Deuteronomy 32-34
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Prophet Deuteronomy 32-34 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዚህ በመጨረሻው በዘዳግም ክፍል ወደ ምንቀጥልበት መነሻ ለመስጠት በዘዳግ( 31፡ 30) እንጀምራለን ፤ የሁሉንም ትምህርት ማጠቃለያ እሰጣቸኃለሁ ከዚያም አንድ ቃል ላይ አተኩራለሁ ፡፡
ትምህርት
ዘዳግም(31፡ 30)፡ በቁጥር 30 ሙሴ ህጉ እንዲፅፈው እና ለሁሉም እስራኤል ጉባኤ ለ 2 ሚሊዮን ህዝብ ያክል የህጉን ሁሉንም እንዲደግም ተነገረው ፡፡ በተጨማሪም በዘጸ (15፡ 1-18) በቀይ ባህር ላይ ስለዳኑ እንደምስጋና(መታሰቢያ) የፃፈው ሌላ ዜማ(መዝሙር) ነበረው እንዲሁም በዘኁ 21 ህይወት ሰጪ ምንጭ ተሰጥቶአቸው ስለነበር እስራኤላዊያን ዘምረው ነበር ፡፡ ይህ ከሞቱ በፊት የዘመረው የሙሴ የቀብር ስርዓት መዝሙር ነበር ፡፡ በመሳ 5 ድቦራና ባርቅ እስራኤላዊያን ከነዓናዊያንን ካሸነፉ ቦኃላ የድል መዝሙር ዘመሩ ፤ በ 1ሳሙ (18፡ 6-7) የእስራኤል ሴቶች ጎልያድን የዳዊትን ማሸነፍ ለማክበር መዝሙር ዘምረዋል ፤ አብዛኛዎቹ እነዚህ መዝሙሮች ያሸነፉአቸው ስለ ህይወት ሰጪ ድል ነበሩ ፡፡ በ 2ዜና (29፡ 30) ሌዋዊያን ለኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የምስጋና እና የስግደት መዝሙር ዘመሩ ፡፡ የሙሴ መዝሙር በዚህ ምዕራፍ እንደ አመፀኛ ህዝብ ስለ እስራኤል ነበር፡፡
ዘዳግም(32፡ 1-14)፡ እግዚአብሄር ፅኑ ነው ነገር ግን ሌላ አይደለም በተለይ እስራኤላዊያን ፅኑ ነበሩ ፡፡ ዋይርስቤ የሚለው በዚህ ሂደት ሙሴ የእግዚአብሄርን ባሕርይ መለየት ጀመረ ፤ ቁጥር 4 እግዚአብሄርን የሚገልፀው እንደ “ እርሱ አምላክ ነው(እንደ አለት) ፤ ስራውም ፍፁም ነው ፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው ፤ የታመነ አምላክ ክፋትም የሌለበት እርሱ እዉነተኛና ቅን ነው ፡፡” በዚህም የእስራኤል የእግዚአብሄር ምርጫ የቀረበ(የተሰጠ) ነው ፤ እግዚአብሄር ለእስራኤል እቅድ ነበረው (ቁጥር 8-9) ፤ የሙሴ መዝሙር በምድረበዳ ለእነርሱ የእግዚአብሄርን ጥበቃ በማስታዎስ ጀመረ ፡፡ እግዚአብሄር ይጠብቃቸው ነበር ፤ ሙሴ የእግዚአብሄር በረከት ተስፋ በገባላቸው ምድር ላይ እንደነበር አሳሳባቸው (ቁጥር 13-14) ፡፡
ዘዳግም(32፡ 15-21)፡ በቁጥር 15 ግን ሙሴ የእግዚአብሄርን መልካምነት መተውን(መግፋትን) አቀረበ፡ “ ይሹሩን ወፈረ ረገጠ…..የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ “ ፤ “ይሹሩን” ለእስራኤል ሌላ ስሙ ነው በዚህም የዚህ ቁጥር መጨረሻው ላይ ያሉ ቃሎች እንዴት አይሁዶች በአዲስ ኪዳን መዓዘን ድንጋዩን እንደሚገፉት የሚያመለክቱ ትንቢታዊ እንደሆኑ አምናለሁ ፡፡ እስራኤላዊያን በዚህ ስፍራ ከተቀመጡ እግዚአብሄር በእነርሱ ፊት ያመጣውን ሁሉንም ነገር ይገፋሉ ፤ እስራኤላዊያን ለሰይጣን በመሰዋት እንካን ከእግዚአብሄር በጣም ርቀው ሄዱ (ቁጥር 17)፡፡ ለሰይጣናዊ አምልኮ እና ለወደቁ መልአክቶች ዕያመጡ ነበር ፤ በምላሹ እግዚአብሄር ቁጣውን ያፈስስባቸው እና ፊቱንም እንካን ከእነርሱ ይሰዉርባቸው ነበር (ቁጥር 20) ፡፡ ባልታወቁ አምላኮች የእግዚአብሄርን ቅናት አነሳሱት (ቁጥር 21) ስለዚህ “ በትንሽ ህዝቦች ቅናታቸውን አስነሳለሁ ፤ በተናቁ ህዝቦች አናድዳቸዋለሁ “ አለ ፡፡ ይህ ከአጠቃለልን ቦኃላ የምንሰፍርበት(የምናርፍበት) ጥቅስ ነው ፡፡
ዘዳግም(32፡ 28-52)፡ እስራኤላዊያን እግዚአብሄር አዝዞአቸው በነበረው ላይ ጭፍን እልኸኝነታቸውን አሳዩ (ቁጥር 28-33) ስለዚህ እግዚአብሄር የእስራኤልን ኃይል አሳነሰ (ቁጥር 34-38) ፡፡ እግዚአብሄር እጁን ወደ “ ሰማይ እዘረጋለሁና እንዲህም እላለሁ ለዘላለም እኔ ህያው ነኝ የሚንቦገቦግ ሰይፌን እስለዋለሁ “ ይላል (ቁጥር 40-42) በራዕይ የክርስቶስ የሚንቦገቦግ ሰይፍ የሚያምር ስዕል ተሰጥቶናል ፡፡ በቁጥር 43 እግዚአብሄር ስለፈወሳቸው ህዝቡ መደሰት ይችላሉ ፤ “ ምድሩን እና ህዝቡን ያነፃል ፡፡” የሙሴ መዝሙር የማስጠንቀቂያ ሆነ (ቁጥር 46) ስለሆነም ህዝቡ ማስጠንቀቂያውን ሊቀበሉ ያገባቸዋል ፡፡ በመቀጠል እግዚአብሄር ሙሴን ባለማመኑ ወደ ሚሞትበት ወደ ናባው ተራራ እንዲወጣ ነገረው ፤ ሙሴ የከነዓንን ምድር መመልከት ይችል ይሆናል ይሁን እንጂ በፍፁም አይገባባትም (ቁጥር 48-52) ፡፡
ዘዳግም 33፡ በቁጥር 1-5 ሙሴ ጠቅላላ ለእስራኤላዊያን በረከትን ሰጠ ከዚያ በመቀጠል በቁጥር 6 መጀመሪያ ሙሴ ለሮቤል፣ ለይሁዳ፣ ለሌዊ፣ ለቢኒያም፣ ለዮሴፍ፣ ለዛብሎን፣ ለጋድ፣ ለዳን፣ ለንፍታሌም እና ለአሴር ነገዶች ባረካቸው ፡፡ በቁጥር 26-29 እስራኤላዊያንን በዚህ ሁሉ እግዚአብሄርን እንዲያተኩሩ አዘዛቸው ፡፡
ዘዳግም 34፡ ሙሴ የተስፋይቱ ምድር እይታ ተሰጥቶት ነበር (ቁጥር 1-4) ከዚያም በቁጥር (5-8) ሙሴ ሞቱ መላው ሀገርም አዘነ ፡፡ ቁጥር 9-12 ኢያሱ ብዙ ጥበብ እንደተሰጠው መዝግቦአል ነገር ግን እስካሁን ደግሞ ልክ እንደ ሙሴ ስም አልነበረም ፡፡ ይህ የሙሴ ዘመን መጨረሻ ነበር መሪነቱም ወደ ኢያሱ ተላለፈ ፡፡
አሁን ወደ ዘዳ (32፡ 21) ስንመለስ ሙሴ ወደ ሌላው ነብይ ኢየሱስ በማመልከት እንደ ነብይ አገልግሎአል ፤ የዘዳግም ታሪክ ያ ነው ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በአመፃቸው የሚቀጥሉ ከሆነ በጣም እንደሚቀና እስራኤላዊያንን(አይሁዶችን) ለማስቀናት ታናሽ(የተናቀ) ህዝቦችን እንደሚጠቀም አስጠመቀቃቸው ፡፡ እግዚአብሄር አይሁዶችን እንደሚያስቀናባቸው ያወራው የነበረው ቡድንአይሁዶች ያልሆንን አህዛቦች እኛ ነን ፡፡
ለምን ህግን(ኦሪትን) ማጥናት በጣም ያስፈለገው ይህ ነው ፤ እንደ አማኝ የእግዚአብሄርን ቃል ከአይሁዶች በላይ በጣም ልናውቅ ያስፈልገንል ፤ ለምን ? በክርስቶስ ምን እንዳለን እንዲፈልጉ እገልጋለሁ ፡፡ ባጠቃላይ የመጀመሪያዎቹ አምስት የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍት በመጨረሻ ወደ ኢየሱስ በዘር፣ በነፃ አዉጪ፣ በአስተሰሪይ፣ በአለት እና በነብይ ያመለክታሉ ፤ እነዚህ አምስት ቃላቶች ወደ ኢየሱስ ያመለክታሉ ፡፡
አይሁዶች እስካሁን የእግዚአብሄር ምርጫ ህዝቦች ናቸው ፤ “ ለአምላክህ ለእግዚአብሄር አንተ ቅዱስ ህዝብ ነህና ፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አህዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ህዝብ ትሆኑለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሄር መረጠህ ፡፡ እግዚአብሄርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአህዛብ ሁሉ በቁጥር ስለ በዛችሁ አይደለም ፤ እናንተ ከአህዛብ ሁሉ በቁጥር ጥቂቶች ነበራችሁና ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ ስለዚህ እግዚአብሄር በጽኑ እጅ አወጣችሁ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉስ ከፈርዖን እጅ አዳናችሁ “ (ዘዳ 7፡ 6-6) ፡፡ አይሁዶች የእግዚአብሄር ምርጫ ህዝቦች ነበሩ ፡፡
ሮሜ (1፡ 16) “ በወንጌል አላፍርምና ፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰዉ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሄር ኃይል ለማዳን ነውና ፡፡” “ አስቀድሞ” የሚለው ቃል ወንጌል ለአይሁድ ነበር ማለት ነው ፤ ነገር ግን ወንጌልን(አድስ ኪዳን) ከመግፋታቸው የተነሳ ድነት ለአህዛብ መጣ ፡፡ የህግን መፅሀፍት በማጥናት እስራኤላዊያንን ኢየሱስ ክርስቶስን መግፋታቸው ትርጉም ይሰጣል ፡፡
ሮሜ (11፡ 11)፡ “ እንግዲህ የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነውን ? እላለሁ ፡፡አይደለም ፤ ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአህዛብ ሆነ ፡፡” በእምቢትኝነታቸው ምክንያት በነሱ ፋንታ ድነት ወደ አህዛብ መጣ ፡፡ ዘዳ (32፡ 21) ወንጌል ወደ አህዛብ ሲመጣ አይሁዶችን ያበሳጨዋል ይህን ክስተት ተንብዮታል ፡፡ በእግዚአብሄር ላይ እንደ ክርስቶስ እመነታቸውን ያደረጉ የአይሁድ ቅሪቶች አሉ ፡፡ በዘዳግም የሆነው ሁሉ ወደ አህዛብ ስለ ሚመጣው ድነት ይመራል ፡፡ እግዚአብሄር አይሁዶችን አልገፋቸውም ፤ እስካሁን ለመረጣቸው ህዝቦቹ እቅድ አለው ፡፡
ሮሜ (10፡ 19-20)፡ “ ነገር ግን እስራኤል ባያውቁ ነው ወይ ? እላለሁ ፡፡ ሙሴ አስቀድሞ እኔ ሕዝብ በማይሆነው አስቀናችኃለሁ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣችኃለሁ ብሎአል ፡፡ ኢሳያስም ደፍሮ ላልፈለጉኝ ተገኘሁ ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ አለ ፡፡” አህዛቦች እግዚአብሄርን አልፈለጉትም ነበር ነገር ግን አይሁዶችን ለማስቀናት እግዚአብሄር ድነትን ለመስጠት መረጣቸው ፡፡ ከቅናት ቦኃላ ወደ ኢየሱስ ለተመለሱት አይሁዶች መጋረጃው ይነሳል ወደ ወይን ማፈራታቸው እንደገና ይሆናል በአለምም ላይ ኃብታሞችን ያመጣሉ ፡፡
ሮሜ (11፡ 12)፡ “ ዳሩ ግን በደላቸው ለዓለም ባለ ጠግነት መሸነፋቸውም ለአሕዛብ ባለ ጠግነት ከሆነ ይልቁንስመሙላታቸው እንዴት ይሆን ! “
ሮሜ (11፡ 24)፡ “ አንተ በፍጥረቱ የበረሀ ከነበር ወይራ ተቆርጠህ እንደ ፍጥረትህ ሳትሆን በመልካም ወይራ ከገባህ ይልቁንስ እነዚያ በፍጥረታቸው ያሉት ቅርንጫፎች በራሳቸው ወይራ እንዴት አይገቡም ? “ በሰው መውደቅ ምክንያት ወደ ቤተሰቡ ተመልሰዉ እንዲመጡ ይፈልጋል እግዚአብሄር ለአይሁዶች ድነታቸውን እንዲቀበሉ የሚያስፈልጋቸው ነበር ፡፡ ይህ አይሁዶች መቸተ ነው የሚያገኙት ? ለኢየሱስ አዎ እንዳልነው አይሁዶች ያለንን ይፈልጋሉ ፡፡ በክርስቶስ እነርሱን በሚያስቀና መንገድ እየኖርንን ነው ? ምን እንዳለን እንዲያዩ የተለየን ለእነርሱ ልዩ መሆን ይገባናል ፡፡ አይሁዶች ከገፉት ጀምሮ ለተቀበልነበው መንፈሳዊ በረከት አመስጋዮች መሆን ይገባናል ፡፡ ወደ አይሁዶች የእግዚአብሄር ምርጫ ህዝቦች ተመልሰን ልናፈስ(ልናጠጣ) ያስፈልገናል ፤ በእግዚአብሄር ምርጥ ህዝቦች ጀመረ በእግዘሂአብሄርም ምርጥ ህዝቦች ያበቃል(ይጨርሳል) ፡፡
ሮሜ (15፡ 27)፡ “ ወደዋልና የእነርሱም ባለ እዳዎች ናቸው ፤ አህዛብ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ተካፋዮች ከሆኑ በስጋዊ ነገር ደግሞ ያገለግሉዓቸው ዘንድ ይገባቸዋል ፡፡” እንደ አህዛብ ለአይሁዶች በሚያስፈልጋቸው በአካላዊና በተጨባጭ ልናገለግላቸው ተገደናል(ግዴታ አለብን) ፡፡
መዝጊያ
በአይሁዶች እንቢተኝነትና በእግዚአብሄር ላይ በአመፅ በሄዱበት ተጠቃሚዎች ነን ፤ በማንኛውም መንገድ በምንችለው ማገልገል እና ወደ እነርሱ መመለስ የኛ ስራ ነው ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 449.
ጥያቄዎች
-
እስራኤል ታሪኩን ወደታች የሚያስተላልፉበት እንዱ መንገድ ዜማ ነበር ፤ በዘዳ (32፡ 1-43) እግዚአብሄር ሙሴን መዝሙር ለመማር የእስራኤልን ህዝብ እንዲረዳቸው ታዘዘ ፡፡ በብዙ የተናገራችሁ የዚህ መዝሙር የትኛው አካል ነው ? በምትወዱት በአንድ ቅኔ ወይም ዝማሬ አሁን እግዚአብሄርን አመስግኑ ፡፡
-
መዝሙር እንደጀመረ ሙሴ እንዲያዳምጠው የተየቀውን ማን ነበር ? (ዘዳ 32፡ 1) ቀጥሎ ትኩረቱን በመመለስ እና እግዚአብሄርን ለማመስገን ሙሴ ምንድን አደረገ ? (ዘዳ 32፡ 3-4)
-
የእግዚአብሄርን ብስጭት ለማስነሳት እስራኤላዊያን ካደረጉት ዉስጥ ጥቂቱን ጥቀሱ (ዘዳ 32፡ 15-19; መሳ 10፡ 6) ? የአለመታዘዛቸው ቅጣት ምንድን ነበር ? ስለ ራሱ ሊያስተምራቸው እግዚአብሄር ምንድን እየሞከረ ነበር ?
-
በዘዳ 33 ሙሴ ከአንዱ በስተቀር እያንዳንዱን ነገድ ባረከ ፤ የትኛው ነገድ ነበር ያልተጠቀሰው (ዘፍ 49፡ 5-7)? ከያዕቀብ በተጠቀሰው እርግማን ድርጊት የተሳተፉ ቢሆንም የሌዊ ነገዶች ለምን እንደተባረኩ ምን ታስባላችሁ (ዘዳ 33፡ 8-11) ? ሚል (2፡ 5)
-
ሙሴ ህጎቹን ወከለ ወደ ተስፋይቱም ምድር መግባት አልቻለም ፤ የህጉ የታሰበው(ተገቢ) አላማው ምንድን ነበር (ሮሜ 3፡ 19-20; ገላ 3፡ 24) ?እንዴት ኢያሱ ኢየሱስን ይወክላል ? (ዮሐ 14፡ 6)
-
በዘዳ(32-34) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Deuteronomy 33:29
How happy you are, Israel! Who is like you, a people saved by the LORD? He is the shield that protects you, the sword you boast in. Your enemies will cringe before you, and you will tread on their backs.
ሙሴ በ120 ዓመቱ በሞዓብ ምድር ከመሞቱ በፊት፥ የመጨረሻዉን መዝሙረ በመዘመር፥ የመጨረሻዉን በረከት ለእስራኤላዉያን ተናግሯል። የተናገራቸዉ ቃሎችም፥ ስለሳላፈዉ መልካም እና ከባድ ጊዜያት ትዉስታ እና ሙሴ የሚያዉቃቸዉ ህዝቡን ወደፊት የሚገጥማቸዉ ነገሮችን ያካተተ ነበረ። እስራኤላዉያን የእግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እጅ ምስክር እንዲሆኑ የተመረጡ ወገኖች፣ የዳኑ እና በእግዚአብሔር የተጠበቁ ናቸዉ። ሙሴ፥ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ያየ፥ ህዝቡን እንዲመራ በእግዚአብሔር የተመረጠ፥ እንደ ሌላ ያልሆነ ነብይ፥ የእግዚአብሔር ሰዉ ነበረ። ሙሴ ወደፊት ህዝቡ ለእግዚአብሔር እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ አስቀድሞ ቢናገርም እንኳን፥ በንግግሩ ዉስጥ "አሁንስ ምን?" የሚል አንድምታ አለዉ። ሙሴ ከሞተ በኃላ እስራኤላዉያን በእግዚአብሔር ፊት የሚመላለሱት እንዴት ይሆን? እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸዉ፣ ነፍሳቸዉ እና ኃይላቸዉ የሚከተሉበት በቂ እና ብዙ ምክንያት አላቸዉ! ነገር ግን ምን ይወስኑ ይሆን?
እንደ አማኝ፥ ለአንተም ተመሳሳይ ነዉ! ዛሬን እንዴት ታሳልፈዉ ይሆን? እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ ትከተለዋለህ? በእርሱ መንገድ ትመላለሳለህ? የትናንትናዉን ታማኝነቱን ታስታዉሳለህን? ነዉ ወይስ ፊትህን በእርሱ ላይ ማዞርን መርጠህ፥ የራስህን መሻት ትከተላለህን? ዛሬ፥ እግዚአብሔር በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ፍቅር እና በሙሉ ልብህ እንድትወደዉ እንደሚሻ ማመንን ምርጫህ አድርግ። የፍቅሩን እዉነት እየተቀበልክ በሄድክ ቀጥር፥ በመንገዱ በፅናት የምትመላለስበትን እና ሌሎችን የምትወድበትን አቅም ታገኛለህ!
"እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።"
ኦሪት ዘዳግም 33:29
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 28:7፦ "እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።"
- መዝሙረ ዳዊት 143:8፦ "አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 16:25-27፦ "እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥ ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 110
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።