Preparing for Battle
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዘዳግም 19 በከነዓን መማፀኛ ከተሞች ላይ ያወራል ፤ በተጨማሪም ታስቦበትና ሳይታሰብበት የሆነን ነፍስ ግድያ፣ የወዳጆች ሚና እንዴት ማስማማት እንዳለበት እና ክፉው እንዴት በሁለት ወይም በሰዎስት ምስክሮች ሊነፃ እንደሚችላ ይገልፃል ፡፡ ዩገን ሜረሪል ዘዳግም 20 “ የጦርነት መመሪያ “ በማለት ለይቶታል(ገልፆታል) ፡፡ እስራኤላዊያን ወደ ምድሪቱ አልሁዱም(አልገቡም) ነበር ወይም ጦራቸውን በጋራ አስቀመጠዋል ፤ መጀመሪያ መመሪያ ነበራቸው ከዚያ በመቀጠል ጦር ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም(20፡ 1)፡ የተቃራኒው ጦር ከእስራኤላዊያን ቢበልጥም የመጀመሪያዉ መመሪያ መፍራት የለባቸውም ፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን ሳያቆዓርጥ ይገለጥላቸው እና ተስፋይቱ ምድርም እንዲገቡ ከእነርሱ ጋር ነበር ፡፡ በዚያ ፈንታ በእምነት መጎአዝ ያስፈልጋቸዋል ጦርነቱ የእግዚአብሄር ስለሆነ (መዝ 20፡ 7; ዘጸ 15፡ 3; ዘዳ 20፡ 4) ፡፡
ዘዳግም(20፡ 2-4)፡ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ካህኑ ከፊታቸው በመሄድ ጦሩን ይነግራቸዋል (ቁጥር 2) ከዚያም ካህናቱ መለከቶችን ይነፋሉ (ዘኁ 10፡ 8-9) ፡፡ በቁጥር 3 ካህኑ የሚሰጣቸው መልዕክት “ ልባቸው መደንገጥ እንደሌለበት ፤ መፍራት፣ መንቀጥቀጥ እና መደንገጥ እንደሌለባቸው “ ነበር ፡፡ ይህ መልዕክት እንዳለ ለጳጳሱ ተሰጥቶት ነበር (ዘፍ 15፡ 1; 46፡ 3; ዘጸ 14፡ 13; ኢሳ 41፡ 10; ሉቃ 1፡ 13, 30) ፡፡ እነዚህ እያንዳንዳቸው በእምነት ወደ ማይታወቅ ወደ አድስ ስፍራ እየሄዱ ነበር ፤ አንዳንድ ጊዜ በክስተት ስጋት እና ጭንቀት የሆነ ነገር በራሳችን መስራት እንዳለብን እናስባለን ፡፡ “ ከእናንተ ጋር የሚሄድ ያድናችሁም ዘንድ ጠላቶቻችሁን ስለ እናንተ የሚዋጋ አማላካችሁ እግዚአብሄር ነውና “(ቁጥር 4) ፤ ስለዚህ ካህኑ በጦሩ እና በእግዚአብሄር እንደ አገናኝ ያገለግላል ፡፡ 1ዜና (27፡ 5) በጦርነት የካህኑን ጥቅም ያሳያል ፡፡
ዘዳግም(20፡ 5)፡ በቁጥር 5 ለወታደሮቹ ከዉጊያው ነፃነት ይሰጣቸው ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ያስቀመጠው(የተናገረው) “ ነፃ ማድረግ በሀሳባቸው ሌላ ቦታ(ቤታቸው፣ ወይን ፍሬአቸው ጋር፣ ሚስታቸው) ጋር ለሆነ ወይም ልባቸው ከእርሱ ጋር ያልሆነ(ለፈሩትን) ሰዎች የእግዚአብሄርን ርህራሄ ያሳያል ፡፡” ዋይርስቤ ሰዎስት አይነት ነፃ አደራረግን(ነፃነትን) ለይቶአል ፤ የመጀመሪያው ነፃነት ስለ ቤት ነበር “ ወታደሩ ለእግዚአብሄር አዲሱን ቤቱን እንዲያቀርብ እና በውስጡ መኖር እንዲ ጀምርበት…… በቤቱ ውስጥ ከቤተሰቡ ጋር መኖር እንዲ ጀምርበት እና እንዲደሰትበት ይፈቀድለታል ፡፡” ይህ በጦርነቱ መቃረቢያ ላይ ይደረጋል በዚህም ከኃላው ቀርቶት በነበረው ነገር ወታደሩ በጦርነቱ ላይ ትከረት ማድረግ ካልቻለ ለእርሱ እዚህ አለመሆኑ የተሸለ እንደሚሆን ይነገራል ፡፡ ዩገን ሜረሪል የሚለው “ በግጭቱ መሀከል ላይ ፍርሀት ወይም ከባድ ሀሳብ እንዲህ የሆነውን ሰው ህይወት ብቻ ሳይሆን የሰውየውን አጋሮች(ጎአዶቹን) አደጋ ላይ መጣል እንደሚችል በደንብ የተረጋገጠ እውነት ነው ፡፡” (ሉቃ 9፡ 23-27; 57-62; 2ጢሞ 2፡ 4; ያዕ 1፡ 8)
ዘዳግም(20፡ 6)፡ ነፃ ለማድረግ ዋይርስቤ የገለፀው ሁለተኛው ምክንያት ስለ መከር ነበር “ ወታደሩ ፍሬዋን ቀምሶአት የማያውቀዉን የወይኑን እንዲሰበስብ ” ወደ ቤቱ እንዲመለስ ወታደሩ ይፈቀድለታል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚገልፀው “ ለወይን ተክል ፍሬ ማፍራት ለመጀመር ቢበዛ አምስት አመት ይወስዳል ፤ አንድ ሰው የመጀመሪያ ፍሬ ከወይኑ ለማምረት ብዙ አመታት ሲጠብቅ የነበረው ፍሬ እስኪያፈሩ ድረስ እንዲመለከት(እንዲጠብቅ) ይፈቀዳል ፡፡” ይህ ለቤተሰብ የእግዚአብሄር ርህራሄ ስዕል ይሆናል - በአጭር ጦርነት ላይ
መሆን ቤተሰቡ ምርታቸውን እንዲያጡ መጥፎ አልነበረም ፡፡
ዘዳግም(20፡ 7)፡ ዋይርስቤ የገለፀው ሰዎስተኛው ነፃ ማድረግ ስለ ሙሽርና ነበር “ የታጨው ወታደር ወደ ቤቱ ሄዶ እንዲያገባ ይፈቀድለታል “ ፤ ዘዳ(24፡ 5) የሚለው “ አዲስ ሚስትም ያገባ ሰው ወደ ጦርነት አይሂድ ነገርም አይጫኑበት ፤ ነገር ግን አንድ አመት በቤቱ በፈቃዱ ይቀመጥ የወሰዳትንም ሚስቱን ደስ ያሰኛት ፡፡” በመስክ ተልኮ ጊዜ ድርጅትን ለማነሳሳት መምጣት የሚፈልጉ ሁለት ወጣት ወንዶችን ጠይቀን ነበር ነገር ግን ሁለቱም የሚያገቡ ነበሩ(ሊያገቡ ነበር) ፤ መለስናቸው ምክንያቱም በዚያን ጊዜ በወር አንድ ሳምነት መንገድ ላይ ከመሆናቸው በፊት ለእነርሱ ትዳራቸውን መመሰረት በታማ አስፈላጊ እንደነበርን ስላሰብን ፡፡ ይህ የሚመስለው ወደ ዚያ ሀሳብ ያመለክታል፡ ይህን ከማድረጋችሁ በፊት ትዳራችሁን መሰረት አስይዙ ፡፡
ዘዳግም(20፡ 8-9)፡ ይህ ሌላ ነፃ ማድረጊያ ነው ፤ ወታደሩ የሚፈራ ወይም የሚሸበር ከነበር ወደ ቤቱ ይሄዳል ፡፡ ኮንስታብል የሚለው “ የእግዚአብሄር አላማ በእግዚአብሄር ተስፋ እንደሚያሸነፉ በራስ መተማመን በነበራቸው ምርጥ ወታደሮች ብቻ መጠቀም ነበር ፡፡ “ እግዚአብሄር ትልቅ ጦር አላስፈለገውም ምክንያቱም ስራው በእርሱ ነበር፡፡ አስታዉሱ በጌዲዎን ምን እንደተፈጠረ ? በ32,000 ወንዶች ጀመረ ነገር ግን 22,000 ተመለሱ (መሳ 7፡ 1-3)፡፡ በማሸነፍ ክብር ለመቀበል ለእግዚአብሄር በጣም ብዙ ነበሩ ፡፡
ዘዳግም(20፡ 10-15)፡ በእያንዳንዱ ከተማ በመጡ ጊዜ በመጀመሪያ በሰላም ያቀርባሉ ፤ ሰላሙን ከተቀበሉ የእስራኤላዊያን ባሪያዎች ይሆናሉ (ቁጥር 10-11) ፤ ከተማይቱ ሰላም ካላቀረቡ(የሰላምን ምርጫ ካልተቀበሉ) እስራኤላዊያን የቶርነት ዘመቻ ያደርጋሉ ሁሉንም ወንዶችም ይገድላሉ (ቁጥር 12-13) ፡፡ ከወንዶች ጎን ሁሉንም ነገር - ሴቶችን፣ ልጆቻቸውን፣ ሁሉንም ከብቶች እና በከተማዋ የነበረውን ሁሉ ለመበዝበዝ ይቀመጣል(ይጠበቃል) (ቁጥር 14) ፡፡ ይህ በሩቅ ነበሩት ከተሞች ላይ የተፈፀመው ነበር (ከነዓን ከተሞች ላይ አይደለም) ፡፡
ዘዳግም(20፡ 16-18)፡ ወደ ከነዓን ከተሞች በሄዱ ጊዜ ሁሉንም ነገር ያጠፋሉ (ቁጥር 16-17) ፤ ይህ ከነበር ከነዓናዊያን አስራኤላዊያንን በሀሰተኛ አምላኮቻቸው አይበክሉዓቸውም (ቁጥር 18) ፡፡
ዘዳግም(20፡ 19-20)፡ አስራኤላዊያን ለከተማዋ ለረጅም ጊዜ ምሽግ ባስቀመጡ ጊዜ ዛፎቹን አይቆርጡም ምክንያቱም ዛፎቹ ምግብ ሊሰጡዓቸው ይችላሉ ፤ ነገር ግን ምግብ የማይሰጡትን ዛፎች መቁረጥ ይችላሉ ወይም ለመስራት ያስፈልጉዓቸው የነበሩትን “ እስክታሸንፉት ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ “(ቁጥር 20)፡፡
መዝጊያ
ለጦርነት እግዚአብሄር እንዲዘጋጁ እያደረገ ነበር ፡፡ እውነታው በነቃን ጊዜ ሁልጊዜ በብዙ በጦርነት ነን ፤ ውጊያ ላይ እንዳላችሁ ታውቃላችሁ ?
ኤፌ(6፡ 12-18)፡ “ መጋደላችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለምና ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካላ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር ነው እንጂ ፡፡ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃዎም ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሄርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሱ ፡፡ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ ፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፋ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሱ ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው ፡፡በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ ፡፡”
ዘዳግም 19 የፃፈው የመማፀኛ ከተሞች ምን እንደነበሩ ፤ ዘዳግም 20 ወደ ውጊያ ማን እንደሚሄድ ይገልፃል ፡፡ ካህናቱ መሀከለኞች ይሆናሉ ፡፡ በጦርነት ለመዋጋት የሚያስችሉ ሰዎስት ነፃነቶች አሉ፡ ቤት፣ ምርት እና የጫጉላ ጊዜ መጨረስ ፡፡
Eugene Merrill, Deuteronomy, p. 282; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes, p. 122; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/deuteronomy.pdf.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 1999), p. 255.
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs: David C. Cook, 2001), p. 428.
Merrill, p. 283-284.
Wiersbe, p. 428.
Radmacher, Allen, and House, p. 255.
Wiersbe, p. 428.
Constable, p. 123.
ጥያቄዎች
-
ሙሴ ቀድሞ በዮርዳኖስ ምስራቅ በኩል ሰዎስት የመማፀኛ ከተሞችን አስቀምጦ ነበር (ዘዳ 4፡ 41-43) ፤ በዚህ ጊዜ ምን ያክል ከተሞች እንዲለዩ እግዚአብሄር አዘዘ (ዘዳ 19፡ 2; ኢያ 20፡ 7-8) ? ለመማፀኛ ከተሞች ምንድን ነበር አላማው (ዘዳ 19፡ 3-6; ዘኁ 35፡ 9-28) ? እነዚህ የመማፀኛ ከተሞች እንዴት አድርገው ወደ ኢየሱስ ያመለክታሉ ? (መዝ 46፡ 1; ዕብ 6፡ 18)
-
እግዚአብሄር ግዛታቸውን ሲያሳድግ እስራኤላዊያን ምንድን ያደርጋሉ (ዘዳ 19፡ 8) ? ይህን የሰፋ ምድር የማግኘት የእግዚአብሄር ሁኔታ ምንድን ነበር ? (ዘዳ 6፡ 5; 11፡ 22)
-
ዘዳ(19፡ 16-20) የዘጠኙ ትዕዛዞች ልብ(ዋና) ነው (ዘጸ 20፡ 16) ፡፡ በአንድ ሰው ላይ ሀሰተኛ ምስክር ሆኖ መቆም ቅጣቱ ምን ነበር ? በራሳችን ሀገር ላይ እየተካሄደ ባለው በሁሉም ነገር(ክስ) ጥቂቱ እወነት ጥቂቱ ደግሞ ዉሸት ነው የሀሰት ክስን ለመከላከል ይህ ህግ ዉጤታማ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በዙሪያቸዉ ያሉትን ጠላቶቻቸውን እንዳይፈሩ ነገራቸው ምክንያቱም እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ነበር ፤ ዘዳ (20፡ 1-4) እንዴት ልትወስዱት እና ለራሳችሁ ሁኔታ ላይ ልተገብሩት ትችላላችሁ ? ወንጌልን ለማካፈል ይህን እንዴት ልተገብሩት ትችላላችሁ ?
-
እግዚአብሄር ሰጥቶአቸው በነበረው ከተሞች ውስጥ እንዲያደርጉ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ምንድን አዘዛቸው (ዘዳ 20፡ 16-17) ? ያን የሚመስል ነገር እንዲሰሩ የእርሱ ምክንያቱ ምንድን ነበር ? (ዘዳ 9፡ 5; 12፡ 30)
-
በዘዳ(19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 20:3-4
“He is to say to them: ‘Listen, Israel: Today you are about to engage in battle with your enemies. Do not be cowardly. Do not be afraid, alarmed, or terrified because of them. For the LORD your God is the One who goes with you to fight for you against your enemies to give you victory.’”
እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት በተዘጋጁ ጊዜ፥ ፊት ለፊታቸዉ ስለሚገጥማቸዉ ጦርነት አዘጋጃቸዉ። ሙሴ ልክ እንደ የጦርነት መምርያ የሚመስል ነገር ሰጣቸዉ።
አካላዊ ጦርነት ባላበት ፊት ለፊት ላይ ለጦርነት ላትሰለፍ ትችላለህ። ነገር ግን እንደ ክርስቶስት አማኝ በየቀኑ፥ ከዓለም፣ ከራስህ ስጋ እና ሰይጣን ጋራ መንፈሳዊ ጦርነት ላይ ነህ። ፀንተህ በመቆም፥ ራስህን በእግዚአብሔር የጦር እቃ ማስታጠቅ አለብህ። እግዚአብሔር በሁሉም ላይ አሸናፊ ነዉ! ጠላቶችህን ከአንተ ጋራ አብሮ ለመፋለም ደግሞ የተስፋ ቃል ይገባልሃል! ዛሬ፥ የምትፈራበት ሳይሆን፥ ፀንተህ የምትቆምበት ቀንህ ነዉ! በሚገጥምህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይረዳሃል። በክርስቶስ ኢየሱስ የምታሸንፍበት ታላቅ ቀን ይሆናል!
"እስራኤል ሆይ፥ ስሙ፤ ዛሬ ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ትቀርባላችሁ፤ ልባችሁ አይታወክ፥ አትፍሩ፥ አትንቀጥቀጡ፥ በፊታቸውም አትደንግጡ፤ ከእናንተ ጋር የሚሄድ፥ ያድናችሁም ዘንድ ጠላቶቻችሁን ስለ እናንተ የሚወጋ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና።"
ኦሪት ዘዳግም 20:3-4
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 20:7፦ "እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።"
- ትንቢተ ኢሳይያስ 41:10፦ "እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።"
- ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:12-13፦ "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ። ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 102
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።