The Pentateuch Deuteronomy

Firstfruits, Tithe & Covenant Summary

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 25-26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 105 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በኦሪት(በህግ) በመጨረሻው መፅሀፍ ላይ ነን እናም ወደ አድስ ኪዳን ሽግግር ላይ ነን ፡፡ ከኦሪት ወደ ወንጌል እንሄዳለን ከዚያም ወደ ብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መፅሀፎች እንመለሳለን ፡፡

ትምህርት

ዘዳግም 25፡ የሚከተሉትን የሚያካትት የደንቦች ተጨማሪ ዝርዝሮች አሉን፡ በሰዎች መሀከል ፀብ ቢኖር እስከ 40 ጊዜ ሊገረፉ ይችላሉ ፤ የቤተሰብ አባል በሞተ ጊዜ እንዴት የቤተሰቡን ዘር እንደሚዳን ፤ ተገቢ መጠን እና ሚዛን ፤ እና በአሜሌቃዊያን ላይ በቀልን ፡፡

ዘዳግም(26፡ 1-4)፡ ምድሪቱን በወሰዱ ጊዜ የምድሪቱን በኩራት መሰብሰብ ያስፈልጋቸው ነበር በእቃውስጥም በማስቀመጥ እግዚአብሄር በሚያድረበት በመቅደሱ ውስጥ ያስቀምጣሉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚያመለክተው እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን የሚቀረው ምርት እንደሚደርስ እርግጠኛ መሆን ባይችሉም ወይም እንደ ልምድ የሚሰበስቡ ቢሆንም እንካን ለእነርሱ እንደሚሰጣቸው በእግዚአብሄር ላይ መታመናቸውን እንዲያሳዩ ፈለጋቸው ፡፡ ማን ያገለግል እንደ ነበር ለካህናቱ ይናገራሉ “ ዛሬ ለአምላክ ለእግዚአብሄር አስታውቃለሁ ለአባቶቻቸሁ ለመስጠት ወደ ወደ ማለላቸው ምድር ትገባለህ ፡፡” ከዚያም እነዚህን ስጦታዎች ይቀበላል ለእግዚአብሄርም በመቅደሱ ያስቀምጣቸዋል ፡፡ ዋይርስቤ ይህን እንደ “ የእግዚአብሄር መልካምነት ማወጅ “ ይጠቅሰዋል ፡፡

ዘዳግም(8፡ 11-19)፡ “ ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትዕዛዙንና ፍርዱን ስርዓቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሄርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ ፤ ከበላህና ከጠገብህ በኃላ መልካምም ቤት ሰርተህ ከተቀምጥህበት በኃላ የላምና የበግ መንጋ ከበዛልህ ቦኃላ ልብህ እንዳይጎአደድ ፤ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን እባብና ጊንጥ ጥማትም ባላብት ዉኃም በሌለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን ከጭንጫ ድንጋይም ውኃን ያወጣልህን ፤ በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግልህ ዘንድ ሊፈትንህ ሊያዋርድህም አባቶችህ ያላወቁትን መና በምድረበዳ ያበላህን አምላክህን እግዚአብሄርን እንዳትረሳ ፤ በልብህም ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ እንዳትል ፡፡ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያፀና ዘንድ ሀብት ለማከማቸት እርሱ ጉልበት ሰጥቶሀልና አምላክህን እግዚአብሄርን አስብ ፡፡ አምላክህንም እግዚአብሄር ብትረሳ ሌሎችንም አማልክት ብትረሳ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል ብታመልካቸውም ብትሰግድላቸውም ፈጽሞ እንድትጠፉ እኔ ዛሬውኑ እመሰክርባችኃለሁ ፡፡”

ዘዳግም(26፡ 5-10)፡ ያዕቆብ የሚንከራተት ሶሮያዊ እና የ12 ነገድ አባት ነበር ፤ በድርቅ ምክንያት ወደ ግብፅ ሄደ፡፡ የነበራቸውን ሁሉንም ነገር ወሰዱ -ሁሉም ቤተሰብ እና ሁሉንም ንብረታቸው (ዘፍ 46፡ 3-7) ፤ በጠቅላላ ከ70 ሰዎች ጋር ሄደ(ወረደ) ፡፡ ዘጸ (1፡ 7) የተመዘገበው፡ “ የእስራኤልም ልጆች አፈሩ እጅግም በዙ ተባዙም እጅግም ጸኑ ምድሪቱንም በእነርሱ ሞላች ፡፡” ግምቶች 70ዎቹ ወደ 2 ሚሊዮን ህዝብ እንደ ተባዙና ታላቅም ህዝብ እንደሆኑ ይናገራሉ ፡፡ በግብፅ በኩል የሄዱበት መከራና ጭፍጨፋ ህዝቡን ወደ መብዛት ይመራል (ዘጸ 2፡ 23-25) ፡፡ በአዲስ ኪዳንም ተመሳሳይ እውነት ነው ፤ ሁል ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ይገደሉ እና ይበተኑ ነበር በቁጥር በዝታለች ፡፡

እግዚአብሄር የእስራኤላዊያንን ማቃሰት እና ለቅሶ ሰማ ፤ ከግብፅም በጠንካራ እጁ ምልክት እና ድንቅ ወተት እና ማር ወደ ምታፈስሰው ምድር አመጣቸው ፡፡ ከተስፋይቱ ምድር በኩር እስራኤላዊያን ሁሉንም እግዚአብሄር አድርጎላቸው የነበረውን እንዲያስታውሱ እንዲያደርጉአቸው ለእግዚአብሄር ያቀርባሉ ፤ እግዚአብሄርን ለማምለክ በግንባራቸው ተደፉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የገለፀው “ ለአምልኮ በጣም የተለመደው የእብራዊያን ቃል በቀጥታ “ ለአንድ ሰው ለመስገድ መውደቅ ማለት ነው ፡፡” ወደ መሬት መደፋት አምልኮ እና ማክበር ያመለክታል ፡፡

ዘዳግም(26፡ 12-15)፡ዋይሰርቤ እነዚህን ቁጥሮች እንደ “ ታማኝነትና ለጋስነት የእምነት ቃል “ ለይቶታል ፡፡ በሰዎስተኛው አመት እስራኤላዊያን አስረኛውን ከፈለው በጨረሱ ጊዜ ለሌዋዊን፣ ለመፃተኛው፣ ለየቲሙ እና ለመበለት ይሰጣሉ - በጣም ይፈልጉዓቸዋል (ቁጥር 12) ፤ ከዚያም ይህንን በእግዚአብሄር ፊት ፈፀምን(አድርገናል) ይላሉ (ቁጥር 13) ፡፡ ደግሞም ከዚህ ምንም አይበሉም ነበር ወይም እንደ ከነዓናዊያን ለሞተ አያቀርቡም ፡፡ ይህ ማለት ኮንስታብል የጠቀሰው “ የእግዚአብሄር ህዝብ አሁን ባይጨብጡትም የተስፋውን በረከት ለመፈፀም በእርሱ መታመንን መቀጠል ይጠበቃባቸዋል ፡፡”

ዘዳግም(26፡ 16-19)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች እንደ “ መታዘዝ የእምነት ቃል “ ለይቶታል ፡፡ እስራኤላዊያን እነዚህን ትዕዛዞች በሙሉ ልባቸው እና ነፍሳቸው ይከተላሉ (ዘዳ 6፡ 5 - ሴማ(ዋና) ተብሎ ይጠራል) ፤ ይህም ደግሞ በማቴ(22፡ 34-39) የኢየሱስ ቐንቐ ነበር (ኤር 31፡ 33; ሕዝ 11፡ 19; 36፡ 26) ፡፡ ዋይስርቤ የገለፀው የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ የእምነት ወደ ምድሪቱ ወደ ፊት ያመለክቱ ነበር (ቁጥር 17) ፤ ቀጣዩ “በዛሬ” እግዚአብሄር ሂወታቸው እንደሆነ ያረጋገጡበት፣ የተለዩ ህዝቦቹ እንደ ነበር እግዚአብሄር እንደ አረጋገጠበት ይናገራል (ቁጥር 18) (ዘጸ 19፡ 5; ሚል 3፡ 17) ፡፡ እግዚአብሄር እንደ ቅዱስ ህዝብ ለእግዚአብሄር በሌሎች ህዝቦች ላይ እንዲያመሰግኑ፣ እንዲታወቁ እና እንዲከበሩ ከፍ ሊያደርጋቸው ቃል ገባላቸው(ተስፋ ሰጣቸው) (ቁጥር 19; መዝ 81፡ 11-14, 16) ፡፡

መዝጊያ

የእስራኤል ህዝብ በረከት መሆን እፈልጋለሁ ፡፡ እግዚአብሄርን በመውደድ እና ሌሎችን በመውደድ የልብ ሁኔታ ላይ የተደገፈ ነው ፡፡

ዘዳግም 25 ብዙ ህጎች እና ደንቦች ነው ፤ ዘዳግም 26 በብዛት በኩርን ስለመስጠት እና ለመጀመሪያዎቹ ሰዎስት አመት አስረኛን ስለ መስጠት ከዚያም የሰዎስቱን አመት ለድሀ እንደሚሰጡት ነው ፡፡ እነዚህ እግዚአብሄር እንደሚያቸው ሰዎችን እንዲያዩ ልባቸውን የሚቀይሩ ህጎች ናቸው ፡፡ እነዚህ ሀሳቦች በልባችን ውስጥ ካሉ እነዚህን ለማድረግ ችግር አይኖርብንም ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 1999), p. 259.

  2. Warren Wiersbe, The Bible Exposition commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 422.

  3. Radmacher, Allen, and House, eds., p. 260.

  4. Wiersbe, p. 423.

  5. Thomas Constable, Dr. Constables Expository (Study) Notes: Deuteronomy, p. 152; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/deuteronomy.pdf.

  6. Wiersbe, p. 424..

  7. Wiersbe, p. 424.

ጥያቄዎች

  1. በዘዳ(25፡ 4) የሚያበራየውን በሬ እንዳያስር ህግ ይከለክላል ፤ በ 1ቆሮ (9፡ 9-11) መሰረት የዚህ ህግ ትክክለኛ አላማው ምንድን ነው ? (1ጢሞ 5፡ 18)
  2. የተለያዩ(ሀሰተኛ) ከረጢት መለኪያዎች ሰዎችን የሚሰርቀዉን ህግ ይከለክላል (ዘዳ 25፡ 13-16) ፤ ለህዝቡ በዚህ አይነት የእግዚአብሄር የራሱ ትኩረት ጥልቀቶች አላስገረማችሁም ? (ምሳ 11፡ 1; 16፡ 11; 20፡ 10)
  3. በዘዳ(26፡ 16) መሰረት እግዚአብሄር ከህዝቡ መታዘዝን ብቻ አልፈለገም በፍፁም ልባቸው እና በፍፁም ነፍሳቸው እንዲታዘዙም እንጂ ፤ ሁልጊዜ መታዘዛችሁ ከልባችሁ ነው ? ካልሆነ ያን ለመቀየር በተለየ ምን ማድረግ ትችላላችሁ ?
  4. በዘዳ(25-26) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Deuteronomy 26:16

“The LORD your God is commanding you this day to follow these statutes and ordinances. You must be careful to follow them with all your heart and all your soul.”

ሙሴ ትዕዛዛቱን፣ ህግጋቱን እና ስርዓቶቹን ለሁለተኛዉ የእስራኤል ትዉልድ እንደገና ነገራቸዉ። ወደኃላ መለስ ብለዉ የእግዚአብሔርን ታማኝነት እና የማዳን ሥራ አስታወሱ። የህጉን ዝርዝር ሁሉንም ከለሱት። እናም ሙሴ አሁንም እንደገና የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸዉ እና ነፍሳቸዉ ይከተሉት ዘንድ አሳሰባቸዉ።

የእስራኤል ማህበረሰብ አካል ላትሆን ትችላለህ፥ ነገር ግን ከኢየሱስ ጋር ባለህ ህብረት ይህ እዉነታ ተግባራዊ ይሆናል። ቆም በልና ልብህን መርምር! ልብህ ጌታን ሙሉ በሙሉ የማይወድ ከሆነ እርሱን መከተል ከባድ እና አስቸጋሪ ስሜት እንደሆነ ሊሰማህ ይጀምራል። ስለዚህም ልብህን ዛሬ መርምር! ከራስህ ጋራ ሓቀና ሁንና እንዲህ ብለህ ጠይቅ፥ "በሙሉ ልቤ እግዚአብሔርን እወደዋለሁን?" ቆም በልና፥ አድምጥ! ልብህ ድርጎቶችህን ይመራቸዋል! ልብህን ከእግዚአብሔር ጋራ ካስተካከልክ ሌላዉ በህይወትህ ያለዉ ነገር በሙሉ በነፃነት ይፈሳል!

"አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ሥርዓትና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ዛሬ አዝዞሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ጠብቀው፥ አድርገውም።"

ኦሪት ዘዳግም 26:16

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኤርሚያስ 31:33፦ "ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።"
  • መፅሃፈ ምሳሌ 4:23፦ "አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።"
  • የማቴዎስ ወንጌል 22:37-38፦ "ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 105