The Pentateuch Numbers

War with Midian

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 90 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና በዘኁ 29 ስለ መስዋዕት ቀን አቆጣጠር አውርተናል ፤ ምዕራፍ 30 ግን አልተጠቀሰም ነበር ስለ ስለት ህጎች፣ ስለት ስለ ማድረግ፣ ስለ መጠበቅ እና እርስ በእርስ ስለ መግባባት ትዕዛዝ ይሰጣል ፡፡ በምዕራፍ 31 ሽግግር ጊዜ ላይ ነን ፤ ዋረን ዋይርስቤ የፃፈው “ በከነዓን ምድር እስራኤል ለሚገጥሙት ጦርነት ይህ ጦርነት የልምምድ መስሪያ ይሆናል ፡፡“ ይህ ጦርነት ለሙሴ ከሞሞቱ በፊት የመጨረሻው ነበር ፡፡ ኢያሱ ስልጣኑን ከሙሴ ተቀብሎ ነበር አሁን የእስራኤል ልጆች መጎአዝ ጀመሩ ፡፡

ትምህርት

ዘኁልቁ(31፡ 1-2)፡ እግዚአብሄር ለሙሴ ተናገረው በቀልም እንዲያደርግ ነገረው ! ዘዳ 32፡ 35 የሚያወራው በቀል የእግዚአብሄር እንደሆነ ነው ነገር ግን አሁን እግዚአብሄር በምድያም ላይ በቀሉን እንዲፈፅሙ እንዲሄዱ እስራኤልን ይነግራቸው ነበር ፡፡ ለምን ምድያማዊያንን ? እስራኤልን የሳቡ፣ በአካዊ እና በመንፈሳዊ መዳራት አባብለው የወሰዱ የህዝብ ቡድን ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን በምድያማዊያን ላይ በቀል እንዲወስዱ ነገራቸው ፤ ከዚያም ሙሴ ይሞታል ከወገኖቹም ጋር ይሆናል ፡፡

ዘኁልቁ(31፡ 3-4)፡ ሙሴ ህዝቡን ወደ ውጊያ እንደሚሄዱ እና ጥቂት ሰዎችን እንዲያዘጋጁ ነገራቸው ፡፡ እግዚአብሄር ከእስራኤላዊያን ጋር ነበር እናም የእግዚአብሄርን በቀል ይፈፅማሉ ፤ ሙሴ በጀነራል ስልጣን ተነሳ ፡፡ ሁሉም 12ቱም ነገዶች 1,000 ወንዶችን ይልካሉ ፤ ለጦርነቱ 12,000 ወንዶች ተዘጋጁ ፡፡

ዘኁልቁ(31፡ 5-7)፡ የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ እቃዎቹን የሚመራ ጦረኛ ነበር ፡፡ ፊንሐስ እስራኤላዊውን ዘንበሪ እና ምድያማዊቱን ከስቢን በመግደል ድርጊት የወሰደ ነበር በዚህም በእስራኤል ላይ የሞት መቅሰፍትን አቆመ (ዘኁ 25፡ 6-15) ፡፡ እስራኤላዊያንም ጦርነት ተዋጉ ሁሉንም ወንድ ገደሉ ፤ ጅምላ ጭፍጨፋው ሲታሰብ ሺዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ገደሉ !

ዘኁልቁ(31፡ 8-9)፡ እስራኤላዊያን የምድያምዋያንን ንጉሶች ገደሉ፡ ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑሪና ሪባ ፡፡ ደግሞም አህያው መለዓክ መንገዱን እንደዘጋበት የነገረችውን በለዓምንም ገደሉት(ዘኁ 22፡ 22-27) ፤ በለዓም የጦርነቱ ሰበብ ወይም ከምድያማዊያን ጋር የተገናኘ(የተያያዘ) ነበር ፡፡ እስራኤላዊያን ሁሉንም የሴት እና የልጆች ምርኮኛ ወሰዱ ፤ ከብቶቻቸውን፣ መንጎቻቸውን እና ንብረታቸውን ዘረፉ ፡፡ ሁሉንም እቃ ለመሰብሰብ እና ለማሳለጥ ለመሞከር አስቡ ፡፡

ዘኁልቁ(31፡ 10-11)፡ ሁሉም ከተሞቻቸው እና መስፈሪያዎቻቸው ተቃጠሉ ምንም አልቀረም ፡፡ ምርኮኞች እና የተሰረቀ እቃዎች ተሰበሰቡ ፤ ይህ ሁሉ ሙሉ በጦርነቱ ነበር ፡፡

ከእኛ ውስጥ ጥቂቶቻችን ከአካላዊ ጠላቶቻችን ጋር ጦርነት ዉጊያ ላይ ነን ፡፡ ጠላታችን ስጋና ደም ወይም በአይን የሚታይ አይደለም ፤ ዉጊያችን ከዓለም፣ ከስጋ ዌም ሰይጣን በእኛ ላይ ከሚጥላቸው ነገሮች ጋር ነው ፡፡ ሁል ጊዜ ማለዳ ስንነቃ በጦርነት ነን (ኤፌ 6፡ 10-11) ፡፡ የእግዚአብሄር እቃ ጦር ሙሉ ልንለብስ እና በኃይል ልንነቃ ይገባናል ስለዚህ ወደ ቀድሞው መንገዱ ተመልሶ በመውደቅ በረከቱን እንደ ለቀቀው በለዓም አንጨርስም ፡፡ ጦርነት ላይ መሆናችንን ለመርሳት እናዘነብላለን ፤ መንፈሳዊ ጦርነት ነው ፡፡ በመለዓክት የምታምኑ ከሆነ በሰይጣን ልታምኑ ይገባችኃል በዚህም የሰይጣን እንቅስቃሴ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊጥላችሁ ወደ እናንተ ለመምጣት የሚሞክር ነው (ኤፌ 6፡ 12-13) ፡፡ እንደ እስራኤላዊያን የተዘጋጀን እና አዘጋጆች መሆን አለብን ፡፡

ዘኁልቁ(31፡ 12-14)፡ ጦረኞቹ ለሙሴና ለዓልዓዛር እና ለሁሉም እስራኤላዊያ ማህበር በጦርነቱ የተሰረቁ እቃዎችን አመጡ ፡፡ ስኬታቸውን ለማካፈል ፈለጉ ፤ ሙሴ፣ አልዓዛር እና መሪዎቹ ከሰፈሩ ውጪ ተገናኙአቸው ፡፡ ሙሴ ፖሊሶቹን እና ኮማንደሮቹን የያዘውን ጦር ፈራ ፡፡

ዘኁልቁ(31፡ 15-16)፡ ሁሉም ምድያማዊያን ሴቶች እንዲኖሩ ትተዋቸው ነበር ፤ ጦሩ ወደ ሰፈር ተመልሰው ችግር አምጥተው ነበር ! ሴቶቹ ከእስራኤላዊያን ወንዶች ጋር የሚዳሩ ነበሩ ፤ የፌጎር ክስተት ምክንያቱ ይህ ነበር(ዘኁ 25)፡፡በእስራኤላዊያን ላይ መቅሰፍት የሆነው ለዚህ ነው ፡፡

ዘኁልቁ(31፡ 17-20)፡ አሁን ጦሩ ሁሉንም ወንድ ልጆች ይገድላሉ ፤ የምድያዊያን ዘር ይቆረጣል ፤ በተጨማሪም ጦሩ ፆታዊ ግንኙነት የነበራቸውንም ሴቶች ይገድላሉ ፤ እነዚህ ሴቶች ጉዳይ ይሆኑ ነበሩ ፤ ማን ፆታዊ ግንኙነት እንደነበረው እና እንዳልነበረው ጊዜአዊ ስሌት ይወስዳሉ ፡፡ ሙሴ በዚህ ዙሪያ አይስትም ነበር ፤ ትኩርት በጣም የሚያስፈልገው ነበር ፡፡ ለራሳቸው ድንግል ሴቶችን መጠበቅ ይችላሉ ፡፡ የጦርነት ወንዶች የሞተ ከነኩበት ራሳቸውን እስኪያነፁ ድረስ ከሰፈር ዉጪ መቆየት ያስፈልጋቸዋል ፤ ሁሉንም ያነፃሉ፡ ልብሶችን፣ የቆዳ እቃዎችን፣ ከፍየል ፀጉር የተሰሩ ነገሮችን እና የእንጨት ዉጤቶችን ፡፡

ዘኁልቁ(31፡ 21-23)፡ ከእግዚአብሄር የሆነው ህጋዊ(ትክክለኛው) ስርአት ቀረበ ፤ ምርጫ ሳይሆን ትዕዛዝ ነበር ፡፡ ማንኛውም በእሳት ማለፍ የሚችለው በእሳት ይነፃል ፤ ለምሳሌ ወርቅ፣ ብር፣ ነሐስ፣ ብረት፣ ቆርቆሮ እና እርሳስ ፡፡ እሳት ለማንፃት ሂደት ያስፈለገበት ይህ ብቸኛው ጊዜ ነበር ፡፡ የቀሩት ሁሉም በውሃ ውስጥ የሚያልፉ ነበሩ ፡፡

የማጣሪያው እሳት የማንፃት ሂደት ነው ፡፡ የነፃ መሆን ኃይለኛ ነው ፡፡ ውዳቂው ነገር የሚነፃ ነው ፡፡

  • ሚል (2፡ 17; 3፡ 1-2)፡ የወርቅ፣ የብር፣ የብረት ወዘተ ሀሳብ ፤ ከዘኁ 31፡ 23 ፡፡
  • ሚል(3፡ 3-4)፡ በእሳት ማለፍ እንደሚችሉ ያውቃል ፤ እንደ አለፊው ጊዜ እግዚአብሄር እንደገና የተደሰተ ይሆናል ፡፡
  • ሚል(3፡ 5)፡ የእሳት ፍርድን የማያልፉት፡ አስማተኞችእና ዝሙተኞች፣ በሀሰት የሚምሉት እና ከዘመቻ የተገኘውን የሚሰርቁት፣ የመበለቶች እና የየቲሞች ጨቆአኞች እና ለእንግዳው የፍትህ ከሀጂ(አጎዳዮች)፡፡
  • ሚል(3፡ 6)፡ እግዚአብሄር አልተቀየረም ፤ የማይረባውን ነገር ልናነፃ ያስፈልገናል ፡፡ በሚያጣራው እሳት ማን ማለፍ እንደሚችል እንመልከት ፡፡

ማቴ(3፡ 11-12) አንብቡ ፤ መንፈስ ቅዱስን፣ በህይወታችሁ የእግዚአብሄርን መገኘት እና የእግዚአብሄርን እሳት መለማምድን ታገኛላችሁ ፤ የሚያስደንቅ ስዕል ነው ፡፡ በህይወታችሁ መንፈስ ቅዱስ ስትለምዱት የመንፈስ ስጦታዎች በእናንተ በኩል ሲሰሩ በግልፅ ማሳየት ትችላላችሁ - የአገልግሎት ስጦታ፣ የትንቢት ስጦታ፣ የትምህርት፣ የማስተዳደር ስጦታ፣ የእንግዳ ተቀባይነት እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይታያሉ ፡፡ ግን የእግዚአብሄር ያልሆኑት ገለባውን የማቃጠል፣ ኃጢዓትን የማቃጠል እነዚህን ነገሮች የእግዚአብሄር እሳት በእናንተ ውስጥ የማያቃጥል ከሆነ ስጦታዎቹ አይሆኑም ፤ የእሳት ጥምቀት በውስጣችሁ ያለማቐረጥ የማይነድ ከሆነ ለእርሱ ክብር እና አክብሮት በሚያገኝበት መንገድ መንፈስ ቅዱስን አትገልፁትም ፡፡

የእስራኤል የሆኑት ወደ ጦርነት ወጥተው የሄዱት እና ተመልሰው ዘርፈው ያመጡትንበእሳት ውስጥ ይልኩታል ስለሆነም እግዚአብሄር ይጠቀምበታል ፡፡ ከእኛ አስተሳሰብ ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ ወጥተን ወደ ጦርነት ስንሄድ ይህ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ እና የእግዚአብሄር እሳት እንዳለን ልንረዳ ይገባንል ፤ ያ የእግዚአብሄር እሳት የእግዚአብሄር ያልሆነውን እና መኖር የሌለበትንም ማንኛውንም ነገር ያቃጥለዋል፡ ኩራት፣ ስስት፣ ዝሙት፣ የውሸት አምልኮ፣ ቅንዓት ወይም ማንኛውም ሌላውን ነገር የእግዚአብሄር ያልሆነውን ፡፡

ዘኁልቁ(31፡ 24-25)፡ እስራኤላዊያን ራሳቸውን በውሃ እና በእሳት ባነፁ ጊዜ ንፁህ ይሆናሉ ፡፡ ከዚያም በዚህ ብቻ ወደ ወደ ሰፈሩ ይገባሉ ፡፡ የተዘረፈውን ተከፋፈሉት ፡፡

መዝጊያ

ሁላችንም ጦርነት ላይ ነን መንፈሳዊ ጦርነት ላይ ለዚህም የተዘጋጀን መሆን ያስፈልገናል ፤ ጦርነቱን ለመግጠም በሙሉ የተዘጋጀን መሆን ያስፈልገናል ፡፡ የእግዚአብሄርን የጦር ልብ ልንለብስ ያስፈልገናል ፤ የእግዚአብሄር መንፈስ እና በእኛ ውስጥ የሚነድደው የእግዚአብሄር እሳት የእግዚአብሄር የጦር ልብስ ነዳጅ ናቸው ፡፡ ይህ ጦርነቱን የምንቐቐምበት እና ጠንካራ የምንሆንበት በቸኛው መንገድ ነው !

  1. Warren Wiersbe, The Wiersbe Commentary: Numbers (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 297.

ጥያቄዎች

  1. በዘኁ 31፡ 8 ጦረኞቹ የምድያምን ንጉሶች ገደሉ ፤ አምስቱ የተገደሉት እነማን ነበሩ ? ስድስተኛው ሰው የተገደለው ማን ነበር ?
  2. ከጦርነቱ ቦኃላ ጦሩ የተሰረቁትን እቃዎች በመውሰድ ምንድን አደረገ (ዘኁ 31፡ 9-11) ? በቁጥር(14-18) ሙሴ ለምን ነበር የተናደደባቸው ?
  3. ለሰባት ቀን ወንዶቹ ከሰፈር ዉጪ እንዲቀመጡ የተደረጉት ለምን ነበር ? (ዘኁ 31፡ 19) የወሰዱትን እቃዎች የሚያነፁባቸው ሁለት መለያ መንገዶች ምንድን ነበሩ ? (ቁጥር 22-24)
  4. ዘኁ 31 መጨረሻ ላይ የሰረቁትን እቃዎች ይከፋፈላሉ ፤ የወሰዱትን እንዴት አድርገው እንዲካፈሉ እግዚአብሄር ነገራቸው ?
  5. በዘኁ 31 በጥናት ወይም በትምህርት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 31:1, 20, 24b

“The LORD spoke to Moses, ‘Execute vengeance for the Israelites against the Midianites. After that, you will be gathered to your people...Also purify everything: garments, leather goods, things made of goat hair, and every article of wood...After that, you may enter the camp.’”

ወደ እስራኤል ሰፈር አድብተዉ በመግባት የዝሙት ኃጥያት እንዲገባ ያደረጉትን የሚድያም ሰዎችን፥ እስራኤላዉያን እንዴት እንደሚበቀሉዋቸዉ እግዚአብሔር ለሙሴ ትዕዛዝን ሰጠዉ። ይህ ትግል ንፁህ ያልሆኑ ሰዎችን በሙሉ አጠፋቸዉ። እስራኤላዉያን ይህንን ጦርነት ካሸነፉ በኃላ፥ ራሳቸዉንና ያገኟቸዉን እቅዎች በማንፃት ስርዓት ዉስጥ አሳለፉ! ይህንንም ያደረጉት ወደ ህዝቡ ከመቀላቀላቸዉ በፊት ነበር።

እግዚዓብሔር ከህዝቡ ንፅህናን ይፈልጋል። በየዕለቱ ለትግል ተጠርተሃል! በየቀኑ በትግል ዉስጥ በምታልፍበት ጊዜ፥ እንዲሁ የንፅህና ሂደቱ በህይወትህ ይከናወናል። በአንተ ዉስጥ ያለ ከኢየሱስ ክርስቶስ ያልሆነ ነገር ሁሉ ይጠፋል። እነዚህ የሚገጥሙን አስጨናቂ ጊዜያቶች፥ በህይወታችን ዉስጥ አድብተዉ የገቡ፥ እንደ ትዕብትን፣ ፍትወትን፣ ራስ ወዳድነት፣ ምሪት እና ሌሎች ስጋዊ መሻቶችን አይነቶችን ያስወግድልናል። እግዚአብሔር ከህይወታችን ዉስጥ የሚጠራዉ ነገር ምን ይሆን? ጌታ፥ በእሳት ዉስጥ እንድታልፍ የሚፈቅደዉ እርሱን መስለህ እንድታሳየዉ ነዉ! ዛሬ፥ ትግሉ የእግዚአብሄር ነዉና ልብህ በእርሱ ይበራታ!

"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦...ልብስንም፥ ከቁርበትም የተዘጋጀውን ሁሉ፥ ከፍየልም ጠጕር ከእንጨትም የተሠራውን ሁሉ ንጹሕ አድርጉ። በሰባተኛውም ቀን ልብሳችሁን እጠቡ፥ ንጹሕም ትሆናላችሁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትቀርባላችሁ።"

ኦሪት ዘኁልቁ 31:1, 20, 24

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 17:47፦ "ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደል ያውቅ ዘንድ ነው። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፤ እናንተንም በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።"
  • ትንቢተ ሚልኪያስ 3:2-3፦ "ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው? እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፤ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።"
  • ወደ ኤፈሶን ሰዎች 6:10-13፦ "በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 90