Baptism by the Holy Spirit and Fire
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በመጀመሪያዎቹ ሁለት ምዕራፍ ማቴዎስ የኢየሱስን ቤተሰብ ግንድ እና የአይሁድን ንጉስ ለመመልከት የመጡትን ሰበዓ ሰገልን መዝግቦአል ፡፡ በዚህ ምዕራፍ መጥምቁ ዮሐንስ ለአይሁድ ንጉስ መንገዱን ሊያዘጋጅ እንደ መጣ ያውጃል ፡፡ የንጉሱን መምጣት አሳውቆ የነበረው መንገድ ጠራጊ(መልዕክተኛ) ተብሎ ይጠራ ነበር ፤ ዮሐንስ ዋልቮርድ የሚለው መልዕክተኛ ንጉሱ ከተማዋን ሊጎበኝ እንደሚመጣ እና ከተማዋ እርሱን ለመቀበል ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደነበረች እርግጠኛ ለማድረግ ከንጉሱ ፊት ይሄዳል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለሚመጣው ንጉስ መንገዱን ለማሳተካከል መልዕክተኛ ጥቂት ስራዎችን ለመስራት የሚጠይቁ ይሆናል ለመድረሱም ያዘጋጃል ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (3፡ 1)፡ ዮሐንስ የነበረበት አካባቢ ከሙት ባህር(ከጨው ባህር) በስተ ምዕራብ በኩል የሚገኝ ነው ፡፡ ለምን የሆነ ሰው ማንም ባልነበረበት በምድረበዳ አካባቢ የንጉሱን መምጣት ለማሳወቅ እየሰበከ መምጣት ያስደንቃችኃል ነገር ግን ይህ እግዚአብሄር እንዴት አቅዶት እንደነበር ያሳያል (1ቆሮ 1፡ 26) ፡፡ እግዚአብሄር መጥምቁ ዮሐንስን በምድረበዳ አስቀመጠው ስለዚህ ሁሉም ስለ እግዚአብሄር እንጂ ስለ እርሱ እንዳልነበር ያዉቃሉ ፡፡
ማቴዎስ (3፡ 2)፡ በቁጥር 2 ዮሐንስ ይህን መልዕክት “ መንግስተ ሰማይ ቀርባለችና ንስሀ ግቡ !” ንስሀ መግባት ማለት ነገሮችን የምታደርጉበትን አሮጌ መንገድ ወዲያዉኑ መቀየር፣ ነገሮችን እንዴት የምትሰሩበትን ሀሳባችሁን ወዲያዉኑ መቀየር፣ በኃጢዓት ላይ ጀርባችሁን ማዞር እና ወዲያዉኑ ወደ መንግስተ ሰማይ መሮጥ ማለት ነው ፡፡ አይሁዶች “ እግዚአብሄር” የለውን ስም ማለት አይፈልጉም ምክንያቱም እርሱን ማክበር እና መታዘዝ ነው የሚፈልጉት ፤ ስለዚህ ማቴዎስ “ የእግዚአብሄር መንግስት” በሚለው ፋንታ “ የሰማይ መንግስት” የሚለውን ቃል ተጠቀመ ፡፡ ማክአርቱር የሚገልፀው የማቴዎስ “ የሰማይ መንግስት “ ወደ “ በህዝቡ ልብ ዉስጥ በሚኖር…. እና የውስጥ ንስሀን እንጂ የዉጪ መታዘዝን የማይፈልግ “ ወደ “ ኢየሱስ መንግስት “ ያመለክታል ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ለህዝቡ ልባቸውን መቀየር መጀመር እንደሚያስፈልጋቸው ተናገረ ፡፡
ማቴዎስ(3፡ 4-6)፡ ዮሐንስ “ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር ፤ ምግቡም አንበጣና የበርሀ ማር ነበር ፡፡” ዘሌዋ(11፡ 22) እነዚህ እንደሚበሉ ተፈቅደው ነበር፡ “ ማንኛውንም አይነት አንበጣ፣ ፌንጣ፣ አንበጣ እና ትልቅ ቀንድ ያለው አረንጎአዴ አንበጣ “ ፡፡ በ 2ነገ( 1፡ 8) የሌለኛዉ የኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክተኛ የነቢዩ ኤልያስ ቀለፃ ነው፡ “ ሰውየው ጠጉራም ነው በወገቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር አሉት “ ፤ ሁለቱም ኤልያስና መጥምቁ ዮሐንስ በህዝቡ ፊት የሚመሳሰል መልክ ይኖራቸዋል ፡፡ ህዝቡ ወደ ዮሐንስ ጎረፈ (ቁጥር 5) ከዚያም “ ኃጢዓታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር “(ቁጥር 6) ፡፡
እንደ መልዕክተኛ መጥምቁ ዮሐንስ ቆይቶ ኢየሱስ በምን እንደሚያናግራቸዉ(እንደሚያገለግላቸው) ያንፀባርቃል ፡፡ ኔልሰን ማብራሪያ የመጥምቁ ዮሐንስን እና የኢየሱስን ንፅፅር ሰጥቶአል፡ 1) ሁለቱም በእግዚአብሄር የተላኩ የእግዚአብሄር ወኪል ነበሩ; 2) ሁለቱም ለማዎጅ መልዕክት ነበራቸው; 3) ሁለቱም ከእስራኤል ጋር ግጭት ይገጥማቸዋል; 4) ሁለቱም በእስራኤል እጅ ተላልፈው የሚሰጡ እና የሚሞቱ ይሆናሉ እና 5) ሁለቱም በመጥፎ እና በሚያሳፍር መንገድ ይሞታሉ ፤ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ለመልዕክተኛው የተፈፀሙ ናቸው ከዚያም ኢየሱስ ላይ ፡፡
የመጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀት ከኢየሱስ ጥምቀት የሚለየው እንዴት ነበር ? ምን እንደሚመጣ ጥላ ነበር ፤ ሙሉ ስዕል አልነበረም ፡፡ በብሉይ ኪዳን እስራኤላዊያን የመንፃት ስርዓት ነበራቸው ስለዚህ በጥምቀጥ እና በብሉይ ኪዳን መካከል ግንኙነት አለ ፡፡ አንድ አይሁዳዊ በእግዚአብሄር ፊት የሚመጣ ከነበር ንፅህ መሆን ነበረበት በመጀመሪያሙ ንፁህ ልብሶችን ይለብሳል ፡፡
ማቴዎስ(3፡ 7-12)፡ ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን ለንሰሀ እየመጣ ከነበረው ህዝብ ጋር ተቀላቀሉ (ቁጥር 7) ፤ ዮሐንስ ለእነርሱ “ እናንተ የእፉኝት ልጆች ከሚመጣው ቁጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ ? አላቸው (ቁጥር 7) ፡፡ በዚህ እና በሚከተሉት ጥቅሶች ቐንቐው ልክ እንደ ኢየሱስ ቃላት በጣም ጠንካራ ነው (ማቴ 12፡ 34) ፤ ዮሐንስ የተናገረው በአነዚህ ኃይማኖት መሪዎች ኑሮ የተካሄደ እዉነተኛ ንስሀ ከነበር በኑሮአቸው ተጨባጭ ፍሬ(የተለወጠ) መኖሩን ማየት ይጀምራሉ ( ቁጥር 8) ፡፡ 1ተሰ (1፡ 9) የእዉነተኛ ንስሀን መልክ ይሰጣል ፡፡ ፈሪሳዉያን እና ሱድቃውያን ንስሀ ገበትው ከነበር በራሳቸው ላይ ያተኮሩ ወይም በኃይማኖታዊ ተግባራቸዉ ያተኮሩ አይሆኑም በእግዚአብሄር ላይ እንጂ ፡፡ ከዚያም ዮሀንስ ፈሪሳዉያንን እና ሰዱቃዉያንን የአብርሀም ዘር በመሆናቸው መደገፍን ማሰብ እንዲያቆሙ ነገራቸው (ቁጥር 9) ፤ በእግዚአብሄር እቅድ የተለየ ስፍራ ለመቀበል በኃይማኖታዊ ዘራቸው ላይ መደገፍ አይችሉም ምክንያቱም ቦታቸዉን የሚቀበሉ ልጆች እግዚአብሄር አስነስቶአል ፡፡ በቁጥር 10 መጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው ፍሬ የማያፈራውን ዛፍ ምሳር ከስሩ ይቆርጠዋል ፤ እንደ መልዕክተኛ መጥምቁ ዮሐንስ አድርጎት የነበረው ጎባጣዉን ማዘጋጀት፣ ጎድጎአዳዉን ለማስተካከል እና ኃያማኖታዊ ቆሻሻን ያስወግዳል ስለዚህ ሁሉም ለኢየሱስ የተዘጋጁይሆናሉ ፡፡
ዮሐንስ ፈሪሳዉያንንና ሰዱቃዉያንን የሚመጣው ማሰሪያውን እንካን ልፈታ የማይገባኝ (ቁጥር 10) እና የሚመጣው በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ያጠምቃል ብሎ ነገራቸው ፡፡ ማክአርቱር የገለፀው እዚህ ጋር ሰዎስት አይነት ጥምቀቶች ተጠቅሰዋል፡ 1) “ ለንስሀ በዉሀ ጥምቀት” - የመጥምቁ ዮሐንስ የንስሀ ጥምቀት; 2) “ የመንፈስ ቁዱስ ጥምቀጥ “ - ሁሉም አማኞች የተቀበሉት እና 3) “ የእሳት ጥምቀት “ - የፍርድ እና የመንፃት መለኪያ (ሐዋ 1፡ 5, 8) ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ኢየሱስ መልዕክተኝ እንደመጣ እንደገና ተመልሶ ለሚመጣው የኢየሱስ መልዕክተኞች ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ ታጥቀናል ፡፡ የምንዘጋጅበት መንገድ በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት የተጠመቅን መሆን ነው ፡፡
ዘሌ (6፡ 13) የሚለው፡ “ ዘወትር በመሰዊያው ላይ እሳት ይነድዳል ፤ አይጠፋም ፡፡” በእግዚአብሄር መገኘት እሳት አይጠፋም ፡፡ በእናንተ ውስጥ ያለው የእግዚአብሄር እሳት በፍፁም አይጠፋም ፤ የእሳት ጥምቀት በእናንተ ውስጥ ያለዉን ገለባ አቃጥሎ ያስወግደዋል በዚህም ምክንያት በሁል ጊዜ ህይወታችሁ መንፈስ ቅዱስን መግለፅ ትችላላችሁ (ቁጥር 12) ፤ ለምን ? ስለዚህ ለመሲሁ መመለስ መልዕክተኛ መሆን ትችላላችሁ ፡፡ የገለባው መቃጠል ሁልጊዜ እኝን ወደ እርሱና ወደሌሎች ያመለክተናል ፤ በኑሮአችን ያለውን ገለባ በውስጣችን ያለው የእግዚአብሄርን እሳት አቃጥሎ ማስወገዱን በፍፁም የማንረዳ ከሆነ በኑሮአችን ጉዳያችንን በፍፁም አንደርሰዉም እንደገናም ኃይማኖተኛ እንደምንሆን አምናለሁ ፡፡ ንስሀ የሚገቡትን ነገር ግን በፍፁም ፍሬ የማያፈሩትን(የማይሸከሙትን) እንሆናለን ፡፡
ማቴዎስ (3፡ 13-17)፡ በቁጥር 13-14 ለጥምቀት ኢየሱስ ወደ መጥምቁ ዮሐንስ መጣ ፤ ዮሐንስ የኢየሱስን ማሰሪያ ለመፍታት እንካን እንደሚገባው አላሰበም ነበር እንዲሆም ኢየሱስን ለማጥመቅ ፤ ኢየሱስ መልሶ “ አሁንስ ፍቀድልኝ ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈፀም ይገባንላን አለው “(ቁጥር 15) ፤ ዮሐንስ ኢየሱስ እንደጠየቀው አደረገ ፤ ኢየሱስ በእዉነቱ በዉሀ ተጠመቀ ፡፡ ሁሉንም ገባ - ሁሉም ረጠበ(ተነከረ) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው በኢየሱስ ጥምቀት የምንመለከታቸው አራት ነገሮች አሉ፡ 1) ሞትንና ትንሳኤን ይስላል; 2) በጥምቀት ኢየሱስን የሚከተሉትን ክርስቲያኖች አስፈላጊነት ያመላክታል; 3) የኢየሱስ የመጀመሪያ በህዝብ መለየት ኃጢዓታቸውን ሊሸከም ከመጣው ጋር በህዝብ ፊት መለየቱን ያሳያል እና 4) ቀጥታ ከሰማይ ምስክርነት በአደባባይ የኢየሱስን መሲህነት አረጋግጦአል ፡፡
መዝጊያ
ዋይርስቤ እግዚአብሄር ሰዎስት ጊዜ እንደተናገረ አመልክቶአል፡ “ በክርስቶስ ጥምቀት ላይ፣ መልኩ በተቀየረ ጊዜ (ማቴ 17፡ 3) እና ኢየሱስ መስቀሉን እንደቀረበ (ዮሐ 12፡ 27-30) ፡፡” ዋይርስቤ በቀድሞው እግዚአብሄር ለልጁ እንደተናገረው ነገር ግን ያ ዛሬ ኢየሱስ በአባቱ ቀኝ እንደተቀመጠ እና እግዚአብሄር በልጁ በኩል እኝና እንደሚናገረን ቀጠለ ፤ ይህ የሚያስደንቅ ስዕል ነው ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር በጠበቀ ትስስር ማግኘት ከፈለጋችሁ ስለ ኃይማኖታዊ ስርዓት መቀጠል አይደለም ፤ በአባቱ አጠገብ በተቀመጠው በልጁ ስለመጣው ነው ፡፡ ሁሉም የጀመረው በመታዘዝ ነው ፤ እግዚአብሄር ወደ እርሱ እንድትመለሱ ጠይቆአችኃል ? ጠይቆናል ከሆነ ያላችሁን አድርጉት ምክንያቱም አብ ለእኛ የሚናገረን በልጁ በኩል ስለሆነ ፡፡
John Walvoord, Matthew: Thy Kingdom Come (Grand Rapids, MI: Kregel, Inc., 1974), p. 29; quoted in Dr. Constable’s Expository (Study) Notes, p. 52; available online at www.soniclight.com.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 1124.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1142-1143.
MacArthur, p. 1125.
Radmacher, et al, p. 1145.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Nashville: Thomas Nelson, 1989), p. 17.
Wiersbe, p. 17.
ጥያቄዎች
-
በዮሐንስ ጥምቀት እና በኢየሱስ ጥምቀት መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው ? (ማቴ 3፡ 2, 11)
-
በማቴዎስ (3፡ 7-10) ዮሐንስ ለፈሪሳዉያን እና ለሰዱቃዉያን ምንድን እዉነት ገለጠላቸው ? በቁጥር “ ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሳለት እግዚአብሄር ይችላል “ ምን ማለት ነው ?
-
መጥምቁ ዮሐንስ በምን መንገድ “ለጌታ መንገዱን አዘጋጀ “ ? እግዚአብሄር እንድታውቁት ለእናንተ መንገድ ለማዘጋጀት ሰዎችን/ነገሮችን በምንድን መንገድ ተጠቀመ ? ሌሎች ክርስቶስን እንዲቀበሉ ለማዘጋጀት በእግዚአብሄር እንዴት አድርጋችሁ ትጠቀማላችሁ ?
-
በማቴዎስ (3፡ 12) “ የማዝሪያዉ/መለያዉ ወንፊት “ ወይም “ የማዝሪያው መንሽ “ ምንድን ነው ?
-
ማቴዎስ (3፡ 17) ለልጁ ስለ እግዚአብሄርን ፍቅር ምንድን ይገልፃል ? የእግዚአብሄር ልጆች ከሆናችሁ እግዚአብሄር እንደሚወዳችሁ እና እግዚአብሄር በእናንተ ደስ እንዳለው በእዉነት ታምናላችሁ ? (መዝ 86፡ 15; 149፡ 4; 1ዮሐ 3፡ 1)
-
በማቴዎስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 3:11-12
“I baptize you with water for repentance, but the One who is coming after me is more powerful than I. I am not worthy to remove His sandals. He Himself will baptize you with the Holy Spirit and fire. His winnowing shovel is in His hand, and He will clear His threshing floor and gather His wheat into the barn. But the chaff He will burn up with fire that never goes out.”
ከክርስቶስ በፊት የተላከው መልእክተኛው መጥምቁ ዮሐንስ በንሰሐ እና በሚመጣው የሰማይ መንግስት ላይ ያተኮረ መልዕክት ሰብኳል፡፡ ተከታዮቹን በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ስለሚያጠምቃቸው ፥ሊመጣ ስላለው ስለኢየሱስ ተንብዮአል፡፡ ንሰሐ ብዙውን ጊዜ የሰዎችን ህይወት ወደ ውጫዊ ለውጥ ይመራል፥ ነገር ግን ኢየሱስ እውነተኛ የሆነ ውስጣዊ ለውጥ ያመጣል፡፡
የክርስቶስ ተከታይ ስትሆኑ እና ንሰሐ ስትገቡ፥ እሳትን እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ትቀበላላችሁ፡፡ እሳት ገለባውን ያቃጥላል፡፡ ገለባ በህይወታቸሁ ውስጥ እንደ ራስ ወዳድነት፣ ትዕቢት፣ ሌሎች አማልክትን ወይም ጣዖታትን ማምለክ ወይም ቁጣን የመሳሰሉ ክርስቶስን የማያንፀባርቁ ቦታዎችን ይወክላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን ብርሀን የበለጠ እንድታንፀባርቁ ፥እናንተን በማጥራት ፥እነዚህን ቦታዎች በማያቋርጥ እሳት ከህይወታችሁ በማቃጠል፥ በውስጣችሁ ይሰራል፡፡ እግዚአብሔር አብ በሚወደው ልጁ ደስ እንደሚለው ሁሉ ኢየሱስ በእናንተ ደስ ይሰኛል ደግሞም ይወዳችኋል፡፡ እርሱን ስትፈልጉት እና ከእርሱ ጋር በቅርበት ስትሄዱ ይወዳል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በህይወታችሁእንዲሰራ ዛሬ ፍቀዱለት፡፡ እናንተም ደማቅ የብርሃን ፀዳል እና ለክርስቶስ ምጽዓት ቀዳሚ መልዕክተኛ እንድትሆኑ ኃይሉ በእናንተ ይስራ፡፡
“እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለው፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤ መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል፡፡”
— የማቴዎስ ወንጌል 3:11-12
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ትንቢተ ሕዝቄል 36:26 — “ አዲስም ልብ እሰጣኋለው አዲስም መንፈስ በውስጣቸሁ አኖራለው፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለው፡፡ ”
- የማቴዎስ ወንጌል 3:17 — “ እነሆም፥ ድምጽ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡’”
- የሐዋሪያት ስራ 1:5 — “ ዮሐንስ በውሀ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 3
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።