Celebrating Freedom from Bondage
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 15-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ክፍል 100 አድርገናል ! ዘፍጥረት፣ ዘጸዓት፣ ዘሌዋዉያን፣ ዘኁልቁ እና አሁን ዘዳግም መፅሀፍ ፡፡ 100 ክፍሎችን በኦሪት መፅሀፍቶች ውስጥ ቆፍረናል ፤ ላለፉት 100 ቀናት ፀሀፊው ሙሴ ነበር ፡፡ እንደ ዘሌዋዉያን በጥቂት ጠንካራ ትምህርቶች ውስጥ እያለፍን ነው ፡፡ በዘዳግም 16 ስለ በዓላት እና ድግሶች እንደገና እናዎራለን ፤ የመጀመሪያው የዘዳግም 15 ክፍል እንደገና እንደ ዘሌዋዉያን የሚሰረዝ እዳን በመሸፈን፣ ለድሀ ለሚሰጥ መስፈርትን እና በእያንዳንዱ ሰባተኛ አመት ስለ ሚለቀቅ አገልጋይ በማውራት ይመስላል (ቁጥር 1-18) ፤ ከዚያም በቁጥር 19-23 በኩርን የመስጠት ውይይት አለ ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም 16፡ የቀናቶቹ ጠቀሜታ
በቀን አቆጣጠሮቹ ላይ ለምን በደንብ ማብራራት አስፈለገ ?ዋረን ዋይርስቤ የገለፀው፡ “ ማን እንደነበሩ ለማስታዎስ እንዲረዳቸው እና ለእነርሱ አድርጎላቸው የነበረውን ለማሰብ እንዲነሳሱ እግዚአብሄር የተለየ ቀን አቆጣጠር ሰጣቸው ፡፡ “ የምንረሳ ሰዎች ነን ነገር ግን እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ከአመታት በፊት፣ ከአስር አመታት በፊት እና ከ100 አመታት በፊት ያደረገላቸውን እንዲረሱ አልፈለገም ፡፡
በቀን አቆጣጠሩ ላይ አንዳንድ ቀናቶች ቀድመው የተመሰረቱ ነበሩ ፤ የቀን አቆጣጠሮቹ ሳምንት በሰባተኛው ቀን ላይ ማንም ስራ አይሰራም ፤ እያንዳንዱ ሰባት አመት የሰንበት አመት ነበር ማንም ስራ አይሰራም ፡፡ እያንዳንዱ 50 አመት ስራ የለም በዓል ማክበር ብቻ ! እግዚአብሄር በተለየ ጠቃሚናቸው ብሎ የተናገራቸው ሰዎስት የተለዩ በዓላት አሉ ፡፡ በጠቅላላው ሰባት በዓላት አሉ ነገር ግን እዚህ ስለ ሰዎስቱ በዓላት እናወራለን ፡፡
ዘዳግም(16፡ 1)፡ ለእስራኤላዊያን የመጀመሪያው ትዕዛዝ የኃይማኖታዊ ቀን አቆጣጠር የመጀመሪያዉ ወር የሆነውን አቢብ ወርን ማክበር ነው (የነፃነት ቀናቸውን) ፤ ከግብፅ ወደ ነፃነት የተለቀቁበትን(መውጣታቸውን) በዓል ያደርጋሉ (ቁጥር 1) ፡፡ የመጀመሪያው በዓል ከባርነት እና ከግብፅ የወጡበትን ነፃነታቸውን የሚያከብሩበት የፋሲካ በዓል ነው (ዘጸ 12፡ 8) ፡፡
ዘዳግም(16፡ 2)፡ እስራኤላዊያን የፋሲካን እንስሳ ይሰዋሉ ፤ እንዴት ይህ ወደ መሲሁ ያመለክታል ? የሂሶጵ አበባው በተሰዋው ጠቦት ደም ውስጥ ይነከራል ከዚያም በእያንዳንዱ ቤት በበር ቆአሚዎቹ እና መቃኖቹ ላይ ይረጫል ፡፡ ያ ደም በዚያ ቤት ላይ የሞት መንፈስ እንዲያልፍ ይፈቅድለታ በዚህም ምክንያት የበኩር ሞት በዚያን ቤተሰብ ላይ አከሰትም (ዘጸ 12) ፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡን ነፃ አድርጎአቸው ነበር እናም ህይወትን እንዲያከብሩ ፈለጋቸው ! ቶም (ቲቲር ሰራተኛው ጋር) “ የሁሉንም ቤት የበኩር ልጅ በምድሪቱ ውስጥ በመግደል የሞት መልዓኩ መንገዱን አደረገ ፤ ነገር ግን በጠቦት ደም የተሸፈነውንሁሉንም ቤቶች አለፈ “ የሚለውን ወረቀት ከፅሁፉ ሰጠኝ ፡፡
ፋሲካ በትክክል ስለ ክርስቶስ ነበር ነገር ግን እሳካሁን አይሁዶች አያዉቁትም (1ቆሮ 5፡ 7) ፡፡ ለእኛ የፋሲካ በዓል በጎልጎልታ መስቀል ስለ ክርስቶስ ሞት የሚያስታውስ ነው ፤ ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ፋሲካ መፈፀም ነበር ምክንያቱም ያ ሞት ስለ ተፈፀመ ፡፡ አስታዉሱ ጥቂቶቹ በዓላት እስካሁን አልተፈፀሙም ፡፡ አሁን ፋሲካ በእኛ ቀን አቆጣጠር (በሮማናዊያን/ጌርጌሮሳዊያን አቆጣጠር) መጋቢት እና ወይም ሚያዚያ ወር ይከሰታል ፤ በተጨማሪም አቢብ የኃይማኖታዊ አድስ አመት የመጀመሪያ ወር ነው ፡፡
ዘዳግም(16፡ 3-8)፡ እስራኤላዊያን በፋሲካ የቦካ ቂጣ አይበሉም ነገር ግን ለሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ይበላሉ (ቁጥር 3)፡፡ ያልቦካ የቂጣ በዓል አይሁዶችን ከግብፅ እንዴት በፍጥነት ወጥተው እንደነበር እና ቂጣ ለመስራት እስኪቦካ እንዳልጠበቁ ያስታውሳቸዋል ፡፡ ያልቦካ ቂጣ ማለት “ የመከራ ቂጣ” ማለት ነው ፡፡
ያልቦካው የፋሲካ ቂጣ ወደ ኢየሱስ ያመለክተናል ፡፡ እርሾ ኃጢዓትን ይወክላል ፡፡ ኃጢዓት የማያውቀውን ክርስቶስን በሚወክለው ቂጣ ውስጥ ያለ “ኃጢዓት” የለም (2ቆሮ 5፡ 21) ፡፡ ክርስቶስ ኃጢዓት አልነበረበትም ግን ለእኛ ኃጢዓት ምትክ(ተተኪ) ሆነ ፡፡ በዚህ ጊዜ የእስራኤላዊያን ቤቶች ከሁሉም እርሾ ነፃ ይሆናሉ ፡፡ ቶም ወደ ሰጠኝ የፅሁፍ ወረቀት ስንመለስ፡ “ ኃጢዓት እና ቅዱስ አምላክ አብረው መሆን አይችሉም እንዲሁም ቅዱስ አምላክ ኃጢዓት እንዳይቀጣ አይፈቅድም ፤ በዓሉ ለሰባት ቀናት ይቆያል ፤ የመጀመሪያው እና የመጨረሻው ቀናት የተለዩ ነበሩ ፡፡” በፋሲካ በዓል ላይ እና በቂጣ በዓል ላይ ሁሉም ወንድ መሳተፍ ይጠበቅባቸው ነበር ፡፡
ቁጥር 4 የሚለው ለፋሲካን ሰባት ቀናት በግዛታቸው ውስጥ እናካን እርሾ አይሆንም እናም ማታ ተሰዉቶ የነበረው እስከ ጥዋት መቆየት የሚችል ስጋ አይኖርም ፤ በተጨማሪም እስራኤላዊያን እግዚአብሄር ሰጥቶአቸው በነበረው በማንኛውም ከተማ እንዳይሰው ተነግሮአቸዋል (ቁጥር 5) ፡፡ በመገናኛ ድንካኑ ማደሪያ “ እግዚአብሄር አምላካቸው ስሙ እንዲያደርበት በመረጠው “ቦታ ብቻ ይሰዋሉ (ቁጥር 6) ይህንንም ሊነጋ ሲል ከግብፅ እንደወጡበት በተመሳሳይ ያደርጉታል ፡፡ በቁጥር 7 የእግዚአብሄር ምርጫ በሆነዉ ቦታ ላይ ምግቡን እንዲያበስሉት እና እንዲበሉት ተነገራቸው ከዚያም በማለዳ ወደ ድንካናቸው ይመለሳሉ ፡፡ በቁጥር 8 ለስድስት ቀን የቦካ ቂጣ እንዳይበሉ ተነገራቸው ፡፡ የፋሲካው በግ(ጠቦት) ክርስቶስን ይወክላል ፤ ክርስቶስ ለእኛ የሞተው በግ(ጠቦት) ነው ፤ ዮሐ 1፡ 29 ኢየሱስን እንደ “ የአለምን ኃጢዓት ሁሉ የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ !” መጥምቁ ዮሐንስ መንገድን እያዘጋጀ ነበር እዩ - እዩ ! ኃጢዓታችንን የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ ይህ ነው ብሎ ተናገረ !
አስታውሉ እንዴት “በግ” እና “ የአለም ኃጢዓት” አብረው ተወከሉ በተጨማሪም እንዴት የፋሲካ በዓል፣ በጉ እና ያልቦካዉ ቂጣ እንደተደራረቡ ! 1ጴጥ 1፡ 19 የሚለው “ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ ፡፡” ደግሞ እና ደግሞ መፅሀፍ ይህ ለእኛ የሚገባንን ቅጣት በራሱ ላይ የወሰደው የክርስቶስ መልክ ነው ፡፡
ዘዳግም (16፡ 9-13)፡ የሳምንታት በዓል መከሩ መታጨድ ከጀመረበት ሰባት ሳምንታት ነበር መርሀ ግብሩ ከዚያም ይከበር ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እንዴት ባርኮአቸው እንደነበር መጠን እንዲሰጡ ታዘዙ ፡፡ ሁሉም ሰው መከርን ያከብራሉ “ አንተ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህና ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ በአገርህም ደጅ ውስጥ ያለው ሌዋዊ በመካከልህም ያሉት መጻተኛና ድሀ አደግ መበለትም - “(ቁጥር 11) ፡፡
በጣም እናከብራለን ! ከአሮጌ ህይወት ወደ አድስ ህይወት ስለመጣን እናከብራለን ፤ ከዚህ ባሪያ ከመሆን ሀሰብ ነፃ ስለሆንን እናከብራለን ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው ይህ ምን እንደነበርን እና አሁን ምን እንደሆንን የሚከበር ነው ፡፡
መዝጊያ
ለምን እናከብራለን ( 1ቆሮ 5፡ 7-8; ማቴ 16፡ 6; ገላ 5፡ 9; 2ጢሞ 2፡ 19; 2ቆሮ 7፡ 1) ? ከዚህ ቦኃላ በአሮጌው እርሾ አናከብርም ፡፡ ከዚህ ቦኃላ የምቀኝነት ስሜት እና ክፋት ለእኛ ምርጫ አይደለም ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው ለመስራት በምንጠቀምባቸው ነገሮች ካለው ከማመቻመች እርሾ እንጠንቀቅ ፤ በግብዝነት በመኖር አናከብርም ፤ ምንም እንካን ዱሮ በምቀኝነት፣ በክፋት፣ በግብዝነት እና ባለማመን ብንኖርም አሁን ነፃነታችንን እናከብራለን ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች በመጎአዝ ማክበር እንችላለን ፡፡ እስራኤላዊያን በአካል ከግብፃዊያን ባርነት ነፃ ነበሩ እናም አሁን ከቀድሞው ኃጢዓታችን በአካላውም በመንፈሳዊም ነፃ ነን ፡፡ ሁልጊዜ የሚያነፃው አንዱ(ብቸኛው) ክርስቶስ ነው ፡፡
ወደ 1ቆሮ(5፡ 8) ስንመለስ “ ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም “ በዚህ እተዋችኃለሁ ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, Co: David C. Cook, 2001), p. 415.
Wiersbe, p. 416
ጥያቄዎች
-
በዘዳ (15፡ 12-18) የቱ ላይ ነው ባሪያ ነፃ መሆን የሚችለው ? ምንድን ነበር የሚሰጣቸው ? ባሪያው ከቤተሰቡ ጋር መቀመጥ ከመረጠ ምንድን ይፈጠራል ?
-
በእያንዳንዱ ሰባት አመታት መጨረሻ ላይ ነፃ ይደረጋል ፤ በዘዳ (15፡ 1-3) ከምንድን ማን ነበር የሚነፃው ? ለዚህ ነፃነት ማን ነበር የተለየው(የሚለየው) ?
-
በዘዳ(15፡ 7-11) እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን ስለ ድሀው እንዲጠነቀቁ እና እዳውን እንዲሰርዙ ነገራቸው ፤ ያንን ጊዜ ከአሁኑ ጋር ብታወዳድሩት እነዚህን የእግዚአብሄርን ትዕዛዞች እንደያዙት ማህበር(ህብረተሰብ) ነን? ለምን ወይስ ለምን አይደለንም ?
-
በዘዳ(16፡ 5-6) እስራኤላዊያን እግዚአብሄር በመረጠው ቦታ እንጂ በከተማዋ መግቢያ ላይ እንዳይሰው ተነገራቸው ፤ ለእነዚህ መስዋዕቶች እግዚአብሄር የመረጠው ቦታ የት ነው ?
-
በዘዳ(15-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 15:10
“Give to him, and don’t have a stingy heart when you give, and because of this the LORD your God will bless you in all your work and in everything you do.”
ሙሴ አሁንም እስራኤላዉያንን ውደተስፋይቱ ምርድ ከገቡ በኋላ ምን አይነት ህይወት መኖር እንዳለባቸዉ የሚያሳይ መመሪያዎችን ይሰጣቸዉ ነበር። ለሌሎች በመስጠት ለጋስ እንዲሆኑ እና ስግብግብ የሆነ ልብ እንዳይኖራቸዉ አዘዛቸዉ! እግዚአብሔር ለልጆቹ መልካም ስጦታን የሚሰጥ ለጋስ አምላክ ነዉ። ነገሮችን ራሳቸዉ ጋራ ባለማስቀረት፥ የተሰጣቸዉን መልሰዉ ለመስጠት ምን ያክል ይበልጥ ለጋስ ይሆናሉ?
ዛሬ፥ እግዚአብሔር ለጋስ የሆነን ልብ እንዲሰጥህ ለምነዉ! በህይወትህ ዉስጥ ይበልጡኑ ልግስና የሚያስፈልጋቸዉን ነገሮች እግዚአብሔር እንዲገልጥልህ ለምነዉ። ጊዜህን፣ ሀብትህን፣ ንብረትህን፣ እንዲሁም ህይወትህን በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፈህ መስጠት ትችላለህ። በልግስና መንፈስ በተመላለስክ ቁጥር፥ እግዚአብሔር በእነዚያ መንገድ ሁሉ ይበልጥኑ ይባርክሃል። እግዚአብሔር በልግስና የሚሰጥን ሰዉ ይወዳል!
"እጅህን በምትጥልበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ስለዚህ በሥራህ ሁሉ ይባርክሃልና ፈጽመህ ስጠው፥ በሰጠኸውም ጊዜ በልብህ አትጸጸት።"
ኦሪት ዘዳግም 15:10
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የሉቃስ ወንጌል 11:13፦ "እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?"
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:7፦ "እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።"
- 1ኛ ጢሞቴዎስ 6:18-19፦ "እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ፥ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፥ መልካምን እንዲያደርጉ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፥ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 100
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።