The Pentateuch Deuteronomy

Deuteronomy 29-30

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 29-30 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 108 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የዘዳግምን ጥናት በዘዳግም ውስጥ ወደ መሲሁ ስለ ሚያመለክቱት ሁሉም ነገር እንዴት እንደመናምን አውርተን እንጨርሳለን ፡፡ ወደ ልባቸው እንዲገባ የእግዚአብሄርን ቃል በመፍቀድ በብዙ ተማሪዎች በንባባቸው ቀስ ማለት በርትቻለሁ(ተነሳስቻለሁ) ፤ ያ ነው ከዚያ ቦኃላ የሆነው ፤ ያ በዘዳ 30 መሰረት ልባችንን እንዲገርዘው መንፈስ ቅዱስን ፈቀድን ፡፡ የዘዳግም 29 ዋና ዋና ሀሳብ እዚህ ነው ፤ የመጀመሪያዎቹ ስምንንት ቁጥሮች ታሪክ ክለሳዎች ናቸው ፡፡ ዘዳግም ብዙ የተደገሙ መረጃዎችን ይዞአል ፤ ሁሉንም ነገር እንደተረዱት እርግጠኛ ለመሆን ሙሴ ህጉን ወደ ተስፋይቱ ምድር ይገቡ ስለነበሩት ወጣት ትውልድ ደገመላቸው ፡፡ በአሜሪካ ሁሉንም ወጣት ሰዎች በአንድ ላይ አግኝቶ በነፃነት አዋጅ እና በሌላ ታሪካዊ ሰነዶች ውስጥ በመጎአዝ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ እንደሚያስፈልገን አስባለሁ ምክንያቱም ስለማናውቃቸው ፡፡ ምናልባት ሙሴ ወጣቱ ትውልድ እንዚህን ህጎች እንደሚረሱዓቸው በውስጡ ፈርቶ ነበር ስለዚህ የታሪክ ክለሳ አደረገ ከዚያም የኪዳን ክለሳን አደረገ (ቁጥር 9-15) - ድንጋዮች እንዲሰበስቡ፣ ህጎቹን ነጭ ዳራ ላይ እንዲፅፉ እና የሚቃጠል መስዋዕት እንዲያደርጉ መታዘዛቸው ፡፡እግዚአብሄር ምን አድርጎላቸው እንደነበር እና በኑሮአቸዉ እንዲጎአዙበት ያስታውሳሉ ፤ በመጨረሻም በዘዳ(29፡ 16-29) ያለመታዘዝ ዉጤቱ ተሰጥቶአቸው ነበር ፡፡ በቁጥር 20 መሰረት በብሉይ ኪዳን ውስጥ የአለመታዘዝ ስሞች መደምሰስ ይሆናል ፡፡

ትምህርት

ዘዳግም(30፡ 1-3)፡ ቁጥር 1 የሚለው እስራኤላዊያን ከበረከት እና እና ከእርግማን ቦኃላ ከየትኛውም ከሳደዱት ቦታ በሀሳባቸው(ከልባቸው) በመጡ ጊዜ እግዚአብሄር ለራሱ መልሶ ይመልሳቸዋል ፡፡ ቶም ኮንስታብል የሚገልፀው በእነዚህ አስር ቁጥሮች ውስጥ የመልሶ ግንባታ ቁልፍ ናቸው ፡፡ ወደ እግዚአብሄር በተመለስን ጊዜ መታደስ ሊሆን ይችላል እናም በህዝቡ ላይ ርህራሄ ስለሚኖረው ወደ ራሱ መልሶ ይሰበሰባቸዋል ፡፡ ኔልሰን የሚገልፀው “ እግዚአብሄር ሙሴን የእስራኤልን የወደፊት ክህደት እና ህዝቡን በአሕዛብ መካከል የእግዚአብሄርን መበተንን ቀድሞ እንዲያይ ፈቀደለት…..(በተጨማሪም) የእስራኤልን የመደፊት ንስሃ እና ወደ ምድሪቱ መመለስን አየ “ ወደ ፊት የሚፈፀም ይሆናል ፤ ተለቆ የነበረው ትንቢታዊ ቃል ነበር ፡፡ በሐዋ(3፡ 19-21) “ እንግዲህ ከጌታ ፊት የመፅናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ ኃጢዓታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሀ ግቡ ተመለሱ “ በማለት የንስሀ ስዕል በጴጥሮስ በኩል የታየ ነው ፤ በንስኃ እና ወደ እርሱ መመለስ በጀመርን ጊዜ በመጨረሻም መታደስ ከኢየሱስ ይመጣል (ቁጥር 19) ፡፡ ያ የመታደስ ጊዜ በኢየሱስ በኩል ይመጣል ፤ የዚህ ግማሹ እንደተፈፀመ አምናለሁ ነገር ግን ሁሉም አይደለም ፡፡በመመለስ እና በንስኃ እንዴት መታደስ እንደሚመጣ ያወሩ ጥቂት ነብያቶች አሉ (ኢሳ 54፡ 7-8; ሕዝ 36፡ 33-38; ሆሴ 14፡ 4-8; ኢዩ 3፡ 16-21) ፡፡

በእነዚህ ቁጥሮች በትንሽ ቡድናችን ሚናችንን እግዚአብሄር ለማሳየት እየጀመረ ነው ፡፡ የእስራኤል ስልሳ ፐርሰንቱ በነጌቭ(በደቡብ እስራኤል በርሀ) ምድረበዳ ነው እናም ትንሽ በትሽ(ቀስ በቀስ) ወደ ኤደን ገነት እግዚአብሄር መመለስ ጀምሮአል ፡፡ እግዚአብሄር እንደና እየገነባው ባለው እና ባደሰው ህዝቦች በመጨረሻ በፍርሀት ይሆናሉ እግዚአብሄርም እንደ መንጋ የአይሁዶችን ቁጥር ለማብዛት ተስፋ ገባ ፤ በ1948 እንደ ህዝብ የወቅቱዓ እስራኤል ተመሰረተች ተበታትኖም የነበረው ህዝብ መመለስ ጀመረ ፤ የቀድሞ ከተማዋ ኢየሩሳሌም አሁን በሰዎች መንጋ ዉስጥ እንደምትጎአዙ ይሰማችኃል ፡፡ አይሁዶች ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው መጥተዋል (ሕዝ 36፡ 33-38) ፤ ነገሮች የተበተኑ ሲመስሉ እግዚአብሄር ክህደታቸውን ይፈውሳቸዋል ህዝቡም በማረፊያ እና በጥበቃ ጥላው ስር ለመኖር ይመለሳሉ (ሆሴ 14፡ 4-8) ፡፡

ኢየሩሳሌም ቅዱስ ከተማ ትሆናለች እንደገና በፍፁም እንግዶች አይወርሩአትም ፡፡ ግብፅ እና ኤዶም የበርሀ ጠፍ ምድር ይሆናሉ ይሁዳ ግን ለዘላለም ይኖራል ፤ የእግዚአብሄር መገኘት በፂዎን ያድራል በመጨረሻም በኢየሩሳሌም እንደገና ምንም ሁሌም አይወድቅም (ኢዩ 3፡ 16-21) ፡፡

ዘዳግም(30፡ 4)፡ ይህ ቁጥር እግዚአብሄር ህዝቡን ከአለም ሩቅ ጫፎች እንካን መልሶ እንደሚያመጣቸው ተስፋ ይሰጣል ፡፡

ጥያቄ የሚሆነው አሁን ከእስራኤል ጋር ምን እያደረግን ነው ?ዋይርስቤ አድሲቱ እስራኤል ብዙ ቦታዎች እንዴት ልትበከል እንደምትችል ይገልፃል ፡፡ ጥቂት ሰዎች አሁን ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን እስራኤል ወይም መንፈሳዊዋ እስራኤል እንደምትሆን እና ሁሉም የእግዚአብሄር ተስፋ በቤተ ክርስቲያን በኩል እንደሚመጣ ያምናሉ ፤ ሁሉም የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች እና ተስፋዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሁን እንደተፈፀሙ ያምናሉ ፡፡ ሌሎች የሚሉት እነዚህ ትንቢቶች “ በሚታይ ዋጋ ላይ የተወሰደ መሆን አለበት “ እናም ያ “ በምድር ላይ መንግስቱን ለመመስረት ኢየሱስ ሲመጣ መፈፀማቸውን እንጠብቃለን “ ፤ ያ ማለት በእነዚህ በጥቂት ትንቢቶች ላይ ለኢየሱስ እስኪመለስ የሚያቆም ቁልፍ አለ ማለት ነው ፡፡ ዋይስርቤ የሚለው “ ሙሴ እዚህ ላይ የሚናገረው ስለ እስራኤል እንጂ ስለ ሌሎች ወደ ፊት የእግዚአብሄር ህዝ ስለሚሆኑት ምሳሌ እንደ ቤተ ክርስቲያን እንደማይሆኑ ያመስላል ፡፡” “የእግዚአብሄር ህዝብ” በእዉነቱ የእስራኤል ህዝብ እንደሆኑ አስባለሀ ፡፡ “ለአብርሃም እና ለዘሩ እግዚአብሄር ለሰጣቸው ምድር ቤተ ክርስቲያን ከእስራኤል ምድር ጋር ምንም የኪዳን ግንኙነት የላትም” (ዘፍ 15) ፤ እግዚአብሄር ይህን ምድር ለእስራኤል ሰጠ ለኛ አይደለም ሁሉም በረከት እና እርግማንም ለእስራኤል ተሰጠ ለእኛ አይደለም ፡፡ የእስራኤል ህዝብ የሚያደርጉት እና የማያደርጉት ብዙዎቹ ተስፋዎች በሁኔታ የሚቀየሩ ነበሩ ፡፡ እነዚህን ሁለት አለሞች በአንድ ላይ ለምን መቀልቀል አንዳስፈለገ ምን ይሰማናል ? ለምን ለእስራኤል እቅድ እና ለቤተ ክርስቲያን እቅድ ሊኖር ስለመቻሉ ምን እናስባለን ?

ዘዳግም(30፡ 5)፡ “ አባቶችህም ወደ ወረሱዓት ምድር አምላክህ እግዚአብሄር ያገባሀል ትወርሳትማለህ ፤ መልካምም ያደርግልሀል ከአባቶችህም ይልቅ ያበዛሀል “ ፤ ያ የቤተ ክርስቲያን ተስፋ አይደለም ምክንያቱም በፍፁም መሬት አልወሰድንም ፡፡ ዛሬም እስራኤል እስካሁን ተስፋ የተሰጣቸው ሁሉም ምድር የላቸውም ፤ እግዚአብሄር ለህዝቡ ሊያበለፅጋቸው እና ሊያበዛቸው እቅድ አለው ፡፡ እስራኤል በእግዚአብሄር አይን ፖም ነው ፡፡

ዘዳግም(30፡ 6-7)፡ “ በሕይወትም እንድትኖር አምላክህን እግዚአብሄርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ አምላክህ እግዚአብሄር ልብህን የዘርህንም ልብ ይገርዛል ፡፡” ይህ ሁኔታ ነው፡ “ …ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ “(ዘዳ 10፡ 16) ፡፡ “ ለእግዚአብሄር ራሳችሁን ገርዙ ፤ የልባችሁን ሸለፈት አስወግዱ “ (ኤር 4፡ 4)….ወይም የእግዚአብሄር ቁጣ ይሰብራል ፡፡ በእግዚአብሄር ቃል ራሳችንን መገርዝ አለበን ይህ ከሆነ ልባችን መቀየር ይችላለም እንኖራለንም ፡፡

ዘዳግም(30፡ 8-10)፡ ስርአቱን እንድንጠብቅ እና “ በፍፁም ልባችን እና በፍፁም ነፍሳችን ወደ እርሱ እንድንመለስ” ታዘናል ፤ ህይወትን ለምን አንመርጥም ? ለምን ወደ እግዚአብሄር አንመለስም ለምንስ ህይወታችንን ቃሉ እንዲገርዝ አንፈቅድለትም ?

ዘዳግም(30፡ 19-20)፡ “ በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ ፤ እግዚአብሄር ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድር ትቀመጥ ዘንድ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሄርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ ፡፡”

ይህ እነዚህ ጥቅሶች ለእኛ እንዳልሆነ ያረጋግጣሉ ፤ የእኛ ያልሁኑ ነገሮችን ቀጥታ ለራስ አለማድረግ አስፈላጉ ነው ፡፡

መዝጊያ

ሐዋ(17፡ 28) የሚለው “ ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ እኛ ደግሞ ዘመዶቹነንና ብለው እንደ ተናገሩ በእርሱ ሕያዋን ነንና ብለው እንደ ተናገሩ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን ፡፡” ኢየሱስ ህይወት ሊሰጠንና ህይወት እንዲትረፈረፍልን ይመጣል ፤ ጥፋትን ሊያመጣብን አልፈለገም ፤ ሕይወትን ወይም ሞትን መምረጥ እንፈልግለን ምርጫ አግኝተናል ፤ በእርሱ ህይወትን ምረጡ !

  1. Tom Constable, Dr. Constable’s Notes on Deuteronomy (available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/deuteronomy.pdf), p. 165.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 264.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 445.

  4. Wiersbe, p. 445.

  5. Wiersbe, p. 445.

ጥያቄዎች

  1. ባለማመናቸው ምክንያት (ዕብ 3፡ 1) ከግብፅ የወጣዉ ወጣቱ ትውልድ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደማይገባ ስናስታውስ (ዘኁ 14፡ 22-23) ከዚያም በዘዳ(3፡ 19) ሙሴ ለእስራኤላዊያን በመድረሱ ምንድን እያደረገ ነበር ?
  2. በዘዳ(29፡ 18) ሙሴ በመራራ ፍሬ የሚሸከም ስር ወይም ሀሞት ስለማለቱ ምን ታስባላችሁ ? (ኤር 9፡ 15; አሞ 6፡ 12; ዕብ 13፡ 15)
  3. ዘዳ(30፡ 6) ስለተገረዘ ልቦች ያወራሉ ፤ የዚህ መገረዝ አላማው እና ዉጤቱ ምንድን ነው (ሮሜ 2፡ 28-29)? ልባቸውን የሚገርዘው ማነው ?
  4. በሮሜ (10፡ 6-8) ሐዋሪያው ጳዉሎስ ዘዳ(30፡ 12-14) ጠቅሶታል ፤ በሮሜ (10፡ 8) “ ለቃል…” ወይም “ መልዕክቱን….” እንደ እምነት ቃል በመጥቀስ ጳዉሎስ ምንድን ማለቱ ነበር ?
  5. በዘዳ 30 እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን እንዲወዱ ምን ያክል ጊዜ ተጠርተዋል ? እንዲታዘዙት ምንያክል ጊዜ ተጠርተዋል ? አስፈላጊ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ዮሐ 15፡ 10; 1ዮሐ 2፡ 5; 3፡ 24; 2ዮሐ 1፡ 6)
  6. በዘዳ(29-30) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Deuteronomy 30:11, 14

This command that I give you today is certainly not difficult or beyond your reach . . . But the message is very near you, in your mouth and in your heart, so that you may follow it.

ሙሴ እስራኤላዉያን ወደ ተስፍይቱ ምድር ከመሻገራቸዉ እና እርሱ ከመሞቱ በፊት በህዝቡ መካከል የመጨራሻ ንግግር አድርጓል። ህዝቡንም በፊታቸዉ ምርጫ እንዳላቸዉ ነገራቸዉ! እናም እግዚአብሔር አምላካቸዉን እንዲወዱት፣ በእርሱ መንገድ እንዲመላለሱና ትዕዛዛቱንም እንዲጠብቁ አዘዛቸዉ። ሙሴ ከዚህ በላቀ መንገድ ይህ መንገድ ከእነሱ አቅም በላይ እና አስቸጋሪ እንዳልሆነ፥ ብሎም ቃሉ በልባቸዉ እና በአፋቸዉ ቅርብ እንደሆነ ነግሯቸዋል። እግዚአብሔርን እንዲወዱ በኃይል ማስገደድ እንደማይችል ሙሴ ቢገባዉም፥ እግዚአብሔር አምካቸዉን እንዲመርጡ የመጨረሻ ተማፅኖዉን ግን አድረጓል! ልጆቹን እንደሚያፈቅር አባት፥ ሙሴ እስራኤላዉያን ከእግዚአብሔር ጋራ እንዲመላለሱ እና ወደ ሌሎች አማልክት ፊታቸዉን እንዳያዞሩ አጥብቆ ፈልጓል።

እንደ አማኝ፥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝህ ስትቀበለዉ፥ በክርስቶስ ለህይወትህ ሁሉ ዉሳኔን ወስነሃል! ነገር ግን ከክርስቶስ ዉጪ እንድትመለከትና ፊትህን እንድታዞር ትፈተናለህ። ዛሬ፥ ዓይንህን ኢየሱስ ላይ አድርግ! እግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ እንደሚቀጥል የተስፋ ቃል ስለሰጠህ፥ ፀንተህ በመቆየት እና ሳታወላዉል በክርስቶስ እምነት ያለዉን አጥብቀህ ያዝ!

"እኔ ዛሬ የማዝዝህ ይህች ትእዛዝ ከባድ አይደለችም፥ ከአንተም የራቀች አይደለችም።... ነገር ግን ታደርገው ዘንድ ቃሉ በአፍህና በልብህ ውስጥ ለአንተ እጅግ ቅርብ ነው።"

ኦሪት ዘዳግም 30:11, 14

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:58፦ "ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።"
  • ወደ ዕብራዉያን 10:23፦ "የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤"
  • ወደ ዕብራዉያን 12:1-2፦ "እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 108