The Pentateuch Numbers

Boundaries of the Promised Land

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 34 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 93 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዘኁልቁ መፅሀፍ ውስጥ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን መታመን፣ እግዚአብሄርን ማስታዎስ እና ሁልጊዜ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን መቀበልን ተማሩ ፤ ለምን ? ምክንያቱም ወደ አድስ ቦታ የሚገቡ ስለነበሩና እግዚአብሄር ለእነርሱ ያደረገላቸውን ማስታዎስ ስለሚያስፈልጋቸው ፡፡ ዘኁልቁ 33 የማስታዎስ ጊዜ ነበር ፤ ዘኁ (33፡ 53) የሚለው “ ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኃለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም ፡፡” ዘፍ(15፡ 18-21) ተስፋ የተሰጠው “ በዚያ ቀን እግዚአብሄር ለአብርሃም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ ከግብፅም ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጠስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ ፤ ቄናውያንን፣ ቄኔዛውያንንም፣ ቀድሞናውያንንም፣ ኬጢያውያንንም፣ ፌርዛውያንንም፣ ራፋይምንም፣ አሞራውያንንም፣ ከነዓናዊያንንም፣ ጌርጌሳውያንንም እና ኢያቡሳውያንንም ፡፡ “ በአሁኑ ጊዜ እንካን ሁሉም ነገር በእስራኤል ስለ ምድር እና ስለጋዛቶች ነው ፤ በማንኛውም ጊዜ እስራኤል ለምድር ዛሬም ይደራደራሉ በትንቢት ስተዋል ፡፡

ትምህርት

ዘኁልቁ(34፡ 1-12)፡ እግዚአብሄር ሙሴን እስራኤላዊያን ወደ ከነዓን ምድር በገቡ ጊዜ ከድንበሮቹ ጋር እንደ ውርስ እንዲካፈሉ ነገረው (1ነገ 8፡ 56) ፡፡ የደቡብ ድንበር ከኤዶም ድንበር አጠገብ ከፂን ምድረበዳ የሚጀምር ሲሆን የምስራቅ ድንበር ጨው ባህር ይሆናል (ቁጥር 3) ፡፡ ድንበሩ በአቅረቢም ወደ ላይ ከፂን ቀጥሎ ደቡብ ይዞርና መጨረሻው በደቡብ ቃዴስ በርኔ ይሆናል ፤ ከዚያም ክረምት በሚሞላው የግብፅ ጅረት የሚዞርና ባህሩ ጋር በሚያበቃው ድንበሩ ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓፅሞንም የሚቀጥል ይሆናል(ቁጥር 4-5) ፡፡

በአሁኑ ጊዜ እስራኤል በሁሉም መንገድ አልሄደም ፡፡ በምዕራቡ በኩል የሜደትራሊያን ባህር ጠረፍ አጠገብ ይሆናል (ቁጥር 6) ፤ ኢያ (14-19) በጥቂቱ በተለየ ይገልፀዋል፣ ምድሪቱን ወደ ነገዶች ምድር ከፋፍሎታል ፡፡

የሰሜን ድንበር ከሜደትራሊያን ባህር እስከ ሆር ተራራ ከዚያም ከሆር ተራራ እስከ ሐማት ይሆንና እና ድንበሩ ጽዳድ ይደርሳል ፤ ዳርቻውም ዚፍሮን ይሄዳል ሐጸርዔናንም ላይ ያበቃል (ቁጥር 7-9) ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሌሎች አገሮች የትም ቢሆኑ ችግር የለው በመጨረሻም እስራኤል እንደገና ይቺ ምድር ትኖራቸዋለች ፤ የመፅሀፍ ጉዳይ ነው (ሕዝ 47፡ 15-17; ዘኁ 13፡ 21) ፡፡

ምስራቅ ድንበር ከሐጸዔናንም እስከ ሴፋም ይጀምራል ከሴፉም እስከ ምስራቅ ዓይኔ ሪብላ ወደ ምስራቅ ወሽመጥ ባህር ይወርዳና ድንበሩ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ይሄድ እና በጨው ባህር ያበቃል (ቁጥር 10-12) ፡፡ ሁሉም ድንበሮቾአ የተገለፁት ምድሪቱ ይህቺ ናት (ዘፍ 15፡ 18-21; ኢያ 1) ፡፡

ዘኁልቁ(34፡ 13-19)፡ ሙሴ ለእስራኤላዊያን ዘጠኑ ነገዶች እና ግማሹ ነገድ የሚቀበሉዓት ምድር ገለፀላቸው ፤ የሮቤላዊያን፣ የጋድያዊያንና የምናሴ ግማሽ ነገዶች ከእነርሱ ጋር አልነበሩም ምክንያቱም ዮርዳኖስን ተሻግረው ከተስፋይቱ ምድር ፊት ሳይደርሱ ስለቆሙ (ቁጥር 13-15) ፤ ከዚያም ሙሴ ምድሪቱን እንዲያከፋፍሉ ሾሞአቸው የነበራቸውን ሰዎች ስም ሰጣቸው፡ ካህኑ አልዓዛር እና የነኔዎ ልጅ ኢያሱ (ቁጥር 16-19) ፡፡

ዘኁልቁ(34፡ 20-29)፡ እያንዳንዳቸው ነገዶች ምድሪቱን መከፋፈል እንዲርዱ አንድ መሪ ይልካሉ በቁጥር ተጠቅሰዋል፡

  1. ከይሁዳ ነገድ ካሌብ
  2. ከስምዖን ነገድ ሰላሚኤል
  3. ከብንያም ነገድ ኤልዳድ
  4. ከዳን ነገድ ቡቂ
  5. ከምናሴ ነገድ አኒኤል
  6. ከኤፍሬም ነገድ ቀሙኤል
  7. ከዛብሎን ነገድ ኤሊሳፈን
  8. ከይሳኮር ነገድ ፈልጢኤል
  9. ከአሴር ነገድ አሒሁድ
  10. ከንፍታሌም ነገድ ፈዳሄል

መዝጊያ

እነዚህን አስር መሪዎች ለእኛ እንደ ማናሳሻነት ለመሄድ እና ሰዎችን ለእነርሱ…ዘላለማዊ ህይወት በክርስቶስ በኩል የሚጠበቅ ውርስ እንዳላቸው ለመንገር መጠቀም እንችላለን ፡፡

ዕብ(9፡ 15) “ ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲ ቀበሉ እርሱ የአድስ ኪዳን መካከለኛ ነው ፡፡”

ምድር ተሰጣቸው ፤ ዘላለማዊ ተስፋ ተሰጥቶናል ፡፡

1ጴጥ(1፡ 4) “ …ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ እድፈትም ለሌለበት ለማያልፍ ርስት …ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኃል፡፡” ይህ ውርስ በፍፁም የማይጠፋ ነው ፡፡

ኤፌ(1፡ 11)፡ “ እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሰራ እንደ እርሱ አሳብ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን ፡፡”

ኤፌ(1፡ 18)፡ “ ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ታውቁ ዘንድ ነው ፡፡”

ከሌላ ሰው ጋር ይህን ስለ አለማካፈል እንዴት አድርገን ማሰብ እንችላለን ? የጥሪውን ተስፋ መረዳት እንድትጀምሩ እፀልያለሁ እናም በክብር የበለፀገ ርስቱን መለማመድ ትጀምራላችሁ ስለዚህ ለእናንተም እንዲሁም የሚጠብቅ ውርስ አለ ማለት ትችላላችሁ ፡፡ ለርስት ለመዘጋጀት ምርጡ መንገድ ሁሉም ሰው ስለ ርስት ማወቃቸው እርግጠኛ መሆን ነው ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ለእስራኤላዊያን የተስፋይቱን ድንበሮች መዘርዘሩ ለእግዚአብሄር ምን ነበር አስፈላጊነቱ ?
  2. ምድሪቱን ለመከፋፈል ለመርዳት ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሰው ባስፈለገ ጊዜ (ዘኁ 34፡ 18) ሙሴ ከመምረጡ ይል እግዚአብሄር ለምን እንደመረጣቸው ምን ታስባላችሁ ? (ዘኁ 34፡ 29; 1ሳሙ 16፡ 7)
  3. በዘኁ 34 በጥናት ወይም በትምህርት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 34:1-2

“The LORD spoke to Moses, ‘Command the Israelites and say to them: When you enter the land of Canaan, it will be allotted to you as an inheritance with these borders.’”

ዓለት

የተስፋይቱ ምድር ዳርቻዎች

ኦሪት ዘኁልቁ 34 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚአብሔር ለሙሴ የምድሪቱን ርስት እንዴት ማከፋፈል እንዳለበት ዝርዝር የሆኑ ትዕዛዞችን ሰጥቶታል። ርስት እንዳላቸዉ ቢያዉቁም እንኳ፥ ደግሞም የተስፋይቱ ምድር ዉስጥ ገብተዉ እየረገጡ ቢሆንም፥ ስለርስቱ ጉዳይ፣ የመዳረሻዉ ዝርዝር፣ ምድሩቱን ለመከፋፈል ለእያንዳንዱ ነገድ መሪዎችን በመመደብ፥ ሙሴ ለህዝቡ ማብራራት ይጠበቅበታል።

እንደ አማኝ ከጌታ ዘንድ የወረስከዉ የዘላለም ህይወት ርስት አለህ። ልክ እንደሙሴ ይህንን ርስት ለሌሎች ማስረዳት አለብህ። ይህንን እዉቀት ለራስህ ብቻ አታድርገዉ! ሌሎች በክርስቶስ ስላለህ ርስት ያዉቃሉ ብለህ አታስብ! ይህ ርስት ሁሉም እንዲቀበለዉ የተዘጋጀ ነዉ። አንንዳንድ ሰዎች አንተ እዉነቱን ካላካፈልካቸዉ ፈፅሞ በክርስቶስ ስለሚገኛ ርስት ላይሰሙ፥ ላያዉቁ ይችላሉ!

"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ ርስት ትሆናችሁ ዘንድ በዕጣ የምትደርሳችሁ ምድር፥ በዳርቻዋ ያለች የከነዓን ምድር፥ ይህች ናት፤"

ኦሪት ዘኁልቁ 34:1-2

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘኁልቁ 34:12፦ "ዳርቻውም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፥ መውጫውም በጨው ባሕር ይሆናል። ምድራችሁ እንደ ዳርቻዋ በዙሪያዋ ይህች ናት።"
  • ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:18-19፦ "ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤"
  • ወደ ዕብራዊያን 9:15፦ "ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 93