Unsolved Murders, Captured Women & Rebellious Sons
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና በዘዳግም 20 ለጦርነት ስለ እስራኤላዊያን ዝግጅት ተምረናል ፡፡ እስከ ዘኁልቁ መፅሀፍ ጦሩ አልተዋቀረም ነበር ነገር ግን በመጠኑም መመሪያ ተሠጦቶአቸው ነበር ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም(21፡ 1-9)፡ እግዚአብሄር ሰጥቶአቸው በነበረው ምድር ላይ በነፍስ ግድያ የተጠቃ ሰው ቢገኝ እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ተግባረዊ ትዕዛዝ ሰጣቸው ምዕራፍ 21 ምን እንደሚደረግ በመግለፅ ይጀምራል ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው ኃጢዓቱ “ምድሪቱን ያረክሳታል ” ፤ በምድሩ ላይ ደም ከነበረ የሆነ ሰው ለዚያ ማሰርየት ይኖርበታል ፡፡ ተጎጂው ተገኝቶ ከነበር ፈራጆች(አለቆች) እና ሸሽማግሌዎች ለተጎጂው ኃላፊነቱን መውሰድ የነበረበትን ለማየት ወደ ቅርብ ከተሞች ርቀቱን ይለካሉ (ቁጥር 2) ፡፡ ያልተፈቱ ጉዳዮች ለዛች ምድር ከባድ የሚሆን ችግር ሊያመጡ ይችላሉ (ዘፍ 4፡ 10-12; 9፡ 5-6; ዕብ 12፡ 24; መዝ 9፡ 12 እና ኢሳ 26፡ 21) ፡፡
ለተጎጂው ቅርብ ከተሞች ሽማግሎዎች ቀንበር ያልተጫነባት ወይም ያልተጠቀሙባትን ወጣት ላም ያመጣሉ (ቁጥር 3) ከዚያም ሳያቆአርጥ ወደ ሚፈስ ወንዝ በማምጣት አንገቶአን ይሰብራሉ (ቁጥር 4) ፡፡ ካህኑ ወደ ፊት እንዲመጣ እና በረከትን እንዲያውጅ እና መሪነትን እንዲሰጥ ታዝዞ ነበር (ቁጥር 5) ፡፡ ከዚያም ሁሉም ሽማግሌዎች በኪደሩአ ላይ በወንዙ እጆቻቸውን ይታጠባሉ (ቁጥር 6) ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው በማህበሩ ላይ የሚያርፈውን ጉድለት እያስወገዱ ነበር ለዚያም ለጥፋታቸው አንገቶአን በመስበር እና ይቺን ጊደር በማቅረብ ስርየት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ሽማግሌዎቹ ከመርከሳቸው እራሳቸውን እያነፁ ነበር(ዘሌ 18፡ 24-25) ፤ “ ይህንን ደም እጆቻችን አላፈሰሱም አይኖቻችንም አላዩትም “ እያሉ እንዲያዉጁ ታዘዋል በዚህም ለፈሰሰው ደም ከኃላፊነት ነፃ ይሆናሉ (ቁጥር 7) ፡፡ ኃጢዓት ወደ ሞት ይመራል ፤ ኢየሱስ ለእኛ ያደረገው ይህ ነው ፤ እዚህ እንደሞተቸው ጊደር ኢየሱስ ለኃጢዓታችን ሞቶአል (ሮሜ 6፡ 23; 5፡ 12; ዕብ 9፡ 13-14; ዮሐ 1፡ 29; 1ዮሐ 4፡ 14; ኤፌ 5፡ 25-26; ኢሳ 53፡ 8) ፡፡ ኢየሱስ ለእስራኤል ሞቶአል ፡፡
ለእግዚአብሄር የእስራኤላዊያን ፀሎት ህዝቡን ይቅር እንዲል እና ይህን በእነርሱ ላይ እንዳያፀና ነበር (ቁጥር 8) ፤ ደግሞም ከፈሰሰው ከንፁሁ ደም ጥፈተኛነት እራሳቸውን እንዲያነፁ ተነግሮአቸው ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ ላደረግነው ለራሳችን ኃጢዓት የምናፈሰው ብቸኛው መንገድ ወደ ክርሰቶስ እና ለእኛ ወደ አፈሰሰው ደም መመለስ ነው ፡፡
ዘዳግም(21፡ 10-14)፡ ቁጥር 10-14 የተያዙ ሴቶችን በትክክል ስለመያዝ ትዕዛዞችን ይሰጣሉ ፡፡ እስራኤላዊያን በጦርነት ላይ እያሉ የጠላቶቻቸውን ሚስቶች ካዩ እን የራሳችው እንድትሆን ከፈለጉ ቤታቸው ይወስዱዓታል፣ ፀጉሩዓን ትላጫለች በተጨማሪም ጥፍሮቾአን ትቆርጣለች (ቁጥር 10-12) ፤ ከዚያም የቀድሞ ልብሶቾአን ታስወግዳለች፣ በእስራኤላዊያንም ቤት ትኖራለች ከዚያም ለቤተሰቦቾአ 30 ቀን ታዝናለች ፤ 30 ቀናቶቹ ባለቁ ጊዜ እስራኤላዊው እንደ ሚስት መውሰድ ይችላል (ቁጥር 13) ፡፡ እስራኤላዊው ካልረካ(ደስተኛ ካልሆነ) እንድትሄድ ይፈቅድላታል ነገር ግን ለገንዘብ ሊሸጣት አይችል (ቁጥር 14) ፡፡ ከትዳር የመዉጫ መንገድ ነበራቸው ግን ሚስትን በመሸጥ አልነበረም ፡፡
ዘዳግም(21፡ 15-17)፡ ቁጥር 15-17 የበኩር ልጅ መብቶችን ያሳያሉ ፡፡ አንድ ሰው አንድ የተወደደች እና አንድ ያልተወደደች ሁለት ሚስት ካሉት ሁለቱም ወንድ ልጆች ካላቸው ያልተወደደችዉ ሚስት ልጅ በኩር ከነበር ለሁለተኛው ልጅ አድሎ ማሳየት አይችልም (ቁጥር 15-16) ፡፡ በዚያ ፋንታ ሰውየው በውልደት ቅደም ተከተል በኩሩን ዕውቅና መስጠት አለበት የውርሱንም ሁለት እጥፍ ይሰጣል(ቁጥር 17) ፡፡
ዘዳግም(21፡ 18-21)፡ የመጨረሻው ትዕዛዝ ስለ አመፀኛ ልጅ የሚያወሳ ነበር - አስቸጋሪ ልጅ (ቁጥር 18) ፡፡ አመፀኛው ልጅ ለእናቱ ወይም ለአባቱ የማይሰማ ከሆነ እና በቅጣትም ለመቀየር እምቢ ካለ ከዚያ በመቀጠል ቤተሰቦች ሽማግሌዎች ከነበሩበት ወደ ከተማዋ በር ያመጡታል(ቁጥር 19) ፡፡ ልጃቸው እልከኛ እና አመፀኛ፣ ስስታም እና ሰካራም እንደነበር ለሽማግሌዎቹ ከነገሩዓቸው በኃላ የከተማዋ ሰዎች እስኮሞት በድንጋይ ይወግሩታል (ቁጥር 20-21) ፤ ከራሳቸው እና ከሁሉም እስራኤል ክፉውን እንዲያስወግዱ ተነግሮአቸዋል ፡፡ ዋይርስቤ የአንድ ሰው ኃጢዓት መላው ህዝብ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አመልክቶአል ፡፡
በአባካኙ ልጅ ታሪክ ላይ (ሉቃ 15፡ 11-13) ልጁ አመፀኛ ነበር፣ ውርሱን ወሰደና ክፉ ህይወት ለመኖር ተወ ፡፡ ልጁ ተመልሶ በመጣ ጊዜ አባቱ ወጥቶ ተቀበለው (ቁጥር 15፡ 20) ፤ ምናልባት በድንጋይ መወገር ነበረበት ፡፡ ኢየሱስ ይህን ስዕል በሰጠ ጊዜ ልጁ የሚገጥመውን ቅጣት አድማጮቹ ያውቃሉ ፤ ነገር ግን በአባቱ በመታቀፍ ከዚያ ቅጣት ድኖ ነበር ፡፡ አባታችን በእጆቹ ይዞናል ስለዚህ የሚገባን ሞት አያገኘንም ፡፡
ዘዳግም(21፡ 22-21)፡ ማናኛውም ሞት የሚገባው ጥፋት ጥፋተኝነት ቢገኝበት እና ቢፈረድበት ሰውነቱን በዛፍ ላይ ስቀለው በዚያን ምሽት አውርደህ ወስደህ ቅበረው ፡፡ ማንኛውም በዛፍ ላይ የሚሰቀል በእግዚአብሄር ርግምን ስር ነበር ፡፡ የዚህ ፍላጎቱ ለእግዚአብሄር ህጎች ላለመታዘዝ ለእስራኤላዊያን ፍራት ለማምጣት ነበር ፡፡ ይህ ምዕራፍ እንደ እርስት አድርጉ እግዚአብሄር ሰጥቶአቸው የነበረውን ምድር ማርከስ የለባቸውም በሚል ንግግር ይጨርሳል ፡፡
መዝጊያ
ለእኛ ያንን ቦታ አንድ ሰው ብቻ ወሰደ ፤ ኢየሱስ በእርግማን ተወሰደ በእንጨትም ተሰቀለ፡
ገላ 3፡ 13፡ “ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተፅፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆነ ከእግ እርግማንም ዋጀን “፤ ኢየሱስ እርግምንን ወሰደልን ስለዚህ በረከት ሊኖረን ችሎአል(ይችላል) ፡፡
ሐዋ 5፡ 30፡ “ እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሳው ፡፡”
1ጴጥ 2፡ 24፡ “ ለኃጢዓት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ እራሱ በስጋው ኃጢዓታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ ፡፡ “
እርግማንን በመውሰድ ኢየሱስ ፈወሰን ፤ ክርስቶስ ዋጀን ፤ ራሱ ኃጢዓታችንን ተሸከመ ፡፡ ሁልጊዜ ህጉ ወደ መሲሁ ያመለክታል ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 430.
Wiersbe, p. 420.
Wiersbe, p. 432.
ጥያቄዎች
-
እስራኤላዊያን ከማህበራቸው ውስጥ የግድያ ጥፋትን ለማንፃት እንዴት ነበር ያደረጉት(የተሸሙት) ? (ዘዳ21፡ 1-9)
-
ዘዳ(21፡ 15-17) የበኩር ልጅን ክብር እና በትክክል የእርሱ የነበረውን ውርሱን መስጠትን ይጠቅሳል ፤ እግዚአብሄር ይህን ህግ የከበበት(ያኖረበት) ጥቂት ምሳሌዎች ምንድን ናቸው ? አድሎ በሚመስል ለምን እንዳሳየ ምን ታስባላችሁ ? (ዘዳ 10፡ 17; 1ሳሙ 16፡ 6; 1ዜና 5፡ 1-2; ሮሜ 2፡ 11; 9፡ 10)
-
አመፃኛ በነበረ ልጃቸው ላይ ቤተሰቦቹ ምንድን ያደርጉ ነበር ? (ዘዳ 21፡ 18-21) ፤ በመፅሀፍ እስካሁን ይህ መፈፀሙን የሚያመላክት የለም ግን በእንዲህ አይነት ቅጣት ላይ የእንንተ ሀሳብ ምንድን ነው ? በእስራኤላዊያን የተጠቀሙአቸውን እነዚህን ተመሳሳይ ቐንቐዎች (አመፅ እና እምቢተኛ(ግትር)) እንዴት ታዩአቸዋላችሁ ? (መዝ 78፡ 8; ኤር 5፡ 23)
-
በዘዳ(21፡ 22-23) ተፅፎ የነበረውን ኢየሱስ እንዴት አድርጎ ፈጸመ ? (ማቴ 27፡ 57-58; ዮሐ 19፡ 31; 2ቆሮ 5፡ 21; ገላ 3፡ 13)
-
በዘዳ(22፡ 22) አንድ ሰው ከአንዲት ሴት ጋር ዝሙት ከፈፀመ ሁለቱም ይሞታሉ ፤ በቤተ ክርስቲያን በአመንዛራ ጉዳይ ጳዉሎስ እንዴት ገለፀው (1ቆሮ 5፡ 1-13; 6፡ 9-13) ? እነዚያ ሰዎች ንስሀ ከገቡ ቤተ ክርስቲያን እንዴት መመለስ ይጠበቅባታል ? (2ቆሮ 2፡ 5-11)
-
በዘዳ(21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 21:20-21
“They will say to the elders of his city, ‘This son of ours is stubborn and rebellious; he doesn’t obey us. He’s a glutton and a drunkard.’ Then all the men of his city will stone him to death. You must purge the evil from you, and all Israel will hear and be afraid.”
ሙሴ ለእስራኤላዉያን ከሰጣቸዉ መመሪያዎች ዉስጥ እንቢተኛ እና አመፀኞች ልጆችን የሚመለክት ህግ እና ቅጣት አካቷል። ልጆች ወላጆቻቸዉን በማይታዘዙበት፣ ሰካራሞችና በላተኞች በሚሆኑበት ወቅት፥ ቤተሰቦቻቸዉ ልጆቻቸዉን ወደ ከተማይቱ ሽማግሌዎች ይዙዉ መሄድ ነበረባቸዉ። ሰካራም ማለት በመጠጥ ብዛት ተጎድቶ፥ የራሱን ባህርይ መቆጣጠር እስኪያቅተዉ መድረስ ማለት ነዉ። በላተኛ ማለት በጣም ለሆነ ነገር የሚታይ ትልቅ የሆነ ፍላጎት እና አቅም ያለዉ ማለት ሲሆን ፥ ይህም ለምግብ፣ ለመጠጥ፣ ለሥራ እና ለቁሳዊ ነገር ሊሆን ይችላል። ሁለቱም በላተኛ እና ሰካራሙ፥ ለደስታቸዉ ከእግዚአብሔር ይልቅ ከልክ ባለፈ ሌሎች ነገሮችን የሚፈልጉ ናቸዉ።
የአዲስ ኪዳን አማኞችም እንቢተኞችና አመፀኞች ሊሆኑ ይችላሉ። ሰይጣን ከልክ በላይ መብላትን፣ ከመጠን በላይ መሥራትን፣ ከልክ በላይ መጠጣትን፣ ብኩን መሆንን ትክክለኛ እንደሆነ በማስመሰል ሊፈትንህ ይችላል። ይህም ቤተሰቦቻቸዉን መስማት እንዳቆሙ እንቢተኛ እና አመፀኞች ልጆች፥ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት እስከምታቆም ድረስ ሊያደርስህ ይችላል። እግዚአብሔር በየቀኑ እርሱን እንድትሻዉ ይፈልጋል! በሙሉ ልብህ ስትፈልገዉ ደግሞ ታገኘዋለህ! የእግዚአብሔር እጆች ተዘርግተዉ ወንድ እና ሴት ልጆቹን፥ በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተዉ ፍቅሩ ለመቀበል ዝግጁ ናቸዉ። ዛሬ፥ የጌታን ድምፅ ስማ! ለደስታህም ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተመለስ!
"የከተማውንም ሽማግሌዎች፦ ይህ ልጃችን እልከኛና ዓመፀኛ ነው፥ ለቃላችንም አይታዘዝም ስስታምና ሰካራም ነው ይበሉአቸው። የከተማውም ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፥ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።"
ኦሪት ዘዳግም 21:21-22
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 81:11-13፦ "ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥ እስራኤልም አላዳመጠኝም። እንደ ልባቸው ሥራ ተውኋቸው፥ በልባቸውም አሳብ ሄዱ። ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፤"
- የማቴዎስ ወንጌል 5:6፦ "ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።"
- የሉቃስ ወንጌል 15:20፦ "ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 103
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።