Deuteronomy 28
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 28 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዘዳግም 27 መጨረሻ ላይ የእግዚአብሄርን ህጎች እስራኤላዊያን ካላከበሩ የሚገጥማቸውን የተዘረዘሩ እርግማን ተመልክተናል ፡፡ ለሁሉም 12 እርግማኖች እስራኤላዊያን መስማማታቸውን “አሜን !” በማለት ይመልሳሉ ዘዳ(27፡ 26) የሚያወራው አንዱዓን ትዕዛዝ ቢጥሱ ሁሉንም በመጣስ ጥፋተኛ ይሆናሉ ፡፡ በዘዳ 27-28 በምዕራፍ 27 በርግማን(ላይኛው ኬክ) ለመታዘዝ በረከትምዕራፍ 28 መጀመሪያ ላይ(የስጋው አካል) ቀጥሎምበምዕራፉ መጨረሻ ላይ ብዙ ርግማን(ታችኛው ኬክ) አይነት “ ወቀሳ ግሰፃ ሳንዱች“ ተፈጥሮ ነበር ፡፡ ብዙ ጊዜ በረከት/ርግማን/በረከት እናስባለን ነገር ግን ይህ ተቃራኒ ነው ፡፡ ከዘዳግም 28 “ በስጋው ክፍል” ጀምረናል ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም(28፡ 1)፡ ቁጥር 1 የሚለው እስራኤላዊያን ዛሬ የሰጣቸውን ትዕዛዞች የሚከተሉ ከሆነ ( አስታዉሱ “ ዛሬ” ዘዳግም 27 ሙሴ ህጎችን የሰጠባቸው እና እንዲፅፉት የነገረባቸው ቀን ነበር ) ከመረጡ እና ምርጫቸው ራሳቸውን ሳይሆን እግዚአብሄርን ለመከተል ከነበር በአለም ካሉት ህዝቦች በብዙ አስበልጦ(ከላይ አድርጎ) ያስቀምጣቸዋል በረከቱንም በላያቸው ላይ ያፈስስባቸዋል ፡፡ ከዚያም ሙሴ ለእነርሱ እነዚያን በረከቶች ጋር መጥቀስ ጀመረ ፤ እግዚአብሄር በምድር ህዝቦች ላይ ከላይ ያስቀምጣቸዋል እንዲያመሰግኑዓቸው፣ ዝናቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲያከብሩዓቸው ከፍ ያደርጋቸዋል ከዚያም በእግዚአብሄር ፊት የተለየ ቅዱስ ህዝብ ይሆናሉ (ዘዳግም 26፡ 19) ፤ ነገር ግን በዘዳግም(8፡ 1) እግዚአብሄር የተናገረው ይህን ነጥብ ለማግኘት እስራኤላዊያን ትዕዛዙን መከተል ይጠበቅባቸው ነበር ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እስካሁን እስራኤል የሚበልጥ ዉሻ ሆኖአል ይህ ተጨባጭ ሆኖ አናየውም ነገር ግን የምናውቀው የእስራኤል ንጉስ የሁሉም ንጉስ ይሆናል ስሙም ንጉስ ኢየሱስ ነው (ሮሜ 11፡ 25-27) ፡፡ ይህ በመጨረሻ ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ የሚሆን ነው ፡፡ ይህ የሚሆንበት ብቸኛው መንገድ የአህዛብ ሙሉነት ወደ እግዚአብሄር ሲመለሱ ይሆናል ፤ አይሁዶች ይቀናሉ ያም በመሲሁ መመለስ ይደረሳል ፤ ከዚያም እስራኤል ከሌሎች ህዝቦች በልጣ ከፍ ትላለች ፡፡
መጨረሻም አይሁዶች ለሁሉም ብርሀን ይሆናሉ (ኢሳ 49፡ 6) ፤ ያም መንግስቱ በደረሰ ጊዜ በመጨረሻ በኢየሱስ በኩል ይመጣል እናም በአይሁድ ሰዎች በኩል ይመጣል ፡፡ ዘር በዘፍጥረት በመጨረሻም ወደ እግዚአብሄር አዳኝነት መራ እናበኢየሱስ በኩል ይደረስበታል እስራኤልንም ከሁሉም ህዝብ በላይ ያደርጋል ፡፡ ለዚያ ነው የእስራኤል ህዝብ ከምድር ሊጠፉ የማይችሉት ምክንያቱም በዚያች አግር እና በህዝቡ እግዚአብሄር የማዳኛ እቅድ ስላለው ፡፡
ዘዳግም(28፡ 2-4)፡ በዚህ ቁጥር እነዚህ ሁሉ በረከቶች በመታዘዝ ውስጥ ይመጣሉ ፡፡ የሚመጡ የእነዚህን በረከቶች ግማሽ መፈፀም እንዳለ እናውቃለን ፡፡ በኢያ (21፡ 45) መሰረት “ እግዚአብሄር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም ” ፤ እኔ ያልኩት ከፊል ነው ምክንያቱም የምንደርስበት የአንዲሺ ዘምን እስካሁን አልሆነም ፡፡ ህጉን ስለ ታዘዙ የሚባረኩ ይሆናሉ ፤ በመሰረቱ ቁጥር 3 የብሉይ ኪዳን ብፁእ ነው ፤ በከተማ እና በሀገረ በረከት ይሆናል ፡፡ ቁጥር 4 ዘራቸው እንደሚባረክ እና የነኩት ሁሉ እንደሚባረክ ይጠቅሳል ፡፡
ዘዳግም(28፡ 6-7)፡ በቁጥር 5 “ እንቅብህ እና ቡሃቃህ ቡርክ ይሆናል ፡፡“ በዘዳግም (28፡ 17) የዚህ ቁጥር የእርግማን ጎኑ ተሰጥቶአል ፤ ቁጥር 16 የሚለው በከተማ እና በሀገሩ እርጉም ይሆናል ፤ ደግሞ ደግሞ እንደገና ይህ አውነት ነው ፡፡ ቁጥር 18 ከቁጥር 4 ይመሳሰላል ፡፡ ይህ የሳንዱቹን ምሳሌነት በደንብ ያየንበት ቦታ ነው - የተረገመ ሊሆን የሚችልበት መንገድ አለ ወይም የተረገመ ሊሆን የሚችለበት መንገድ አለ ፡፡ በቁጥር 6 በየቀኑ ህይወት በረከት ይሆናል ወይም በቁጥር 19 እርግማን በየቀኑ ህይወት ይሆናል በመረጡት መሰረት ፡፡ በኑሮአችን ሁሉንም ውሳኔዎች መቆጣጠር አንችልም ነገር ግን ለችግሮቹ መልስ የምንሰጥበትን ውሳኔአችን መቆጣጠር እንችላለን ፡፡ ቁጥር 7 ተባርኮ የነበረውን የሚያጠቁ ጠላቶች በሰባት አቅጣጫ ይሸሻሉ ፡፡
ዘዳግም(28፡ 8-10)፡ በቁጥር 8 እግዚአብሄር ጎተራውን ይሞላል - በማትረፍረፍ ይሞላቸዋል - እና ታዛዥ ተከታዮች የሚሰሩትን ሁሉንም ነገር ይባርካል ፤ በቁጥር 9 ታማኝ መሆንን በመረጡ ጊዜ፣ ትዕዛዙን ባከበሩ ጊዜ እና በመንገዱ ሲጎአዙ እግዚአብሄር እንደ ራሱ ቅዱስ ህዝብ ታዛዥ ተከታዮቹን ይመሰርታል ፤ ሁሉም የምድር ህዝቦች ታማኝ ተከታዮቹን ያያሉ በኑሮአቸውም እግዚአብሄርን ያከብሩታል (ቁጥር 10) ፡፡ እስራኤል ለሌሎች ህዝቦች ምስክሮች ይሆናሉ ፤ ለሌላ ለሁሉም ብርሀን ይሆናሉ በመጨረሻ ቀናትም የሚመሰከርላቸው ህዝብ ይሆናሉ ፡፡
ራዕ(7፡ 4-8) ይህን ክስተት መዝግቦታል “ የታተሙትንም ቁጥር ሰማሁ ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት 144 000 ነበሩ “ በሚለው ቃሎች ይጀምራል ከዚያም በቁጥር 9 “ ከዚህ ቦኃላ አየሁ አንድ እንካ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብ እና ከነገድ ከወገንም ከቐንቐም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ ፤ ….በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ ፡፡” በቁጥር 10 እየጮሁ “ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችንና ለበጉ ማዳን ነው አሉ !“ ገምቱ ማነው ይህን ሂደት ያነሳሳው ? በመጨረሻዎቹ ቀናት እንደ ምስክር የሚያገለግሉት የአይሁድ ሰዎች ፤ ስለዚህ በዘዳግም መጨረሻ ላይ ህዝቡ ብርሃን እንዲሆኑ፣ ለሁሉም ምስክር እንዲሆኑ ተነገራቸው ምክንያቱም ያ በመጨረሻዎቹ ቀናት በጣም መጨረሻ ላይ የሸከማሉ ፡፡ መፅሀፍ ደግሞ የሚለው እስራኤል የመንግስቱ መያዣ ጊዜ ሲደርስ ምስክሮች ይሆናሉ (ዘካ 8፡ 1-12) ፤ ኢየሩሳሌም እንደ እምነት ከተማ በመሆን ትታዎቃለች የእግዚአብሄርም ተራራ እንደ ቅዱስ ተራራ በመሆን ይታዎቃል (ዘካ 8፡ 3) ፡፡ እዉነታው ኢየሩሳሌም መሀል እምብርት፣ ሁሉም የእግዚአብሄር መንግስት ቁልፍ አካል ትሆናለች ከዚያም ሁሉም እግዚአብሄር በዚያ ምን እንደሚያደርግ ያያሉ ፡፡
ዘዳግም (28፡ 10) ይጠቀልለዋል - በትዕዛዙ ከተጎአዛችሁ እግዚአብሄር እንድታደርጉት ለጠራችሁ ከታዘዛችሁ ሰዎች በእግዚአብሄር አምላክ እንደተጠራችሁ ያያሉ በፍርሃት ይቆማሉ ፡፡ ለእኔ ሁሉም ነገር ሁልጊዜ ወደ ትልቅ ስዕል ያመለክታል ፤ ስለ እኛ አይደለም ሁሉም ስለሱ ነው ፡፡
ዘዳግም(28፡ 11-14)፡ የበረከቶች ዝርዝር በቁጥር 11 ይቀጥላል በልጆች መበልፀግን፣ በከብቶች መበልፀግን እና በመሬት መበልፀግን ያካትታል ፡፡ ቁጥር 12 የተትረፈረፈ የጎተራ በረከትን ሰማይንና ዝናብን ይጨምራል ምክንያቱም ዝናብ የሚያመጣ እግዚአብሄር ነው ፡፡ በሚያስደንቅ መልኩ የእግዚአብሄር ተከታዮች መበደር አያስፈልጋቸውም ነገር ግን ለአለም ባንክ እንደሚሆኑ ይገልፃል ፤ በቁጥር 13 የእግዚአብሄር ተከታዮች ከእርሱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም እስካላሉ ድረስ ወይም ሌሎች አምላኮችን እሳካላመለኩ ድረስ ወደ ላይ ከፍ ይላሉ እንጂ ወደታች ዝቅ አይሉም መሪዎች ይሆናሉ (ቁጥር 14) ፤ አንድ ሀተታ ሰጪ የፃፈው “ በሰዎች ላይ የእግዚአብሄር ባህሪይ መሰሪያ መታዘዝ ነው ፡፡“ ቁጥር 1-14 በእዉነቱ እስራኤል የሚቀበለው የበረከት ዝርዝሮች ናቸው፡ በግብርና፣ በቤተሰብ፣ በፋይናንስ እና በጦር በረከቶች ፡፡ እርግጥ ነው በምዕራፍ 27 እና 28 መሀከል ከበረከቶች አራት ዕጥፍ የሚበልጡ እርግማኖች አሉ ፡፡
ዘዳግም(28፡ 15-24)፡ በቁጥር 15 አለመታዘዝ እንደተረገመ እናያለን ፤ በበረከት ፋንታ ማናኛውም እርግምንን የሚመርጡት ለምን ይሆን ? በቁጥር 18 አለመታዘዝ ማለት ልጆችህ የተረገሙ ይሆናሉ ፡፡ በቁጥር 20 ባለመታዘዛቸው እስራኤላዊያን በሚሰሩት ሁሉም ነገር ላይ “ ርግማንን፣ ሽሽትንና ተግሳፅን “ ተላከባቸው ፤ እናም እርግምኑ በምዕራፉ ሙሉ ቀጠለ ፤ ከእነዚህ አንዱ እስከዛሬ ይተገበራል ? አንዳንድ አለመታዘዞች እና ኃጢዓቶች በራሳችን ላይ ወደ ምናመጣው ዉጤት ሊያመሩ ይችላሉ ፤ መልካሙ ነገር ከዚህ ሁሉ ኢየሱስ ሊለየን መቻሉ ነው ፡፡
ዘዳግም(28፡ 25-68)፡ በጥቅስ (25-68) አለመታዘዝ በጦርነት ወደ መሸነፍ መምራት እንደሚችል እና ሬሳቸው ለወፎች ምግብ እንደሚሆን እናያለን ፤ በቁጥር 28 አለመታዘዝ ወደ ሀሳብ መደናገር መምራት ይችላል ፡፡ እነዚህ ሁሉ በብሉይ ኪዳን ምን እንደተፈጠረ ምሳሌዎች ይሆናሉ (ኤር 8፡ 10; ሶፎ 1፡ 13; አሞ 5፡ 11) ፡፡ በአለመታዘዝ ሁኔታ ሲቀመጡ ምንም በትክክል ለመሄድ አይመስልም ፤ ስለዚህ እስራኤል በዚህ አለም ለሌላ ህዝብ አሰቃቂ ወይም ብርሃን መሆን ይችላል ፡፡ በቁጥር 64 እግዚአብሄር በመላው ምድር ላይ ሰዎቹን ይበትናቸዋል ፤ በተጨማሪም ወደ ግብፅ እንካን መልሶ ይወስዳቸዋል ነገር ግን ተፈላጊ አይሆኑም (ቁጥር 68) ፤ ነገር ግን የእግዚአብሄርን ትዕዛዞች ለመታዘዝ ወይም ላለመታዘዝ ምርጫ ነበራቸው ፡፡ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሄር መንገድ ወደ ሚወስድ መስመር በብዙ እየሄድን ነው ፤ በረከት ወይስ እርግምን ?
መዝጊያ
ሉቃ (12፡ 48) ለአማኞች ያሳስበናል “ ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል ፡፡” በኢየሱስ ህይወት በረከት በህይወት ስጦታ ተቀመጥን ፡፡ የእግዚአብሄር ቅዱስ ህዝብ ነን ፡፡ በብዙ እንደ አህዛብ ለአለም እግዚአብሄርን እንወክላለን ፡፡ በረከትን ወይስ ርግምንን እንፈልጋለን ? የአምላክነቱን ባህርይ የምናሳይ(የምናስታውቅ) ነን ፡፡
1ጴጥ (4፡ 17) የሚያሳየው፡ “ ፍርድ ከእግዚአብሄር ቤት ተነስቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና ፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀምር ከሆነ ለእግዚአብሄር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን ? መምረጥ እንችላለን(ምርጫ አግኝተናል) ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዘዳ(28፡ 1-14) እግዚአብሄር ለልጆቹ የሰጣቸው በረከቶች ምንድን ናቸው ?
-
በቁጥር(15፡ 68) እግዚአብሄር ባለመታዘዝ ምን እንደሚሆን ነገረን(እርግማን) ፤ የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡ አሞ (5፡ 11), ሶፎ (1፡ 13) እና ኤር (8፡ 10) ፡፡ ዘዳግም 28 የሚለውን ይህ ይከተላል ? በአሁኑ ጊዜ እነዚህ እርግማኖች እስካሁነ ተገቢ(አግባብ) ናቸው ?
-
በዘዳ(28፡ 53-57) ብዙ መከራዎች(ችግሮች) ተገልፀዋል ፤ ለዛ ለተለየ ጊዜ ይህ ማስጠንቀቂያ እንደነበር ወይም ምን እንደሚመጣ ስዕል ነው ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ወይስ ለምንስ አታምኑም ?
-
ሁሉም በረከቶች እና እርግማኖች ተሻግረው(በማለፍ) መጥተዋል ? ለምን ለምንስ አልፎ አልመጣም ?
-
በዘዳ 28 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 28:13-14
The LORD will make you the head and not the tail; you will only move upward and never downward if you listen to the LORD your God’s commands I am giving you today and are careful to follow them. Do not turn aside to the right or the left from all the things I am commanding you today, and do not go after other gods to worship them.
እግዚአብሔር እስራኤላውያን ትዕዛዛቱን ሰምተዉ ከታዘዙ እና ከተከተሏቸዉ፥ ወደ ከፍታ እንጂ ፈፅሞ ወደኃላ እንደማያወርዳቸዉ ተናግሯቸዋል። ሁልጊዜ ራስ እንጂ ጭራ እንደማይሆኑ ነግሯቸዋል! ነገር ግን ይህ እንዲሆን እስራኤላዉያን ግራ ቀኝ ሳይሉ፥ ሌሎችንም ጣኦታት እንዳያመልኩ ታዘዋል!
በህይወትህ በስተ-ቀኝና በስተ-ግራ ያሉ ነገሮች ከመስመርህ ያስወጡህ ይሆን? እግዚአብሔር ሁልጊዜ እርሱን እንድትፈልገዉ ይጓጓል። ከእርሱ ጋራ ህብረት በማድረግ እንድትመላለስ ይሻል። ከኢየሱስ ጋራ ሌሎች ነገሮችን አዳብለህ እንድትኖር አይፈልግም! በፀጋዉ እና በኢየሱስ ብቻ እንድትኖር ይፈልጋል! ከኢየሱስ ጋራ ህብረት ማድረግ በቂ ነዉ! ፍላጎቶችህን ለመሙላት ቃል ገብቷል። በመንገዱም ሁሉ አትረፍርፎ ይባርክሃል!
"ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም።"
ኦሪት ዘዳግም 28:13-14
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መፅሃፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1:7፦ "ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።"
- መዝሙረ ዳዊት 24:5-6፦ "እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል። ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ።"
- መፅሃፈ ምሳሌ 4:25-27፦ "ዓይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም በቀጥታ ይመልከቱ። የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና። ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከክፉ መልስ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 107
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።