The Pentateuch Deuteronomy

False Prophets

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 13-14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 99 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዘዳግም(12፡ 32) የሚለው “ እኔ የማዝዝህን ነገር ሁሉ ታደርገው ዘንድ ጠብቅ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምር ከእርሱም ምንም አታጉድል ፡፡” በህጉ ላይ መጨመርም ማጉደልም አይቻልም ፡፡ ያለው እንዳለ ነው ፤ ክርስቶስን በመከተል ፋንታ መፅሀፍ ወደ ሀሰተ አስተሳሰብ ከሚስቡት ከሀሰተኛ ነብያት እና መምህራን ተጠንቀቅ ይልላ ይህ ወደ ዘዳግም 13 መሸጋገሪያ ነው ፡፡

ትምህርት

ነብይ ምንድን ነው ? ዩገን ሜርሪል ነብይን እንደ “ በሌሎች ፊት እርሱን የሚወክል ለእግዚአብሄር የሚናገር ሰው ነው “ ብሎ ገልፆታል ፡፡ ነብያቶች አዋጂዎች (ዘጸ 4፡ 15-16) እና ተናጋሪዎች ነበሩ (ዘጸ 7፡ 1) ፤ አሮን የታላቅ ካህና ሚናን ይፈፅማል በተጨማሪም እንደ ነብይም ይነጋገራል ፡፡

ዘዳግም (13፡ 1-5)፡ዋረን ዋይርስቤ በዘዳግም 13 ለመመልከት ስለ ሰዎስት የፍላጎት(የምኞት) አይነት ያወራል ፤ የመጀመሪያዉ ከሀሰተኛ ነብያቶች የሆነ መጎምጀት ነው (ቁጥር 1-5) ፡፡ ሙሴ ሀሰተኛ ነብይን ሌሎች አምላኮችን ማምለክ የሚፈልግ በህልም ወይም በንግገር ወይም በምልክት ወይም በድንቅ የመጣን ሰው ብሎ ገልፆታል (ቁጥር 1-2) ፡፡ በቁጥር 4 ሙሴ እግዚአብሄርን እንዲከተሉት ብቻ ሳይሆን እንዲፈሩት ተናግሮአል ፤ “ እርሱንም ፍሩ ትዓዛዙንም ጠብቁ ቃሉንም ስሙ እርሱንም አምልኩ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ “(ቁጥር 4) ፡፡ ፈተናን ለመረጃ 1ጴጥ 1፡ 6-7; ያዕ 1፡ 2-4; ማቴ 7፡ 15; 2ቆሮ 11፡ 3-4 እና 1ጢሞ 1፡ 6-7 ተመልከቱ ፡፡ የጠራን እና የተፈተንን የምንሆንበት ጊዜያት አሉ በእግዚአብሄር ቃል ላይ መደገፍ አለብን እንጂ በእነዚህ ሀሰት ነገሮች አይደለም ፤ ሀሰተኛ መምህሮች ይጠፋሉም ይሞታሉም ፡፡

ሙሴ ሀሰተኛ ነብያቶች መገደል እንዳለባቸው ተናግሮአል ምክንያቱም ህዝቡን ከእግዚአብሄር ስለ ሚያርቁ (ቁጥር 5) ፡፡ በዘዳግም “ ክፉውን ከእናንተ አስወግዱ “ የሚለው ሀረግ ስምንት ጊዜ የተጠቀመበት ነው ፤ ለምን ? ምክንያቱም ህዝቡ ከእግዚአብሄር ወደ ሌሎች መመለሳቸው ለእርሱ አስከፊ ናቸው (1ቆሮ 5፡ 6-8, 13) ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው “ ልክ እንደ ቀዶ ሀኪም ከህመምተኛው አካል ውስጥ ከመስፋፋት ለመጠበቅ ካናሰር ያለባቸውን ህዋስ እንደሚያስወግድ የአማኞች አካል ህመምም ቢኖረውም የቤተክርስቲያንን መንፈሳዊ ጤንነትን ለመጠበቅ ቀዶጥገናን መልመድ አለበት ፡፡” ህመሙ ምንም ይሁን ሌሎችን ከእግዚአብሄር ዞር የሚያደርገው ሰው መወገድ አለበት ወይም የባሰ ሳያገኝ ፡፡ ኮንስታብል የሚለው “ እግዚአብሄር ህዝቡ ፍቅር ለመፈተን በተለየም ለእርሱ ታማኝ ሆነው እንደሚቀሩ ለማየት ነብያቱን የሀሰት ትንቢት እንዲፈፅሙ ፈቀደ ፡፡” እግዚአብሄር የህዝቡን ፍቅር ለአምላካቸው ያላቸውን ለመፈተን ሀሰተኛ ነብያቶችን ወደ አካባቢው እንዲመጡ ይፈቅዳል ፡፡

የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ለመጠብቅ ድምፁን መስማት (ቁጥር 4) ማለት በእግዚአብሄር ቃል መሰረት እየመራን መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ያለማቆዐረጥ የሚናገረውን መረዳት ነው ፡፡ በፍፁም አይፃረርም፣ አይጨምርም ወይም ከመፅሀፍ ማንኛውንም ክፍል አያስወጋድም ፡፡ ሀሰተኛ አስተሳሰብ ከክፉውአለም መንፈስ በመቀበል ህዝቡን ከእግዚአብሄር እና ከእውነት በማራቅ ይመራሉ ፤ በዙሪያው መንገድ የለም ፡፡ ህዝቡ በስጋቸው ውስጥ አለም ይሰራባቸዋል ወይም ከክፉዉ አለም መንፈስ ይቀበላሉ ፡፡ ሙሴ ተፅዕኖ ያደረሰባቸውን የፈርዖንን ድግምተኞች አስቡ (ዘጸ 7; 11; 22) ፡፡ በእውነቱ እዉነትን የሚመስሉ ነገሮችን ይቀበሉ ነበር ፤ የነቃችሁ ሁኑ እዉነትን እወቁ በሀሰተኛ ነብያቶች መረጃ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ ፡፡

ዘዳግም (13፡ 6-11)፡ ዋይርስቤ የሰጠው ሁለተኛው መጎምጀት(ምኞት) እስራኤላዊያን ይገጥማቸው የነበረው ምኞት(ጉትጎታ) ከቤተሰቦቻቸው እና ከጎአደኞቻቸው ነበር (ቁጥር 6-11) ፡፡ ቁጥር 7-8 የሚለው በተቻለ መጠን ከጎአደኞች እና ከቤተሰቦች ርቀትን መጠበቅ እና ላለማዳን የሚብራራ ወይም ወደ ኃሰት መንገድ ለሚመራችሁ ሰው ጋሻ(ተከላካይ) አለመሆን ፡፡ ይህ “ ከዚህ ጋር አለመሄድን(አለመተባበርን) ” ይይዛል ምክንያቱም ለእነርሱ ይቅርታ ይሰማችኃል ፤ የሚናገሩትንም እንካን አታዳምጡም ፤ ኮኮብ ቆጣሪዎችን ባለመንካት ወይም ምንም ነገር እንደሌለው ከምታውቁት የሆነ ነገር በመልመድ ከሚሰባችሁ ፤ ወዲያዉኑ ባለመስጠት ምክንያቱም “ ለእነርሱ እዚህ መሆን “ ትፈልጋላችሁ ወይም “ ትረዱዓቸዋላችሁ” ፡፡

የሰለሞን ሚስቶች ችግር ፈጠሩበት ፤ ንጉስ ሰለሞን ተጣብቆባቸው እና ወዶአቸው የነበሩ 700 ሚስቶች (የፈርዖንን ሴት ልጅ ይጨምራል) እና 300 ቁባቶች ነበሩት (ከብዙ ህዝብ የሆኑ)(1ነገ 11፡ 1-3) ፡፡ ሁሉም እንዲጋቡ ከተወሰኑት(ከተመረጡት) ህዝቦች አልነበሩም ፤ እነዚህ ሴቶች የሰለሞንን ልብ ከእግዚአብሄር ወሰዱትም አዞሩትም (ማቴ 10፡ 21) ፡፡ ኢየሱስ ይህ ኢነደሚሆን ተናግሮአል - ይህ የቀጠለ ዉጥረት ከእግዚአብሄር ጋር ስትጎአዙ ይቀጥላል፡፡ ሁል ጊዜ የኛ አገልግሎት እንዲህ አይነት ጥያቄዎችን እንሰማለን፡ “ ለምንድን ኢየሱስን ለመከተል እና ሁሉንም ነገር መስጠት ፈለጋችሁ ?“ መልሱ ጥሩ ይሆናል ፤ ሁል ጊዜ ይህንን ማድረግ አይተበቅባችሁም ፡፡” “ ድጋፋችሁን ከፍ ማድረግ አይጠበቅባችሁም ትንሽ ነው ፡፡” ከቤተሰቦቻችን በላይ እግዚአብሄርን ልንወደዉ ያስፈልገናል ፤ አንዳንድ ጊዜ ከእዉነተኛ ጥሪያችን ሊያባብለን የሚሞክረው ቤተሰባችን ነው (ማቴ 10፡ 34-36) ፡፡

እንደ ወንድም አሮን ወርቅ ጥጃዉን በመስራት ያመልኩ በነበረ ጊዜ ሙሴና አሮን ፈጣን የሆነ ዉጥረት ዉስጥ ገቡ(ወደቁ) (ዘጸ 32) ፤ በወንድሞች መሀከል መከፋፈል ወዲያዉኑ ተፈጠረ ፡፡ እዉነት እንደሚሆን በምናዉቀው ላይ የሚያስነሳንን ከጎአደኛ እና ቤተሰብ ምክር እንጠነቀቃለን ፣ በዚያን ጊዜ በእውነቱ ከቤተሰባችን እንደንለይ ተጠርተናል ይህ ጥብቅ ድምፅ ነው (ሉቃ 14፡ 26) ፡፡ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የተጣበቅን መኖን ይገባናል ይህ ከሆነ ሁል ጊዜ በመለየት(በመረዳት) እናድጋለን ፡፡

ቁጥር 9 ጣዖት የማምለክን ጉጉት የፈጠረው እንዲገድለው እና ሁሉም ህዝብ እጃቸውን እንዲያነሱበት ያዝዛል ፤ በቁጥር 10 ጣዖት አምላኪዉ በድንጋይ ተወግሮ እንዲሞት ትዕዛዙ ይቀጥላል ፡፡ ሌሎቹ ባይሳቡም ጣዖት አምላኪው ግን ጥፋተኛ ነበር ፤ ለምን በጣም ፅኑ የሚሆነው ? ስለሆነም ሙሉ እስራኤል ይሰማሉ ይህንንም ክፉ ነገር ደግመው መስራት እንደሌለባቸው ያውቃሉ (ቁጥር 11) ፡፡ ከእነርሱ ማንኛውም ከእግዚአብሄር ዞር ለማለት የሞከረ ይገደላል፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን እርሱን ስለመከተል እና ከቃሉ ቃር ስለ መጣበቅ የእርሱን ቆራጥነት እንዲያዉቁ ይፈልጋል ፡፡

1 Eugene Merrill, Deuteronomy: An Exegetical and Theological Exposition of Holy Scripture (New American Commentary) (Nashville, TN: Holman, 1994), p. 230; quoted in Dr. Constable’s Expository (Study) Notes, pp. 93-94, available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/deuteronomy.pdf.

ዘዳግም (13፡ 12-18)፡ የዋይርስቤ ጉጉትን ዝርዝር የሚጨመር አንድ አለ፡ ሰዎስተኛው ፍላጎት ከብዙዎች ነው ፡፡ በቁጥር 14 ሰዎስት ቁልፍ ድርጊቶች መፈለግ፣ መመርመር እና መጠየቅ እነዚህ ጣዖት አምላኪዎች ለመለየት ተሰጡ ፤ በአንድ ላይ እነዚህ ቃላቶች በዝርዝር መስራት ማለት ነው ፡፡ ከእግዚአብሄር ሊስቡዓቸው የሞከሩ ህዝቦች ከተገኙ በሰይፍ ይገደላሉ (ቁጥር 15-16) ፤ በእርግጥ በከተማዋ ዉስጥ የነበሩ ሁሉም ነገር ሙሉ ለሙሉ ጠፍተዋል መኖሪያቸውን እና ከብቶቻቸዉን ጨምሮ ፡፡ የሚፈጠረውን የተበላሸውን የከተማዋን ክምር አፍር እንካን አቃጥለዋል ፤ ምንም ነገር የከሰረ አያስቀሩም ወይም ለግለሰብ ጥቅም ከከተማዋ ተሸክመው አላወጡም ፡፡ በቁጥር 18 ሙሴ ምህረትና መብዛት እግዚአብሄርን ለሚታዘዙ እና ትዕዛዙን ለሚጠብቅ እንደሚሰጣቸው ገለፀ ፤ ፅሁፉ “በአምላካችሁ በእግዚአብሄር አይን ትክክል የሆነውን አድርጉ “ በሚለው ያበቃል ፡፡

መዝጊያ

ምኞት(መጎምጀት) ከሀሰተኛ ነብያቶች ይመጣል ፤ ፍላጎት ከቤተሰብ እና ከጎአደኞች ይመጣል ፤ ፍላጎት ከባዙ ይመጣል ፡፡ ይህ ማለት ቤተ ክርስቲያን መጠንቀቅ አለባት ፡፡ ሰይጣን ሁሉንም ነገር የሚያደርገው ሊገድል፣ ሊሰርቅ እና በእርሱ ያላችሁን እምነት ሊያጠፋ ነው ፤ እምነታችሁ ይህ ነገር እዉነት ነው ይሆናል ማለት ነው ፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገን በእግዚአብሄር አይን ትክክል የሆነውን እንድናደርግ ነው ፡፡ ይህን እንዴት ታደርጋላችሁ ? ቀላል በእናንተ እይታ ውስጥ የመጣውን በእግዚአብሄር ቃል መፈለግ፣ መመርመር እና መጠየቅ ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook Publishers, 2001), p. 407.

  2. Wiersbe, p. 408

  3. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Deuteronomy, p. 94, available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/deuteronomy.pdf

  4. Wiersbe, p. 408.

  5. Wiersbe, p. 408.

ጥያቄዎች

  1. (ዘዳ 13፡ 1-3) ሀሰተኛ ነብያትና እን ህልመኞችን ይመለከታል ፤ ሀሰተኛ ነብይ ወይም ስለ ኢየሱስ የሚያጣምም ሰዉ ገጥሞአችኃል ? ምን አሉ እንዴትስ መለሳችሁ ?
  2. ወደፊት ሆኖ የሚያቆምን ምልክትን ወይም ድንቅን ማሳወቅ ለሀሰተኛ ነብያት ይቻላል ? ሀሰተኛ ነብያትና እና እውነተኛ ነብያትን እንዴት ትለዩአቸዋላችሁ ? (ማቴ 7፡ 15-20; 24፡ 24; 2ጢሞ 4፡ 3-4; ኤር 23፡ 16)
  3. ማቴ (10፡ 35-37) እና ሉቃ (14፡ 26-27) አንብቡ ፤ እነዚህ ጥቅሶች በዘዳ (13፡ 6-11) እንዴት ይተሳሰራሉ? እግዚአብሄር ከጠራችሁ ትክክል ወደ አልሆነ መንገድ የሚመራ ወደ እናንተ(ወደ ጎአደኞቻችሁ እና ቤተሰቦቻችሁ) በምንድን መንገዶች ሊቀርባሉ ይችላሉ ? በአሁኑ ጊዜ(ዛሬ) ለዚህ እንዴት መልስ ትሰጣላችሁ/እንዴት መመለስ ትችላላችሁ ?
  4. በዘዳ (14፡ 22-29) እስራኤላዊያን ከምርታቸው በአስረኛው ምንድን እንዲያደርጉ ታዝዘው ነበር ?
  5. በዘዳ (13-14) በትምህርት ወይም በትናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Deuteronomy 13:4

“You must follow the LORD your God and fear Him. You must keep His commands and listen to His voice; you must worship Him and remain faithful to Him.”

ሙሴ ወደፊት ወደተስፋይቱ ምድር በሚገቡበት ጊዜ ስለሚኖሩት ቀናቶች፥ ለእስራኤላዉያን መመሪያዎችን መስጠቱ ቀጥሏል። እጅግ ደጋግሞ፥ ሙሴ እግዚአብሔር አምላካቸዉን በሙሉ ልባቸዉ እንዲወዱ ያስታዉሳቸዋል። እንዲሁም ሌሎችን አማልክትን እንዳያመልኩ እና ሀሰተኛ ነብያትን እንዳይከተሉ ያስጠነቅቃቸዋል። ሙሴ እግዚአብሔርን እንዲከተሉ እና እርሱን እንዲፈሩት እስራኤላዉያንን አዟቸዋል። እስራኤላዉያን ትዕዛዛቱን ሲጠብቁና ድምፁን በሚሰሙበት ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ያላቸዉን ፍቅር ያሳያሉ።

በዚህ ዘመን ላሉ አማኞችም ተመሳሳይ ነዉ። ወደ ኢየሱስ እየተጠጋህ በሄድክ ቁጥር፥ ለእርሱ ድምፅ እና ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ ጆሮህ የተቃኘ ይሆናል። ምክንያቱም ስለምትወዱትና እርሱን ለመታዘዝ ስለምትፈልጉ ነዉ። በግ የእረኛዉን ድምፅ ሰምቶ ወደሰማዉ ድምፅ እንደሚራመድ ሁሉ፥ አንተም የእረኛህን ድምፅ ልትከተል ይገባሃል። ዛሬ፥ እርሱ ምን እያለህ ነዉ?

"አምላካችሁን አግዚአብሔርን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩ፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።"

ኦሪት ዘዳግም 13:4

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የዮሐንስ ወንጌል 10:27፦ "በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤"
  • የዮሐንስ ወንጌል 14:15-16፦ "ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤"
  • የዮሐንስ ራዕይ 3:20፦ "እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 99