The Pentateuch Deuteronomy

Lists to Live By

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 104 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እነዚህ የተለያዩ ነገሮች ብዙ ዝርዝሮች ለእስራኤላዊያን እንደ መጠበቂያ(መምሪያ) ተፈጥረው የነበሩ ናቸው ፡፡ በጭቃ ላይ እየተጎተትን እንደሆነ ይሰማል ፤ ስለ ሚጠቃለሉ እና ስለ ማይጠቃለሉ፣ ስለ ሰፈሩ መንፃት፣ ስለ ጎረቤቶቻቸው ዘር እና ስለ ትዳር እናወራለን - እናም ሁሉም እንደ ህጋዊነት ያሰማል ፤ ነገር ግን ከዚያ ቦኃላ የልባችን ሄኔታ ምንድን ነው ፡፡

ትምህርት

ዘዳግም 23፡ ይህ ምዕራፍ ወደ ማህበሩ የሚካተቱትና እና የማይካተቱትን አባላት፣ የሰፈሩን መንፃት፣ ከጊዜያዊ ባሪያዎች ጋር እንዴት እንደሚስማማ፣ ጋለሞታነትን የማስወገድ አስፈላጊነትን፣ ስለ ብድር ወለድ፣ ስለትን መጠበቅ ስላለው ጠቀሜታ እና ስለ ባልንጀራ ፍሬ እንዴት እንደሚያደርግ መመሪያዎችን ይሸፍናል ፡፡

ዘዳግም(24፡ 1)፡ በፍቺ ላይ ለማስተማር በፍፁም ቀላላ አይደለም እናም እነዚህ ደንቦች ለመቀበል ቀላል አይደሉም ፡፡ መጀመሪያ አንድ ሰው ካገባ እና ስለ ሚስቱ ተገቢ ያልሆነ ነገር ቢያገኝባት የፍጪ ወረቀትን መፃፍ ይችላል ፤ የወሲባዊ ኃጢዓት ወይም የፀና ወሲባዊ ግንኙነትን እንዳይኖራቸው የሚከለክል የወር አበባ ወጥ አለመሆን ሊኖርባት ይችላል ፡፡ በማቴ(19፡ 3) ፈሪሳዊያን ኢየሱስን አንድ ሰው ሚስቱን መፍታት የሚችልበት ምክንያት ሊኖር ይችላል ብለው ጠየቁት ፤ በአዲስ ኪዳን ለፍቺ ሁለት ምክንያቶች ብቻ አሉ፡ ባሎአ ከሞተባት ሚስት መሄድ ትችላለች (ሮሜ 7፡ 1-3) እና በዝሙት ምክንያት(ዘዳ 22፡ 22) ፡፡ ፍቺ ምርጫ አልነበረም ፡፡ ጥቂት ምርጥ ታሪኮች የመጡት በባለቤቶች በመሰራት ከዝሙት ቦኃላ ትዳራቸውን በመመለስ ነው ፡፡

ሴቶአ የሌላ ሰው ሚስት ብትሆን እና ሁለተኛውም ሰው ደግሞ ቢጠላት፣ ቢፈታት እና ከእርሱ ቢልካት ወደ መጀመሪያዉ ባሎአ ተመልሳ መሄድ አትችልም ምክንያቱም ረክሳለች (ቁጥር 2-4) ፡፡ ትዳርን ሁለት በአንድ ላይ እንደተጣበቁ ቁራጭ እንጨቶች ማየት እንችላለን ፡፡ ቁራጮቹ ከተለያዩ ለንፁህ መለያየት ምንም መንገድ የለም ምክንያቱም ሁልጊዜ በአንድኝው እንጨት ላይ የአንዱ አካል ይኖራል ፤ ያ ማለት የእናንተ አካል እስካሁን ወሲባዊ ግንኙነት ካደረጋችሁት እያንዳንዱ ሰው ጋር አለ ፡፡

ዘዳግም(24፡ 5)፡ አድስ ያገባ ወንድ ለመጀመሪያው አመት ወደ ጦርነት አይሄድም ስለዚህ ትቶአት ከመሄዱ በፊት ሚስቱን ማስደሰት ይችላል ፡፡

ዘዳግም(24፡ 6-9)፡ እስራኤላዊያን የቤተሰባቸውን መተዳደሪያ ደህንነት ለመጠበቅ ህይወታቸውን የሚሰሩበት ስለ ነበር ለእዳ እንደ ዋስትና ወፍጮ ወይም መጅ እንዳይወስዱ ታዘዙ (ቁጥር 6) ፡፡ የሆነ ሰው ከእስራኤላዊያን አንድ ወንድሙን ቢያግተው ይሞታል ስለዚህ ያ ሞት ክፉውን ከማህበሩ ያስወግዳል (ቁጥር 7) ፡፡ የሆነ ሰው የሚተላለፍ የቆዳ በሽታ ከነበረበት እስራኤላዊያን ሌዋዊይ ካህን እንዳዘዛቸው ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ እንዲያደርጉ ታዘዙ (ቁጥር 8) ፡፡ አስታውሱ እስራኤላዊያን ከግብፅ ከወጡ ቦኃላ በጉዞ ላይ እግዚአብሄር ለማሪያም ያደረገውን በለምፅ ተመትታ ነበር (ቁጥር 9) ፡፡

ዘዳግም(24፡ 10-13)፡ ቀጣይ የተቀመጡት ትዕዛዦች ለማን ያበድሩ እንደነበር የህዝቡን ምልከታ ያሳያል፡ (1) የሆነ ሰው ብድር ሲጠይቅ እንደ ዋስትና አቅርቦት የነበረውን ለመሰብሰብ ወደ ቤቱ አይገቡም (ቁጥር 10); (2) ለአበዳሪው ዋስትናውን እውጪ ይመጣል እዉጪም ይጠብቁታል (ቁጥር 11); (3) ብድር የተቀበለው ሰው ድሀ ከነበር እንደ መያዣ ልብሶቻቸውን የተቀበላቸው ሰው በዚህ መተኛት አይችልም ግን ከብርድ መከላከል እንዲሰጣቸው(ከብርድ እንዲከላከልላቸው) በእያንዳንዱ ምሽት መለሰው ይሰጣሉ (ቁጥር 12) እና (4) ተበዳሪው እንደ ዋስትና ያለውን ብቸኛ ልብሶች አይቀበሉም (ቁጥር 13) ፡፡

ዘዳግም(24፡ 14-18)፡ ድሀ የነበሩ ተቀጥረው የሚሰሩ ቀን በቀን ይከፈላቸዋል (ቁጥር 14-15) ፡፡ ለልጆቻቸው ቅጣት አባቶች ወይም ልጆች ለአባቶቻቸው ቅጣት አይገደሉም (ቁጥር 16) ፤ ይልቁንስ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ኃጢዓት ተጠያቂ ይሆናል (ኢያ 7፡ 24-25; ዘጸ 20፡ 5) ፡፡ ኃጢዓት ወደ ሞት ይመራል ግን እግዚአብሄር ይመስገን ፍቅሩን በማምጣት ከሞት ተጠነቀቀልን ፡፡ ፍትህ ለእንግዶች(ለሌላ አገር ሰው)፣ የቲም እና መበለቶችን ይሰጣቸዋል (ቁጥር 17) ፡፡ እስራኤለዊያን እግዚአብሄር ከመዋጀቱ በፊት በግብፅ ባሪ እንደነበሩ ምን እንደሚመስሉ ያስታውሳሉ እነዚህንም ቡድኖች በዚያ መሰረት ያስተናግዳሉ (ቁጥር 18) ፡፡

ዘዳግም(24፡ 19-22)፡ እስራኤላዊያን ለምፃተኝቹ፣ ለየቲሞች እና ለመበለቶች እንዲኖራቸው ነዶ እንዲተውላቸው ታዘዙ (ቁጥር 19) ፤ እና በወይራ ቅርንጫፎቹ ላይ ከከረከሙ ቦኃላ ወይም ፍሬውን ከለቀሙ ቦኃላ የወይኑን ለእነርሱእንዲሆን ይተዉላቸዋል (ቁጥር 20-21) ለመፃተኞች፣ ለየቲሞች(ድሀ አደጎች) እና ለመበለቶች የእግዚአብሄርን ትኩረት ያሳይል ፡፡ እግዚአብሄር እንደገና እስራኤላዊያንን ለንዴ ባሪያዎች እንደነበሩ እና በእርሱ ብቻ እንደተዋጁ አሳሰባቸው ፤ ስለዚህ እንዳዘዛቸው ያደርጋሉ(ቁጥር 22) ፡፡

እነዚህ ሁሉ ትዕዛዞች እስራኤላዊያን እንዴት እርስ በእርሳቸው በሚገባ እንደተያዩ በልባቸው ሁኔታ ላይ ያወሳል ፡፡ ኢየሱስ ለእነዚህ ትዓዛዞች አድስ እይታ አመጣ ፤ ማቴ (5፡ 17-20) የሚለው “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም ፡፡ እውነት እላችኃለሁ ሰማይ ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም ሁሉ እስኪፈፀም ድረስ ፡፡ እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት እንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግስተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል ፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሰተ ሰማያት ታላቅ ይባላል ፡፡ እላችኃለሁ ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳዊያን ጽድቅ ካልበለጠ ወደ መንግስተ ሰማያት ከቶ አተገቡም ፡፡”

ማቴ (5፡ 21-48)፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ህግ ከመግደል ጋር በተያያዘ ብስጭትን በመጨመር ዘረጋው ፤ በተመሳሳይ ኢየሱስ ዝሙትን በማስፋት ምኞትን ጨመረው፣ በፍቺ ላይ ቀጥተኛ መመሪያ አስቀመጠ በተጨማሪም በቀልን አገደ (ቁጥር 21-42) ፤ ከዚያም ኢየሱስ ባልንጀሮቻችሁን ውደዱ የሚለውን የእግዚአብሄርን ህግ ጠላታችሁንም ደግሞ ውደዱ የሚለውን በማካተት አሰፋው (ቁጥር 43-48) ፡፡በእነዚህ ሁኔታ መሄድ የምንቸ ልበት ብቸኛው መንገድ በህጋዊነት ያልተመሰረት የተቀየረ ልብ ሲኖረን ነው ፡፡

በማቴ (23፡ 27) ኢየሱስ የተናገረው “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳዊያን በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጥ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ ወዮላችሁ ፡፡”

በሮሜ (8፡ 10) ጳዉሎስ የፃፈው “ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢዓት ምክንያት የሞተ ነው መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው ፡፡” በህጋዊነት የውሸት መጎአዝ አትችሉም ፡፡ ኢየሱስ በውስጣችሁ ሁሉንም ነገር ለማድረግ ይፈልጋችኃል ፡፡ ፅድቅ የሚመጣበት ብቸኛው መንገድ እምነታችን በክርስቶስ ላይ እንጂ በራሳችን ካላደርግ ነው ፡፡

መዝጊያ

እንደገና ብዙ ደንቦችን እናወሳለን ፤ ዘዳግም 23 ወደ ጉባኤው ማን መግባት እንደሚችል፣ ስለ ሰፈር መንፃት፣ ስለ ጊዜያዊ ባሪያዎች፣ ስለ ገለሞታዎች፣ ስለ ብድር፣ ስለትን ስለ መጠበቅ እና ስለ ሚሰበሰብ ዘር ላይ ሄደንበታል ፡፡ ከዚያም ዘዳግም 24 በትዳር፣ በእዳ፣ በእገታ እና በቆዳ በሽታ ላይ ተነጋግረናል ፡፡ ሙሴ የሰዎችን ፍላጎቶች ጥንቃቄ በመውሰድ በተለየም የመፃተኞችን፣ የድሀ አደጎችን እና መበለቶችን አብራርቶአል ምክንያቱም እስራኤላዊያን በኑሮአቸው የእግዚአብሄርን ጥበቃ ተቀብለው ነበር ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ዘዳ(23፡ 19-20) እስራኤላዊያን ለአገራቸው ሰው ወለድ እንዳይቀበሉ(ወለድ እንዳይጭኑ) ታዘዋል ፤ ወለድ ሊከፍል የሚችለው ማነው ? ለምን ይህ ልዩነት ሆነ ? ለቅሬታው ወጤቱ ምን ነበር ?
  2. በዘዳ(23፡ 22) መሰረት ለእግዚአብሄር ተፈልጎ ያልነበር ወይም (በፍቃዱ/ሳይጠየቅ) ስለት ከተደረገ ለምን ሰዎች ያደርጉታል ? ለእግዚአብሄር ስለት አድርጋችሁ ታዉቃላችሁ ? ምን አነሳሳችሁ ?
  3. እግዚአብሄር እስራኤላዊያን መፋታትን ፈቅዶላቸዋል (ዘዳ 24፡ 1) ነገር ግን ኢየሱስ በማር( 10፡ 2-9) ፈሪሳዊያንን ምን ነገራቸው ? ይህን እንደ ተፃራሪ ታዩታላችሁ ? ለምነ ወይስ ለምን አታዩት ?
  4. በዘዳ(24፡ 16) እና ሮሜ(3፡ 23) መሀከል ግንኙነቱን ታዩታላችሁ ?
  5. ሁለቱንም ጥበቃን እና መስጠትን ያካተተ ከእንግዶች፣ ከድሀ አድጎች እና ከመበለቶች አንፃር የሙሴ ህግ ብዙ ጊዜ ስርዓትን ጠቅሶዓል ፤ ይህ በጣም ያስፈለገው ለምን ነበር ? ከእነዚህ ቡድኖች በአንዱ ተለይታችሁ ታውቃላችሁ ?
  6. በዘዳ(23-24) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Deuteronomy 24:19

“When you reap the harvest in your field, and you forget a sheaf in the field, do not go back to get it. It is to be left for the foreigner, the fatherless, and the widow, so that the LORD your God may bless you in all the work of your hands.”

እግዚአብሔር፥ እስራኤላዉያን በማህበረሰቡ ዉስጥ ያለዉን ችግር እንዴት እንደሚፈቱ እቅድ ነበረዉ። ከእርሻቸዉ ስንዴን በሚሰበስቡበት ጊዜ፣ ከወይራ ዛፍ ፍሬ በሚቆርጡበት ወቅት እና ከወይን ማሳ ወይንን በሚሰበስቡበት ወቅት፥ የተወሰነዉን ምርት መሰብሰብ ካልቻሉ፥ እዚያዉ እንዲተዉት ተነግሯቸዋል። ስለዚህ የቀረዉ እህል የሚሆነዉ፥ ለመፃተኞች፣ ወላጅ ለሌላቸዉ ልጆች እና ባልቴቶች ነዉ። እግዚአብሔር በተለየ መንገድ በማህረሰቡ ዉስጥ የተቸገሩ ሰዎችን እና እነሱን መንከባከብ እንዳለባቸዉ ተመልክቷል።

አከባቢህ ላይ ያሉትን መፃተኞች፣ ወላጅ አልባ ልጆች እና ባልቴቶች ለማየት ዓይኖችህን ክፈት። በአንተ አከባቢ ልትረዳዉ እና ልትከታተልዉ የምትችለዉ፥ እግዚአብሔር በልብህ ያስቀመጠዉ ሰዉ ማነዉ? ክርስቶስ አንተን እንደወደደህ አንተም እንዲሁ ሰዎችን እንድትወድ ይፈልጋል። ዛሬ፥ አከባቢህ ላይ ያሉትን መፃተኞች፣ ወላጅ አልባ ልጆች እና ባልቴቶች እንድትወድ እና እንድትንከባከባቸዉ ጌታ ለአንተ ያለዉን እቅድ ጠይቀዉ!

"የእርሻህን መከር ባጨድህ ጊዜ ነዶም ረስተህ በእርሻህ ብታስቀር፥ ትወስደው ዘንድ አትመለስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ፥ ለመጻተኛና ለድሃ አደግ ለመበለትም ተወው።"

ኦሪት ዘዳግም 24:19

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 82:3፦ "ለድሆችና ለድሀ አደጎች ፍረዱ፤ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ፤"
  • የዮሐንስ ወንጌል 13:34፦ "እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።"
  • የያዕቆብ መልዕክት 1:27፦ "ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 104