The Pentateuch Deuteronomy

Remember What You Have Been Taught

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 7-9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 97 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዘዳግም ማለት “ ሁለተኛ ህግ” መለት ነው ፡፡ ዘዳ(17፡ 18)፡ “ በመንግስቱም ዙፋን በተቀመጠ ጊዜ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ ይህን ህግ ለራሱ በመፅሀፍ ይጻፍ ፡፡” ይህ አድስ ህግ አልነበረም; እንደገና እየተጠቀሰ የነበረ በቀድሞ አባቶቻቸው ቀድሞ የተነገረ ነበር ፡፡ ሙሴ ይህንን ትምህርት ለወጣት እስራኤላዊያን በሞዓብ ሜዳ ላይ ይሰብክ ነበር ፡፡ ዘዳግም 6 ይህ ህግ መጀመሪያ በእስራኤላዊያን ልብ ላይ እንደሚሆን ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

ዘዳግም 7፡ ይህ ምዕራፍ ስለ ተስፋይቱ ምድር ድል ማድረግ ተጨባጭ ትዕዛዝ ይሰጣል ፡፡

ዘዳግም(8፡ 1-10)፡ ሙሴ እስራኤላዊያንን የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ መከተል ጥቅሙን አሳሰባቸው በዚህም ይኖራሉም ይበዛሉም እናም የተስፋይቱን ምድር ንብረት ይወስዳሉ(ቁጥር 1) ፡፡ ከዚያም እስራኤላዊያንን በምድረበዳ የ40 አመት ጉዞ እግዚአብሄር አዉጡቶአቸው እንደነበር አሳሰባቸው (ቁጥር 2) ፤ ሙሴ “ አስታውሱ” የሚለውን ቃል በቀጣዮቹ ጥቂት ምዕራፎች በቀድሞ እግዚአብሄር ለእነርሱ አድርጎላቸውን የነበረውን የእስራኤላዊያንን መልስ ለማብራራት አራት ጊዜ ተጠቅሞታል ፡፡ ዋይርስቤ የሚያመለክተው “ በእኛ ላይ ክፉ እንዲመጣብን ሰይጣን ይስጎመጀናል ነገር ግን በእኛ ላይ የተሸለ ለማምጣት እግዚአብሄር ይፈትናል ፡፡ “

1ጴጥ(1፡ 6-7)፡ “ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኃል ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኃል ፡፡”

ያዕ(1፡ 3)፡ “ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ እወቁ ፡፡”

መዝ(17፡ 3)፡ “ ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጎበኘኸው ፤ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘህብኝም; የሰውን ስራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው ፡፡ “

መዝ(66፡ 10)፡ “ አቤቱ ፈትነኸኛልና ብርንም እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናልና ፡፡ “

ራዕ(2፡ 23)፡ “ ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኩላሊንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ስራችሁ እሰጣችኃለሁ ፡፡ “

ሙሴ እግዚአብሄር ህዝቡን እንዲራቡ በማድረግ ትሁታን አድርጎአቸው እንደነበር(ቁጥር 3) ከዚያም አባቶቻቸው እንካን የማያውቁትን መና እንደሰጣቸው ይጠቅሳል ፤ ይህ ሁሉ ህዝቡ በዳቦ ብቻ መኖር እንደማይቻል ያስተምራል(ማቴ 4፡ 4; ዮሐ 4፡ 34) ፡፡ ዋይስርቤ የተናገረው “ በእያንዳንዱ ማለዳ የምድረበዳ ጎዞአቸው እግዚአብሄር “ የመለዓክትን ምግብ “ ለአይሁድ ሰዎች ላከላቸው በሚያስፈልጋቸው በእግዚአብሄር መደገፍን እንዲማሩ ፡፡” እግዚአብሄር ትምህርቱን ለመቀበል የሚማርን መንፈስ ሰጥቶናል ፡፡

በቁጥር 4 ሙሴ እስራኤላዊያንን በጉዞው ልብሶቻቸውን እንዳላወለቁ እና እግሮቻቸው እንዳላበጡ አሳታወሳቸው(አሳሰባቸው) ፤ ዋይርስቤ ይህ ለእነርሱ የእግዚአብሄር ጥበቃ እንደ ነበር አሳይቶአል ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ጥበቃ በማቴ(6፡ 31-33) ገልፆዓል፡ “ እንግዲህ ምን እንበላለን ? ምንስ እንጠጣለን ? ምንስ እንለብሳለን ? ብላችሁ አትጨነቁ ይህንስ ሁሉ ይፈልጋሉ ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና፡፡ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሄርን መንግስት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኃል “ (መዝ 37; 1ጴጥ 5፡ 7; ነህ 9፡ 21) ፡፡

በቁጥር 5 ሙሴ እስራኤላዊያንን አባት ልጁን እንደሚያደርገው እግዚአብሄር ቀጥቶአቸው(አስተምሮአቸው) እንደ ነበር አሳሰባቸው ፤ ዋይሰርቤ የገለፀው “ ቅጣት የእግዚአብሄር ፍቅር ማስረጃ እና በእግዚአብሄር ቤተሰብ ውስጥ አባልነታችን ነው ፡፡ “ ቅጣት ማለት ምርጫ እንደሌለን የሚገልፅ ሲሆን ፤ ፈተና ምርጫ ይሰጠናል ፡፡ እግዚአብሄር ሲቀጣን ፍሬውን እናያለን ፡፡

ዕብ(12፡ 5-11)፡ “ እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር ፡፡ ልጄ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቅልል በሚገስፅህም ጊዜ አትድከም ፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኃል ፡፡ ለመቀጣት ታገሱ ፤ እግዚአብሄር እንደ ልጆች ያደርግላችኃልና ፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው ? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላቸሁም ፡፡ ከዚህም በላይ የቀጡን የስጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር ፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን ? እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣንል ፡፡ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ዳሩ ግን በኃላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል ፡፡”

ሙሴ በመቀጠል ለእስራኤላዊያን በጣም አስፈላጊ የነበሩት ትዕዛዞች ደገመላቸው ፤ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በመንገዱ በመሄድ እና እርሱን በመፍራት ይጠብቃሉ ፤ ከዚያም እግዚአብሄር በተስፋይቱ ምድር የተትረፈረፈ ይሰጣቸዋል (ቁጥር 6-7) ፡፡ ሙሴ እስራኤላዊያንን እግዚአብሄር በረከቱን በእነርሱ ላይ ያፈስ እንደነበር እና ማስታዎስ እንደሚጠበቅባቸው ነገገራቸው (ቁጥር 10-14) ፡፡

መዝጊያ

ዘዳግም 9 ስለ እስራኤል ታሪክ እና ወደፊት ነው - የእስራኤላዊያን የግል ፅድቅ እና አመፅ እና የሙሴ መማለድ ፡፡ ሙሴ የእግዚአብሄርን ትዓዛዞች እስራኤላዊያንን ማሳሰብ ቀጠለ ፤ አልፈውበት የነበረውን ሁሉንም እና እግዚአብሄር ነግሮአቸው የነበረውን ሁሉ እንዲያስታውሱ ይፈልጋል ፡፡ ደግሞ እና ደግሞ እንደገና ሙሴ እስራኤላዊያንን እግዚአብሄር አድርጎላቸው የነበረውን ሁሉ እንዲመለከቱ እና ትዕዛዙን እንዲጠብቁ አዘዛቸው ይህ ከሆነ ይባረካሉ ፡፡ እግዚአብሄር በምድረበዳ በ40 አመታት ጊዜ እስራኤላዊያንን ፈትኖአቸው፣ ተናግሮአቸው እና ቀጥቶአቸው ነበር ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 395.

  2. Wiersbe, p. 395.

  3. Wiersbe, p. 396.

  4. Wiersbe, p. 396.

ጥያቄዎች

  1. ለምንድን እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ከሌሎች ህዝቦች ጋር እንዳይጋቡ ነገራቸው ? ያለመታዘዝ ዉጤቱ ምንድን ነበር ? (ዘዳ 7፡ 3-4; 2ቆሮ 6፡ 14)
  2. በዘዳግም 7፡ 1-2 ሙሴ እስራኤላዊያን የሚያጠፉዓቸው ህዝቦች ከእነርሱ የሚበልጡ እና ጉልበታም እንደሆኑ ነገራቸው ፤ በማን ጥንካሬ ላይ ተደግፈው ነበር ? ከእናንተ የሚበልጥ ወይም ጉልበታም ነገር ቢገጥማችሁ እንዴት አፀፋ(ሪአክት) ታደርጋላቸሁ ? ጊዜውን አስታውሱ የእግዚአብሄር ጥንካሬ ከእናንተ በሚበልጥ ሁኔታ ውስጥ የተሸከማችሁን ጊዜ ፡፡ (2ቆሮ 12፡ 9)
  3. እንደ እግዚአብሄር ቅዱስ ህዝብ እስራኤል የተመረጠው ለምን ነበር (ዘዳ 7፡ 6-8) ? እግዚአብሄር እኛን ለምን መረጠን (ሮሜ 5፡ 8; 1ቆሮ 1፡ 9; 1ጴጥ 2፡ 9) ? በዚህ ልክ የእግዚአብሄርን ፍቅር ስታዉቁ እንዴት ይሰማችኃል ?
  4. እግዚአብሄር ለምን እስራኤላዊያንን ዝቅ አደረጋቸውስ ፈተናቸስ (ዘዳ 8፡ 2-5; ሮሜ 5፡ 3-5) ? እምነታችሁን ቢፈትን ወይም ቢቀጣችሁ እንዴት መልስ ትሰጣላችሁ ?
  5. ኢየሱስ በዘዳ(8፡ 3) የተፃፉትን ቃሎች በሰይጣን በተፈተነ ጊዜ ተናግሮአቸዋል (ማቴ 4፡ 4) ፤ በህይወታችን በዚህ እንዴት እንኖራለን ?
  6. በዘዳግም 7-9 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Deuteronomy 7:18b-19

“Do not be afraid of them. Be sure to remember what the LORD your God did to Pharaoh and all Egypt: the great trials that you saw, the signs and wonders, the strong hand and outstretched arm, by which the LORD your God brought you out. The LORD your God will do the same to all the peoples you fear.”

ኦሪት ዘዳግም 7-9

እስራኤላዉያኑ ወደ ተስፋይቱ ምድር በተቃረቡ ጊዜ፥ በዓመታቶቹ ዉስጥ የነበረዉን የእግዚአብሔር ታምኝነት ሙሴ አስታወሳቸዉ። ከግብፅ ባርነት ነፃ ወጥተዋል! በምድረ-በዳ ሲማስኑ የእግዚአብሔር መግቦት እና ኃይሉ አልተለያቸዉም!

በህይወትህ አዲስ ወራትን ለመጀመር በምትዘጋጅበት ወቃት፥ ባለፈዉ መንገድህ ያለዉን የእግዚአብሔርን ታማኝነት እያስታወስክ እና ለማሰላሰል የተወሰነ ጊዜ ዉሰድ። ለየት ያሉትን የኃይሉን ድንቅ ሥራ እና በመንገዱ ሁሉ ርህራሄ የተሞላበትን ጥንቃቄዉ ልብ በላቸዉ! እናም የማይታወቀዉን የወደፊት ጉዞ ስትመለከት፥ ምንም አትፍራ! አስታዉስ፥ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም እግዚአብሔር ያዉ ነዉ! በሚመጡት ቀኖች ሁሉ ታማኝ እና ጉልበታም በሆነ መንገድ ከአንተ ጋራ ይሆናል!

"ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፅ ሁሉ ያደረገውን፥ አምላክህ እግዚአብሔር፥ ዓይንህ እያየች፥ ታላቅን መቅሠፍት ምልክትንም ተአምራትንም የጸናችውን እጅ የተዘረጋውንም ክንድ አድርጎ እንዳወጣህ፥ አስብ፤ እንዲሁ አምላክህ እግዚአብሔር አንተ በምትፈራቸው በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።"
ኦሪት ዘዳግም 7:18-19

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 77: 11-12፦ "የእግዚአብሔርን ሥራ አስታወስሁ፤ የቀደመውን ተአምራትህን አስታወሳለሁና፤ በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ በሥራህም እጫወታለሁ።"
  • መዝሙረ ዳዊት 98:3፦ "ለያዕቆብ ምሕረቱን ለእስራኤልም ቤት እውነቱን አሰበ፤ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ።"
  • ወደ ዕብራዉያን 13:8፦ "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 97