Satan's Temptations
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለሪቫይቭ ተ/ቤት አድስ ከሆኑ እንካን ወደ ማቴዎስ ጥናትችን በደህና መጡ ፡፡ ሁልጊዜ አንድ ስዕል እና አንድ ቃል ወይም ሀረግ በእያንዳንዱ የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ውስጥ ወደ ኢየሱስ የሚያመለክት አለን ፡፡ ለማቴዎስ ቃላችን ንጉስ ነው ፡፡ በዚህ መጸሀፍ እስካሁን ያጠናነውን ታሪክ ዛሬ ስንማር ማየት እንችላለን፡ የኢየሱስን ቤተሰብ ግንድ፣ የኢየሱስን መወለድ እና ከምስራቅ ኮኮቡን የተከተሉትን ጥበበኞች፣ መጥምቁ ዮሐንስ ለኢየሱስ መንገድ አዘጋጀ ከዚያም ኢየሱስ ህዝቡን በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት እንደሚያጠምቅ ተናገረ እና ኢየሱስ በዉሀ ተጠመቀ ይህ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ተፈፀመ ፡፡ ምናልባት ዛሬ ወደ ሁሉንም ጥቅስ አንሸፍንም እናም ምናልባት ለአሁን ትረዱታላችሁ በዚያም ደስተኛ ነኝ ፤ በራሳችሁ ስታጠኑ ሁሉንም ቀን አንብቡ፣ ንባብ አጋዥ አላችሁ፣ ትንሽ የዉይይት ቡድን፣ የላውራ የዕለት ቃል መሰጠት እና በእኔ ትምህርት ያልተሸፈነውን የሚሞላ መንፈስ ቅዱስ አላችሁ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ (4፡ 1)፡ በቁጥር 1 ኢየሱስ “ በሰይጣን ሊፈተን ” ወደ ምድረበዳ ተወሰደ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር በማትሄዱበት መንገድ ይወስዳችሁ እና ያስቀምጣችኃል ፤ ምናልባት ዮሴፍ ወደ ግብፅ መሄድ መሄድ አይፈልግም ነገር ግን የእግዚአብሄርን ቃል እና ትንቢቱን ለማስፈጸም ወደዚያ መሄድ እንደሚያስፈልገው ያውቃል ፡፡ እምነታችንን በእግዚአብሄር ላይ ካስቀመጥን በውስጣችን መንፈስ ቅዱስ አለ በብዙም ሊመራን ይቻለዋል (ሮሜ 8፡ 14) ፡፡ ኢየሱስ በሰይጣን ለመፈተን በመንፈስ ተመራ በእግዚአብሄር አይደለም (ቁጥር 1) ፤ ክፉው ሁሉም ፈተና ያደርጋል (ያዕ 1፡ 13) ፡፡ ፈተና ሁሉም ቦታ አለ - ሰይጣን በግልፅ በር ላይ የደፈጠ ነው ፤ ትግሉ ለፈተናዎቹ እጅ አለመስጠት ነው (ዕብ 4፡ 15-16) ፡፡ ከእኛ ጋር ለመገናኘት እየፈተነ የሄደበት እንዱ መንገድ ይህ ነበር ፤ “ ኢየሱስ ለዚህ ፈተና እጄን መስጠት አልፈልግም “ በምንል ጊዜ “ እሺ ፤ እዚህ እሆናለሁ በአንዱም አልሰጣችሁም “ ማለት ይችላል ፡፡
አዳም ሰይጣንን በሚያምር መናፈሻ(ጥብቅ) አገኘው ኢየሱስ ሰይጣንን በበርሀ ምድረበዳ አገኘው ፤ አዳም ሁሉም ነገር በገነት ነበረው ፤ ኢየሱስ በምድረበዳ ምንም አልነበረው ፡፡ አዳም ተሸነፈ ፤ ኢየሱስ አሸነፈ ፡፡ አዳም የሄደበትን ኢየሱስ ዋጀው (ዮሐ 12፡ 31) ፡፡ ለፈተና እጁን ባለመስጠቱ ምክንያት በማሸነፉ ኢየሱስ የዚህን አለም ገዢ ይጥለዋል፤ በዚህም ቆላ (2፡ 15) የታሪኩ መጨረሻ እንደሆነ ታውቃላችሁ ፡፡ ኢየሱስ አሸነፈ !
ኢየሱስ በሄደባቸው በሰዎስቱ ፈተናዎች ስንሄድ ልንረዳው በጣም የሚስፈላገው ነገር ኢየሱስ ለምንም ነገር እጁን እንዳልሰጠ ነው ፡፡ እንዴት አልሰጠም ?ዋይርስቤ ኢየሱስ ዉጊያውን የተዋጋው እንደ አንድ ሰው በመንፈስ እና በእግዚአብሄር ቃል ላይ በመደገፍ እንደሆነ አብራርቶአል ፤ ኢየሱስ የየቀኑአን ዉጊያ በመንፈስ ቅዱስ እን በእግዚአብሄር ቃል እርዳታ ተዋጋ ፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ምን እንደተፈጠረ የማስበው ስለ መንፈስ ቅዱስ ለማውራት እናመነታለን ስለ እግዚአብሄር ቃል ብቻ ማውራት እንደምንፈልግ ነው ፤ ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ የሆነ ነገር በእግዚአብሄር ቃል እያሳየን እንደሆነ አናውቅም ፤ ያ ማለት ይህ ሁሉ እዉቀት አለን ነገር ግን የሆነ ነገር ለማድረግ በዚህ ካልተመራን ወደ ፈተና በመስጠት የሚመራን ይሆናል ፡፡ ለዚያ ነው እነዚህ ታላቅ ወንዶችና ሴቶች በእግዚአብሄር ቃል ያሉ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ ያልተመሩ ለፈተና የሚሰጡ ያሉን ፡፡ ኢየሱስ ምሳሌዉን አሳይቶናል ፡፡ ፈተናን እንዴት እንዋጋዋለን ? በእግዚአብሄር መንፈስ እና በእግዚአብሄር ቃል ፡፡
ማቴዎስ (4፡ 2)፡ ቁጥር 2 የሚጀምረው “ 40 ቀንና 40 ለሊትም ከፆመ ቦኃላ “ ፤ ምንም ሳይመገብ ለ 40 ቀንና ሌሊት በምድረበዳ ነበር ፡፡ ከዚህ ጊዜ ቦኃላ ኢየሱስ ተርቦ ነበር ፤ ለምን ? ምክንያቱም ኢየሱስ ሰው ነበር ፡፡ አርባ ቀን እና 40 አመታት በብሉይ ኪዳን ዉስጥ ትርጉም የያዙ ናቸው ፤ ይህ አይሁዶች የተረዱት መነሻ ነው (ዘፍ 7፡ 4; ዘኁ 14፡ 33; 32፡ 13; ዘዳ 9፡ 25; ዮና 3፡ 4) ፡፡
ማቴዎስ(4፡ 3-4)፡ ቁጥር 2 ካነበብን ቦኃላ ቁጥር 3 እንደሚሆን እንጠብቃለን ምክንያቱም እንደተራበ ይናገራል፡ “ፈታኝም ቀርቦ የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንህ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው ፡፡” የመጀመሪያዉ ፈተና አካላዊ ፍላጎት ነበር ምክንያቱም በ40 ቀናት በልቶ ስላልነበር ፤ ኢየሱስ ዘዳ(8፡ 3) በመጥቀስ በመንፈስ ቅዱስ እና በእግዚአብሄር ቃል ፈተናውን ተዋጋው ፡፡ አካላዊ ፍላጎት በዘፍጥረት መጀመሪያ ያስቸገረ(የታገለ) ነበር (ዘፍ 3፡ 1; 1ዮሐ 2፡ 16) ፡፡ ኢየሱስ ጊዜያዊ የነበረን ነገር ለመስራት በአይን ፍላጎት ተፈትኖ ነበር ፤ ዋረን ዋይርስቤ የተናገረው “ የእግዚአብሄርን ቃል መመገብ እና መታዘዝ አካላዊ ምግብ ከመውሰድ ይልቅ በጣም አስፈላጊ ነው ፤ በእርግጥ ምግባችን ነው ፡፡ “ ለአካላዊ ፍላጎታችን ፈተና እንዲሆን መፍቀድ አንችልም ፡፡
ማቴዎስ (4፡ 5-7)፡ ሁለተኛው ፈተና የግል ጥቅም ነበር ፡፡ ሰይጣን ኢየሱስን ከመቅደሱ ወደ ደቡብ ምስራቅ ጫፍ 450 ጫማ ከኪድሮን ሸለቆ በላይ ወሰደው ፡፡ በሚል (3፡ 1) መሰረት አይሁዶች መሲሁ ከመቅደሱ ተራራ መሲሁ እንደሚመጣ ይጠብቃሉ ፡፡ በቁጥር 6 በዚህ ጊዜ በመዝ (91፡ 11-12) ያለውን የእግዚአብሄርን ቃል ሰይጣን በማጣመም ጠቀሰ ፤ ኢየሱስም “ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአልና አለው “ (ቁጥር 7) ፡፡
ሰይጣን ራሱን ወደታች ከወረወረ ለኢየሱስ ሁሉንም ነገር እንደሚሰጠው ቃል ገባለት ፡፡ ሁሉንም ነገር ሰይጣንን ለመቃዎም ኢየሱስ የተጠቀመበት ከብሉይ ኪዳን የመጣ ነው (አዲስ ኪዳን ተፅፎ ስላልነበር ) ፤ ኢየሱስ ፈተናዉን ለመቃወም ብሉይ ኪዳንን እንደተጠቀመ እኛም እንችላለን (ዘፍ 3፡ 4; ማቴ 4፡ 7) ፡፡ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ኢየሱስን በስጋ ፍላጎት ፈተነው (1ዮሐ 2፡ 16) ፡፡
ለአለም የሆነው ሁሉም ነገር የስጋ ፍላጎት አካል ነው ፡፡
ማቴዎስ (4፡ 8-10)፡ ሰዎስተኝዉ ፈተና ስልጣን ነበር ፤ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ኢየሱስን ወደ ታላቅ ተራራ ምናልባትም ወደ ኢያሪኮ በመውሰድ አለምን አሳየው (ቁጥር 8) ፤ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ከኢየሱስ ሙሉ ስግደትን ነበር የፈለገው ምክንያቱም አምላክ መሆን ስለፈለገ (ኢሳ 14፡ 12) ፡፡ ሰይጣን እንድታልኩት ለማድረግ የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል ፤ አንድ ሰዎስተኛ መልአክት ሰይጣንን እንደሚከተለ አስታዉሱ ፡፡ እንደ ዳብይሎስ በመንፈሳዊ ዉጊያ እነዚህን መለዓክት እናገኛቸዋለን ፤ አሁን ሰይጣን የአየሩ መሪ ነው ፡፡ አሁን ሰይጣን ነፃ ስልጣን አለው ከእኛም ቦኃላ ይመጣል ነገር ግን ዮሐ(12፡ 31) የሚለው፡ “ አሁን የዚህ አለም ፍርድ ደርሶአል ፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዥወደ ዉጭ ይጣላል ፡፡” የዚህ እድሜ አምላክ(ትንሽ አምላክ) እንደሆነ ተመለከተው (1ቆሮ 4፡ 4) ፤ በመሆኑም አሁን ሰይጣን ይህ ስልጣን አለው በመጨረሻም ኢየሱስ አሸናፊ ይሆናል (ዘፍ 3፡ 5; ማቴ 4፡ 10; 16፡ 21-23; 1ጴጥ 1፡ 11; 1ዮሐ 2፡ 16)፡፡
ማቴዎስ (4፡ 11-13)፡ ክፉዉ በተወዉ ጊዜ መለዓክቶች ኢየሱስን ሊያገለግሉት መጡ ፤ በመንፈስቅዱስ እን በእግዚአብሄር ቃል ኃይል አገልግሎቱን ተከላለከ ከዚያም በአገልግሎቱ መጎአዝ ጀመረ ፡፡ ኢየሱስ በዛብሎን እና በንፍታሌም ክልል ከናዝሬት ወደ ቅፍርናሆ ሄደ በዛብሎንና በንፍታሌም ትንቢታዊ ቃል ውስጥ መጎአዝ ጀመረ ፡፡ ኢየሱስ ለእኛ የፈተናን ዘር ለመወጣት ጀመረ ፡፡
ማቴዎስ (4፡ 23-25)፡ በእነዚህ ፈተናዎች ላይ ድል ስላደረገ ኢየሱስ ያስተምርና ይሰብክ እና “ በህዝቡም መሀከል ሁሉንም ደዌ እን በሽታ ይፈውስ ነበር ፡፡ “ በዚያ ታላቅ ደስታ ምክንያት ዜናው በመለዉ ሶሪያ መሰራጨት ጀመረ (ቁጥር 24) ፤ አነዚህን ፈተንዎች ኢየሱስ በመቐቐሙ ምክንያት ለአገልግሎት በሩ ፈነዳ(ተከፈተ) - ሁሉም ሰው ወደ ኢየሱስ መጉረፍ ጀመረ (ቁጥር 25) ፡፡
መዝጊያ
ኢየሱስ ይህን ጊዜ በምድረበዳ እና እነዚህን ፈተናዎች ለአገልግሎቱ ለመዘጋጀት እንደተጠቀመባቸው አምናለሁ ፡፡ ፀሎቴ በማቴዎስ 4 ለመኖር ምን እንደሚያስፈልጋችሁ እግዚአብሄር እንዲያሳያችሁ ነው ፡፡
William W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 18.
ጥያቄዎች
-
መንፈስ ወደ ምድረበዳ በሰይጣን እንዲፈተን ለምን እንደመራዉ ምን ታስባላቹሁ (ማቴ 4፡ 1) ? ሰይጣን ኢየሱስን የፈተነበት በምን መንገድ ነበር ? (ማቴ 4፡ 2-10)
-
ኢየሱስ በሚፈተን ጊዜ ሰይጣንን ለመዋጋት ምንድን ዘዴ ተጠቀመ ? ይህ እንዴት ያነሳሳችኋልስ እንዴትስ ወደ ህይወታችሁ መተግበር ትችላላችሁ ? እንዴት ፈተናን ትዋጉታላችሁ ? (1ቆሮ 10፡ 13; ገላ 5፡ 16; ዕብ 2፡ 18; ያዕ 1፡ 13-18)
-
በማቴዎስ 4 በኢየሱስ አገልግሎት ኢሳ (9፡ 1-2) እንዴት ነበር የተፈፀመው ?
-
የኢየሱስ የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ በቀረባቸዉ ጊዜ ምን እያደረጉ ነበር (ማቴ 4፡ 18-12) ኢየሱስስ እንዴት አገኛቸው ? ስለ ኢየሱስ ለማዉራት እንዴት ሰዎችን ትቀርባላችሁ ? የመጀመሪያዎቹነረ ደቀመዛሙርት “ከጠራበት” ምሳሌ ከኢየሱስ ምን ልትማሩ ትችላላችሁ ?
-
በተግባር ስለ ኢየሱስ ዜናው እንዴት ተሰራጨ (ማቴ 4፡ 24-25) ? ሰዎች ጓደኞቻቸውን/የቤተሰብ አባሎችን ለፈዉሱ ወደ ኢየሱስ በሚያመጡቸው ጊዜ ስለ ሚያሰላስሉት እምነት እና ምልከታ ዉይይቱ ይመስል እንደ ነበር ምንድን ታስባላችሁ ?
-
በማቴዎስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 4:20
“Immediately they left their nets and followed Him.”
ኢየሱስ የመጀመሪያዎቹን ደቀመዛሙርት እንዲከተሉት በጠራ ጊዜ አራቱም ሰዎች፥ ስምኦን፣ እንድሪያስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ፥ እርሱን ለመከተል ወዲያውኑ መረባቸውን፣ ጀልባዎቻቸውንና አባቶቻቸውን ተው፡፡ ወዲያውኑ ማለት በአንድ አፍታ፣ ሳይዘገይ፣ በቅጽበት ማለት ነው፡፡ ደቀመዛሙርቱ ሳይዘገዩ ምላሽ ሰጡ፥ ወዲያውኑም ኢየሱስ የመንግስቱን ምስራች ሲሰብክ እንዲሁም የሰዎችን በሽታ እና ደዌ ሲፈውስ አዩ፡፡
በፍጥነት እየሄደ ባለ የዛሬው ባህል፥ በህይወት ወስጥ ያሉ ብዙ ነገሮች በቅጽበት በእጃችሁ ናቸው፡፡ ሰዎች ምንም ነገር መጠበቅ አይወዱም ስለዚህም ቴክኖሎጂ ለዚህ የፈጣን እርካታ አኗኗር ፈቃድ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ ይሁን እንጂ ኢየሱስን ስለመከተል እና በተዛዥነት ወደ መኖር ሲመጣ፥ ወዲያውኑ ምላሽ ትሰጣላችሁ? በእውነት ከእግዚያብሄር ስለመስማታችሁ ተጠራጥራችሁ ቀጣዩን እርምጃ ላትወስዱ ትችላላችሁ፡፡ ዛሬ፥ ወዲያው በሆነ ታዛዥነት ተመላለሱ እና የጌታን ታማኝ እጅ በህይወታችሁ ተመልከቱ! ስራ ተው፥ ትኩረታችሁን ከሚሰርቅ ነገር ራቁ፥ ከሀጢያት ንሰሀ ግቡ፥ ይቅርታ ጠይቁ፥ በሚስዮን ጉዞ ሂዱ ወይም ደግሞ እግዚሃብሔር በልባችሁ ያስቀመጠውን ስጦታ ስጡ፡፡ ምናልባት ለኢየሱስ እሺ ሳትሉ ለእናንት ያለውን ፍቅር በእምነት አልተቀበላችሁም ይሆናል፡፡ ከመጠን በላይ መመራመር አቁሙ እና ክርስቶስን ተከተሉ! ዛሬ ለኢየሱስ ወዲያውኑ አዎን የሚባልበት ቀን ነው!
“ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡.”
— የማቴዎስ ወንጌል 4:20
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የማቴዎስ ወንጌል 21:2-3 — “ እንዲህም አላቸው፦ በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያም ውርንጫም ከእርሷጋር ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ ወዲያውም ይሰዳቸዋል፡፡’”
- 2ኛ ዮሐንስ 1:6 — “እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርሷ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት፡፡.”
- የዮሐንስ ራእይ 14:12 — “የእግዚያብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚፀኑት ቅዱሳን ትዕግስታቸው በዚህ ነው፡፡.”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 4
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።