From Egypt to Jordan
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 33 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ስራችን በዓለቱ ላይ መቆም ነው ያም ክርስቶስ ነው ፡፡ 1ቆሮ (10፡ 4) የሚለው “ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና ያም ዓለት ክርስቶስ ነበር ፡፡” በምድረበዳ አለቱ ክርስቶስ ነበር ፤ በዘኁ 32 ጋዳዊያን፣ ሮቤላዊያንና ግማሽ ምናሴያዊያን ነገዶች በእግዚአብሄር ላይ መደገፍ እንዳልፈለጉ አይተናል ፤ የእግዚአብሄርን መገኘት በመከተል ፋንታ የነበሩበት ቦታ ለመቖየት ወሰኑ ፤ ያም ወደ ዘኁ 33 ይመራናል ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(33፡ 1-10)፡ ምዕራፍ 33 የእስራኤላዊያን የጉዞ እርምጃ በወታደራዊ ክፍላቸው ከግብፅ እንደ ወጡ ይሸፍናል (ቁጥር 1) ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ቀጣይ እርማጃ እግዚአብሄር የታየላቸው እና የተጎአዙትን የጅማሬ ስፍራውን በመለየት ጎዞአቸውን እንዲመዘግብ አዘዘው (ቁጥር 2) ፡፡ ዛሬ ስድስት ኡደቶችን እንሸፍናለን ፤ እግዚአብሄር ሙሴን እነዚህን ወደ ታች(በደንብ) እንዲፅፍ አዘዘው ምክንያቱም እስራኤላዊያን ሰዎች ለእነርሱ እግዚአብሄር ያደረገላቸውን መርሳት ስለ ቀጠሉ (ዘዳ 4፡ 9, 6፡ 12, 8፡ 2, መዝ 143፡ 5) ፡፡
ነገሮችን ለማስታዎስ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን የጠየቀበትን የተለያዩ መንገዶች አስቡ፡
- ፋሲካ እና በዓላት
- በመቅደሱ የመናው ማድጋ
- የለመለመችው፣ ያበበችው እና ፍሬ የሰጠችው የአሮን በትር
- አስዕርቱ ትዕዛዝ
- በቀሚሶቻቸው ላጥ ፈርጥ
(1ቆሮ 11፡ 25; ሉቃ 22፡ 19 ለራሱ ማስታወሻነት ኢየሱስ የወሰደውን ተመሳሳይ ሀሳብን ያሳያል ፡፡)
ወደ ዘኁ (33፡ 3-4) ስንመለስ ሙሴ ለጉዞአቸው እርምጃ መነሻ ቦታን ፅፎአል፡ እግዚአብሄር ገድሎአቸው የነበረውን ግብፃዊያን በኩሮቻቸውን እየቀበሩ ከፋሲካ ቦኃላ ባላው ቀን ከመጀመሪያው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጎአዙ ፤ ከዚያም እስራኤላዊያን ራምሴን ትተው ሱኮት ሰፈሩ (ቁጥር 5) ፤ ሱኮትን ትተው በምድረበዳ ዳርቻ ኤታም ላይ ሰፈሩ (ቁጥር 6) ፤ ኤታምን ትተው ወደ ምስራቅ ባኣልዛፎን ወደ ፊሀሒሮት ተመልሰው ሚግዶል አጠገብ ሰፈሩ (ቁጥር 7) ፤ ፊሀሒሮትን ትተው በባህሩ ውስጥ ወደ ምድረበዳ አለፉ ከሰዎስት ቀናት ቦኃላ ማራ ላይ ሰፈሩ (ቁጥር 8) ፡፡ እስራኤላዊያን ከማራ ተጎአዙ 12 ምንጮች እና 70 የዘንባባ ዛፎች ወደ ነበሩባት ወደ ኤሊም መጡ (ቁጥር 9) ፤ ከኤሊም ተጉዘው ቀይ ባህር ጋር ሰፈሩ(ቁጥር 10) ፡፡ የሚያውቁት ነገር ቀይ ባህር ጋር በደረሱ ጊዜ የሚሄዱበት ምንም ቦታ አልነበራቸውም ፤ ይህ የመጀመሪያቸው የጉዞአቸው አካል ከራምሴ ወደ ቀይ ባህር ወሰዳቸው በደመናም ይመሩ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(33፡ 11-17)፡ እስራኤላዊያን ከቀይባህር ተጎአዙ እና በሲና በርሀ ሰፈሩ በሂደትም ከድብልልቅ ወደ ጥቂት ድርጅታዊ ቅርፅ ሄዱ (ቁጥር 11) ፡፡ ከሲን ምድረበዳ ተጉዘው በራፉቃ ሰፈሩ (ቁጥር 12) ፤ ከራፉቃ ተጉዘው ኤሉስ ሰፈሩ (ቁጥር 13) ፤ ከኤሉስ ቦኃላ ለመጠጣት ውሃ ወደ አልነበረበት ራፊዲም ሄዱ (ቁጥር 14) ፤ ከራፊዲም ተጎአዙ በሲናም በርሃ ሰፈሩ (ቁጥር 15) ፤ ከዚያም እስራኤላዊያን ከሲና በርሃ ተጉዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ (ቁጥር 16)፡፡ ቀዓትዋዊያን ሲጎአዙ በእያንዳንዱ ጊዜ የመገናኛ ድንካን ማደሪያውን ይሸከማሉ ከዚያም ንዋይ ቅዱሳት እቃዎች ከመድረሳቸው በፊት መልሰው ይተክላሉ (ዘኁ 4፡ 4; 10፡ 21) ፤ ሁለተኛውን ጉዞአቸውን ይህ ይጨርሰዋል ፡፡
እስራኤላዊያን ለመልቀቅ እና ወደ ቀጣዩ ሰፈር ለመጎአዝ እንዴት አድርገው ያውቃሉ ? ዘኁ (9፡ 17) የሚገልፀው “ ደመናውም ከድንካኑ ላይ በተነሳ ጊዜ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጎአዙ ነበር ደመናውም በቆመበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር ”(ዘኁ 9፡ 20) ፡፡ በእግዚአብሄር መገኘት የመደገፍ ታላቅ ስዕል ነው ፡፡
ዘኁልቁ(33፡ 18-31)፡ በቁጥር 18 ጅማሬ የጉዞው ሰዎስተኛው አካል ነው፣ ሰላዮች ወደ ታራን በረኃ ሰላዮቹ ከተላኩበት ታሪክ ጀምሮ ተመዝግቦአል ፤ ከዚያም በአራተኛው ጊዜ እስራኤላዊያን ከቃዴስ ወደ ብኔያዕቃን ተጎአዙ(ቁጥር 26-31) ፡፡
ዘኁልቁ(33፡ 32-49)፡ የጉዞአቸው አምስተኛው ጊዜ እስራኤላዊያን ወደ ኤዶም የደረሱበትን የበርሀ ጉዞ እና የአሮንን ሞት መዝገብ ይሸፍናል ፤ የጉዞው ስድስተኛው ጊዜ እስራኤላዊያንን ከፋኖን እስከ ሞዓብ ይከታተላል ፤ ሌሎች ስነ መለኮታዊያን ጉዞውን ወደ 42 ደረጃዎች ይከፍሉታል ፡፡ በሚያስደነቅ ሁኔታ ሙሴ 42 ጊዜ ከአንድ ቦታ ተጉዘው እና ሌላ ቦታ ሰፍረው እንደ ነበር ፅፎአል ፡፡
ዘኁልቁ(33፡ 50-53)፡ በሞዓብ ሜዳ ላይ እግዚአብሄር ለሙሴ ተናገረው (ቁጥር 50)፣ እስራኤላዊያን ከነዓን በገቡ ጊዜ ከሁሉም መኖሪያዎች ሊያባርሩአቸው እና ሁሉንም ጣዖቶቻቸውን እና ማምለኪያ ቦታቸውን ማጥፋት እንደሚይገባቸው በደንብ ያብራራዋል (ቁጥር 51-52) ፡፡ እግዚአብሄር ንብረታቸውን እንዲወስዱና ምድሪቱ ላይ እንዲቀመጡ በደንብ ገልፆዓል ምክንያቱም ሰጦትአቸው የነበረችው ምድር ስለነበረች (ቁጥር 53) ፤ ይቺ ምድር የእነርሱ እንደነበረች እግዚአብሄር አሳሰባቸው (ቁጥር 54) ፤ በተጨማሪም ከማስጠንቀቂ ጋር ትዕዛዝ መጣ፡ እስራኤላዊያን ከተስፋይቱ ምድርን መኖሪያዎች የማያባርሩ ከሆነ እስራኤላዊያንን የነዘንዙዓቸዋል (ቁጥር 55) ከዚያም “ ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚዋጋ” ይሆኑባችኃል ፤ በተጨማሪም እንዳዘዛቸው ባለመስራት ለመውደቃቸው እስራኤላዊያንን እግዚአብሄር ይቀጣቸዋል (ቁጥር 56) ፡፡
መዝጊያ
እነዙህ ሁሉ ወደ ሮሜ(8፡ 14) “ በእግዚአብሄር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሄር ልጆች ናቸውና ” ይመራሉ ፡፡ ይህ ማለት በእግዚአብሄር መንፈስ ልንመራ ይገባናል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ካልተደገፋችሁ በጉዞዓችሁ ከክርስቶስ ጋር ምንድን ታደርጋላችሁ ? እንደ ሮቤላዊያን እና ጋዳዊያን “ በእውነት ወደ ተስፋይቱ ምድር መሄድ አንፈልግም “ በማለት እዚሁ ትቀመጣላችሁ ? በእግዚአብሄር መመራት የምትፈልጉ ከሆነ በብዙ መንፈስ ቅዱስ ሊኖራችሁ ይገባል ፡፡ እግዚአብሄር መገኘቱን በብዙ እንድንቀምሰው ይፈልጋል ፤ በራሳችን ሳይሆን በመሪነቱ እርሱን እንድንታመነው ይፈልጋል ፡፡
ጥያቄዎች
-
እስራኤላዊያን በእያንዳንዱ ቦታ የሚሰፍሩበትን እና የሚጎአዙበትን ጊዜ እንዴት አድርገው ያውቃሉ ? (ዘኁ9፡ 17)
-
ከግብፅ በመውጣት ወደ ኃላ የእስራኤላዊንን የጉዞ ደረጃ በመመልከት(ዘኁ 33) የትኛው ለእነርሱ በጣም አስፈላጊ እንደነበር ይሰማችኃል ?
-
ከግብፅ እስከ ተስፋይቱ ምድር የነበረው ጉዞ ረጅም ጉዞ ነበር ፤ በጅማሬ፣ መሀል ላይ እና መጨረሻ ላይ በሂደቱ ውስጥ እስራኤላዊያን ተሰምቶአቸዋል ብላችሁ የምታስቡትን ስሜታዊነት ግለፁ ?
-
በዘኁ 33 ደግሞ የመቁጥር ክስተቶች(ቅፅበቶች) አስፈላጊነት የተመዘገበ ነው ፤ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች ዘዳ(4፡ 9 እና 6፡ 12) አንብቡ ፡፡ እንድታስታውሱ የእግዚአብሄር ጥሪ በጉዞአችሁ ላይ አስፈላጊ ነገሮች/ክስተቶች ምንድን ናቸው ? አሁን ለቀጣዩ ትውልድ ወይም ለልጆቻችሁ የምታስተምሩት ወይም የምታሳልፉት የለመዳችሁት ወይም የተማራችሁት ነገሮች ምንድን ናቸው ?
-
በዘኁ 33 በጥናት ወይም በትምህርት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 33:55-56
“But if you don’t drive out the inhabitants of the land before you, those you allow to remain will become thorns in your eyes and in your sides; they will harass you in the land where you will live. And what I had planned to do to them, I will do to you.”
ከግብፅ እስከ ዮርዳኖስ
ኦሪት ዘኁልቁ 33 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እስራኤላዉያን እግዚአብሔር በሚሰጣቸዉን ምድር እንደ አዲስ መጀመር ያስፈልጋቸዋል። እግዚአብሔር ቀድሞ እዛ ይኖሩ የነበሩ አህዛቦችና ነገሮችን ከምድሪቱ ካላጠፉዋቸዉ፥ ለእርሱ ህዝብ በጣም አስጨናቂ እንደሚሆኑ፥ በዓይናቸዉ እና በጎናቸዊ እንደ እሾህ እንደሚሆኑባቸዉ ያዉቃል!
በህይወት ወስጥ አንዳንዴ፥ አዲስ ሥራ ስትጀምር፣ ወደ አዲስ ቤት ስትቀይር፣ አዲስ ትምህርት ቤት ስትገባ፥ ቀድመዉ ከአንተ ጋራ ከነበሩ ሰዎች፥ ስፍራዎች እና ነገሮችን ለመቀላቀል ልትሞክር ትችላለህ። ሁለቱም ለማስደስት ትፈልጋለህ! ማንም በአንተ ምክንያት እንዳይታመም እና እንዳይጨነቅ ትጥራለህ! እዉነታዉ ግን፥ ሁለቱኑም ጎን ደስተኛ ባለማድረግ ወደ አስጨናቂ ሁኔታ ዉስጥ ልያስገባችሁ ይችላል። እግዚአብሔር እያዘዘ የነበረዉ እና የሚፈልገዉ የቀድሞ ህይወታቸዉን ወደ ኃላ ጥለዉ እንደ አዲስ ከእርሱ ጋራ እንዲራመዱ ነዉ። ምናልባት ዛሬ አንተ ይህንን መስማት ይኖርብህ ይሆናል። ከባዱን ዉሳኔ ወስንና እንደ አዲስ ጀምር። የመጀመሪያዎችን እርምጃዎች መራመድ በምትጀምርበት ጊዜ፥ በርትተህ ጀግና ሁን! እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለበጎ ያደርገዋል።
"የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል። እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ።"
ኦሪት ዘኁልቁ 33:55-56
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘኁልቁ 33:52-53፦ "የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም።"
- መፅሃፈ ምሳሌ 16:1-4፦ "የልብ መዘጋጀት ከሰው ነው፤ የምላስ መልስ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ንጹሕ ነው፤ እግዚአብሔር ግን መንፈስን ይመዝናል። ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች። እግዚአብሔር ሁሉን ለእርሱ ለራሱ ፈጠረ፥ ኀጥእን ደግሞ ለክፉ ቀን።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28፦ "እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 92
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።