The Pentateuch Deuteronomy

Priests & Prophets

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 101 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለዘዳግም ቃሉ ነብይ ነው እናም ዛሬ ስለ ነብይ ሚና እናዎራለን ፡፡ ዘዳግም 17፡ 18-19 ነብዩ ስለ ሚፅፈው እና የእግዚአብሄርን ቃል ስለሚገለብጠው ፅሁፍ ያወራል ፡፡ ነብዩ የለቀቃቸው ቃላቶች የዘዳግም 18 ዋነ ነው ፡፡

ትምህርት

ዘዳግም(18፡ 1-2)፡ ለነብያት ሙሴ ትዕዛዝ እንደ ፃፈ የካህናቱን ሚና ጠቀሜታ ዘርዛሮአል ፡፡ ሙሉ የሌዊ ነገድ ወደ ተስፋይቱ ምድር በገቡ ጊዜ እንደ መስዋዕት በሚሰጡት በህዝቡ ስጦታ ላይ ጥገኛ ይሆናሉ ምድር አይቀበሉም (ቁጥር 1) ፡፡ ኮንስታብል ሌዋዊያን እንደ “ በሌሎቹ እስራኤላዊያን መሀከል እንዳሉ እንግዶች ……የራሳቸው ከተሞች እንደነበሩዓቸው ” ገልፆዓል ነገር ግን ከሌሎች እስራኤል ነገዶች የምድር ውርስ ምንም አልተቀበሉም ፡፡ እግዚአብሄር የሌዋዊያን ውርስ ነበር (ቁጥር 2; ማቴ 6፡ 33) ፡፡

ሌዋዊያን በክህነት ሚናቸው ሲጎአዙ ምግባቸው እና ገንዘብ ከየት እንደሚመጣው ስለ አቅርቦታቸው ሊጨነቁ አይችሉም ፤ ይህ የእግዚአብሄር ነበር ፤ የእነርሱ ምርጫ አልነበረም (ዘዳ 10፡ 8-9) ፡፡ ለሌዊ ነገድ ሙሴ የእግዚአብሄርን ተስፋ ደጋግሞ እየተናገራቸው ነበር ፡፡ መጀመሪያ ጊዜ ላይ አገልግሎቱን ለማነቃቃት ለመሄድ ለመቀጠል እና ወንጌልን ለማካፈልና ደቀመዝሙር ለማድረግ ለገንዘብ እና ለእርዳታ መጠየቅ ጭንቀት(ፍርሀት) ይሰማል ፡፡ ወደ ዋልማርት ሄዶ ሰዎች በሰጡን ገንዘብ መግዛት ጭንቀት ይሰማል ፤ ሁሉም ሰው እየተመለከተ እንደነበር ይሰማል ፤ ነገር ግን የሌዋዊያን አስተሳሰብ ካላችሁ እግዚአብሄር በተለየ ለዚህ ሚና ጠርቶአችኃል ፡፡ በክርስቶስ አካል ውስጥ ሰዎች ይህን ጥሪ ረድተው በደገፉ ጊዜ እናንተ እንደ ሌዋዊያን እግዚአብሄር የእናንተ ድርሻ እንደሆነ በደንብ ይገባችኃል ፡፡ በዉሃዎች ላይ ለመሄድ ትንሽ ጊዜ ይወስዳል እናም ምናልባት ለጥቂት ሌዋዊያን ጭንቀት ተስሞቶአቸዋል ፡፡

ዘዳግም(18፡ 3-8)፡ በሬዎች፣ በግ ወይም ፍየሎች ሲሰው ካህናቱ ወርቾቻቸው፣ ጉንጮቻቸው እና ጨጎአራቸው ተሰጥቶአቸው ነበር ፤ በተጨማሪም ካህናቱ የእህል፣ የወይን፣ የዘይት እና የተሸለተውን በጉን ፀጉር በኩራት ተሰጥቶአቸዋል (ቁጥር 4) ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተወካይ በእግዚአብሄር ወደ አገልግሎት ተጠሩ በኩራትም ይሰጣቸው ነበር (ቁጥር 5) ፡፡ ለሌዋዊያን ወደ ኃላ መመለስ አልነበረም ምክንያቱም ይህ የእነርሱ ጥሪ ነበር (ቁጥር 6) ፡፡

በዚህ ክፍል ላይ በደንብ በጥልቅ አልሄድም ምክንያቱም በአጠቃላይ በዘዳግም ውስጥ በጣም ጠቃሚ ናቸው ብዬ የማስባቸውን ለመሸፈን በቂ ጊዜ ስለምፈልግ ፡፡ እሰከዚህ ድረስ የምንረዳው(የሚገባን) ስለ ሌዋዊያን ካህናት እያወራን ነው ፡፡

ዘዳግም(18፡ 9-13)፡ ለነብያቱ የተቀመጡት የመጀመሪያው ትዕዛዞች ማድረግ የሌለባቸው ነገሮች ነበሩ፡ አስከፊ የሆኑ ልምዶችን ማስመሰል ወይም አስማትን መተግበር የለባቸው; በልጅ መስዋዕት፣ ጥንቆላ ላይ፣ መልካም እድል መናገር(ትንበያ)፣ ሞራ ገላጮች፣ አስማት ላይ መሳተፍ የሌባቸውም; ድግምቶችን አለ ማዘጋጀት፣ ሙታንን የሚያናግር መሀከለኛ/የተለመደን መንፈስ አለማናገር ወይም ሙታን ጠሪ አለመሆን (ቁጥር 9-11) ፡፡ ይህ ሁላ በእግዚአብሄር እይታ በጣም አስፀያፊ ነበር “ ስለዚህም ርኩሰት አምላክህ እግዚአብሄር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ” (ቁጥር 12) ፡፡ ስለዚህም ወደ ማህበረሰቡ በመጡ ጊዜ እነዚህን ድርጊቶች እግዚአብሄር ቀድሞ አጥፍቶአቸው ስለ ነበር ተመልሰው አይመጡም ፤ ከሚያርቁአቸው ሰዎች ወይም ወደ አሰፀያፊ ቀድሞ ድርጊታቸው እንዲመለሱ ከሚፈልጉት እንዲጠነቀቁ እየነገራቸው ነበር ፤ በዚያ ፋንታ በንፁህ ልብ በእግዚአብሄር ፊት ይመጣሉ (ቁጥር 13) ፡፡

በእነዚህ በአስፀያፊ ነገሮች መሀከል ላይ ሴማን(ዋና አላማን) አስቡ(ዘዳ 6፡ 4-9) ፤ ዘዳ(6፡ 5-6)፡ “ አንተም አምላክህን እግዚአብሄርን በፍጹም ልብህበፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ ፡፡ እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ ፡፡” ይህ ጥቅስ በግድግዳችሁ ወይም በሳጥናችሁ ላይ ከሆነ በልባችሁ ውስጥ ካልሆነ ህጋዊነት ሊሆን ይችላል ፡፡ ሁሉንም መጥፎ ነገር በማስተካከል ለሁሉም የእግዚአብሄር ነገር የልብ ሁኔታችን ከዚህ አለም የተለየ ይሆናል ፡፡

ዘዳግም(18፡ 14)፡ ነብያቶች ለሀሰተኛ ነብያቶች እንዳይሰጡ ወይም አስፀያፊ እንዳይሆኑ ተነግሮአቸው (ቁጥር 14) ፡፡ ወደ ሚገቡባት ምድር በመንገዱዓ ጣልቃ አይገቡም (ዘጸ 22፡ 18; ዘሌ 17፡ 7) ፡፡ “ ወደ ቀዱሞው እንዳትመለሱ አድስ የሆነ ነገር እንድትለምዱ እፈልጋለሁ “ እነዚህ እግዚአብሄር ደግሞ ደግሞ ይናገራቸው የነበሩ ሁለት ስዕሎች ናቸው ፤ ለዚያ ነው የምናከብረው እዛ ነበርን አሁን እዚህ ነን ፡፡

ዘዳግም(18፡ 15)፡ “ አማላክህ እግዚአብሄር ከአንተ መካከል ከወንድሞች እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል ፤ እርሱንም ታደምጣለህ ፡፡” እግዚአብሄር ከአንዱ ነገድ እንደ ሙሴ አይነት ነቢይ ያስነሳላቸዋል ፡፡

የዚህ ነቢይ ጥራት የሚይዛቸው፡ እስራኤላዊ ነው፣ በእግዚአብሄር የተጠራ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተሞላ፣ የእግዚአብሄርን ቃል ተናጋሪ፣ በአምላክ ስም ለመናገር የተሸመ፣ በእግዚአብሄር ህዝብ ላይ መልካም እረኛ እና በምላክቶች የሚያረጋግጥ ፡፡ ሙሴን መምሰል ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ፤ ሙሴ እስራኤላዊ ነበር፣ በእግዚአብሄር የተጠራ ነበር፣ በላዉ ላይ የመጣ መንፈስ ነበረበት፣ ተናጋሪ ሰው ነበር፣ የተሸመ ነበር፣ መልካም እረኛ ነበር እናም በምልክቶች ያረጋግጥ ነበር ፡፡ ሙሴ ነቢይ ነበር የሚመጣውም ተመሳሳይ ጥራትና ባህሪይ ይኖረዋል፡

መመሳሰል

ሙሴ

ኢየሱስ

በልጅነት መዳናቸው

ዘጸ 2፡ 1-10

ማቴ 2፡ 13-15

ንጉሳዊ ቦታ መተዋቸው

ዕብ 11፡ 24-27

ፊል 2፡ 5-8

ለህዝቡ ያላቸው ርህራሄ

ዘኁ 27፡ 15-17

ማቴ 9፡ 36

ስለ ሌሎች ምላጃ(ፀሎት) በማድረግ

ዘዳ 9፡ 18

ዕብ 7፡ 25

የኪዳን መሀከለኛ(መሀከለኛ ሰው) በመሆን

ዘዳ 29፡ 1

ዕብ 8፡ 6-7

መጥምቁ ዮሐንስ፣ ጴጥሮስ እና ስቴፈን የዘዳግም(18፡ 15) ነቢይ እንደሆነ ስለ ኢየሱስ አውርተዋል (ዮሐ 1፡ 19-27, 43-45; 5፡ 45-47; 6፡ 14-15; 7፡ 40) ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ መንገድ ብቻ አልነበረም ያዘጋጀው ነገር ግን ዮሐንስ የፊልጶስንም ንግግር መዝግቦታልም “ ሙሴ ስለሱ የፃፈለትን አግኝተነዋል ”(ዮሐ 1፡ 43-45) ፡፡ ደግሞ ደግሞ ምልክቶቹ ስለ ኢየሱስ መምጣት አመልክተዋል (ሐዋ 3፡ 17-20; 7፡ 37; ዕብ 3፡ 1-6) ፡፡

መዝጊያ

ሁሉም ነገር ወደ ኢየሱስ ያመለከተው ከነቢዩ ሙሴ ይበልጣል ሙሴም ተስማምቶአል ፤ ሙሴ ህዝቡን “ የሚመጣ ነቢይ አለ እርስን ላዳምጠው ያስፈልጋል ፤ እኔ ሙሴ ህዝቡን ማዳን አልችልም እርሱ ባቻ ይችላል” ብሎ ነገራቸው ፡፡ ዘዳግም 18 የመሲሁ መምጣት መድረስን ምልክቶች የሚናገር ነበር ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Consable’s Expository (Study) Notes, p. 114; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/deuteronomy.pdf.

  2. Samuel J. Schultz, Deuteronomy, p. 7; quoted in Constable, p. 118.

ጥያቄዎች

  1. የሆነ ሰው ሌሎች አምላኮችን፣ ፀሀይን፣ ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ሲያመልክ ከተያዘ በዘዳ(17፡ 2-7) መሰረት ቅጣታቸው ምንድን ነበር ? ከአንድ በላይ ምስክር ለምን እንዳስፈለገ ምንታስባላችሁ ? (ዘዳ 19፡ 15; ዕብ 10፡ 28)
  2. የህግ ጉዳይ ክስተት ውሳኔ የማይደረግባቸው ወደ ሌዋዊያን ካህናቶች ይቀርባል ፤ አንድ ሰው የተሰጠውን ፍርድ አለመቀበልን ቢመርጥ ምን ይሆናል ? (ዘዳ 17፡ 11-13)
  3. በዘዳ(18፡ 9-12) ለእግዚአብሄር እንደ አስከፊ ሰዎች ምሳሌ ተዘርዝረው የነበሩት የሰዎች ባህሪያት ምንድን ነበሩ ?
  4. በዘዳ(18፡ 15-19) እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ነብይ እየሰጣቸው እንደነበር ገለፀ ፤ አዲስ ነብይ ለማስነሳት እግዚአብሄር የሰጠው ምክንያት ምንድን ነበር ? በዘዳ(18፡ 15) የሙሴ ቃላቶች ወደ ኢየሱስ ያመለክታሉ ወይስ የሙሴን ተተኪ ? (ዮሐ 1፡ 21; 6፡ 14; 7፡ 40)
  5. በዘዳ(18፡ 22) ትንቢቱ ከእርሱ እንደነበር ወይም እንዳልነበር እንዴት እንዲያዉቁ እግዚአብሄር ምንድን ተናገረ ?
  6. በዘዳ(17-18) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Deuteronomy 18:15

“The Lord your God will raise up for you a prophet like me from among your own brothers. You must listen to him.”

ሙሴ ከእስራኤላዉያን ጋራ ስለአህዛብ ነብያቶች በሚነጋገርበት ወቅት ድፍረት የተሞላበት ንግግር ተናግሯል። ሙሴ በመተማመን መንፈስ፥ እግዚአብሔር እንደ እርሱ አይነት ነብይ እንደሚያስነሳ እና የሚመጣወን ነብይ ደግሞ የግድ መስማት እንዳለባቸዉ ተናግሯል። ወደ አዲስ ኪዳን በፍጥነት ስንሄድ፥ ዮሐንስ፣ ጴጥሮስና እስጢፋኖስ ሙሴን እንደነብይ ይጠቅሱታል። ከዚያም ኢየሱስ ማን እንደሆነ በማስረገጥ፥ ነብይ ብቻ ሳይሆን በተስፋ ቃሉ የተነገረዉ መሲሁ እንደሆነ ይነግሩናል። ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ዉስጥ እንደ ታማኛ አገልጋይ ህጉን ለመፃፍ መጣ! ኢየሱስም ከሙሴ ጋራ ብዙ የሚያመሳስለዉ ነገር ቢኖርም የመጣዉ ግን ሁሉም የዘላለም ህይወት ይኖራቸዉ ዘንድ ነዉ።

እንደ አማኝ፥ ከተስፋ ቃሉ ነብይ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ፥ ነፃነትን፣ ፀጋን፣ የዘላለምን ህይወት ተቀብለሃል። እግዚአብሔር አንተ እንድተሰማዉ ይህንን ነብይ እና መሲህ አስነስቶታል! ኢየሱስ ዛሬ ምን እያለህ ይሆን?

"አምላክህን እግዚአብሔርን በኮሬብ ስብሰባ ተደርጎ በነበረበት ቀን፦ እንዳልሞት የአምላኬን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ አልስማ፥ ይህችን ታላቅ እሳት ደግሞ አልይ ብለህ እንደ ለመንኸው ሁሉ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።

ኦሪት ዘዳግም 18:15-16

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የዮሐንስ ወንጌል 1:45-46፦ "ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ። ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።"
  • የሐዋርያት ሥራ 7:37፦ "ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች፦ እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት ያላቸው ሙሴ ነው።"
  • ወደ ዕብራዉያን 3:5-6፦ "ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ፥ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፤ እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 101