤዎች

ጠቦቶች

ፍየሎች

28፡ 3-8

በየቀኑ

2

28፡ 9-10

ማንኛውም ሰንበት

ሻባት

2

28፡ 11-15

የወሩ የመጀመሪያ ቀን

2

1

7

1

28፡ 17-25

ፋሲካ

ያልቦካ የቂጣ በዓል

2

1

7

1

28፡ 26-31

ጴንቴኮስታ

የሳምንታት በዓል

2

1

7

1

29፡ 1-6

የመለከት መንፋት በዓል

ራሽ ሀሽናህ

1

1

7

1

29፡ 7-11

የስርየት ቀን

ዮም ኪፑር

1

1

7

1

29፡ 12-39

የመገናኛው ድንካን ማደሪያ በኣል

የዳስ በዓል

ቀን 1

13

2

14

1

ቀን 2

12

2

14

1

ቀን 3

11

2

14

1

ቀን 4

10

2

14

1

ቀን 5

9

2

14

1

ቀን 6

8

2

14

1

ቀን 7

7

2

14

1

ቀን 8

1

1

7

1

ዘኁልቁ(29፡ 40)፡ “ ሙሴም ለእስራኤል ልጆች እግዚአብሄር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው ፡፡”

መዝጊያ

ጎርደን ዌንሐም የተመለከተው “ ከአንድ አመት በላይ በሆነው ቆይታ 113 በሬዎች፣ 1,086 ጠቦቶች፣ ብዙ ቶን ዱቄት እና ሺዎች ጠርሙስ ዘይት ተጠቅመዋል ፤ ህዝቡ የሰዋው ያ ያደረጉት ነው ! የግለሰብ መስዋዕትን አያካትትም፡፡”

ዋይርስቤ ለእነዚህ ሁሉም መስዋዕቶች ጥያቄዎችን እንድንመልስ እንዲረዱን ሰዎስት ሀሳቦችን አስቀምጦዓል፡ በእነዚህ ሁሉ ምንድን ታደርጋላችሁ ? ይህ እንዴት ነው ተግባራዊ ይሆናል ?

እነዚህ ሁሉ መስዋዕቶች በክርስቶስ ተፈፅመዋል (ዕብ 10፡ 1-18) ፡፡

የእስራኤል ህዝብ በዚያን ጊዜ ከካህናት ዉጪ ማድረግ አይችሉም (ዕብ 4፡ 14-16) ፡፡

መስዋዕቶች በጣም ውድ ናቸው ፡፡

እግዚአብሄር ይመስገን ከእነዚህ አንዱንም ማስታዎስ አይጠበቅብንም ! በግልፅ በኢየሱስ ፊት መምጣት እንችላለን ምክንያቱም ራሱን እንደሰጠን እናዉቃለን ስለዚህ ወደ እርሱ ተመልሰን መሄድ እንችላለን ፡፡

  1. Gordon Wenham, Tyndale Old Testament Commentary, Numbers: An Introduction and Commentary, vol. 4 (Downer’s Grove, IL: University of Michigan, 1981), p. 197.

  2. Warren Wiersbe, Be Counted: Living a Life that Counts for God (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1999), p. 162.

ጥያቄዎች

  1. በተለየ ቀን እና በሰባተኛው ወር ሳንምታት ጊዜ ስለ መስዋዕቱ ሙሴ ትእዛዙን እንዲደግ እግዚአብሄር ለምን አደረገ (ዘሌ 16፡ 29; 23፡ 24, 34; ዘኁ 29) ? በእነዚህ ምዕራፎች ከዚህ በፊት ያልተሰጠ እግዚአብሄር በዝርዝር ምንድን ሰጥቶ አደረገ ? (ዘሌ 23፡ 34-43)
  2. አንዲት ሴት ለእግዚአብሄር ስለት ባደረገች ጊዜ የቱ ጋር ነው አባቶአ(ወይም ባል አግብታ ከነበር) ስለቶቻን እንዳትጠብቅ የሚከለክላት (ዘኁ 30፡ 5, 8) ? አንድ ሰው ለእግዚአብሄር አድርጎት ከነበረው ስለት ከመፈፀም ሊያስወጡት የሚችሉ የተዘረዘሩ ሁኔታዎች ነበሩ (ዘኁ 30; ዘዳ 23፡ 21) ? ስለታቸውን ማክበር ባለመቻል ወይም በራF067 ከነበራት ፅንፍ መጥፎ ሀሳብ ከጥፋተኝነት ሰለ ሴቶች የእግዚአብሄር ጥበቃ ይህ ምን ይላል ?
  3. ማቴ 5፡ 33-37 አንብቡ ፤ በእነዚህ ትዕዛዞች ኢየሱስ የተመለከተውን(ያለው) ምን እንዳሰባችሁ ግለፁ ፡፡
  4. በዘኁልቁ 29- 30 በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 29:39-40

“‘You must offer these to the LORD at your appointed times in addition to your vow and freewill offerings, whether burnt, grain, drink, or fellowship offerings.’ So Moses told the Israelites everything the LORD had commanded him.”

አሁንም አንደገና እግዚአብሔር ሙሴን፥ እስራኤላዉያን እንዴት መስዋዕትን እና ስጦታን እንደሚያቀርቡ ትዕዛዛትን ሰጠዉ። በየዓመቱ በሚከበሩት ብዙ በዓላቶች፥ እስራኤላዉያን ለኃጥያታቸዉ ስርየት እንዲሆንላቸዉ ሀብታቸዉን በመስዋዕት እና በስጦታ መልክ ይለግሱ ነበር። ስለስርየት መንገድ እስራኤላዉያን ያወቁት ይህንን ነበር!

ነገር ግን በአዲስ ኪዳን፥ ክርስቶስ መጥቶ ለዘልአለም የሚሆን የኃጥያት መስዋዕት አቀረበ። ህይወቱን አሳልፎ በመስጠት፥ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የኃጥያትን ዋጋ ከፍሏል! በዚህ አንድ ስጦታ በኩል በእርሱ የፀደቁትን እነሱን ለዘልአለም ፍፁማን አድረጓቸዋል። ለዘላለም ይቅር ተብለሃል! ስለዚህም መስዋዕት ማቅረብ እና ስጦታ አስፈላጊ አይደለም። ስለ የመስዋዕት ፍቁሩ እግዚአብሔርን አወደስ!

"እነዚህንም፥ ከስእለታችሁና በፈቃዳችሁ ከምታመጡት ሌላ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእህልም ለመጠጥም ቍርባን፥ ለደኅንነትም መሥዋዕታችሁ በበዓላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ሙሴም ለእስራኤል ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ ነገራቸው።"

ኦሪት ዘኁልቁ 29:39-40

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:2፦ "ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።"
  • ወደ ዕብራዉያን ሰዎች 10:10-12፦ "በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል። ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤ እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥"
  • ወደ ዕብራዉያን ሰዎች 10:17-18፦ "ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል። የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 89