Instructions Before Entering the Promised Land
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 4-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሙሴ ስብከቱን(ትምህርት) በዘዳ(1-3) ጀምሮአል ፡፡ ሙሴ አልፈውት የነበሩትን ጦርነቶች በማስታወስ እና ኢያሱ እንደሚመራቸው በመናገር ለእስራኤል ልጆች በቀጥታ ነገራቸው ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም 4፡ ይህ ምዕራፍ እንደ ጥበበኛ ሰው እንዴት መኖር እንዳለባቸው(ቁጥር 1-40) ትዓዛዝ ይሰጣል፣ የመማፀኛ ከተሞች ምንድን እንደነበሩና ለማን እንደነበሩ(ቁጥር 41-43) እና ሙሴ እንደ ገና በትዕዛዞቹ ላይ ሄደ ምክንያቱም ነገሮችን የሚረሱ ሰዎች ነበሩ (ቁጥር 44-49) ፡፡
ዘዳግም 5፡ ይህ ምዕራፍ የእግዚአብሄርን ኪዳን ከህዝቡ ጋር ስላደረገው(ቁጥር 1-5)፣ ስለ አስዕርቱ ትዕዛዝ(ቁጥር 6-22) እና ሙሴ በእስራኤላዊያን እና በእግዚአብሄር መሀከል መሀከለኛ እንደ ነበር(ቁጥር 23-33) መረጃ ይሰጣል ፡፡
ዘዳግም 6 ለእስራኤላዊያን እና ለአይሁዳ ባህል ዛሬም አስፈላጊ ነው ፡፡ ዋይርስቤ የገለፀው “ እግዚአብሄር ህጉን ሰዎችን በየግላቸው ለመምራት ብቻ ሳይሆን እንደ ህዝብ በአንድ ላይ ለመምራት ሰጠ ፡፡” የተሰጡ 613 ህጎች ነበሩ የኃይማኖት መሪዎችም ህጎቹን በመውሰድ ባህላቸውን በመጨመር ሊታገሱዓቸው የማይቻሉ እንደሆኑ አመለከቱ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እስራኤል አስከፊ ነው ምክንያቱም ህዝቡ ሁሉንም ህጎች እና ደንቦች ሊኖርባቸው አልቻለም ፡፡ ሐዋ(15፡ 10) በአይሁድ ላይ ስለ ህግ ቀንበር ያወራል ፤ ገላ(5፡ 1) ክርስቶስ ከዚያ ሸክም ነፃ እንዳወጣን ይናገራል; መዝ 119፡ 14፣ 45፣ 103፣ 105 ደግሞ በህግ ስለ ሀብት እና ስለ ጣፋጭነት ይናገራሉ ፤ በህግም ውስጥ ነፃነት እንዳለ ፡፡
ዘዳግም(6፡ 1-3)፡ ሙሴ የተናገረው ከእግዚአብሄር የነበረው ትምህርት እስራኤላዊያን ተስፋይቱ ምድር ውስጥ እንዲከተሉት ነበር (ቁጥር 1) ፤ አምላካቸውን እግዚአብሄርን ይፈራሉ ስለዚህ ልጆቻቸው እና የልጅ ልጆቻቸው ረጅም እድሜ ይኖራቸዋል (ቁጥር 2) ፡፡ ሙሴ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በጥንቃቄ እንዲሰሙ እና እንዲከተሉ ነገራቸው ይህ ከሆነ በማርና በወተት ምድር ይበለፅጋሉም ይበዛሉም ፡፡
ዘዳ(4፡ 40)፡ “ ለአንተ ከአንተም ቦኃላ ለልጆችህ መልካም ይሆን ዘንድ አምላክህም እግዚአብሄር ለዘላለም በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝዝህን ስርዓቱንና ትዕዛዙን ጠብቅ፡፡”
ዘዳ(18፡ 5)፡ “ እርሱ ከልጆቹ ጋር ተነስቶ በእግዚአብሄር ስም ለዘላለም ያገለግል ዘንድ አምላክህ እግዚአብሄር ከነገዶች ሁሉ ስለ መረጠው ነው ፡፡” እስራኤላዊያን ከእግዚአብሄር ፈቃድ ዉጮ የሆነ
ነገር ለማድረግ ከመረጡ ህይወታቸውን ሊያሳጥረው ይችላል ፡፡
ዘዳግም(6፡ 4-6)፡ እነዚህ ቁጥሮች ሴማ(ዋና የሆኑ) ተብለው ይጠራሉም “ የእግዚአብሄር የአምላካቸው “ መምሪያዎች ናቸው ፡፡ እስራኤላዊያን አምላካቸውን እግዚአብሄርን በፍፁም ልባቸው፣ በፍፁም ነፍሳቸው እና በፍፁም ኃይላቸው እንዲወዱ ታዝዘዋል ፤ ኢየሱስ ይህን በማቴ (22፡ 37) ጠቅሶታል (በተጨማሪም በማርቆስ 12 እና ሉቃስ 10 ይገኛል) ፡፡ ዘዳ(11፡ 1)፡ “ እንግዲህ አምላክህን እግዚአብሄርን ውደድ ሕጉንም ስርዓቱንም ፍርዱንም ትዕዛዙንም ሁልጊዜ ጠብቅ ፡፡” እነዚህ በልባቸው የሚጠብቁዓቸው ቃሎች ነበሩ(ዘዳ 11፡ 18; መዝ 37፡ 31; 40፡ 8; ኤር 31፡ 33) ፡፡
ቆላ(3፡ 16)፡ “ የእግዚአብሄር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ ፡፡ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገስፁ ፡፡ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሄር ዘምሩ ፡፡”
አብዛኛው ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል ማካፈል ይፈራሉ ምክንያቱም ምን እንደሚናገሩ ስለሚፈሩ ፤ የእግዚአብሄር ቃል በእኛ ውስጥ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ በኩል ይናገራል ፤ ስለ ምን እንደምንናገር አንጨነቅም ፡፡
ዘዳግም(6፡ 7-9)፡ ሙሴ እስራኤላዊያንን ለልጆቻቸው እነዚህን ትዕዛዞች እንዲደግሙላቸው እና በቤታቸው በሚቀመጡ ጊዜ፣ በመንገድ በሚጎአዙ ጊዜ፣ በማለዳ በሚነቁ ጊዜ እና ማታ ላይ በሚያርፉ ጊዜ ስለ ትእዛዞቹ እንዲያወሩ አዘዛቸው ፤ በተጨማሪም ለመታዘዛቸው እንደ ሚታይ ምልክት በእጃቸው እና በግንባራቸው እንዲይዙት(እንዲያጣብቁት) ነገራቸው ፡፡ እነዚህ ምልክቶች እንደ ብራና አይነት ናቸው ይህም የመፅሀፍ ትንሽ ብራናዎች የያዙ ናቸው ፡፡ ሲፀልዩ ይለብሱታል ፤ አሁንም እነዚህን አይሁዶች ይለብሱታል ፡፡
በተጨማሪም ሙሴ በቤቶቻቸው ቆአሚዎች እና በሮች ላይ ሙዛህ (ኃይማኖታዊ ፅሁፍ) ተብሎ የሚጠራውን በበሮቹ ቆአሚዎች ላይ ይቀመጥ የነበረውን(የሚቀመጠውን) ትንሽ እቃ ላይ ትዕዛዞችን እንዲፅፉ ነገራቸው ፡፡ በሙዛህ ውስጥ ትንሽ ብራና ዘዳ (6፡ 4-9፣ 11፣ 13፣ 21) እና ሻዳይ የሚለው የእግዚአብሄር ስም የያዘ ነው ፡፡ የሚያበሳጨው እቃው በልብ ውስጥ ካለው በላይ ጠቃሚ በሆነ ጊዜ የሴም ሀሳብ(ዋና ሀሳቡ) ባጠቃላይ ይሳታል ፡፡
ዘዳግም(6፡ 10-19)፡ ሙሴ ህዝቡን እግዚአብሄር ቃል ወደ ገባላቸው ምድር ሲሄዱ አምላካቸዉን መርሳት እንደሌለባቸውአሳሰባቸው ፡፡ እግዚአብሄርን መፍራት እና እርሱን ማምለክ ይኖረባቸዋል አምላካቸው ቀናተኛ አምላክ ስለሆነ ሌሎች አምላኮችን መከተል የለባቸው ፡፡ በማሳህ ላይ አድርገውት እንደነበረው አምላካቸውን እንዳይፈትኑ እና ሰጥቶአቸው የነበረውን ትዕዛዝ፣ ድንጋጌዎች እና ስርዓቶችን እንዲጠብቁ አሳሰባቸው ፡፡ ስለሆነም ህዝቡ በእግዚአብሄር እይታ ትክክሉ ምንድን ነው እና ጥሩውስ ምንድን ነው ብለው ያደርጋሉ በዚህም ለአባቶቻቸው ተስፋ ወደ ተገባችው ምድር መግባት ይችላሉ ጠላቶቻቸውንም ያጠፋሉ ፡፡
ዘዳግም(6፡ 20-25)፡ ሙሴ ህዝቡን ልጆቻቸው የድንጋጌዎቹን፣ የስርዓቶችን እና የትዕዛዞችን ትርጉም በጠየቁዓቸው ጊዜ በግብፅ ባሪያዎች እንደነበራችሁ እና በታላቅ ምልክት እና ድንቅ ፈርዖንንና ቤቱን ከመታ በኃላ በእግዚአብሄር እንደወጡ እንዲነግሩአቸው ነገራቸው ፡፡ በተጨማሪም ለልጆቻቸው ለአባቶቻቸው ሰጥቶአቸው ወደ ነበረው ምድር እግዚአብሄር እንዳመጣቸው እና ስርዓቶቹን እንዲከተሉ አዞአቸው እንደነበር እና እንዲፈሩት ይነግሩዓቸዋል ፡፡ በመጨረሻም እነዚህን ትዕዛዞች ከተከተሉ ፅድቅ የእነርሱ እንደሚሆን አሳሳባቸው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ይህን፡ “ ሙሴ ህግን በመጠበቅ ህዝቡን የስራ- ፅድቅን አላቀረበም ፤ ፅድቅ ከእግዚአብሄር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት እንደሆነ ነው ፤ እግዚአብሄር ይህን ግንኙነት ያነሳሳል ልጆቹም በፍቅር አገላለፅ ይመልሱለታል ፡፡” (ሮሜ 7፡ 10; ያዕ 2፡ 10; ሮሜ 10፡ 1-10; ገላ 3፡ 11-13) ፡፡
መዝጊያ
ከዚህ መልዕክት ዉጪ የሆነ ማንኛውንም ነገር ብታገኙ ከእምነት በፊት ፅድቅ ስለማይመጣ እንዲሆን ፍቀዱ ግን ከዛይልቅ እምነት ወደ ፅድቅ ይመራል ፡፡ ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመሄዳቸው በፊት እንዲከተሉት እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ሰጥቶአቸው በነበረው ትዕዛዞች ላይ ሄደ ፤ እግዚአብሄር ሰጥቶአቸው የነበረውን አስሩን ትዕዛዞች እና ከእነርሱ ጋር እግዚአብሄር ያደረገውን ኪዳን እንዲያስታዉሱ ነገራቸው ፡፡ በዘዳግም 6 ሙሴ እስራኤላዊያንን በልባቸው ላይ በመፃፍ የእግዚአብሄርን ትዕዛዞች እንዲጠብቁ አዘዛቸው ፡፡ አምላካቸው ቀናተኛ አምላክ እንደሆነ ያስታውሳሉ ፤ ለእነርሱም በግብፅ እግዚአብሄር ያደረገላቸውን ለልጆቻቸው ያሳስቡዓቸዋል ፡፡ የእግዚአብሄርን ትዕዛዞች ከተከተሉ ፅድቅ የእነርሱ ይሆናል ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 388.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 1999), p. 244.
ጥያቄዎች
-
በዘዳግም 4፡ 24 ሙሴ ህዝቡን አምላካቸው እግዚአብሄር የሚባላ እሳት ቀናተኛ አምላክ እንደሆነ ነገራቸው ፤ ምንድን እና ማን ለእግዚአብሄር ቅናት ይሆናል ?
-
ዘዳግም 4፡ 29 ስታነቡ እንዴት እንዲሰማችሁ አደረጋችሁ ? በዚህ መንገድ እግዚአብሄርን በመፈለግ እራሳችሁን ታያላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላያችሁም ?
-
የት ላይ በህግ (በኦሪት) እነዚህ በዘዳግም 5 የተዘረዘሩ ትዕዛዞች የሚመስል ታያላችሁ ?
-
በዘዳግም 6፡ 16 እስራኤላዊያን አምላካቸውን እግዚአብሄርን እንዳይፈታተኑት ተነገራቸው ይህ በማቴ(4፡ 7) እና ሉቃ(4፡ 12) የተጠቀሰ ነው ፡፡ እግዚአብሄርን መፈታተን ምንድን እነደሚመስል ምን ታስባላችሁ ?
-
በዘዳግም 4-6 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 6:4-9
“Listen, Israel. The LORD our God, the LORD is One. Love the LORD your God with all your heart, with all your soul, and with all your strength. These words that I am giving you today are to be in your heart. Repeat them to your children. Talk about them when you sit in your house and when you walk along the road, when you lie down and when you get up. Bind them as a sign on your hand and let them be a symbol on your forehead. Write them on the doorposts of your house and on your gate.”
ሙሴ፥ እስራኤላዉያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባታቸዉ በፊት በጣም ጠቃሚ የሆኑቱን ትዕዛዛት እንዲያስታዉሱ ሰጥቶአቸዋል። እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸዉ፣ ነፋሳቸዉና ኃይላቸዉ ሊወዱት ይገባቸዋል። እነዚህ ቁጥሮች የታላቁ ትዕዛዛት "ሸማሃንድ" በመባል ይታወቃሉ። በእግዚአብሄር የተሰጣቸዉ ቃሎች በልባቸዉ እንዲያኖሩት ነበር። አዎ፥ ለልጆቻችሁ አስተምሯቸዉ! አዎ፥ ስትመጡ እና ስትሄዱ ተነጋገሩበት! አዎ፥ እንደ አምባር እጃችሁ ላይ እና ግንባራችሁ ላይ እሰሯቸዉ። በቤታችሁ መቃን እና በር ላይ ፃፉአቸዉ! ነገር ግን በቅድምያ በልባችሁ ዉስጥ አስቀምጧቸዉ!
እንደ በክርስቶስ እንደሆንን ወንድም እና እህት፥ እግዚአብሔር ስለህግ እና ዉጫዊ ቁመና ሳይሆን በልብህ ከእርሱ ጋራ ስላለህ ህብረት ይገደዋል። በመጀመርያ ልብህን እና ለእግዚአብሔር ያለህን ፍቅር መርምር! ዉስጥህ ወይንም ልብህ በክርስቶስ ፍቅር ሲሞላ፥ የክርስቶስን ፍቅር በዉጩ መግለጥ ተፈጥሮአዊ ነዉ።
"እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤ አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።"
ኦሪት ዘዳግም 6:4-9
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መፅሃፈ ምሳሌ 4:3፦ "እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር።"
- መፅሃፈ ምሳሌ 21:2፦ "የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።"
- የሉቃስ ወንጌል 6:45፦ "በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 96
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።