Journey to the Promised Land
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በአራቱ የህግ መፅሀፍት ውስጥ አልፈናል በሙሴ ተፅፈው ከነበረው ዘዳግም አምስተኛው እና የመጨረሻው ነው ፡፡ ዘዳግም ማለት “ሁለተኛ ህግ” ማለት ነው ፡፡ ዘዳ(17፡ 18) የሚለው “ በመንግስቱም ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ ከሌዋዉያን ካህናት ወስዶ ይህን ህግ ለራሱ በመፅሀፍ ይፃፍ ፡፡” ሙሴ እንደ ራሱ ፈቃድ ወይም በማረፉ የህግ መፀሀፉን ሁለተኛ ፅሁፍ ለመፃፍ የተወሰነ(የታመነ) ነበር ፤ ከእነርሱ ጋር አይሄድም ነበር ምክንያቱም በንደት አለቱን ስለመታ ፤ ሙሴ ደግሞ ደግሞ እግዚአብሄር ከእስራኤላዊያን ጋር እንደነበር፣ አሁንም ከእነርሱ ጋር እንደ ነበር እና ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ስዕሉን ስሎአል ፡፡
በእኛ ስዕል ለእያንዳንዱ መፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ አንድ ቃል አለን፡ ለዘፍጥርት - ዘር፣ ለዘጸዓት - ነፃ አዉጪ፣ ለዘሌዋዉያን - አስተሰሪይ እና ለዘኁልቁ - አለት ፤ ለዘዳግም ቃሉ ነብይ ነው ፡፡ ዘዳ(18፡ 15) የሚለው “ አምላክህ እግዚአብሄር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል ፤ እርሱንም ታደምጣለህ ፡፡”
ሙሴ ያወራለት የነበረው ያ ነቢይ ኢየሱስ ነው ፤ “ ቤትን የሚያዘጋጀው ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው መጠን እንዲሁ እርሱ ከሙሴ ይልቅ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተቆጥሮአልና ፡፡ እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቶአልና ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሄር ነው ፡፡ ሙሴስ በኃላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው ፤ እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን”(ዕብ 3፡ 3-6) ፡፡ ኢየሱስ በእያንዳንዱ የህግ መፅሀፍት ውስጥ፣ ከስምንት ትንቢቶች እና ከዘዳግም መፅሀፍ ውስጥ 16 ጊዜ ተጠቅሶአል ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም(1፡ 6-46)፡ የዚህ ምዕራፍ ጅማሬ እግዚአብሄር እንዴት የሰጠውን ተስፋ ያከብር እንደ ነበር እና እነዚህን ነገሮች ለማሳዎቅ መጀመሪያ መሪነትን እንደሚያመጣ ይገልፃል(ቁጥር 6-18) ፡፡ (በቁጥር 19-46) በቃዴስ - በበርኔ ላይ የእስራኤላዊያንን አለመታዘዝ ይሸፍናል ፡፡
ዘዳግም 2፡ በዮርዳኖስ ወንዝ በምስራቅ በኩል ከርዳኖስ ባሻገር አካባቢ ውስጥ እስራኤላዊያን ተጎአዙ ፡፡
ዘዳግም(3፡ 1-7)፡ በጉዞ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን እንደገና በመናገር ሙሴ የመጀመሪያ ስብከቱን ለቀቀ(ተናገረ) ፡፡ ወደ ባሳን መንገድ ወጣን የባሳን ንጉስ ዖግም በሙሉ ጦሩ በኛ ላይ መጡ (ቁጥር 1) ፤ እግዚአብሄር ንጉስ ዖግን እንዳይፈሩት ቀድሞኑ ተናግሮአቸው ነበር ምክንያቱም ቀዶሞውን ለእስራኤል ሰጥቶት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን ንጉስ ኦግ ላይ በሰዎን ንጉስ ላይ አድርገውት እንደነበረው ተመሳሳይ እንዲያደርጉበት ነገራቸው (ቁጥር 2) ፤ እግዚአብሄር የባሳንን ነጉስ ዖግና እና ጠቅላላ ጦሩን ለእስራኤላዊያን አሳልፎ ሰጣቸው የሚቀርም አልነበረም (ቁጥር 6) ፤ ከተሞቹ ሁሉም በአንድ ጊዜ ተያዙ - በጠቅላላ 60 ከተሞች(ቁጥር 4) ፡፡ ትልቅ ግንቦች ያሉት ምሽግ ፣ በሮች እና መዝጊያዎች እና ብዙ ቁጥር የገጠር አካባቢዎች ቢኖሩም ሁሉም ከተሞች ሙሉ በሙሉ ከወንዶቹ ጋር፣ ሴቶቹ እና ልጆቹ ጋር ጠፍተው ነበር በሰዎን ተደርጎ አንደነበረው (ቁጥር 6) ፡፡ ባሳን በዛፎኦቾአ (ኢሳ 2፡ 13) እና በከብቶቾአ ታዋቂ ነበረች(ኢሳ 32፡ 14) ፤ ሁሉም ለዘረፋ ተዳርገው ነበር (ቁጥር 7) ፡፡ዋረን ዋይስርቤ በዐግ እና በሰዎን ላይ የሆነውን ድል “ ከነዓን በሚደርሱ ጊዜ ለሚያደርጉት ጦርነት ዝግጅት” እንደነበር ገልፆታል ፡፡
ዘዳግም(3፡ 8-11)፡ ከዚያም እስራኤላዊያን ከዮርዳኖስ ማዶ ምድር ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ ወሰዱ (ቁጥር 8-10) ፡፡ የሜዳው ሁሉም ከተሞች ገለዓድ፣ ባሳን፣ ሰልካና ኤድራይ ነበሩ (ቁጥር 10) ፡፡ “ ከራፋይም ወገን የባሳን ንጉስ አግ ብቻውን ቀርቶ ነበር ፤ እነሆ አልጋው የብረት አልጋ ነበር ፤ ከአሞናዊያን በራባት ውስጥ ነው ? ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበር “(ቁጥር 11) ፡፡
ዘዳግም(3፡ 12-20)፡ እስራኤላዊያን የምድሪቱን ንብረት ወሰዱ፣ ሰፈሩባትም እናም ለሮቤላዊያን፣ ለጋድያዊያን እና ለከብቶቻቸው ምድሪቱን ለፈለጉዓት (ቁጥር 19) ለምናሴያዊያን ግማሽ ነገድ ሰጡዓት (ቁጥር 12-13) ፡፡ የምናሴ ዘር ኢያዕር ከእርሱ ቦኃላ(ከተሰጠው ቦኃላ) ባሳንን የኢያር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው (ቁጥር 14) ፡፡ ሙሴ እንዲሻገሩ እና ለምድራቸው ከእስራኤላዊያን ዉጊያ እንዲያግዙ እና መንገድ እንዲመሩ ነገራቸው (ቁጥር 18) ፡
ዘዳ(12፡ 10)፡ “ ዮርዳኖስን ግን በተሻገራችሁ ጊዜ አምላካችሁም እግዚአብሄር በሚያወርሳችሁ ምድር በተቀመጣችሁ ጊዜ ያለ ፍርሀትም እንድትኖሩ ከከበቡዓችሁ ጠላቶች ሁሉ……” ማሸነፍ ስለነበር እረፍት ይፈልጋሉ ፡፡
ዘዳ(25፡ 19)፡ “ ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሄር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ከሚከብቡህ ጠላቶችህ ሁሉ አምላክህ እግዚአብሄር ባሳረፈህ ጊዜ…..”
ዘዳግም(3፡ 21-29)፡ ዋይርስቤ የገለፀው ለብዙ ጦርነት እስራኤላዊያን ተዘጋጁ፣ ወደ ምድሪቱ በመስፈር ጀመሩ ከዚያም በተጨማሪም ከሙሴ ወደ እያሱ መሪነትን ማስተላለፍ ጀመሩ (ቁጥር 21-22) ፡፡ እግዚአብሄር አድርጎት የነበረውን ሁሉንም ነገር ኢያሱ አይቶ ነበር እናም ወደ ሚገቡበት ሁሉም መንግስት እግዚአብሄር ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግ ያውቃል ፡፡
ዘዳ(27፡ 18)፡ “ እግዚአብሄርም ሙሴን አለው መንፈስ ያለበትን ሰው የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን በላዩ ጫንበት ፡፡”
በዘጸ 33 ኢያሱ እንዴት ለሙሴ አገልጋይ እንደነበር አይተናል ፤ ሁሉንም የሚቻለውን መንገድ ለምዶ ነበር፣ ባለቤትነት ተላልፎለት ነበር እና አሁን ለማስቀጠል ዝግጁ ነበር ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄርን ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲሻገር እንዲፈቅድለት ለመነ ነገር ግን እግዚአብሄር በሙሴ እንደተናደደ መለሰለት ምክንያቱም ስላልሰማው ፡፡ በቁጥር 26 መሰረት እግዚአብሄር ሙሴን “ስለዚህ ነገር እኔን እንዳታናግረኝ “ አለው ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን ከፈስጋ ተራራ ጫፍ ላይ በመሆን ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲመለከት ፈቀደለት (ቁጥር 27) ፤ ሙሴ ተስፋይቱን ምድር ከተመለከተ ቦኃላ ኢያሱን እንዲወክል(እንዲሾም) ታዞ ነበር (ቁጥር 28) ፡፡
መዝጊያ
ሙሴ ነብዩ እየመጣ እንደ ነበር በመናገር ህዝቡን አዘጋጀ በተጨማሪም ተግባራትን(ነገሮችን) እንዲመራ ኢያሱንም አዘጋጀ ፡፡ በአድስ ኪዳን መጥምቁ ዮሐንስ መጥቶ ስለነበረው ከእርሱ ለሚበልጥ መንገድን እንዳዘጋጀ አስባለሁ ፤ ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው “የቀጠልንበት” ማሸጋገር ይመስል ነበር ፡፡
ዘዳግም 1 ስለ እግዚአብሄር እንዴት አድርጎ ተስፋውን እንዳከበረ በመከለስ ይጀምራል ፤ ከዚያም በቃዴስ በርኔ የህዝቡ አመፅ ነበር ምክንያቱም በእግዚአብሄር ስላልታመኑ ፡፡ ዘዳግም 2 የዮርዳኖስ ማዶ በኩል ያለውን ጉዞ እናእግዚአብሄር እንዴት በሰዎን እና በአግ ላይ እስራኤላዊያንን ድል እንደሰጣቸው ተመልክተናል ፡፡ በመጨረሻም ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባታቸው በፊት በነበሩት ምድር ነዋሪዎች ጋር የነበሩትን ጦርነቶች አይተናል ፤ በመቀጠልም ሙሴ መሪነቱን ለኢያሱ መለሰ ግን እግዚአብሄር ተስፋይቱን ምድር እንዲያ ፈቀደለት ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 379.
ጥያቄዎች
-
በዘዳግም በመጀመሪያው ምዕራፍ ይህን ታረክ ሙሴ ለማን ነበር የተናገረው ?
-
በዘዳግም (3፡ 6-7) እስራኤላዊያን ማንን አጠፉ ? ምንድን ጠበቁ(አስቀሩ) ?
-
በዘዳግም(3፡ 25-26) ሙሴ ዮርዳኖስን እንዲሻገር እንዲፈቅድለት እና ተስፋይቱን ምድር እንዲያ እግዚአብሄርን ጠየቀ ፤ እግዚአብሄር “አይሆንም “ እናም ደግመህ እንዳጠይቀኝ አለው ፡፡ ሙሴ አይሆንም የተባለው ለምን ነበር ? (ዘኁ 20፡ 8-12)
-
ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደ ማይሻገር ባልተቀበለው ጊዜ በቁጥር 27-28 ምንድን እንዲያደርግ እግዚአብሄር ነገረው ? ለሙሴ ይህ የመጨረሻው በረከት ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልሆነም ?
-
በዘዳግም 1-3 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 3:23, 25
“At that time I begged the LORD...‘Please let me cross over and see the beautiful land on the other side of the Jordan, that good hill country and Lebanon.’”
በኦሪት ዘዳግም የመጀመርያ ምዕራፎች ዉስጥ ለህዝቡ ሙሴ ወደፊት የሚጠብቃቸዉን ነገር አነበበላቸዉ። አዲሱን ትዉልድ ለተስፋይቲ ምድር በሚያዘጋጅበት ጊዜ፥ አሁን እስካሉበት የህይወት ምዕራፍ ድረስ የተፈጸሙትን ክንዋኔዎች አስታወሳቸዉ። ይህንን በሚያደርግበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር እርሱን ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳይገባ የወሰነዉን ዉሳኔ እንደገና እንዲመረምርለት እንዴት እንደተማፀነዉ አስታወሰ። እግዚአብሔር ግን አሁንም አይሆንም አለዉ! ቢሆንም ግን እግዚአብሔር ልቡን መለስ አድርጎ፥ ምድሪቱን ወደ ጲስጋህ ተራራ ጫፍ ወጥቶ በዓይኑ በሩቅ እንዲመለከታት አድርጎታል።
እግዚአብሔር ለህይወትህ ያለዉን ዉሳኔ እንደገና እንዲመረምር ፈልገህ ታዉቃለህን? "ወደ ቀድሞ ቤቴ መመለስ እችላለሁ?" "ልጄን እንደገና እባክህ ጤነኛ ታደረገዋለህ?" "እባክህ ስራዬን እንደገና ማግኘት እችላለሁ?" የምትፈልገዉን እና ለህይወቴ በጣም ጥሩ የምትለዉን አለማግኘት ከባድ ነገር ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን ለአንተ አላማ እንደለዉና ሁሉንም ነገር አያይዞ ለበጎ እንደሚለዉጠዉ የተስፋ ቃል ገብቶልሃል። ለጊዜዉ ምንም ዓይነት ስሜት የማይሰጥ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር የሚጎዳህን ሳይሆን የወደፊት እድል እና ተስፋን እንደሚሰጥህ በማመን በእርሱ ማረፍን ምረጥ!
"በዚያም ዘመን እኔ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ለመንሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህን የጸናችውንም እጅህን ለእኔ ለባሪያህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይና በምድርም እንደ ሥራህ እንደ ኃይልህም ይሠራ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው? እኔ ልሻገር በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።"
ኦሪት ዘዳግም 3:23-25
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ትንቢተ ኢሳያስ 55:8፦ "አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡"
- ትንቢተ ኤርሚያስ 29:11፦ "ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28፦ "እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 95
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።