Deuteronomy 27
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 27 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘዳግም 26 በኩር ስለመስጠት፣ በእያንዳንዱ ሰዎስት አመት ለድሀ የምርት አስር ፐርሰንት ስለ መስጠት እና ስለ ኪዳኑ ማጠቃለያ አውርተናል ፡፡ ሙሴ በሞዓባዊያን ሜዳ ላይ በመሆን ከእስራኤል ወጣቶች ጋር ነበር እናም ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት ተዘጋጅተዋል ፡፡ ዘዳግም 27 ወደ ፊት በእግዚአብሄር መታመን ላይ ያተኩራል ፤ በዘዳግም 27-30 ሙሴ ወደ ፊት ሊሆን እንደሚችል የሚጠብቀውን የእግዚአብሄርን መታመን ገልፆዓል ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም(27፡ 1-4)፡ ይህ ለአከባበር(ለስነ ስርዓት) ጊዜ ነበር ፡፡ ሙሴ እና የህዝቡ አዛዦች እስራኤላዊያንን “ ሁሉንም ትዕዛዝ እንዲጠብቁ “ ነገሩዓቸው ፡፡ ወደ እስራኤል ምድር ዮርዳኖስን ወንዝ በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሄር ሰጥቶአቸው የነበረውን ምድር ጥያቄ ያስነሳል - ያበቃ ስምምነት ነበር ፡፡ ነጭ ዳራ ለመፍጠር በልስን ወይም በኖራ የተሸፈነ ትልቅ ድንጋይ ይተክላሉ(ያስቀምጣሉ) ስለዚህ “ ሁሉንም የተፃፈውን ማየት እንችላለን “ ፤ እናም በዚህ የኃላ ዳራ ላይ “ የዚህን ህግ “ ሁሉንም ቃሎች (ዘዳግም ወይም መላው የህግ መፅሀፍን) ወዲያወኑ ወደ እስራኤል እንደተሸገሩ ይፅፋሉ ፤ ይህን ወዲያውኑ ያደርጋሉ - ማስቀመጥ አይተውም(አይዘገዩም) አይጠብቁም ፡፡
እስራኤላዊያን የሚገቡበት ቦታ ከሰኬም በስተሰሜን በተቀመጠችው በተስፋይቱ ምድር መሀል ላይ ጌባል ተራራ ነበር ፤ ይህ ቦታ እግዚአብሄር ከአብርሃም ጋር የመጀመሪያውን ኪዳን ያደረገበት እና አብርሃም ለእግዚአብሄር መጀመሪያ መሰዊያ የሰራበት ነው (ዘፍ 12፡ 6-7) ፡፡ በዘዳግም እስራኤላዊያን እንደገና መሰዊያ እንዲያስቀምጡ ተነገሩ ፡፡ በዘፍጥረት እና በዘዳግም እግዚአብሄር ምን እንዳደረገ አስቀምጠናል(መዝግበናል) ፡፡
ዘዳግም(27፡ 5-8)፡ ሙሴ ባልተጠረቡ ድንጋዮች መሰዊያ እንዲሰሩ እና የብረት መሳሪያ በላዩ ላይ እንዳይጠቀሙ አዘዛቸው ፡፡ መሰዊያው ለሚቃተል መስዋዕት ነበር - ምርጡን ለማቃጠል ፤ ምርጡ ሙሉ ለሙሉ የሚቃጣል ይሆናል ለእግዚአብሄር ሙሉ መሰጠትን ያሳያል ፡፡ በትልቅ ድንጋዮች እስራእላዊያን እግዚአብሄር ምን እንደ አደረገላቸው ያስታውሱ ነበር በተጨማሪም በድንጋዮቹ መሰዊያ እግዚአብሄርን መሰጠታቸውን ያሳዩ ነበር ፡፡ በብዙ በበፊት እግዚአብሄር ያደረገውን ማየት እንችላለን ፤ አሁን ለእግዚአብሄር በመሰዊያው ላይ የሚቃጠል መስዋዕታችንን የምንሰጥበት ጊዜ ነው ፤ ለምን ? ስለሆነም በአባቶቻችን እና በአያቶቻችን መንገድ ሲሄድ ያየነውን እግዚአብሄርን ማየት እንችላለን ፡፡ ይህ እግዚአብሄር ለአባቶቻቸው ያደረገላቸውን አይቶት የነበረውን ሙሴ ለወጣቱ ትውልድ ይሰጥ የነበረው አስተሳሰብ ነበር ፡፡
ዘዳግም(27፡ 7-10)፡ “ የደኅንነትም መስዋዕት ሰዋበት በዚያም ብላ በአምላክህም በእግዚአብሄር ፊት ደስ ይበልህ፡፡” ራሳችንን ለእግዚአብሄር ማቅረብ ስንቀጥል “ ክርስቲያን ነኝ እና መጥፎ ህይወት ውስጥ ነኝ” በሚል ቁመና ውስጥ መቆየት አንችልም ፡፡ ያን እምነት መከተለ የሚፈልግ ማነው ? ሙሴ ለህዝቡ ይነግራቸው የነበረው “ በእግዚአብሄር ባላችሁ በደስታ እንድታከብሩ እፈልጋለሁ “ ፤ በቁጥር 8 ሙሴ የህጉን ሁሉንም ቃሎች በተለሰነው ድንጋይ ላይ በግልፅ በመፃፍ እርግጠኛ እንዲሆኑ ነገራቸው ፡፡ እስራኤላዊያን ነገሮችን ይፅፉ ነበር ፍቅራቸውን ለእግዚአብሄር እንደ ማረጋገጫ ያከብሩም ደስተኛም ይሆኑ ነበር ፡፡
በቁጥር 9 ሙሴ እና ሌዋዊያን ካህናቶች ለሁሉም እስራኤላዊያን አሉዓቸው ዝም እንዲሉና እንዲያዳምጡ ነገሩዓቸው ፤ በሽግግር ጊዜ ላይ የተሠጠው እና የመሪነቱን ጊዜ በመጠቅለል ይህ በዘዳግም ሰዎስተኛው ስብከቱ ነበር ፤ “ ይህ ቀን የእግዚአብሄር ህዝብ የምትሆኑበት ቀን ነው “ አላቸው ፡፡ አሁን በሁሉም በኩል እግዚአብሄር ለእነርሱ አዘጋጅቶ የነበረውን እየተቀበሉ ነበር - ለእነርሱ እየተላለፈ እየሆነ ነበር ፡፡ በቁጥር 10 ሙሴ እንዴት “ አምላካቸውን እግዚአብሄርን እንደሚታዘዙ እና ዛሬ የሰጠኃችሁን ትዕዛዙእና ስርዓቱን እንደሚከተሉ “ ነገራቸው ፤ በቁጥር 11-12 ሙሴ ህዝቡ እንዲያከብሩ አዘዛቸው ከዚያም ከእስራኤል ነገዶች ስድስቱን በገሪዛን ተራራ ላይ የሚቆሙትን ሰዎች ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍና እና ቢኒያምን ሰየመ ፤ ህዝቡን እንዲባርኩ ተነግሮአቸው ነበር ፡፡
በቁጥር 13 ሌሎቹ ስድስት ነገዶች - ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳን እና ንፍታሌም ወደ ህዝቡ ይረግሙ ዘንድ በጌባል ተራራ ላይ ይቆማሉ ፤ ገሪዛ ተራራ ሁሉም ቅጠል ነበር(ለም ነበር) ጌባል ተራራ ግን ባዶ ነበር ፡፡ ትርጉም አለው በጌባል ተራራ ላይ ርግማን ይቀበላሉ በገሪዛ ተራራ ላይ በረከትን ይቀበላሉ ፡፡ እነዚህ ሁለት ቡድኖች በቁጥር አስራራት ላይ በረከትን ወይም ርግማንን በሚናገሩ ጊዜ ሌዋዊያን ለሁሉም እስራኤል 12 ርግማን ይሰጣሉ ፡፡
ማክአርቱር ይህን በተለያየ ገልፆዓል የህዝቡ ድምፅ የሆኑትን ሌዋዊያን ካህናቶች ከኪዳኑ ታቦት አጠገብ ይቆሙና ስድስቱ ነገዶች በገሪዛ ተራራ ላይ እያሉ እና ሌሎቹ ስድስት ነገዶች ደግሞ በጌባል ታራራ ላይ እያሉ ምናልባትም አንድኛው ቡድን ተራሮች ላይ ባይኖሩም በረከቱንም እርግማኑንም ሁለቱንም ያነባል ፡፡ “ ሁሉም እስራኤላዊ “ የሚለው ሀረግ የሚያሳየው የ12ቱ ነገዶች ተወካዮች የሚገኙ ሲሆን ስለዚህ እያንዳንዱ ምን እየተካሄደ እንደነበር መስማት ይችላሉ ፡፡ እነዚህ ርግማኖች እንደተሰጡ “ይህ በመሆኑ” እያዘኑ ለሁኔታዎቹ እስራኤላዊያን ይስማማሉ ፤ ለዚህ ተስማሙ ፡፡
አንዱ እርግማን ጣዖት በሚያመልኩ ላይ ነበር (ቁጥር 15) ፤ የተረገሙ ያሆናሉ ማለት ምን ማለት ነው ? ማክአርቱር በእርግማን የሚከለል ሆነ(የበረከት ተቃራኒ) ማለት በሽታና ጉዳት በሰዉየው ላይ ይመጣል በማለት ገልፆዓል ፡፡ ዋይርስቤ እርግማንን “ ምን እንደሞሆን የሚያመለክት አልነበረም…..ነገር ግን ከእርሱ ከተመለሱ በህዝቡ ላይ ርግማን ለመላክ በእግዚአብሄር ይጠሩ ነበር ፡፡” ሌላው እርግማን (ቁጥር 16) አባቶቻቸውን እና እናቶቻቸውን ለማያከብሩ ነበር ፡፡ ከእነዚህ ብዙዎቹ በአስርቱ ትዕዛዝ ውስጥ የተጣበቅ ናቸው ፡፡ ሌሎቹ እርግማኖች በስርቆት መልኩ በወዳጁ ድንበር መስመር በሚጎአዘው ላይ(ቁጥር 17); እውርን ሰው በስህተት በሚመሩ ላይ (ቁጥር 18); ለመፃተኛው፣ ለድሀ አደጉ እና ለመበለቲቱ ፍትህ በሚያጎአድሉ ላይ (ቁጥር 19); ከአባቶቻቸው ሚስት ጋር በሚተኙ ወይም በማንኛውም ተገቢ ባልሆነ ወሲባው ስብዕና (ከእንስሳት ጋር, በዘመዳሞች መሀከል, ዝሙት) ላይ (ቁጥር 20-23) እና በድብቅ ግድያ የሚፈፅሙ ወይም የሆነን ሰው ለመግደል ጉቦ በሚቀበል ላይ(ቁጥር 24-25) ነበር ፡፡ እግዚአብሄርን እንድንወድ እና ወዳጆቻችንን(ጎረቤቶቻችንን) እንድወድ ተነግረናል ስለዚህ ወዳጅን መግደል እግዚአብሄር እንድንሆን በነገረን ዋና ነገር ላይ በተቃራኒ መሄድ ነው ፡፡
ከእነዚህ ከእያንዳንዶቹ እርግማኖች ቦኃላ የማይታዘዙ ሆነው ከተገኘባቸው እርግማኑን መቀበላቸውን ለማሳየት “አሜን” ብለው ይመልሳሉ ፡፡ በቁጥር 26 እነዚህን ህጎች የማይታዘዙ ይረገም ነበር ፡፡ ለምን ነበር ይህ የመጨረሻው እርግማን በጣም ያስፈለገው ? ምክንያትም (ሁሉንም ዘዳግም, ምናልባትም ሁሉንም ኦሪት(ህግ)) እነዚህን ህጎች ካላከበሩ እርግማኖችን ይቀበላሉ ፡፡ አስታዉሱ ሙሴ ይህን ስብከት በጀመረ ጊዜ እንዲሰሩት ነግሮአቸው የነበረው ሁሉንም ነገር እንዲፅፉ ነገራቸው ፤ እስራኤላዊያን ሁሉንም ትዕዛዞች መጠበቅ አልቻሉም ፤ እናም ያ ነው ሀሳቡ ፡፡ እስራኤል በሲና ተራራ ላይ የእግዚአብሄርን ህጎች ሊጠብቁ ተስማምተዋል ከዚያም ወዲያዉኑ የወርቅ ጥጃ ሰርተው አመለኩ ፡፡ እንደሚኖሩበት እየተስማሙ ነበር ነገር ግን ማድረግ አልቻሉም ፡፡ የእግዚአብሄር የተሰጠ ልጅ ለመሆን ዋረን ዋይስርቤ ከትምህርት የሚበልጥ እንደሚወሰድ “ ኃይማኖታዊ መዝገበ ቃላት እና የሚያስታውሱ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች እና ኃይማኖታዊ መዝሙሮች “ አጽንዖት ሰጥቶአል ፡፡(ማቴ 7፡ 21-23)
ኢየሱስ ህግን መከታተል ላልቻሉት ሰዎች ይናገር ነበር ፤ የከንፈር አገልግሎት አማኝች እንዳንሆን መጠንቀቅ ይጠበቅብናል - ሁል ጊዜ አሜን በማለት ፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን የዚህን ጥንቃቄ ኢየሱስ ወሰደ (ገላ 3፡ 10-12) ፡፡ ሙሴ እየተናገረው የነበረው ይህ ነው ፡፡ ያዕ 2፡ 10 አንብቡ ፤ ይህ ቁልፍ ነው ! አንዱዓን ህግ መጠበቅ ካልቻልን የሁሉም ጥፋተኞች ነን ፡፡
መዝጊያ
ሁሉም ኃጢዓት …ሁል ጊዜ ሁል ጊዜ ወደ መጨረሻው እርግማን ይመራል ፤ (ሮሜ 3፡ 23; 6፡ 23, ገላ 3፡ 13) ኢየሱስ ከህግ እርግማን ዋጀን ምክንያቱም ኢየሱስ ለእኛ እርግማን ሆነ ፡፡ ኢየሱስ ህጎቹን መጠበቅ እንደማንችል ያውቃል ስለዚህ ያን እርግምን ለእኛ ወሰደ ፡፡ በዚያ እርግማን እስካሁን አጥብቃችሁ ይዛችኃል ወይስ ሁሉንም ለኢየሱስ ሰጥታችሁታል ? ዘዳግም 27 የሚለው በእነዚህ ህጎች መኖር ካልቻላችሁ ተረግማችኃል ፡፡ ኢየሱስ “ ለኔ ስጡኝ ፤ ለእናንተ እርግማኑን እወስዳለሁ “ ስላለው(ያለውን) እወደዋለሁ ፡፡
3 MacArthur, p230.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p 229.
MacArthur, p. 229.
MacArthur, p. 230, “Key Word.”
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), 441.
Wiersbe, p. 442.
ጥያቄዎች
-
በዘዳ(27፡ 5) እስራኤላዊያን ካልተጠረቡ ድንጋዮች መሰዊያ እንዲሰሩ ተነገራቸው ፤ ድንጋዮቹን ለምን የብረት መሳሪያ እንዳይነካቸው እንደተነገሩ ምን ታስባላችሁ ? የት ነበር የሚተክሉት ? መሰዊያው ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ለምን አላሰባችሁም ?
-
በዘዳ 27 ምን ያክል ርግምን ነበር ምን ምንስ ነበሩ ?
-
አነድ ሰዎስተኛው እርግምን ወሲባዊ ኃጢዓት ላይ የተመሰረተ ለምን እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ለእስራኤላዊያን ይህ ምንድን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ኤፌ 5፡ 3; ቆላ 3፡ 5; 1ተሰ 4፡ 1-8)
-
በቁጥር 26 የህጉን ሁሉንም ቃሎች የማያከብር የተረገመ ነው ፤ በእነዚህ ህጎች አሁንም እንከለላለን(እንያዛለን) ? ለምን ለምንስ አንከለልም(አንያዝም) ? (ገላ 3፡ 11-14)
-
በዘዳ 27 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 27:3
And you shall write on them all the words of this law, when you cross over to enter the land that the LORD your God is giving you, a land flowing with milk and honey, as the LORD, the God of your fathers, has promised you.
ሙሴ፥ እስራኤላዉያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኃላ የህጉን ቃላቶች በተለሰነ ድንጋይ ላይ እንዲፅፏቸዉ ትዕዛዝን ሰጣቸዉ። እስራኤላዉያን የእግዚአብሔርን ህግና ትዕዛዛትን እንዲረሱ ሙሴ አልፈለገም! በዛሬዉ ዓለም እንደቀድሞዉ የእግዚአብሔርን ቃሎች በተለሰኑ ድንጋዮች ላይ መፃፍ አይጠበቅባችሁም፥ ቢሆንም ግን የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መፃፍ አሁንም ጥበብ ያለበት ስነ-ስርዓት ነዉ!
መኖርያ ቤትህ ዉስጥ የምትወደዉ ማስታወሻ፣ ያጌጡ ወረቀቶች፣ የጠመኔ ብላክቦርድ እና ነጭ ብላክቦርድ አለህ? እነዚህ እቃዎች ሁሉ በቀኖችህ ስታሳልፉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል በመፃፍ ወደ እዉነት እንዲመራህ ልትጠቀምበት ትችላለህ። በትንሽ የማስታወሻ ወረቀት ላይ ጥቅስ ፃፍና፥ ኮምፒዉተርህ ላይ ለጥፍ፣ የመኪናህ ጎማ በሚሽከረክርበት አጠገብ አስቀምጥ ወይም በመታጠብያህ ክፍል መስታወት ላይ ለጥፈዉ! ለአንተ ትርጉም የሚሰጡህን ጥቅሶች ለመፃፍ ጊዜ ዉሰድ። ከዚያም ቀኑን ሁሉ ጥቅሱን ስታነበዉ፥ በህይወትህ ዉስጥ ስላለ የእርሱ እዉነት እግዚአብሔርን አመስግን።
"አባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠህ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ትገባ ዘንድ በተሻገርህ ጊዜ፥ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ጻፍባቸው።"
ኦሪት ዘዳግም 27:3
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘዳግም 6:9፦ "በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።"
- መዝሙረ ዳዊት 119:105፦ "ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።"
- ትንቢተ ዕንባቆም 2:2፦ "እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ፦ አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 106
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።