Trans-Jordan Tribe Request
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 32 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እስራኤል ከምድያማዊያን ጋር ጦርነት ተጋጥመው ነበር ፤ እግዚአብሄር በቀሉን ሰጥቶ አቸው ነበር ፡፡ ቤታቸውን ያነፁና ሁሉንም ይገድላሉ ግን ወታደሮቹ ሴቶቹንና ልጆቹን ይዘው ተመለሱ ፤ ሙሴ ሁሉንም ወንድ ልጆች እና ማንኛውንም ከወንድ ጋር ፆታዊ ግንኙነት የነበራቸውን ሴቶች (የምድያማዊያን ሴቶች የእስራኤላዊያንን ወንዶች አማለዋል (ዘኁ 25; 31፡ 16-17) እንዲገድሉ ነገራቸው ፡፡ ይህ ለሁሉም እንቅስቃሴ መጥተውበት ለነበረው ወሳኝ(መነሻ) ነው ፡፡ ኢያሱ አሁን ሸክም ላይ ነበር፣ ሙሴ የመጨረሻውን ጦርነቱን ፈፅሞአል እናም ስለሞት እየተዘጋጀ ነበር በተጨማሪም የእስራኤል ልጆች ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት እየተዘጋጁ ነበር ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(32፡ 1-5)፡ ሮቤላዊያንና ጋዳዊያን ብዙ ከብቶች ያሉአቸው ሰዎች ነበሩ ፤ በሰዓቱ የሰፈሩበትን ምድር ከብቶችን ለማሰማረት እንደ ታላቅ ምድር አዩ ፤ በእውነትው እግዚአብሄር ዮርዳኖስን ሲሻገሩ የተሻለ ምድር ነበረው በመልካሚቱ ምድር ሰፍረው ነበር ፤ ጋዳዊያንና ሮቤላዊያን ወደ ሙሴ፣ ወደ አልዓዛር(የአሮን ወንድ ልጅ አድሱ ታላቅ ካህን) እና ወደ ማህበሩ መሪዎች ሄዱ ፤ በዚህ ምድር እንድቆዩና እንዲሰፍሩ ጠየቁ ፤ ዮርዳኖስን መሻገር አልፈለጉም ፡፡
ጀፍ ሀርት(በዚህ መፅሀፍ ቅዱስ ጥናት ክፍለ ጊዜ ላይ አንድ እንግዳ) አስትያየት ሰጠ፡ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ስሜት እንደሆነ ፤ ሁሉም ነገር አሪፍ በሆነ ቦታ ስንሆን ምቹ እንሆናለን “ እዚሁ እንቆያለሁ ፡፡ “ እነዚህ ነገዶች “ ይህን እንድታደርጉ እረዳችኃለሁ ነገር ግን እንድንሄድ አታድረገን “ የሚሉት ይመስላል ፤ ምሳ (3፡ 1-6) ፡፡
ዘኁልቁ(32፡ 6-13)፡ ቀላል ስለነበር ሙሴ ፈጥኖ ለመመለስ “ ምንድነው የምታስቡት ?” የጋዳዊያንንና የሮቤላዊያንን ፍላጎት መጠየቅ ጀመረ ስለዚህ ይህን ቃለ ምልልስ ከሰላዮቹ ሪፖርት ጋር አወዳደረ ፡፡ ከተስፋይቱ ምድር ህዝቡን ተስፋ ካስቆረጡት አባቶቻቸው ጋር ልዩነት አልነበራቸው ፤ በዚህም ሙሴ የሰላዮቹን ታሪክ እና ለ40 አመት በምድረ በዳ መንከራተታቸውን እንደገና ቆጠረ(አሰበ) ፡፡
ዘኁልቁ(32፡ 14-17)፡ ሙሴ የኃጢዓታኞች ትውልድ ብሎ ጠራቸው ፤ የእግዚአብሄር ቁጣ በአባቶቻቸው ላይ እየጨመሩ ነበር ፤ ለመመለስ ከወሰኑ ሁሉም ይጠፋሉ ፡፡ ጋድያዊያንና ሮቤላዊያን በቃለ ምልልስ ሁኔታዉን መግለፅ ጀመሩ ፤ ምድሪቱን ወደዱዓት ነገር ግን መጀመሪያ ጥቂት የበግ ጉሮኖችም እና ማደሪያዎችን መስራት ፈለጉ ፡፡ ከዚያም የሚዋጉ ወንዶቻቸውን እንዲዋጉ ከእስራኤላዊያን ይልካሉ ፤ ሴቶቻቸው እና ልጆቻቸው በከተማዋ ይቆያሉ፡፡
ዘኁልቁ(32፡ 18-19)፡ ሁሉም ነገዶች ውርሳቸውን እሰከ ሚያዙ ድረስ ከእስራኤል ጋር ይዋጋሉ ፤ ከዚያም ወደ ምስራቅ ዮርዳኖስ ቤታቸው ይመለሳሉ ፡፡ ራይ ስቱርድቫት (በዚህ መፅሀፍ ቅዱስ ክፍለ ጊዜ አንዱ እንግዳ) “ የማመቻመች ችግሩ ድምፁ ተገቢና ጥሩ ነው ነገር ግን ማመቻመች ከእግዚአብሄር ጋር ያላችሁን ግንኙነት የሚያጠፋ ነው “ አለ ፡፡
ዘኁልቁ(32፡ 20-24)፡ ሙሴ “ ንግግራችሁን ሰምቻለሁ “ አለ ፤ ከዚያም ሮቤላዊያንንና ጋድያዊያንን ጠላቶቻቸው እስኪሸነፉ ድረስ ጦረኛ ወንዶቻቸውን እንዲለኩ አዘዛቸው ፤ ይህን ብቻ ካደረጉ ያለ ሌላ ኃላፊነት መመለስ ይችላሉ፡፡ ሙሴ “ ቀጥሉም ያቀዳቹሁትን አድርጉ ነገር ግን ቃላችሁን ጠብቁ “ አላቸው ፡፡ ቃላችሁን ካጠፋችሁ በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት ይሆንባችኃል ፡፡ ሙሴ ቃለ ምልልሱን ፈፀመ ፤ ነፃ ማለፊያን ሰጣቸው ፡፡
ዘኁልቁ(32፡ 25-27)፡ ጋዳዊያንና ሮቤልያዊያን ተስማሙ ፤ ጥገኝነታቸው በገልዓድ አረጋግጠው ወንዶች ወደ ጦር ይሄዳሉ ፡፡ እንደ ፖለቲካ መልስ ይሰማል፡ “ እሺ፣ በመቀጠል፣ ውስጥ ነን፣ እንደ ተናገርከው እናደርጋለን ፡፡” በመፅሀፍ የየዎርዳኖስ ወንዝ ምስራቅ በጣም የተወረረ ምድር እንደ ነበር ተጨማሪ እንፈልጋለን ፤ በአሁኑ ጊዜም በምዕራብ በኩል (የብረት ሸድ) የእግዚአብሄር እጅ ጥበቃ አለው ፡፡
ዘኁልቁ(32፡ 28-29)፡ ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር ውስጥ መሄድ ስለማይችል የምድሪቱን ስምምነት(ንግግር) ለመጨረስ በመሪነቱ ሰጣቸው ፡፡ ሮቤላዊያንና ጋዳዊያንን ምድር ተሰጥቶአቸዋል ፡፡ ያ ጡሩ የምድር ስምምነት አልነበረም ፤ በእስራኤል ምድር አልሰጣቸውም ፡፡ በዘፍ(12፡ 3) እግዚአብሄር እስራኤልን ታላቅ ህዝብ እንደሚያደርጋቸው፣ የሚባርኩአቸውን እንደሚባርክ እና የማይባርኩዓችሁን እረግማለሁ ፡፡
ዘኁልቁ(32፡ 30-32)፡ ሙሴ መሪዎቹን “ ከእስራኤል ጋር እንደምትዋጉ እርግጠና ሁኑ “ አላቸው ፤ ካልሆነ በከነዓን ትቀመጣላችሁ ፤ ጋድያዊያን እና ሮቤልያዊያን ተስማም ስለዚህ በምስራቅ “ የውርስ ” ሀብታቸው ይጠበቅላቸዋል ፤ ይህ እንደ አስታራቂ ድምፅ ነው ፡፡
ዘኁልቁ(32፡ 33-41)፡ የምናሴ እኩሌታ ነገድ እንዲገቡ ተወሰነ ! ጥብቅ ስምምነት አሸንፈው እንደነበር ይመስላል ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር አቅዶት እንደነበረው አልነበረም ከእግዚአብሄር ፍቃድ ዉጪ ስስት መራቸው ፡፡ የሲሆን(አሞራዊያን) እና የኦግ(ባሻኒይት) እና በዙሪያ ያለውን አካባቢ መንግስት ተሰጣቸው ፤ ምድሪቱን ሙሴ ሰጣቸው ፡፡ መሪዎቹ(ኢያሱ፣ አልዓዛር) ይህን እንዲፈፅሙ ተናገሩ ፤ የጋድ፣ ሮቤል እና የምናሴ ግማሹ ነገድ (በራሱ ያ ሸለቆ ነበር፣ የተከፈለ ነገድ) የከተሞችን መመሸግ እና የበጎች መኖሪያዎችን መስራት ጀመሩ ፤ ከቀሩት ነገዶች ራሳቸውን እየለዩ ነበር ፡፡ ኮንስታብል የፃፈው “ ከሌሎች ነገዶች መራቅ ቆይቶ አለመግባባትን እና አንድ አለመሆንን አመጣ (ኢያ 22)) ፡፡”
መዝጊያ
ዋረን ዋይሰርቤ አራት አይነት ሰዎችን ይነግረናል፡
- ጥቂጦቻችን ከጠፉት አይሁዶች ጋር እንመስላለን ፤ ለተስፋይቱ ምድር በፍፁም አልሰራንም ፡፡
- ተስፋውን ሰምተናል ነገር ግን በፍፁም አላደረግነውም ፡፡
- ጥቂቶቻችን ከአስሩ ሰላዮች ጋር እንመስላለን ፤ ወደ ምድሪቱ መጣን፣ ሀብቱዓን አይተናል ነገር ግን ለመግባት ወደቅን ፡፡
- ይህ ድምፅ ጥሩ እንደሆነ እንወደዋለን ግን አንሄድበትም ፡፡
- ከዚያም ዮርዳኖስ ተሸጋሪ ነገዶች አሉ - ጋዳዊያን፣ ሮቤላዊያን እና ግማሽ ምናሴያዊያን ፡፡
- ሄይ እንገባለን ነገር ግን መቆየት አንፈልግም ፡፡
- በመቀጠል ወደ ምድሪቱ ይገባሉ እናም ተስፋችንም የሚቀምስ አድስ ትውልድ አለ ፡፡
በሪቫይ ት/ቤት ሁሉንም ለመመዝገብ ፈተናው ይህ ነው - በኦንላይ ወይም በሬድዮ ፡፡ አድስ ትውልድ መሆን እንፈልጋለን ፤ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ እና ለያዕቆብ የተሰጠውን ተስፋ የያዙትን ሰዎች መሆን እንፈልጋልን ፡፡ ምድሪቱ ምንም ብትመስልም ወደ ምድሪቱ እንድንጎአዝ መናገር እንፈልጋለን ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እውነት እንደሆነ እናምናለን ፤ ለእኛ መንገድ እንደዘጋጀ እናምናለን ፡፡ ሁላችንም ማድረግ ያለብን በቀላሉ በዚያ ውስጥ መጎአዝ ነው ፡፡
ፈተናዎቹ እነዚህ ናቸው፡ በፍፁም ያላደረጉትን አይሁዶች ናችሁ ? መንገድ የለም ያሉትን ሰላዮች ናችሁ ? ዮርዳኖስ ተሸጋሪዎቹን ነገዶች ናችሁ አሁን ያላችሁበትን በመውደድ ? ወይስ የገቡትን ለእኛ ያለውን ተስፋውን ለመቅመስ አድሱ ትውልድ ናችሁ ?
Thomas Constable. Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Numbers (Available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/numbers.pdf), p. 179.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 367.
ጥያቄዎች
-
በዘኁ 32 ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመሻገር ይልቅ ከዮርዳኖስ በምስራቅ በኩል መቀመጥ የፈለጉት ሁለቱ ነገዶች እነማን ናቸው ?
-
በቁጥር (16-18) በማምጣት የነገዶቹ ሁለቱ መሪዎች ምንድን አስታራቂ ሀሳብ አደረጉ ? እግዚአብሄር እንድታደርጉት የነገራችሁን ነገር ያስታረቃችሁበት ጊዜ አለ ? ልክ ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ ?
-
ለሁለቱ እና ለአንድ ግማሹ ነገዶች ምንድን(ምን አይነት) ምድር ተሰጣቸው ነበር ? ተሰጥቶአቸው የነበሩት ከተማዎች ስሞቻቸው እነማን ነበሩ ? (ዘኁ 32፡ 33-42)
-
በዘኁ 32 በጥናት ወይም በትምህርት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 32:5-6
“They said, ‘If we have found favor in your sight, let this land be given to your servants as a possession. Don’t make us cross the Jordan.’ But Moses asked the Gadites and Reubenites, ‘Should your brothers go to war while you stay here?’”
የዮርዳኖስ ማዶ
የነገድ ጥያቄ
ኦሪት ዘኁልቁ 32 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
የሮቤል እና የጋድ ልጆች ለቤተሰቦቻቸዉና ለእንሶቻቸው የሚሆን አዲስ እቅድ ይዘዉ መጡ። እቅዱም ከተቀሩት እስራኤላዉያን ጋራ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ መሻገርን አያካትትም። የነበሩበትን ምድር ስለወደዱት፥ ለእነሱ የተሻለ እንደሆነ ወሰኑ! በዚህም ምክንያት፥ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከሌሎቹ ነገዶች ጋራ እንዲሁም ወደ ጦርነት መግባትም አስፈላጊ እንዳልሆነ አሰቡ። ሙሴም ያላቸዉን የእምነት ጉድለት እና ለእግዚአብሔር የመጀመሪያዉ እቅድ አለመታመናቸዉን አይቶ ተቆጣ!
እንደ የክርስቶስ ተከታይ፥ ኢየሱስ እጃችንን አንስተን እያረስን፥ በእምነት እርሱን እንድንከተለዉ ይጠራናል! ነገር ግን ጊዜያዊ ነገሮች በእምነት እንዳንመላለስ ሊፈታተኑን ይችላሉ። በራሳችን ጉልበት ሳንደገፍ፥ በእምነት እየተመላለስን፥ በመሉ ልባችን ጌታን እንድንታመን ተጠርተናል። ምንልባት ዛሬ በራስህ ጉልበት በምትደገፍበት ስፋራ ላይ ሆነህ ሊሆን ይችላል። ጌታ ለህይወትህ ያለዉ ዓላማ እጅግ የላቀ መሆኑን በማመን፥ እምነትህን አጥብቀህ ለመያዝ በርታ! እግዚአብሔር ይወድሃል፥ ዓላማዉም የሚደንቅ ነዉ!
"እኛስ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝተን እንደ ሆነ ይህን ምድር ለባሪያዎችህ ርስት አድርገህ ስጠን፤ ወደ ዮርዳኖስም ማዶ አታሻግረን። ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች አላቸው፦ ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሲሄዱ እናንተ በዚህ ትቀመጣላችሁን?"
ኦሪት ዘኁልቁ 32:5-6
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መፅሃፈ ምሳሌ 3:5-6፦ "በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ፤"
- የሉቃስ ወንጌል 9:62፦ "ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው።"
- 2ኛ ቆሮንቶስ 5:6-7፦ "እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 91
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።