The Search For Jesus
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በማቴዎስ መፅሀፍ ላይ ይህ ክፍል 2 ነው ፡፡ መፅሀፍትን ማጥናት ሁሉም በአንድ እንዴት እንደሚጣጣሙ ያሳያል ፡፡ በማቴዎስ 1 በኢየሱስ የዘር መስመር ኢየሱስ የቀጠለበት የቤተሰብ ግንድ ላይ ተመልክተናል ፡፡ ኢየሱስ ከአብርሃም ልጅ እና ከዳዊት ልጅ እናም ከ 42 ከብሉይ ኪዳን ትዉልድ ቦኃላ መጣ ፤ ዘር መስመሩን ስንመለከት በወንዶቹ ዝርዝር ዉስጥ የተካተቱ አምስት ሴቶች አሉ ፤ ከእነዚህ ጥቂቶቹ ሰዎች የቆሸሹ ቢሆኑም እግዚአብሄር እስካሁን ተጠቀባቸው - ኢየሱስ ሌሎችን ወደ ራሱ ለማመልከት ማንኛውንም መጠቀም ይችልል ፡፡
ሪቫይቭ ት/ቤት ጳዉሎስ ሁል ጊዜ ስለ ቃል ከሚያወሩት ከ 12 ሌሎች ጋር ማጥናቱን በሐዋ 19 መሰረት በማድረግ ተጀመረ ፡፡ ስለዚህ እንደ መሲህ ስለ ኢየሱስ ስናወራ ስለ ኢየሱስ ከሌሎች ሰዎች ጋር በማውራት እየተማራችሁ ያለነውን አካፍሉ ፡፡ ቃሉ ከህንፃው መዉጣት አለበት እናም ከቤተ ክርስቲያን ዉጪ ወደ ሚኖሩ ሌሎች ጋር መሄድ አለበት ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (2፡ 1-3)፡ ቤቴልሄም ማለት “ የእንጀራ ቤት “ ማለት ነው ፡፡ በይሁዳ ቤተልሄም ኢየሱስን ለማግኘት ስዎች ቤታቸውን፣ ቤተሰባቸውን እና አካባቢያቸውን ትተው ይሄዳሉ ፡፡ ሰዎችን በመጠየቅ “ የአይሁድን ንጉስ” ለመፈለግ ሰብዓ ሰገል ወደ ኢየሩሳሌም መጡ (ቁጥር 2) ፤ “ ኮኮቡን በምስራቅ አይተናል ልንሰግድለት መጥተናል ” (ቁጥር 2)፡፡ ሰብዓ ሰገሎቹ ንጉሶች አልነበሩም ፤ ምናልባት አስማተኛ ወይም ኮኮብ ቆጣሪዎች ወይም ኮኮብ አጥኒዎች ይሆናሉ ፡፡ አንዱአን ኮኮብ እንደ ንጉስ ኮኮብ እንዲያዉቁ የሆነ ነገር በፍጥነት አነሳሳቸው ፤ ስለ ኢየሱስ እንደ ንጉስ ለምትፈልጉት ይህ ምርጥ ጥቅስ ነው ፡፡ ስለዚህ ስናስብ…. ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ በራሱ ላይ አስቀምጠውት የነበረው ያ ምልክት “ የአይሁድ ንጉስ” እንደነበር ያውጃል ፡፡ ያ ማዕረግ በህይወቱ በሁለቱም መጀመሪያም እና መጨረሻ ላይ የተገኘ መጨረሻም ላይ በቀልድ የተነገረ ነበር ፤ እዚህ ቦታ ላይ እንካን ከእግዚአብሄር የነበረ አዋጅ እንደነበር አምናለሁ ፡፡ የአሜሪካ የገባና ባህል ሁል ጊዜ ሰዎስት ስብዓ ሰገሎችን ያመለክታሉ ነገር ግን ምን ያክል እንደነበሩ አናውቅም ፡፡ ንጉስ ሄሮድ ሌላ ንጉስ በመታየቱ የተረበሸ ሆነ “ኢየሩሳሌም ሁሉ ከእርሱ ጋር “ (ቁጥር 3) ፡፡ ብዙ ሀተታ ሰጪዎች የሚሉት ኮኮባ አስገራሚ ተወርዋሪ አልነበረችም ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ልክ እንደ እግዚአብሄር ታላቅ ክብር መለኮታዊ እውነት ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት ኮኮባን ሰብዓ ሰገሉን ወዴት እንደሚሄዱ እንድትመራቸው አንቀሳቀሳት ፡፡
ማቴዎስ (2፡ 4-6)፡ በቁጥር 4 ሄሮድስም ሁሉንም የኃይማኖት መሪዎች በአንድ ላይ መሲሁ የት እንደሚወለድ እንዲጠይቁ አመጣቸው ፡፡ ይህ እግዚአብሄር አይሁዶች ያላደረጉትን ወደ ልጁ መንገዱን ለማመልከት የአህዛብን (ጥበበኞቹ ሰዎች) ልዩ እምነት የተጠቀመበት ጊዜ ነው ፡፡ በብሉይ ኪዳን በሚክ (5፡ 2) መሰረት የይሁዳን ቤተ ልሄም አይሁዶች መልሱን ያውቁታል፡ “ እርሱም አንቺ ቤተ ልሄም የይሁዳ ምድር ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና “ ማቴ (2፡ 6) ፡፡ እነዚህን ቡድኖች አስቡ(ፃፎች እና ፈሪሳዊያን, የኢየሩሳሉም መሪዎች) ንጉሴ የት እንደሚወለድ ለሄሮድ ለመናገር መጡ ፡፡
ሚክ(2፡ 5) መሲሁ ወደ ሚፈፅማቸው ሁለት ሚናዎች ያመለክታል -መሪ እንደሚሆን እና እረኛ እንደሚሆን ፡፡ ማክአርቱር ያሚያብራራው “ የግሪክ ቃል “ለመሪ” የጥንካሬ ምስል መገለጫ እንደውም ኃይለኛ መሪነት የሚገልጥ ነው ፤ “ እረኛ “ ደግ ጠባቂ የሚለውን ይገልፃል ፤ የክርስቶስ መሪነት በሁለቱም ያጠነጠነ ነው ፡፡ “ ሚክ (2፡ 5) ወደ ራዕ (12፡ 5) ያመለክታል፡ “ አህዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች ፤
ልጅዋም ወደ እግዚአብሄር እና ወደ ዙፉኑ ተነጠቀ “ ፤ ይህ ንጉስ መሪና እረኛ ነው ፡፡ መዝ (78፡ 70-72) የመሪ/እረኛ የሁለቱንም ሚና ይገልፃል፡ “ ዳዊትንም ባሪያውን መረጠው ከበጎቹም መንጋ ዉስጥ ወሰደው ፤ ከሚያጠቡ በጎችም በኃላ ባሪያውን ያዕቆብን ርስቱንም እስራኤልን ይጠብቅ ዘንድ ወሰደው ፡፡ በልቡ ቅንነት ጠበቃቸው በእጁም ብልሀት መራቸው ፡፡”
ማቴዎስ(2፡ 7-9)፡ ከኃይማኖት መሪዎች ጋር በመነጋገሩ ሄሮድስ ከጥበበኞቹ ጋር ተገናኘ አይተዋት የነበረችውን ኮኮብ የተከሰተጭበትን ትክክለኛ ጊዜ ጠየቃቸው (ቁጥር 7) ፤ በቁጥር 8 ሄሮድስ ልጁን እንዲፈልጉ እና ጠይቀው መልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉለት ወደ ቤተ ልሄም ላካቸው ስለዚህ መሄድ ስለሚችል እሱም ይሰግድለታል ፤ ሄሮድስ ሰበዓ ሰገሎችን ተጠቀመባቸው ፡፡ ከሄሮድስ ጋር ከተገናኙ ቦኃላ ሰበዓ ሰገሎች (ጥበበኞቹ) ትተው እንደገና ኮኮቡን ተመለከቱ ህፃኑ ወደ ነበረበት ትክክለኛ ቦታ ድረስ ተከተሉት (ቁጥር 9) ፤ አስታዉሉ እዚህ ጋር ያለው ቃል “ልጅ “ “ህፃን “ አይደለም ፡፡ በአሜሪካ ገና በዓል ባህል ያደረግነው አድስ የተወለደ ህፃን ለማየት ሰዎስት ጥበበኛ ሰዎች በግርግም ላይ አሳይተውናል ፤ እዉነታው ሰበዓ ሰገሎች የደረሰት ልጁ ከተወለደ ከአንድ ወይም ከሁለት አመታት ቦኃላ ነው ፡፡
ማቴዎስ (2፡ 10-11)፡ ቁጥር 10 የሚለው “ ኮኮቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው ፡፡” ይህን እንዳትስቱ ፤ የእግዚአብሄርን የሆነ ነገር መለማመድ በቻልን ጊዜ በማቆም ያን ክስተት መደሰት አለብን ፤ በእግዚአብሄር መገኘት በደስታ ተሞሉ ፡፡ በጥሪአችሁ መጎአዝ በጀመራችሁ ጊዜ በደስታ ትሞላላችሁ ምክንያቱም ከእግዚአብሄር ስለሚመጣ ፤ 1ጴጥ (1፡ 6-8) የሚለው “ በዚህም እጅግ ደስ ይላችኃል ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኃል ፡፡ እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሴት ደስ ይላችኃል ፡፡ “ በትግል ውስጥ እንካን ደስታ አለ ፡፡ በዚያን ክስተት ሰበዓ ሰገሎች ልጁን አላዩት ነበር ነገር ግን ኮኮቡን አይተዋል በልጁ መገኘት ውስጥ እንደነበሩ ያውቃሉ ስለሆነም በማይነገር እና በታላቅ ደስታ ተደሰቱ ፡፡
ቁጥር 11 የሚለው ወደ ቤት(ቐሚ ወዳልሆነ) ገቡ ልጁንም አዩት በአምልኮ በጉልበቶቻቸው ተነበረከኩ ፤ ቀጥሎም ኢየሱስን አዩት ሰገዱለትም ፤ ከዚያም ስጦታቸውን አቀረቡ ፡፡ እነዚህ ጥበበኛ ሰዎች በእግዚአብሄርፊት በመምጣት አዘጋጁ ፤ ሰዎስት ስጦታዎችን ወርቅ፣ ዕጣን (ከዛፍ ሙጫ) እና ከርቤ ( የደቀቀ እንደ ቁስ አይነት) ፤ በኢሳ (60፡ 6) የእነዚህ ስጦታዎች ትንቢታዊ መልክ ነው፡ “ የግመሎቹ ብዛት የምድያምና የጌፌር ግመሎች ይሸፍኑሻል ፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣል ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሄርንም ምስጋና ያወራሉ ፡፡”
የአህዛብ ጥበበኞች ሰዎች ስጦታዎች ለእግዚአብሄር ለምንሰጠው ስቶታዎቻችን ትኩረት ይጠራል ፤ ሮሜ (15፡ 25-27) ለአይሁዶች ማገልገል እንዳለበት የክርስቲያንን ግዴታ ያደርሳል፡ “ አሁን ግን ቅዱሳንን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ ፡፡ መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ቅዱሳን መካከል ያሉትን ድሆች ይረዱ ዘንድ ወደዋልና ፡፡ ወደዋልና የእነርሱም ባለ ዕዳዎች ናቸው ፤ አሕዛብ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ተካፋዮች ከሆኑ በስጋዊ ነገር ደግሞ ያገለግሉዓቸው ዘንድ ይገባቸዋል ፡፡”
ማቴዎስ(2፡ 12-15)፡ በህልም ሰበዓ ሰገሎችን ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 12) ፤ ሰበዓ ሰገሎች ከሄዱ ቦኃላ መለዓክት በህልም ለዮሴፍ ተገልጦ ቤተሰቡን ወደ ግብፅእንዲወስድ ነገረው (ቁጥር 13) ፡፡ መልዓኩ ዮሴፍን ወደ እስራኤል ለመመለስ ደህን መሆኑን ተመልሶ እስኪነግረው ድረስ በዚያው እንዲቀመጥ ነገረው ፤ ዮሴፍ ይህን በሂደት አላደረገም ወይም ችላ ማለትና እና ማታለልን ላሰበም ወዲያዉኑ ትቶ ሄደ (ቁጥር 14) ፡፡ ዮሴፍ በመታዘዝ ወደ ግብፅ በመውሰድ የአይሁድን ንጉስ አዳነ ፡፡ እስከ ሄሮድስ ሞት ድረስ በዚያ ቆዩ በዚህም ምክንያት በሆሴ (11፡ 1) ያለው ትንቢት ይፈፀማል፡ “ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት “ (ቁጥር 15) ፡፡ ዮሴፍ መለዓኩ ያለውን ሊታዘዝ የቻለው የእግዚአብሄር ቃልን ስለሚያውቅ እና መሲሁ ከግብፅ እንደሚወጣ ትንቢታዊ መልዕክቱን ስለተረዳ ነው ብዬ አምናለሁ ፤ ብዙዎቻችን ከእግዚአብሄር እንሰማለን ነገር ግን በቃሉ አደለንም ስለዚህ የሰማነውን በምን ከቃሉ ጋር እንደምናገናኝ አናውቅም ፡፡ በመንፈስ ስለ መመራት ወላዋዮች ነን ፤ የእግዚአብሄርን ቃል ባወቃችሁ ጊዜ ህይወት በብዙ ቀላል ያደርጋታል ፡፡
ማቴዎስ(2፡ 16-23)፡ በቁጥር 16 ሄሮድስ በሰባ ሰገሎች ተሸዶ እንደነበር አወቀ “ በቤተ ልሄምና በአውራጃዋ የነበሩትን ሁለት አመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ ፡፡ “ ዮሴፍ ከእግዚአብሄር የሆነውን ትዕዛዝን በማክበሩ የአይሁድ ንጉስ ዳነ ከሆሴ የነበረው ትንቢት ተፈፀመ ፡፡ ቁጥር 18 የእነዚህን ቃሎች ከኤር (31፡ 15) መፈፀም መዝግቦአል፡ “ የዋይታና የመራር ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ ፤ ራሄል ስለ ልጆቾአ አለቀሰች ፤ የሉምና ስለ ልጆቹዋ መጽናናትን እንቢ አለች ፡፡” በቁጥር (19-20) መለዓኩ በድንገት ለዮሴፍ ተገለጠና ቤተሰቡን መልሶ ወደ እስራኤል እንዲወስድ ነገረው ፤ ዮሴፍ በእግዚአብሄር ላይ ጠበቀ እግዚአብሄርም ተናገረው ፡፡ በቁጥር 21 ዮሴፍ ታዘዘ ፤ ከእግዚአብሄር የሰማውን አደረገ ፡፡ በቁጥር 22-23 ዮሴፍ እንደገና ታዘዘ ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ቃል ስለሚያውቅ ቤተሰቡንም የት እንደሚወስድ ያውቃል ፡፡
መዝጊያ
ሰበዓ ሰገለ ኮኮቡን አዩት ፤ ዮሴፍ በህልም ከእግዚአብሄር ሰማ ፡፡ እንዴት ከእግዚአብሄር እንሰማለን ሁል ጊዜ የተለያዩ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችንስ እንዴት ከእግዚአብሄር እናያለን ፤ በፓስተሩ የስብከት ትምህርት በኩል ሊሆን ይችላል ወይም ወደ እናንተ ህይወት የሚናገር ከሪቫይቫ ት/ቤት ጋደኛ ሊሆን ይችላል ፡፡ በመታዘዝ ጉዞአችንን ጠብቆ መጎአዝ ያስፈልገናል፣ መጠበቅ እና ከእግዚአብሄር በመስማት ማዳመጥ ምክንያቱም እሱ የአይሁድ ንጉስ ነው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), pp. 1131-1132.
ጥያቄዎች
-
ሰበአ ሰገሎች ኢየሱስን በመፈለግ ትጉህ ነበሩ ፤ በአይምሮአቸዉ አንድ ነገር ነበር እርሱም ኢየሱስን ፈልጎ መስገድ ነበር ፡፡ ስለ አምልኮአችሁ እንዴት ትጉህ ናችሁ ? ለአምልኮ ተርባችኋል ወይስ አለም ህይወታችሁን ተፅዕኖ አድርጎበታል ?
-
በማቴዎስ 2 ከብሉይ ኪዳን ቢያንስ አራት ትንቢቶች አሉ ኢየሱስን በተመለከተ ፤ እያንዳንዳቸዉን በምዕራፉ ዉስጥ ፈልጉና ተመልከቱዓቸው ፤ (ማቴ 2፡6, 15, 18 እና 23) አስታዉሉ፡ በዚህ ምዕራፍ የመጨረሻዉ ትንቢት በብሉይ ኪዳን ዉስጥ የትም አይገኝም ነገር ግን በነቢያቶች የተነገረ እንደሆነ ይታመናል ፡፡
-
በማቴዎስ 2 የዮሴፍ የነበሩት ሰዎስቱ ህልሞች ምንድን ነበሩ (ማቴ 2፡ 13, 19, 22) ? እነዚህን ህልሞች ለመታዘዝ ዮሴፍ ለምን ፈጣን እንደ ነበር ምን ታምናላችሁ ? በህልም ከዚህ በፊት እግዚአብሄር ለእናንተ ተናግሮአችኋል ? የምታከብሩት(የምትታዘዙት) ነገር ነበር ? አዎ ከሆነ አደረጋችሁት ?
-
ሰበዓ ሰገሎቹን እና እረኞቹ ሁለቱም ስለ ኢየሱስን መፈለግ ላይ በነበሩበት ስለ ንፅፅሩ ምንድን አሳወቃችሁ (ማቴ 2፡ 1, 9-11; ሉቃ 2፡ 15-20) ? ከሁለቱ መጀመሪያ ኢየሱስን ማን አየው ?
-
ማቴዎስ (2፡ 16) አይነት ቁጥሮችን ማንበብ አስቸጋሪ ነው ፤ እግዚአብሄር ይህ እንዲሆን ለምን እንደ ፈቀደ ምን ታስባላችሁ ? (መዝ 19፡ 9; ኢሳ 55፡ 11; ኤር 1፡ 12; ማቴ 2፡ 17-18)
-
በማቴዎስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 2:13-14
After they were gone, an angel of the Lord suddenly appeared to Joseph in a dream, saying, ‘Get up! Take the child and His mother, flee to Egypt, and stay there until I tell you. For Herod is about to search for the child to destroy Him.’ So, he got up, took the child and His mother during the night, and escaped to Egypt.
ዮሴፍ፣ ማርያም እና ኢየሱስ፥ ኢየሱስ በመጨረሻ ወደ አደገበት በናዝሬት ከመቀመጣቸው በፊት፥ የትውልድ ስፍራው ከሆነው ከቤትልሔም ወደ ግብጽ ሄዱ፡፡ ሁልጊዜም የሚንቀሳቀሱት ወይም የጉዞ እቅዳቸውን የሚቀይሩት፥ ዮሴፍ ባየው ህልም ምክንያት ነበር፡፡ ከእያንዳንዱ ህልም በኋላ፥ ዮሴፍ ወዲያውኑ ታዝዞ፥ በእኩለ ሌሊት መውጣት ማለት እንኳን ቢሆንም፥ ቤተሰቡን እንዲሄድ ወደ ተነገረበት ስፍራ አዘዋወረ፡፡
ከኢየሱስ ጋር ህብረት እንዳለው አማኝ፥ እርሱ ያናግራችኋል፥ ይህንንም በህልም ሊያደርገው ይችላል፡፡ በህይወታችሁ ህልሞች ሊመጡ እና ሊሄዱ ይችላሉ፥ አንዳንድ ጊዜም ስለ ህልሞቻችው ምንም ላታስቡ ትችላላችሁ፡፡ ቢሆንም ግን፥ በሚቀጥለው ጊዜ ህልም ስታዩ፥ ቆም ብላችሁ ህልማችሁን ፃፉት፥ ጌታንም በህልማቹ ምን እየተናገራችሁ እንደሆነ ጠይቁት፡፡ አንድን ነገር እየገለፀላችሁ ከሆነ፥ በእምነት እና በመታዘዝ ተግብሩት፡፡ ዮሴፍ በእምነት ተንቀሳቀሰ፡፡ ወዲያውኑ እርምጃ በመውሰዱም ልጁን አዳነ፡፡ ሰብአ ሰገል ወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ በሕልም ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፥ ወዲያውኑ በሌላ መንገድ በመሄድ ራሳቸውን አዳኑ፡፡ መንገዶቻችሁን አሳይቶ በእርምጃዎቻችሁ ስለመራችሁ፥ በህልም እንኳን ስለተናገራችሁ ጌታን አመስግኑት፡፡
“ እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕጻኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ ፥እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው፡፡ እርሱም ተነሥቶ ሕጻኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነብይ፦ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብጽ ሄደ፡፡”
—የማቴዎስ 2:13-14
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 119:60 — “ ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም፡፡”
- ትንቢተ ኢዩኤል 2:28 — “ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በስጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራዕይ ያያሉ”
- የማቴዎስ ወንጌል 2:12 — “ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 2
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።