Jesus' Family Tree
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሙሴ ተፅፎ የነበረውን የህግን መፅሀፍትን(ዘፍጥረት፣ ዘጸዓት፣ ዘሌዋዉያን፣ ዘኁልቁ እና ዘዳግምን) ጥናታችንንን ጨርሰን የወንጌልን (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ እና ዮሐንስን) ጥናታችንን አሁን ጀምረናል ፡፡ በሁለት አመት ጊዜ ከብሉይ ኪዳን ወደ አድስኪዳን መጎአዛችንን እንጠብቀዋለን ፡፡ ቃል በቃል “ወንጌል” ማለት “ መልካም(ጥሩ) ዜና “ ማለት ነው ፤ በጠቅላላ በወንጌላት ዉስጥ ስለ ጥሩ ዜና እናወራለን ፡፡ የኃጢዓት እና የሞት መጥፎዜና ሁላችንም አለን ነገር ግን እግዚአብሄር ይመስገን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥሩ ዜና አለን ፡፡ በብሉይ ኪዳንለአጠናናቸው ለእያንዳንዳቸው መፅሀፍት እንድ ቃል እንደሰጠን ለምሳሌ ለዘፍጥረት መፅሀፍ ዘር እናስታውሳለን ፤ በአብርሃም ዘር በኩል በመጨረሻ እንዴት ወደ ዘሩ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተ ማየት እንችላለን ፡፡ ለማቴዎስ መፅሀፍት ስለኢየሱስ የሚያወራው አንድ ቃል ንጉስ ነው ፡፡ በማርቆስ መፅሀፍ ኢየሱስ አገልጋይ ነው ፡፡ በሉቃስ መፅሀፍ ማብራሪያው በሰው ልጅ ላይ ሲሆን በዮሐንስ መፅሀፍ ማብራሪያው በእግዚአብሄር ልጅ ላይ ነው ፡፡ በማቴዎስ ኢየሱስን እንደ ንጉስ ትኩረት እናደርግበታል ፡፡ “ንጉስ “ የሚለው ቃል በማቴዎስ መፅሀፍ ውስጥ 22 ጊዜ የተጠቀመው ሲሆን “ መንግስት ” የሚለው ቃል 32 ጊዜ የተጠቀመው ነው ፤ ፀሀፊው ማቴዎስ ከ 12 ደቀመዛሙርት አንዱ ነበር ፤ በተጨማሪም እንደ ሌዊ ይታወቅ እና ኢየሱስን ከኃላው ለመከተል ሁሉንም ነገሩን የተወ የቀድሞ ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር ፡፡ በብዛት የሚያደምጡት(የእርሱ አድማጮች) አይሁዶች ነበሩ ፡፡
በማቴዎስ 1 በኢየሱስ የቤተሰብ ግንድ ውስጥ እንጎአዛለን ፡፡ ለማቴዎስ መፅሀፍ ብዙ ነገሮች ልዩ ናቸው፡ የኢየሱስ የዘር ግንድ፣ የዮሴፍ ህልም፣ የጥበበኞቹ ሰዎች ጉብኝት፣ ወደ ግብፅ ጉዞ፣ ከሁለት አመት በታች ያሉ ወንድ ልጆችን ለመግደል የሄርዶስ አደራረግ፣ የይሁዳ ንስሀ፣ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ የጲላጦስ ሚስት ህልም፣ የወታደሮቹ ጉቦ እና ታላቁ ተልዕኮ ፡፡ ማቴዎስ 1 የምናጠናው ልክ እንደ ህግ መፅሀፍት ነው ምክንያቱም ከብሉይ ኪዳን ታሪካዊ መዝገቦችን ይሰጣል ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ(1፡ 1-6)፡ ቁጥር 1 የኢየሱስን የዘር መስመር ታሪካዊ መዝገብን ይሰጣል ፡፡ የዘር ግንዱ በራሱ ለጠቅላላ 42 ትውልድ ወደ ሰዎስት እያንዳንዳቸው 14 ትዉልዶች የተከፈለ ነው ፡፡ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ኢየሱስ የተለመደ ስም ነበር የመጨረሻው ስሙ “ ክርስቶስ “ አልነበረም ፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜም በእስፔናይ እና በላቲኖ በተለያዩ ባህል ቅላፄ የተለመደ ስም ነው ፡፡ መጀመሪያ ማቴዎስ ኢየሱስን እንደ ዳዊት ልጅ ነው የገለፀው ፤ 2ሳሙ (7፡ 12) የዚህን መለያ አስፈላጊነት ሰጥቶአል፡ “ ዕድሜህም በተፈፀመ ጊዜ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኃላ አስነሳለሁ መንግስቱንም አጸናለሁ ፡፡” የማቴዎስ አንባቢዎች የኢየሱስን የዘር ግንድ ባነበቡ ጊዜ በዳዊት ልጅ ሰለሞን ወደ ኢየሱስ እንዳለፈ ወዲያውኑ ከዳዊት ኪዳን ጋር ያገናኝቸዋል ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ ለማቴዎስ የኢየሱስ የዘር ግንድ ለምን በጣም ያስፈለገበትን ሰዎስት ምክንያቶች ሰጥቶአል፡ 1) ኢየሱስ እስራኤላዊና አይሁዳው እንደነበር አረጋግጦአል, 2) ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ ተገናኝቶ እንደነበር ለይቶአል እና 3) ለሆነ ኃይማኖታዊ ተግባር ተመርጦ እንደነበር ያሳያል ፤ ይህ ማለት በእርሱ ጥሪ ለመሄድ የሆነ ሰው የዘር ግንድ እንደሚፈቅድለት ያረጋግጣል ማለት ነው ፡፡ ዘፍጥረት 12 ለዘላለም ስለሚመራው ዘር ያወራል ፡፡
በቁጥር 2 የዘር መስመሩ በአብርሃም፣ በይስሐቅ፣ በያዕቆብና በይሁዳ ይጀምራል ፤ የመጀመሪያዉ 14 ትዉልድ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ይሄዳል ፤ በኢየሱስ የዘር መስመር ዉስጥ አምስት ሴቶች ተጠቅሰዋል ትዕማር( በህግ አባቶአ ከሆነው ጋር ወሲባዊ ግንኙነት የነበራት)፣ ረዓብ(እስራኤላዊያንን ሰላዮች የተከላከለችላቸው ሴተኛ አዳሪ) እና ሩት (እንግዳዋና ጣዖት አምላኪዋ) ይይዛል ፡፡ ቶም ኮንስታብል ሴቶቹ ለምን ተካተው እንደነበር ብዙ ምክንያቶችን ይሰጣል፡ 1) ኢየሱስ ለኃጢዓታኞች እንደመጣ ለማሳየት, 2) ኢየሱስ በፃታና በዘር ሳይሆን ለሁሉም እንደመጣ ለመሳየት, 3) አንባቢዎቹን የኢየሱስ የዘር መስመር እንደ አካል ለማሪያም ሚና ለማዘጋጀት, 4) በኢየሱስ የዘር መስመር “ የተዘበራረቀ የጋብቻ ውህድ “ እንደነበር ለማሳየት እና 5) እግዚአብሄር እንዴት አህዛብን “ ከአይሁዶች በተነፃፃሪ ተጨማሪ እምነት “ ለማሳየት እንደተጠቀመባቸው ለማሳየት ፡፡ የዘር ግንዱ ክፍል መጀመሪያ በተጠቀሰው ንጉስ በንጉስ ዳዊት ያበቃል (ቁጥር 6) ፡፡ ይህ እግዚአብሄር በኑሮአቸው ያለው ስህተት ሳይቆጥር በማንኛውም በተሰጠ ጊዜ ማንኛውንም መጠቀም እንደሚችል ያሳያል ፡፡
ማቴዎስ (1፡ 6-11)፡ በቁጥር 6 ማቴዎስ “ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰለሞንን ወለደ “ መዝግቦአል ፡፡ ማቴዎስ ቤርሳቤህን አልጠቀሰም ምክንያቱም እሳን ለኬጥዋዊያን እያያት ነው በተጨማሪም እግዚአብሄር እንግዶችንም መጠቀም እንደሚችል እያሳየን ነው ፡፡ የሁለተኛው 14 ትዉልድ እስራኤላዊያን እንደ ባሪያ ተወስደው በነበረበት ጊዜ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ግዞት የሄዳል ፡፡ ይህ ክፍል ስማቸው በደንብ በማይታወቅ ሰዎች የሞላ ነው እንደገና እግዚአብሄር ማንኛውንም መጠቀም እንደሚችል፣ እንደሚዋጃቸው እና ወደ መሲሁ ለማመልከት እንደሚጠቀምባቸው ያሳያል ፡፡ ዮሐ (1፡ 14) የእርሱን የመምጣቱን አስፈላጊነት ይሰጣል፡ “ ቃልም ስጋ ሆነ ጸጋንና እዉነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ ፡፡“ ማቴዎስ ሁሉንም በዘር ግንድ ዉስጥ እንዳላካተተ እናውቃለን ነገር ግን ያ የኢየሱስ ወይም የዘሩን መስመር መነሻ(ኃላ ታሪክ ላይ) ተፅዕኖ የለውም ፡፡
ማቴዎስ (1፡ 12-16)፡ ሰዎስተኛው የ 14 ትዉልድ መደብ ከባቢሎን ግዞት መጨረሻ እስከ መሲሁ ይሄዳል ፡፡ ማቴዎስ በቁጥር አንድ የዘር ግንዱን በኢየሱስ ጀመረና በኢየሱስ ጨረሰ ፡፡ በቁጥር 16 ማቴዎስ የኢየሱስን የዘር መስመር ከዮሴፍ ጋር አገናኘው ፡፡ ማክአርቱር በስጋ ዮሴፍ የኢየሱስ አባት ባይሆንም ይህ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፃታል፡ “ የዘር ግንድ ያለምንም እንደ የዮሴፍ ህጋዊ ወራሽ ወደ ዳዊትን ዙፋን መብቱን መሰረተ ፡፡“
ማቴዎስ (1፡ 17)፡ ቁጥር 17 የኢየሱስን 42 ትዉልድ ዝርዝሩን ያጠቃልለዋል ፤ የኢየሱስን ቤተሰብ የዘር መስመር ከመሰረተ ቦኃላ ማቴዎስ የኢየሱስን ዉልደት በዝርዝር ለመስጠት ተጎአዘ ፡፡ ቀሪው የማቴዎስ መፅሀፍ ስለ ኢየሱስ ህይወት ነው ፡፡
ማቴዎስ (1፡ 18-25)፡ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ለትክክለኛ ጋብቻ እንደ ማገናኛ እጮኝነት ይታይ ነበር ፡፡ በቁጥር 18 ዮሴፍ “ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች “ ፡፡ ዮሴፍ እንደ ፃድቅ ሰው ማሪያምን ሊተዋት ስላልፈለገ በሚስጥር ሊተዋት ነበር (ቁጥር 19) ፤ ይሁን እንጂ ዮሴፍ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ከመቻሉ በፊት መልዓክ ለእርሱ ተገለጠለት (ቁጥር 20) ፤ መልዓኩ የዮሴፍን የዘር መስመር (የዳዊት ልጅ) አረጋገጠለትም እግዚአብሄር የማሪያምን እርግዝና በመንፈስ ቅዱስ በኩል አዘጋጅቶ እንደነበር ገለፀለት ፡፡ በቁጥር 21 ዮሴፍ የልጁን ስም ተሰጥቶት ነበር “ ኢየሱስ ምክናያቱም ህዝቡን ከኃጢዓታቸው ያድናቸዋል “ ፡፡
መዝጊያ
በአይሁዶች እልኸኝነት በእግዚአብሄር ላይ በአመፅ በሄዱበት ተጠቃሚዎች ነን በዚህም በማንኛውም መንገድ በምንችለው ለማገልገል እና መልሰን ለእነርሱ መልሶ መስጠት የኛ ስራ ነው ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1137.
Tom Constable, Dr. Constable’s Notes on Deuteronomy (available online at www.soniclight.com), p. 24.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), pp. 1120.
ጥያቄዎች
-
በማቴዎስ 1 የተፈፀመው ለአብርሃም የእግዚአብሄርን ተስፋ እንዴት ታዩታላችሁ ? (ዘፍ 12፡ 3; ማቴ 1፡ 1, 16)
-
በቀድሞው የዘር ግንድ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ ፤ በማቴዎስ የዘር ግንድ የተጠቀሱት አራቱ የብሉይ ኪዳን ሴቶች እነማን ናቸው (ማቴ 1፡ 2-6) ? እነዚህ የተለዩ ሴቶች ለምን እንደ ተጠቀሱ ምን ታስባላችሁ ? ይህ ስለ እግዚአብሄር ፀጋ ምንድን ይነግራችኋል ለክብሩስ ለመጠቀም ማንን ይመርጣል ? (ዘፍ 38; ኢያ 2፡ 4-6; ሩት 1; 2ሳሙ 11)
-
ስለ ዮሴፍ አንባቢዎቹ መረዳትን እንዲያገኙ ማቴዎስ የሞከረው ምን ነበር ? (ማቴ 1፡ 16)
-
የእግዚአብሄር መለዓክ ስለ ኢየሱስ ዮሴፍን ምንድን ነገረው ( ማቴ 1፡ 21; ሐዋ 4፡ 12; 13፡ 23; ዕብ 7፡ 25)? ለዚህ ዜና ዮሴፍ እንዴት አድርጎ መለሰ ?
-
በብሉይ ኪዳን በማመንዘር ህግ መሰረት ማሪያም ላይ ምንድን ይሆናል (ዘዳ 22፡ 23-24) ? ይህ ባለመሆኑ ስለ ዮሴፍ ይህ ምንድን ይላል ?
-
በማቴዎስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 1:21
She will give birth to a son, and you are to name Him Jesus, because He will save His people from their sins.
እግዚያብሔር ለአለም ላለው እቅድ አካል ሆኖ፥ ዮሴፍ እና ማርያም በድንግልና የተወለደ ወንድ ልጅ ነበራቸው፡፡ አንድ ሰው ልጅ ወልዷል የሚለውን ዜና ስትሰሙ፥ ብዙ ጊዜ በመጀመሪያ የምትጠይቁት ጥያቄ፥ " ወላጆቹ ህጻኑን ማን ብለው ጠሩት?" የሚል ነው፡፡ የጌታ መልአክ ለዪሴፍ በህልም ከተገለጠለት በኋላ፥ በታዛዠነት ልጃቸውን ፥ኢያሱ ለሚለው የእብራይስጥ ስም የግሪክ ቅርጽ በሆነው ፥ኢየሱስ በሚለው ስም ሰየመው፥ ትርጓሜውም "ያህዌ ያድናል" ነው፡፡ ዮሴፍ እና ማርያም ኢየሱስ በተወለደበት ጊዜ፥ ስሙ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ አላስተዋሉም ይሆናል፥ ይህም አዲስ የተወለደው ልጃቸው የአለም አዳኝ ሊሆን እንደተወለደ ነው፡፡ እርሱ ነቢያት እንደተነበዩት አማኑኤል᎗ እግዚያብሔር ከእኛ ጋር ነበር፡፡
ስለራሳችሁ ስም ትርጉም አስቡ እና በትርጉሙ መሰረት ፀልዩ፡፡ጌታን፥ በእግዚያብሔር መንግስት ውስጥ እንዴት ተጽዕኖ ማምጣት እንደምትችሉ እንዲገልጽላችሁ ጠይቁት፡፡ ስለ ኢየሱስ፥ የሹዋ፥ ታላቁ እኔ ነኝ፥ ከሀጢያታችሁ ሊያድናችሁ እና ነጻ ሊያወጣችሁ ለተወለደው፥ ምስጋና አቅርቡ፡፡
"ልጅም ትወልዳለች፣ እርሱ ሕዝቡን ከኋጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ፡፡"
—የማቴዎስ ወንጌል 1:21
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ዘፍጥረት 32:28 — “ አለውም ፦ከእንግዲ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል ፤ከእግዚያብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና፡፡”
- የሉቃስ ወንጌል 2:11 — “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡”
- 1 ዮሐንስ 4:10 — “ፍቅር እንደዚህ ነው፤ እግዚያብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢያታችንም ማስተሰሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚያብሔርን እንደወደድነው አይደለም፡፡ ”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 1
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።