The Pentateuch Deuteronomy

Covenant, Remember and Obey

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 10-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 98 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የኔ ፀሎት እግዚአብሄር ለእናንተ መናገሩን እንዲቀጥል እና ይህ ጥናት ህጋዊ ነገር ሳይሆን ስለ ልብ ሁኔታ እንደሆነ ነው ፡፡ አስታውሱ እግዚአብሄር ልባችሁን ይፈትናል ፤ ከፈተናችሁ ቦኃላ ያስተምራችኃል ፡፡ ጥቂጦቻችን በአሁኑ ስዓት በቅጣት ደረጃ ውስጥ እየሄድን ነው ነገር ግን ከዚያ ቦኃላ ፍሬ ይመጣል ፡፡

ትምህርት

ዘዳግም 10፡ ኪዳኑ ታድሶአል (ቁጥር 1-11) በተጨማሪም እስራኤላዊያን በዚህ በመሄድ የሚወስዱትን ተነግሮአቸው ነበር (ቁጥር 12-22) ፡፡

ዘዳግም 11፡ እስራኤላዊያን እግዚአብሄር አድርጎላቸው የነበረውን እና ትዕዛዙን ለማክበር ያስታውሳሉ ፡፡ የሚታዘዙ ከሆነ እንደሚባረኩ እና የማይታዘዙ ከሆነ እንደሚረገሙ ተነገራቸው ፡፡

ዘዳግም (12፡ 1-7)፡ ማክአርቱር የተመለከተው(የተናገረው) “ ሙሴ ቀጥሎ ለእግዚአብሄር በሚኖሩበት በሁሉም አካባቢ የሚረዱዓቸውን የተለዩ ህጎችን ገለፀ ፡፡” ሙሴ እነዚህን ስርዓቶች እና ትዕዛዞች እንዲከተሉ አዘዛቸው ፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር የገቡ(ያገኙዓት) ባይሆንም የእነርሱ ስለነበረች ተነገራቸው (ቁጥር 1) ፡፡ በደረሱ ጊዜ አምላኮቻቸውን ያመልኩ የነበሩትን ሁሉንም ህዝቦች ሙሉ ለሙሉ በሁሉም ቦታ - የሀሰት አምላኮቻቸውን የሚያመልኩበትን ተራሮቻቸውን እና ልመነትን የሚወክሉትን ዛፎቻቸውን(ቁጥር 3)፣ መሰዊያዎቻቸውን፣ ምሰሶቻቸውን እና የተቀረፁ ምስሎቻቸውን ያጠፋሉ (ቁጥር 4) ፤ ይህ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን እንዲያመልኩ ይፈቅድላቸዋል ፡፡ በአሁን ጊዜ የአሴር አምዶች የሉንም ነገር ግን ከእግዚአብሄር ከሚስቡን ነገሮች መጠንቀቅ ይገባናል (ኤፌ 4፡ 27) ፤ በዚያ ፋንታ እግዚአብሄር ለመቅደሱ የመረጠው ቦታ እንሄዳለን (ቁጥር 5) ፡፡

መቅደሱ(የመገናኛው ድንካን ማደሪያ) ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶዓል፡

  • ኢያ 18፡ 1፡ “ የእስራኤል ላጆች ማህበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ በዚያም የመገናኛውን ድንካን ተከሉ ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው ፡፡”
  • ኢያ 18፡ 10፡ “ ኢያሱም በእግዚአብሄር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጣላቸው ፤ በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን ከፈለ ፡፡”
  • ኢያ 8፡ 30፡ “ የዚያን ጊዜም በጌባል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሄር መሰዊያን ሰራ ፡፡”
  • ኢያ 24፡ 1፡ “ ኢያሱም የእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበሰበ የእስራኤልም ሽማግሌዎች አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምቶቻቸውንም ጠራ ፡፡ እነርሱም በእግዚአብሄር ፊት ቆሙ ፡፡”
  • 1ሳሙ 7፡ 6፡ “ ወደ ምጽጳም ተሰበሰቡ ፤ ዉኃም ቀድተው በእግዚአብሄር ፊት አፈሰሱ ፡፡”
  • 1ሳሙ 21፡ 1-6፡ “ ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቢሜሌክ ወደ ኖብ መጣ ፤ አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና ፡፡ ስለ ምን አንተ ብቻህን ነህ ? ከአንተስ ጋር ስለ ምን ማንም የለም ? አለው ፡፡ ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን ፡፡ የተላክህበትን ነገርና የሰጠሁህን ትዕዛዝ ምንም አይወቅ ብሎ ንጉሱ አንድ ነገር አዝዞኛል ፤ ስለዚህ ብላቴኖቹን እንዲህ ባለ ስፍራ ተውኃቸው ፡፡ አሁንስ በእጅህ ምን አለ ? አምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን በእጄ ሰጠኝ አለው ፡፡ ካህኑም ለዳዊት መልሶ ፡፡ ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም ነገር ግን የተቀደሰ እንጀራ አለ ፤ ብላቴኖቹ ከሴቶቹ ንጹሐን እንደ ሆኑ መብላት ይቻላል አለው ፡፡ ዳዊትም ለካህኑ መልሶ ፡፡ በእውነት ከወጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሶስት ቀን ጠብቀናል ፤ የብላቴኖቹም ዕቃ የተቀደሰች ናት ፤ ስለዚህ ዛሬ ዕቃቸው የተቀደሰች በመሆንዋ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል አለው ፡፡ ካህኑም በእርሱ ፋንታ ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ ከእግዚአብሄር ፊት ከተነሳው ከገጹ ኅብስት በቀር ሌላ እንጀራ አልነበረምና የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው ፡፡”
  • 2ሳሙ 6፡ 12፡ “ ንጉስ ዳዊትም እግዚአብሄር የአቢዳራን ቤትና የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሄር ታቦት እንደ ባረከ ሰማ ፡፡ ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሄርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደስታ አመጣው ፡፡“
  • መዝ 132፡ 13-14፡ “ እግዚአብሄር ጽዮንን መርጦአታልና ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና እንዲህ ብሎ ፡፡ ይህቺ ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ ፡፡ “

እስራኤላዊያን በተስፋይቱ ምድር ውስጥ እንካን ተቀምጠው መቅደሱ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶአል ፡፡ መሰዊያዎቻቸውን ለመቀዳደድ፣ አምዶቻቸውን ለመሰባበር፣ የተቀረፁ አምላኮቻቸውን ለመቆራረጥ እና ስማቸውን ለማጥፋት ከዚህ ይወስዳሉ ፡፡ የተቀረፁ ምስሎች እና መሰዊያዎች እንደለሉን እውቃለሁ ነገር ግን በሰይጣን የተመኘናቸው ቦታዎች በህይወታችን ይኖራሉ ፤ አስወግዱአቸው ! ኤፌ (4፡ 27) ሲገልፅ፡ “ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት ፡፡ “

እዚህ ትክክለኛ መመለስ እንውሰድ ፤ ዮሐ(2፡ 18-22) ተመልከቱ፡ “ ስለዚህ አይሁድ መልሰው ፡፡ ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ ? አሉት ፡፡ ኢየሱስም መልሶ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሶስት ቀንም አነሳዋለሁ አላቸው ፡፡ ስለዚህ አይሁድ ፡፡ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሰራ ነበር አንተስ በሶስት ቀን ታነሳዋለህን ? አሉት ፡፡ እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር ፡፡ ስለዚህ ከሙታን ከተነሳ በኃላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ ፡፡”

የመገናኛ ድንካኑ ማደሪያ ቆይቶ መቅደስ ሆኖአል ነገር ግን ኢየሱስ ይናገረው የነበረው መቅደስ ስለ ራሱ ነው ፡፡ ዮሐ(1፡ 14) የሚለው “ ቃልም ስጋ ሆነ ፤ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ ፡፡” ከሚንቀሳቀስ መቅደስ(ድንካን) ወደ የሚቆም መቅደስ ከዚያም በእኛ ውስጥ ወዳለው ክርስቶስ ሄድን ፡፡ በዘዳ (12፡ 5) ሙሴ ስለ ኢየሱስ መቅደስ መሆን እና በእኛ ውስጥ እንደሚያድር ትንቢታዊ ቃል ይናገር ነበር ፡፡ 1ቆሮ (6፡ 19) የሚለው “ ወይስ ስጋችሁ ከእግዚአብሄር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖር የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን ? በዋጋ ተገዝታችኃልና ለራሳችሁ አይደላችሁም ፡፡” አሁን ሰውነታችሁ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ነው ፡፡

ዘዳግም(12፡ 8)፡ በእናንተ አይን ሳይሆን በእርሱ አይን ትክክል የሆነውን አድርጉ ፡፡ በእኛ በራሳችን አይን ትክክል እና በእርሱ አይን ትክክል አለመሆኑን የማድረግ ስልጣን የለንም ፡፡ ለእስራኤላዊያን የሆነው ያነው፡

መሳ 17፡ 6፡ “ በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉስ አልነበረም ፤ሰውም ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር ፡፡”

መሳ 21፡ 25፡ “ በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉስ አልነበረም ፤ ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር ፡፡”

ምሳ 12፡ 15፡ “ የሰነፍ መንገድ በዓይኑ የቀናች ናት ፤ ጠቢብ ግን ምክር ይሰማል ፡፡”

ምሳ 14፡ 12፡ “ ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች ፤ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው ፡፡”

ምሳ 16፡ 2፡ “ የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ንጹህ ነው ፤ እግዚአብሄር ግን መንፈስን ይመዝናል ፡፡”

ምሳ 21፡ 2፡ “ የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ንጹህ ነው ፤ እግዚአብሄር ግን መንፈስን ይመዝናል ፡፡”

ዘዳግም(12፡ 9-11)፡ እስራኤላዊያን እስካሁን ምድሪቱን አልተቀበሉም ነበር ፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር በመጡ ጊዜ በመረጠው ቦታ ላይ ወደ እርሱ መመለስ ይኖርባቸዋል ፡፡ ያን ስናውቅ እንደ መንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እናገለግላለን የምንጨነቅለትም ምንም አይኖረንም ፡፡

መዝጊያ

እግዚአብሄር እስራኤላዊያን እንዲፈልጉት ይፈልጋል ፤ በመጨረሻም ኢየሱስ የተናገረው ያንን ነው፡ “ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ “(ዮሐ 14፡ 6) ፡፡ ወደ ኢየሱስ ስትመጡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ትሆናላችሁ ፡፡ በውስጣችሁ እንዳ ታውቃላችሁ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 214.

ጥያቄዎች

  1. የአስዕርቱን ትዕዛዞች ሁለቱን ፅላቶች በሰበረ ጊዜ የእስራኤል የእግዚአብሄርን ትዕዛዞች የመስበርን ወይም ያለመስበርን ሙሴ ታላቅ እይታ ፈጥሮአል ( ዘጸ 32፡ 19; ዘዳ 10፡ 2) ፤ ፅላቶቹን በመተካት የእግዚአብሄርን ፀጋ እና ለእኛ የተፃፉት ቃሎቹ እንዲኖሩን ፍላጎቱን እንዴት ታዩታላችሁ ? (ዘዳ 10፡ 3-5; 2ጢሞ 3፡ 16)
  2. ከሁሉም ነገር ቦኃላ ለእስራኤላዊያን እግዚአብሄር ፈፅሞ ነበር ፤ ይጠይቃቸው የነበረው ብቸኛ ነገሮች ምንድን (ዘዳ 10፡ 12-13; ሚኪ 6፡ 8) ? በራሳችሁ ህይወት ይህ ምንድን ይመስላል ?
  3. እግዚአብሄር በእነርሱ መስራት የሚችለውን ብቻ እንዲሰሩ እስራኤላዊያንን አዘዛቸው ፤ ከመጀመሪያው ጀምሮ እግዚአብሄር ለዕኛ የኖረው ጭንቀት(ሀሳብ) ምንድን ነው ? (ዘፍ 1፡ 26; ዘዳ 10፡ 16; ኤር 4፡ 4; ሉቃ 10፡ 27; ሮሜ 2፡ 29)
  4. በእግዚአብሄር ባህሪይ ላይ መመሰጥ(ማሰላሰል) በዘዳ (10፡ 17-21) ተገልፆዓል ፤ በእነዚህ በተገለፁት ላይ እንዴት በደንብ እርሱን መምሰል ትችላላችሁ ? (መዝ 68፡ 5; 146፡ 9; ሐዋ 10፡ 34)
  5. ዘዳግም (11፡ 18-20) አንብቡ ፡፡ በቤት እንድናደርግ ለእኛ እግዚአብሄር ፍላጎቱ ምንድን ነው ? ለቀጣዩ ትዉልድ በእግዚአብሄር ማስተላለፍ እንዴት አስፈላጊ ነው ? ወደ ታች(ወደ ቀጣዩ) አለማስተላለፍ ዉጤቶቹ ምንድን ናቸው ? ዉጤቶቹን በራሳችን ትውልድ ላይ ታዩአቸዋላችሁ ? ለምን ወይም ለምንስ አላያችሁም?
  6. በዘዳ 10-12 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Deuteronomy 10:14-15

“The heavens, indeed the highest heavens, belong to the LORD your God, as does the earth and everything in it. Yet the LORD was devoted to your fathers and loved them. He chose their descendants after them—He chose you out of all the peoples, as it is today.”

በምድር ይኖሩ ከነበሩ ሰዎች መሃከል፥ እስራኤላዉያን የተባረኩ እና ለእግዚአብሔር እንዲሆኑ የተመረጡ ነበሩ። ከከፍተኛዉ ሰማይ በላይ ሁሉም እስከታችኛዉ ምድር፥ ሁሉም የእግዚአብሔር ነዉ።

እንደ ክርስቶስ ተከታይ፥ እግዚአብሔር መርጦሃል። አዎ፥ አንተን ሊወድህ፣ ሊባርክህ እና የእኔ ብሎ ሊጠራህ! ተመርጠሃል! ተለይተሃል! ታዉቀሃል! ልታስበዉ ከምትችለዉ በላይ ተወድሃል! እግዚአብሔር ከጨለማ ዉስጥ ወደ ሚደንቀዉ ብርሃኑ ጠርቶሃል። በነዚህ ፀጋ በተሞሉ እዉነቶች እረፍ! ሁሉም የጠላት ዉሸቶች ወደ ጎን በመጣል የወደቁ ይሁኑ! ዛሬ፥ የሁሉን ቻዩን እግዚአብሔር ዉዳሴ አዉጅ!

"እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው። ብቻ እግዚአብሔር ስለ አባቶችህ ደስ ብሎታል፥ እነርሱንም ወድዶአል፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መረጠ።"

ኦሪት ዘዳግም 10: 14-15

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘዳግም 14:1-2፦ "እናንተ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን መርጦአልና ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አትንጩ፥ በዓይኖቻችሁም መካከል ራሳችሁን አትላጩ።"
  • ትንቢተ ኤርሚያስ 1:5፦ "በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።"
  • 1ኛ የጴጥሮስ መልዕክት 2:9፦ "እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 98