Deuteronomy 31
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የዘዳግምን እን ሙሴ የፃፈውን ሁሉንም የህግ መፅሀፍት( ፍጥረት, ዘጸዓት, ዘሌዋዉያን, ዘኁልቁ እና ዘዳግምን) ለመጨረስ አንድ ቀን ብቻ ይቀረናል ፡፡ የመጨረሻዎቹ ጥቂት ቀናቶች ስለ ሙሉ በረከት እና እርግማን ጥቅል ነው ፡፡ የምለው ዘዳግም 30 ሙሉ ያለው የነበረውን ህይወት እንምረጥ ፤ ወደ ዘዳግም 31 በጥልቅ ስንቆፍር ስለ ተጨባጭ, ተግባራዊ ታሪክ ልንከተለው ስለምንችለው የምናወራ ይሆናል ፡፡ እርግጥ ነው በመጀመሪያዎቹ አምስት ቁጥሮች በመሪነት ለውጥ አለ - ከሙሴ ወደ ኢያሱ ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም(31፡ 1-2)፡ ቁጥር 1 የሚለው “ ሙሴ ሄዶ ይህንን ቃል ለእስራኤል ሁሉ ነገረ ፡፡” ስብከቱ ቀጠለ ፤ በቁጥር 2 ሙሴ 120 አመት እንደ ነበር እንዳረጀ እና ዮርዳኖስን ተሸግሮ መሄድ እንደማይችል ገለፀ ፡፡
ስለ ሙሴ ህይወት ምንድን እናውቃለን ?
- የመጀመሪያዎቹን 40 አመታት ሙሴ በግብፅ አሳለፈ ፡፡
- ሁለተኛው 40 አመታት በጎችን በመጠበቅ እና ከቤተሰቡ ጋር በመሆን በምድያም አለፈ ፡፡
- የመጨረሻዎቹን 40 አመታት እስራኤላዊያንን ከግብፅ አዉጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር በመምራት ሙሴ በምድረበዳ አሳለፈ ፡፡
- 120 አመቱ ላይ ሞተ የአየኑ እይታው እና ጥንካሬው ሙሉ ነበር ፤ ጤንነቱና ችሎታው መሪነቱን እንዳይቀጥል አላደረገውም (ዘዳ 34፡ 7) ፤ ኃጢዓት ከለከለው ፡፡
- የሙሴ ኃጢዓቱ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳይገባ ከለከለው (ዘዳ 1፡ 37-38) ፡፡
- ሙሴ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲገባና ህዝቡን እንዲመራ እግዚአብሄር እንዲፈቅድለት ለመነው ፡፡
- እግዚአብሄር አልተቀበለውም አድስ መሪነትን ለማምጣት የሙሴን ኃጢዓቱን ተጠቀመበት (ዘዳ 3፡ 23-29) ፡፡
ዘዳግም(31፡ 3-6)፡ ሙሴ ለእስራኤላዊያን ኢያሱ ዮርዳኖስን እንደሚያሻግራቸው ገለፀላቸው (ቁጥር 3) ፤ በአሞራዊያን ነጉሶች በሴዎንና በዐግ ላይ እንዳደረገው ጠላቶቻችሁን ያሸንፋቸዋል ወደ እስራኤላዊያንም ይመልሳቸዋል (ቁጥር 4-5) ፡፡ በኢያ(1፡ 5) መሰረት እግዚአብሄር ኢያሱን “ በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቐቐምህም ፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆኑሁ እንዲሁ ከአንት ጋር እሆናለሁ ፡፡” እስካሁን ያ ቃል መልካም ነው ፤ ምንም ቢገጥመን - ሱስ, የትዳር ጉዳይ, የድህነት ውሳኔም ችግር የለም - እግዚአብሄር አይተወንም ወይም አይጥለንም ፡፡ ስለዚህ በቁጥር 6 ሙሴ ኢያሱን: “ ጽኑ አይዞአችሁ አትፍሩ ከፊታቸውም አትደንግጡ ፤ አምላክህ እግዚአብሄር እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል ፤ አይጥልህም አይተውህም ” አለው ፤ “ እነርሱ “ የሚለው ለእስራኤላዊያን ተዛማጅ ነው ፡፡ ሙሴ ኢያሱ በሚመራቸውን ህዝቦች ድንጉጥ እንዲሆን ወይም ሙሴ ባለመኖሩ ፈሪ እንዲሆን አልፈለገም ፤ ይልቁንም ሙሴ ኢያሱ በእግዚአብሄር ላይ እንዲደገፍ ፈለገ ፡፡ በኢያ 1 እግዚአብሄር ኢያሱን እና ህዝቡን ሰዎስት ጊዜ ጠንካራ እና ፀኑ እንዲሆኑ አዝዞአቸዋል (ቁጥር 6-7, 9) ፡፡ ሎይዝ ቢ. ስሜድስ የሚለው “ ጀግንነት በፀሎት የራሰ ፍራትን ብቻ ነው ፡፡” በጀግንነት መጎአዝ የምንችልበት ብቸኛው መንገድ መፀለየ እና ወደ አድሲቱ ምድር እንድንገባ ፍርሀታችንን እንድንቐቐመው እግዚአብሄርን መጠየቅ ነው ምክንያቱም እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው ፡፡
የእስራኤል ህዝቦች ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲሄዱ(እንዲገቡ) ታዝዘው ነበር ፡፡ ማቴ (28፡ 18-20) የሚለው ሁሉም ስልጣን ባለው በኢየሱስ ወደ ሁሉም አይነት ምድሮች፣ አካባቢያችን ወዳሉ ጎረቤቶች፣ ወደ ትልቅ ከተሞች እና ዉጪ ሀገራቶች በመሄድ በአብ በወልድ እን መንፈስ ቅዱስ ስም እንድናጠምቅ ተሾመናል ፡፡ ይህን በማድረግ ለማስተማር እና ደቀመዝሙር ለማድረግ ተሸመናል ፤ የትም ብንሄድ ችግር የለም እግዚአብሄር በዚያ አለ አይተወንም ፡፡ “እስከ አለም ፍፃሜ” የሚለው ሀረግ ኢየሱስ ተመልሶ እስኪመጣ ማለት ነው ፤ ለዘላለም አብሮን ይሆናል ፡፡ ፍርሀት በመንገድ ላይ ካገኝንይህ ስራ የለም ፡፡
ዘዳግም(31፡ 7-8)፡ ሙሴ ኢያሱን በሁሉም እስራኤላዊያን ፊት ጠራው ህዝቡንም ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደሚመራ ነገረው (ቁጥር 7) ፡፡ ዋልተር ሊፕማን የሚለው “ የአንድ መሪ የመጨረሻው ፈተና ከኃላው ላላ እምነተ ፅኑ ወይም ለሚሸከም መተው ነው “፤ ከሱ ኃላ የሚመራ ሙሴ ኢያሱ ነበረው ፡፡ ይህ በግልፅ የእግዚአብሄር መሪነት መፀሀፍ ቅዱሳዊ ምሳሌ ነው ፤ ስለ ኢየሱስ እና ስለሐዋሪያቱ አስቡ ፤ ያፈሰሰባቸው 12 ሰዎች ነበሩት ፡፡ ለእኛ መነሳሳት ሊሆነን የሚገባው ምንድነው በእርሱ ከተያዙት አንዱ ነው ፡፡ በእዉነት ያፈሰሰባቸው ጢቂቶች የተጠራጠሩ ሰዎስት ነበሩት ፤ ፍፁም ቡድን ነበር ፡፡ ሐዋሪያው ጳዉሎስ ጢሞቲዎስ እና ቲቶ ላይ አፍስሶአል ፡፡ በኢያሱ ጉዳይ ምንድን ሆነ ሙሴ በህዝቡ ፊት በማቆም ኢያሱን በጣም እየታመነበት እንደ ነበር የነገራቸው ነው ፤ የመሪነት ማስተላለፍ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው የመሪነት ቅያሬ ከሌለ በህዝቡ ላይ የእግዚአብሄር ፍርድ ማስረጃ ነው (ኢሳ 3፡ 1-4; ዘዳ 1፡ 38; 31፡ 14; 32፡ 51-52) ፡፡ እግዚአብሄር በቦታው ያስቀመጠው ማስተላለፍ ካልሰራ ባለመታዘዝ የሆነ አለመረጋገት ነው ፤ ኢያሱ ዝግጁ እና ለመቀበል ተዘጋጆቶ ነበር የእግዚአብሄርም እጅ በእርሱ ላይ ነበር ፡፡ በህዝቡ ፊት ኢያሱ ከሙሴ ጋር መጣ የሙሴንም ዜማ ሙሉ ቃሎች ደገመ ፤ ይህ ሙሴ ለኢያሱ ስልጣኑን እየለቀቀለት እንደነበር ያሳያል ስለዚህም ኢያሱ መውሰድ(መቀበል) ይችላል ፡፡
ዘዳግም(31፡ 9-13)፡ መሪነት ከሙሴ ወደ ኢያሱ እንደተቀየረ ሙሴ ካህናቱን በሁሉም ህዝብ ጉባኤ ፊት፣ ወጣቶች እና ለልጆቹም መሳይ በእያንዳንዱ ሰባት አመት ህጉን እንዲያነቡላቸው አዘዛቸው ፡፡ በሸክም ውስጥ ባልነበረበት እንካን የእግዚአብሄር በሌላው ላይ ሁልጊዜ ቅድሚያ ይወስዳል ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ህጉ መሰረታቸው ሆኖ ይቀመጣል (ይቀራል) ፤ እስራኤላዊያን ወደሚሄዱበት ሁሉ ይሄዳል ፡፡
ዘዳግም(31፡ 14-15)፡ የሙሴ የሚሞትበት ጊዜ እንደቀረበ እግዚአብሄር እንዲያዝዘው ኢያሱን እንዲያመጣው ነገረው ፤ እግዚአብሄር በግል ወደ ድንካኑ መግቢያ ላይ በደመና አምድ ተገለጠላቸው ፡፡ እግዚአብሄር ለሙሴ ተገልጦለት ነበር አሁን ደግሞ ለኢያሱ ተግባር እየተገለጠለት ነበር ስለዚህ ህዝቡ ከኢያሱ ጋር እንደነበር ማየት ይችላሉ ፡፡
1 Louis Smeedes, “An Introduction to Mission Beyond the Mission,” Theology, News, and Notes (October 1983), p. 3; quoted in Expository Notes of Dr. Thomas Constable, Deuteron- omy; p. 171; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/deuteronomy.pdf
ዘዳግም(31፡ 16-23)፡ እግዚአብሄር ሙሴን ስለ ሞቱ እና ህዝቡ የማይታዘዙ እና የማያምኑ እንደሚሆኑ ነገረው (ቁጥር 16) ፡፡ እግዚአብሄር በእነርሱ ብስጭቱ እንደሚያድግ እና እንደሚተዋቸው ከዚያም ችግር እንደ ሚገጥማቸውና መቀሰፍት እንደሚያገናቸው ተናገረ ፡፡ እግዚአብሄር ስለተዋቸው አንድ ቀን ችግር እንደመጣ ያውቃሉ (ቁጥር 17) ፤ ስለሆነም ሙሴ ለእስራኤላዊያን ማስተማር የቻለበትን ዜማ(መዝሙር) ይፅፈዋል ስለዚህ ይህ ስለ እግዚአብሄር ምስክር ሊሆን ይችላል (ቁጥር 19) ፡፡ ሙሴ በዚያን ቀን ዜማውን(ህጉን) ፃፈ ለእስራኤላዊያንም አስተማረው (ቁጥር 22) ፤ ኢያሱም ታዘዘ(ተሾመ) (ቁጥር 23) ፡፡
ዘዳግም(31፡ 24-29)፡ የእግዚአብሄር ቃል መጠበቅ ሙሴ በፃፈው ዜማ(ህግ) በኩል መጣ ፤ ምክንያቱም ቁጥር 24 የሚያወራው “ እንዲህም ሆነ ፤ ሙሴ የዚህን ህግ ቃሎች በመጽሀፍ ከጻፈ ከፈጸመም በኃላ “ አንዳንድ ሰዎች ይህን ዜማ(ህግ) በእዉነቱ የተቅላላ የህግ መፅሀፍ ነበር ብለው ያስባሉ ፡፡ ሙሴ በእስራኤላዊያን እንደ ምስክር ህጉን በኪዳኑ ታቦት አጠገብ እንዲያስቀምጠው ታዘዘ (ቁጥር 26) ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ሙሴ በተዋቸው ጊዜ እስራኤላዊን ታዛዥ ነበሩ ነገር ግን እግዚአብሄር ይሆናሉ ብሎ እንደተናገረው ወደ ክህደት ይመለሳሉ (ቁጥር 29) ፡፡
መዝጊያ
የእስራኤላዊያንን የራሳቸውን ኃጢዓት በሚነግር በተፃፈ ውርስ በዚህ ህግ ሙሴ የመሪነቱን ጊዜ አበቃ ፤ ለሙሴ ቀላል ሊሆን እንደማይችል ያውቃል ነገር ግን እግዚአብሄር እንዳዘዘው አደረገ ሙሴ ለእግዚአብሄር ታማኝ በመሆን እና በመታዘዝ የመሪነቱን ጊዜ አበቃ ፡፡
Walter Lippman, Quotes, Britannica, https://www.britannica.com/quotes/biography/Walter-Lippmann.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 447.
ጥያቄዎች
-
በእነርሱ ፊት ያሉትን ህዝቦች ለማጥፋት በእስራኤላዊያን ፊት ዮርዳኖስን የሚሻገረው ማን ይሆናል (ዘዳ 31፡ 3) ? ይህ ክርስቶስ ጠላቶቻችንን ለማጥፋት ከፊታችን እንደሚሻገር እንዴት ይወክላል (ዮሐ 14፡ 3; ቆላ 2፡ 15; 1 ዮሐ 3፡ 8) ? ኢያሱ የሚለው ስም የእግዚአብሄር(ዮሹዋ) ከሚለው እንደሚገናኝ ታውቃላችሁ( እናስ አስፈላጊ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ) ?
-
በዘዳ 31 በቁጥር 3፣ 6 እና 8 ላይ ሙሴ እስራኤላዊያንን እግዚአብሄር በእነርሱ ፊት እና ቀድሞ እንደሚሄድ እና መፍራት እንደሌለባቸው አሳወቃቸው ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች በፍራት ትቸገራላችሁ ? እግዚአብሄር እንደማይጥላችሁ ወይም እንደማይተዋችሁ ታምናላችሁ ? (ማቴ 28፡ 20; ዕብ 13፡ 5-6)
-
በዘዳ(31፡ 9-13) ላይ እንዲያደርጉ ሙሴ ካህናቱን እን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ምንድን አዘዛቸው ? ይህ ለምን ነበር የሚያስፈልገው(ያስፈለገው) ?
-
እግዚአብሄር ሙሴን እስራኤላዊያን እንደሚተውት እና ኪዳኑን እንደሚሰብሩ በዚህም ምክንያት ምንም እንካን የማስጠንቀቂያ እርግማኖቹ ዋጋ የሚያስከፍሉዓቸው ቢሆንም እንደሚገፉት አስታወቀው ፤ እስራኤላዊያን ለእግዚአብሄር ታማኝ ሆነው መቆየት ለምን እንዳልቻሉ ምን ታስባላችሁ ? በአሁኑ ጊዜ በአማኞች ላይ ይህ የሚመስል አዝማሚያ ታያላችሁ ? በራሳችሁስ እንዴት ነው ?
-
በዘዳ 31 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 31:6
Be strong and courageous; don’t be terrified or afraid of them. For it is the LORD your God who goes with you; He will not leave you or forsake you.
ሙሴ የአዛዥነቱን መደብ መለወጥ ሲጀምር እና ኢያሱን እንደ ቀጣይ መሩ ሲልከዉ እነዚህን የሚያበረታቱ ኃይለኛ ቃላትን ሶስቴ ደጋግሞአቸዋል፥
"ጽኑ፥ አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፥ ከፊታቸውም አትደንግጡ፤ አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ አይጥልህም፥ አይተውህም።"
ሙሴ እና ኢያሱ የወደፊት ህይወታቸዉን ሲመለከቱ ለዉጥ እንደሚኖር ተገንዝበዋል። አንተም እርግጠኛ የማትሆንበት የወደፊት ህይወት ሲፈጠር የመለወጥ ጊዜ ይኖርሃል። በፍርሃት እና በመንቀጥቀጥ ወይንም እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ እንዳለና እንደማይጥልህ በማመን፥ በፅናት እና በድፈረት መመላለስ ትችላለህ!
ዛሬ፥ ምንም ዓይነት ነገር ቢገጥምህ፥ በብርታት እንድትሄድ አቅምን በሚሰጥህና እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ በመሆኑ ማወቅ ብርታት ይሁንህ! እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነዉ! ደግሞም ወደፊት በሚገጥሙህ ማናቸዉም ነገሮች ላይ ይረዳሃል። ይህን ማድረግ ትችላለህ!
"ጽኑ፥ አይዞአችሁ፥ አትፍሩ፥ ከፊታቸውም አትደንግጡ፤ አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ አይጥልህም፥ አይተውህም።"
ኦሪት ዘዳግም 31:6
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 32:8፦ "አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።"
- ትንቢተ ኢሳይያስ 43:2፦ "በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።"
- ትንቢተ ኤርሚያስ 29:11፦ "ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 109
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።