The Pentateuch Numbers

Towns for the Levites

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 35-36 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 94 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ የዘኁልቁ መፅሀፉ ጥናት መጨረሻ ነው ፤ እስካሁን ለእያንዳንዱ መፅሀፍ ቅዱስ ለመሲሁ የሚወክል አንድ ቃል በመለየት አጥንተናል ፡፡ በዘፍጥረት በአዳምና በሂዋን በኩል ዘር አለን ፤ በዘጸዓት የሙሴ ፅሁፍ ስለ ነፃ አዉጪ ሙሴ እንዴት ህዝቡን ነፃ እንዳወጣ እና በአድስ ኪዳን ኢየሱስ እኛን እንዴት ነፃ እንዳወጣን ፤ በዘሌዋውያን አስተሰሪይ አለን እናም እንዴት ክርስቶስ እንደ አስተሰሪይ እንዳገለገለን ፤ በዘኁልቁ አለት አለን መሲሁም አለታችን ነው ፡፡ 1ቆሮ(10፡ 4) የሚለው “ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ ፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ አለት ጠጥተዋልና ያም አለት ክርስቶስ ነበር ፡፡ “

በዘኁልቁ 34 ሙሴ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ያወጣባቸውን 42 የተለያዩ ደረጃዎች እንዲፅፍ ታዘዘ ፡፡ በእያንዳንዱ መንገድ እርምጃ እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ነበር ፤ በዘኁ 34 መጨረሻ ላይ ወደ ተስፋይቱ ምድር ስለሚጎአዙ ነበር ፡፡

ትምህርት

ዘኁልቁ(35፡ 1-5)፡ በሞዓብ ሜዳ ላይ እግዚአብሄር ለሙሴ ተናገረው(ቁጥር 1) ሙሴንም እስራኤላዊያንን ለሌዋዊያን ከርስታቸው ከተሞችን እና ማሳማሪያዎችን እንዲሰጡአቸው እንዲያዝዝ ነገረው(ቁጥር 2) ፤ ለሌዋዊያን ከተሞቹ በውስጣቸው የሚኖሩባቸው እና ለመንጎቻቸው እና ለከብቶቻቸው ማሰማሪያ ይሆናሉ (ቁጥር 3) ፡፡ የከተማዎቹ ማሰማሪያ ምድሮች በሁሉም በኩል ከ500 ያርድ ይሰፋል (ቁጥር 4) ፤ እነዚህን ድንበሮች ለመወሰን 1000 ያርድ ከከተማዋ ውጭ ወደ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ከከተማዋ መሀል ይለካል (ቁጥር 5) ፡፡

ዘኁልቁ(35፡ 6-8)፡ የተሰጡት ከተሞች ስድስት የመማፀኛ ከተሞችን በተጨማሪም ሌሎች 42 ከተሞችን የሚያካትት ይሆናል(ቁጥር 6) ፤ ሌዋዊያን በጠቅላላው ማሰማሪያዎቹን ምድር ጨምሮ 48 ከተሞች ተሰጥቶአቸው ነበር (ቁጥር 7) ፡፡ ኢያ(20፡ 7-8) እነዚህን ስድስት የመማፀኛ ከተሞችን ይጠቅሳል ፤ በእነዚህ ስድስት የመማፀኛ ከተሞች ውስጥ የሆነን ሰው ገድለው የነበሩ ሰዎች ደህና(ሰላም) ይሆኑበታል ፡፡ በአሁን ጊዜ በእስራኤል ማንም ምንም ምድር አልያዙም ፤ ሁሉም ከመንግስት የተከራዩት ነው ፡፡ ሌዋዊያን በተስፋይቱ ምድር በመላው ተበትነው ነበር እያንዳንዱም ነገድ አራት ከተሞችን ይሰጥ ነበር ፡፡ ዘጸ (19፡ 5-6) የገለፀው “ አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ እናንተም የካህናት መንግስት የተቀደሰም ህዝብ ትሆኑልኛላችሁ ፡፡ ለእስራኤልም ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው ፡፡” (ዮሐ 4፡ 21-23፡ ኢየሱስ የሚለው የትም ላይ ብትሆኑ ቅዱስ ናችሁ ፡፡) ጥቂት ማብራሪያዎች ጥቂቶች የሌዋዊያን ከተሞች በእውነቱ ትንሽ ሰፈሮች እንደነበሩ ወይም ጥቂት ትንሽ ቤቶች ተሰብሰበው አብረው የጠሰሩ እንደነበሩ ያመለክታሉ፡፡ እያንዳንዳቸው ነገዶች በመጠናቸው መሰረት የተወሰነ የከተሞች ቁጥር ይሰጣሉ(ቁጥር 8) ፡፡

ዘኁልቁ(35፡ 9-15)፡ እግዚአብሄር ሙሴን ለእስራኤላዊያን ወደ ከነዓን ምድር በተሸገሩ ጊዜ እንደ መማፀኛ ከተማ የሚያገለግሉ ከተሞችን እንዲሰይሙ እንዲገልፅላቸው ነገረው ፡፡ አንድ ሰው ሳያስበው የሆነን ሰው ቢገድል ለደህንነቱ የሚሸሽበት ቦታ ነበር (ቁጥር 9-11) ፤ እነዚህ የተሰየሙት ከተሞች ከበቀለተኛ መሸሸጊያ ቦታን ይሰጣሉ ስለዚህ ገዳይ በፍርድ ፊት እስኪቆም ድረስ የሚቀጣ አይሆንም (ቁጥር 12) ፡፡ እስራኤላዊያን፣ የሌላ አገር ዜጋ እና በግዚያዊነት የተቀመጡ ሰዎች ሳያስቡ የገደሉ ሊሄዱበት የሚችሉት(ቁጥር 15) እስራኤላዊያን ስድስት ከተሞችን ሰዎስቱ ከዮርዳኖስ ማዶ ሰዎስቱን ደግሞ በከነዓን ይመርጣሉ (ቁጥር 13-14) ፡፡

ዘኁልቁ(35፡ 16-21)፡ በቁጥር 16-21 የሆነን ሰው የገደለን ሰው እንዴት መዳኘት እንዳለባቸው ተጨማሪ ትዕዛዞች ተሰጡዓቸው ፡፡ አንድ ሰው የብረት ዕቃ በመያዝ ሌላውን ሰው እስኪሞት ቢመታው ገዳይ ይሆናል በሞትም ይቀጣል (ዘፍ 4፡ 15; 9፡ 5) ፤ አንድ ሰው ድንጋይ በመጠቀም ቢመታው ለአንድ ሰው መሞት ምክንያት ቢሆን እሱም ገዳይ እንደሆነ ይፈረድበታል ይገደላልም (ቁጥር 17) ፤ አንድ ሰው የእንጨት እቃ በመጠቀም ቢመታው ያም ለአንድ ሰው ለሞት ምክንያት ቢሆን ገዳይ እንደሆነ ይፈረደበታል ይገደላልም (ቁጥር 18) ፡፡ በእያንዳንዱ ኬዝ የተገደለው ሰው ዘመድ ተበቃይ ይሆናል ገዳዩንም ይገድላል (ቁጥር 19) ፡፡ ማንኛውም ሰው በጥላቻ አንድ ሰው ቢገፋ ወይም በተንኮል ፍላጎት በእርሱ ላይ ቢወረውርበት እና ቢሞት የገደለው ይገደል ምክንያቱም ጋዳይ እንደነበር ስለተፈረደበት (ቁጥር 20-21) ፡፡

ዘኁልቁ(35፡ 22-25)፡ አንድ ሰው በአጋጣሚ(በድንገት) አንድ ሰው ቢገፋው ወይም ከተንኮል ፍላጎት ውጪ እቃ ቢወረውርበት እና ጠላቱ ካልነበር እና ሰውየው ቢሞት ጉባኤው ጥፋቱን ይወስናል ወይም (ቁጥር 22-24) በእነዚህ ትዕዛዞች መሰረት ነፃ ይሆናል ፡፡ ጉባኤው ነፃነት ያገኙትን ከተበቃዮች እጆች ያከላከላሉ(ይጠብቃሉ) ፤ ጉባኤ ወደ መማፀኛ ከተማ እንዲሸሽ ይመልሱታል ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቀመጣል ፤ ከመማፀኛ ከተማ የሆኑ ሰዎች በታላቁ ካህን ሞት ነፃ ነበር ፤ ኮንስታብል የገለፀው “ በስህተት የገደሉትን ለኃጢዓታቸው የታላቁ ካህን ሞት ያስተሰረያል…..ልክ እንደተደረገው የእንስሳት መስዋዕት ፡፡”

መዝጊያ

ምዕራፍ 35 መጨረሻ ላይ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ቀድመው እንዲለቀቁ አስተሰሪይ መስዋዕታቸውን መግዛት እንደማይችሉ ገለፀላቸው ፤ ዋይርስቤ የሚለው “ ጥፋተኛ ኃጢዓተኞች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት መሸሽ ይችላሉም ከእግዚአብሄርም ፍርድ መማፀኛ ይፈልጋሉ ፤ ኢየሱስ ሁሌም የሚኖር ታላቅ ካህን ነው፣ ድነቱም አስከዘላለም አስተማማኝ ነው ፤ ለእነርሱ መማለድን ለማድረግ ሁል ጊዜ ይኖራል ፡፡”

ዕብ(6፡ 18)፡ “ እግዚአብሄር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ በመሓላ በመካከል ገባ ፡፡”

ዕብ( 7፡ 25)፡ “ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሄር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል ፡፡”

ሮሜ(8፡ 1)፡ “ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም ፡፡”

በመማፀኛ ከተሞች ውስጥ አንመለከትም ፤ በክርስቶስ ነፃ ወጥተናል(ሆነናል) ፡፡

  1. Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study) Notes: Numbers, p. 190; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/numbers.pdf.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook Publishers, 2001), p. 369.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር እንደገና ለሌዋዊያን እስራኤላዊያን የምድሪቱን ሀብት በወሰዱ ጊዜ እንደሚሰጡዓቸው እርግጠኛ አደረጋቸው (35፡ 2-3) ፤ ይህንን ለምን አደረገ ? (ዘኁ 18፡ 21, 23-24፣ ኢያ 13፡ 14, 33)
  2. የመማፀኛ ከተሞች ምንድን ነበሩ(ዘኁ 35፡ 9-12) ? በእነዚህ መማፀኛ ከተሞች ውስጥ ገድሎ የነበረው አንድ ሰው ለምን ያክል ጊዜ ደህና መሆን ይችላል (ዘኁ 35፡ 12፣ ዘዳ 19፡ 11-12) ? የመግደል ጥፋተኝነት ከተገኘበት ምንድን ይደረጋል ? (ዘኁ 35፡ 16-18)
  3. የመግደል ጥፋተኝነት የተገኘበትን ሰው የሚገድለው ማን ነበር ? (ዘኁ 35፡ 19-21)
  4. አንድን ሰው በድንገት(ሳያስበው) የገደለ ከመማፀኛ ከተማ ሲወጣ ምንድን አደጋ ይቀበላል ? (ዘኁ 35፡ 26-28)
  5. “ በስህተት ሰው የገደለው” በመማፀኛ ከተማ ውስጥ የሚኖረው በማን ሞት ወደ ውርስ ምድሩ መመለስ ይችላል (ዘኁ 35፡ 28) ? ይህ እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ? (ዮሐ 6፡ 37፣ ዕብ 6፡ 18, 7፡ 23-25)
  6. የተወረሰው ምድር ተካፍሎት በነበረው ነገድ ውስጥ እንዲቆይ ያስፈልገዋል ስለሆነም የአባታቸውን ምድር የወረሱት ሴት ልጆች ምንድን እንዲያደርጉ ታዘዙ ? (ዘኁ 36፡ 6-8) በአሁኑ ጊዜ ወደ እኛ ይህ ይተገበራል አዎ ከሆነ እንዴት ? (1ቆሮ 7፡ 39፣ 2ቆሮ 6፡ 14)
  7. በዘኁ 35-36 በጥናት ወይም በትምህርት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 36:5-6

“So Moses commanded the Israelites at the word of the LORD, ‘What the tribe of Joseph’s descendants says is right. This is what the LORD has commanded concerning Zelophehad’s daughters...’”

ለሌዋዊያን ከተሞች

ኦሪት ዘኁልቁ 35-36 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

በኦሪት ዘኁልቁ መፅሃፍ መጨረሻ ላይ ከምናሴ ዘር የሆኑ መሪዎች ወደ ሙሴ ተመልሰዉ፥ ስለሰለጰዓድን ልጆች የርስት ጉዳይ የተወሰነዉ ዉሳኔ ላይ ጥያቄ አነሱ። ሙሴም በእግዚአብሔር የታዘዘዉን እንዳደመጠ፥ መሪዎችም ልክ እንደሆኑ አረጋገጠ። ከዚያም ሙሴ ስለሰለጰዓድን ልጆች፥ ስለርስታቸዉ፥ ከማን ጋራ መጋባት እንዳለባቸዉ ትዕዛዝ አስተላለፈ። የመለሰዉም፦ በትህትና ከመመለሱ በፊት ከእግዚአብሔር ጥበብን ጠይቆ ነዉ!

መጀምርያ ከሰጣችሁት ዉጪ ሌላ የተለየ መልስ ፈልጎ እንደገና የተጠየቃችሁብት ሁኔታ ተፈጥሮ ያዉቃል? ሌላ ሰው ትክክል እንደሆነ መናገር ትልቅ ትህትናን ይጠይቃል፥ ምክንያቱም አንድምታዉ አንተ ስህተት ነበርክ ማለት ነዉ! ማንም መሳሳትን አይወድም። ነገር ግን፥ እግዚአብሔር አለትህ እና ፅኑ መሠረትህ ሲሆን ትክክል መሆን እና መሳሳት አይረብሽህም! ክርስቶስን ፅኑ መሠረትህ በምታደርግበት ጊዜ፥ በትሁት ልብ ለጌታና ለመንገዱ ሁሉ እዉቅና ስትሰጥ፥ በምንም አትነቃነቅም። ዛሬ፥ ጌታ ዓለትህ እንዲሆን ፍቀድ፥ መንገድህም አይነቃነቅም!

"ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ የዮሴፍ ልጆች ነገድ በእውነት ተናገሩ። እግዚአብሔር ስለ ሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ የወደዱትን ያግቡ ነገር ግን ከአባታቸው ነገድ ብቻ ያግቡ።"

ኦሪት ዘኁልቁ 36:5-6

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 16:8፦ "ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም።"
  • መዝሙረ ዳዊት 62:6-8፦ "እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም። መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው። የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ፥ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው።"
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 10:3-4፦ "ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ፥ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 94