The Gospels Matthew

Fulfillment of the Law

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 115 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በማቴዎስ 4 በፈተናዎቹ ንግግር (ውይይት) በማድረግ እንዴት ኢየሱስ ለአገልግሎቱ እየተዘጋጀ እንደነበር በተለያየ መልኩ ተመልክተናል ፡፡ ኢየሱስ ከፈተናዎቹ ጋር ካወሳ ቦኃላ አገልግሎቱ እየጠፋና ዕየሮጠ ነበር ፡፡ ማቴዎስ 4 መጨረሻ ላይ ኢየሱስ እያስተማረ፣ እየሰበከ እን እየፈወሰ ነበር ህዝቡም ወደ እርሱ እየጎረፈ ነበር ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ (5፡ 1)፡ ይህ የተራራው ስብከት መጀመሪያ ነው በማቴዎስ (5-7) የሚገኝ ነው ፡፡ ኢየሱስ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈፅም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ (ቁጥር 17) ፡፡ “ ለመሻር “ የሚለው ቃል እዚህ ቁጥር ሁለት ጊዜ እንደተጠቀመው አስታዉሉ ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር አላጠፋም ፤ በኢየሱስ ፈፀመው ፡፡ በዚህ ዉይይት ስለ ህጉና ስለ ነብያት አይሁዶች የሙሴያዊ ትምህርቶች ወይም የኤርሚያስ ወይም የመዝሙረኛውን እንካን ለስልጣን ከፍ ያደረጉትን ማንኛዉንም የቃል ልምድ አልጠቀምም ፡፡

ማቴዎስ(5፡ 17)፡ ህጉን በተመለከተ የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው “ ከእስራኤል ጋር እንደ ኪዳን ስርዓት የመቅደሱ መጋረጃ በተቀደደ ጊዜ መስቀሉ ላይ አበቃ አድስ የክህናት ቤተሰብ ተመሰረተ ፤ የመንፈሰዊ እና የስነ ምግብር መርህ ተቀመጠ ዘላለማዊም ነው ፡፡” በጊዜያዊነት እና በዘላለማዊነት ህጉን መመልከት እፈልጋለሁ እንዴትስ ኢየሱስ ወደ ዚህ ተስማማ ፡፡ ህጉ አሁንም ተግባራዊ ነው (ገላ 3፡ 19; ኤፌ 2፡ 15; 1ጢሞ 1፡ 9; ዕብ 7፡ 12) ፤ የህጉ ትክክለኝ ስነ ምግባር አልተወገደም ፤ ስለዚህ የህጉ አካል ጊዜያዊ ነበር ፤ በተመሳሳይ ጊዜም የህጉ አካል ዘላለማዊ ነው ፡፡ ኢየሱስ ህጉን ለማጥፋት የሚመጣ ከነበር ስለ ህጉ ዘላለማዊ የሚሆን ምንም ነገር አይኖርም ፡፡

ማቴዎስ (5፡ 18)፡ በህጉ እስካሁን ያልተፈፀሙ የተወሰኑ ነገሮች አሉ (ሮሜ 3፡ 31; 8፡ 4) ፡፡ ኢየሱስ ህጉን ሊያጠፋ አልመጣም ጊዜያዊ አካሉን ለማስወገድ እንጂ ፡፡ ሉቃ( 24፡ 25-27) ስለ ኤማሆስ መንገድ ነው ፤ ከትንሳኤ ቦኃላ ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር የኢየሱስን ቃለ ምልልሰ ነው ፡፡ ኢየሱስ ሁሉንም ህጎች እና ነብያቶችን ወሰደ እነዚህ ሁሉ ስለ እርሱ እንደነበር ደቀመዝሙሩን ነገራቸው ፡፡ በአዲስ ኪዳን ፀሀፊው ህጉን እና ነብያትን በመደጋገም ይጠቅሳል (ማቴ 7፡ 12; 11፡ 13; ሉቃ 24፡ 44; ሐዋ 13፡ 15) ፡፡

“ መፈፀም” የሚለው ቃል በቀላሉ “ መተለቅ፣ መድረስ ወይም መማላት “ ማለት ነው ፤ ወደ መጨረሻ ማምጣት ማለት አይደለም ፡፡ ክርስቶስ እንዴት ብሉይ ኪዳንን ፈፀመ ? በኔልሰን ማብራሪያ መሰረት ኢየሱስ ብሉይ ኪዳንን በዚህ መንገድ ፈፀመ ፤ መጀመሪያ “ በትክክል አከበረው ትርጉሙንም በትክክል አስተማረ “ ፤ ያ ማለት ኢየሱስ አከበረውም ሄደበትም(ኖረበትም) (ማቴ 3፡ 17; 17፡ 5; ገላ 4፡ 4) ፡፡ ኢየሱስ ህጉ ያለውን በትክክል እያስተማረ ካልነበር እግዚአብሄር በፍፁም ይህን አይልም ፡፡

ሁለተኛ “ ሁሉንም የብሉይ ኪዳን ፅሁፎችን እና ትንቢቶች አንድ ቀን ይፈፅማቸዋል ፡፡” ትናትና አንድ ቀን መሲሁ ወደ መቅደሱ ተመልሶ እንደሚመጣ አይሁዶች ስለያዙት እምነት አውረተናል ፤ ያ እስካሁን አልሆነም ፤ ያ ማለት ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን መፈፀም እየሰራ ነው ፡፡ እስካሁን ያልተካሄደ ትንቢት እየፈፀመ ነው (ገላ 3፡ 13; ዕብ 9፡ 23; 10፡ 8) ፡፡ ይህ ኢየሱስ የህጉን እርግምን እንደተሸከመና ሁለተኝ እንደመሰረተ ያሳያል ፤ የእዚህ ጥቂት የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ተፈፅመዋል ….. መቅደሱ አይኖርም ኢየሱስ መቅደስ ነው ፡፡ ሌላ ትንቢታዊ ቃሎች ወደ ፍሬ እስካሁን ያልመጡ አሉ ፤ ለምሳሌ ኢየሱስ በተመለሰ ጊዜ የዘይት ተራራ(ምናልባት የአረሞኒየም ተራራ) በሁለት ይከፍለዋል ፤ በግልፅ እስካሁን አልሆነም ፡፡

ሰዎስተኛ “ የብሉይ ኪዳንን መስፈርትና ፍላጎት የሚያማላ የድነት መንገድ ሰጠ “ (ሮሜ 3፡ 20-21) ፤ ከእኛ የተፈለገ በስራ መድረስ የምንችለው ፤ ማንም በስራ የሚነፃ አይሆንም ፡፡ በበቂ ፀሎት ወይም በበቂ መፅሀፍትን በማንበብ ወይም እንድናደርግቸው እግዚአብሄርየጠራንን ሁሉንም ማድረግ አንድ እርምጃ ሊያስቀጥለን አይችልም ፤ ነገር ግን በክርስቶስ ፅድቅን መፈለግ እንችላለን ፡፡ ያ አካል በክርስቶስ ድነታችን የተፈጸመ ነው ፤ ነገር ግን ሌሎች ትንቢቶች በብሉይ ኪዳን እስካሁን አልተፈፀሙም ፡፡

ዋይርስቤ ብዙዎች ብሉይ ኪዳን ከእንግዲህ አያስፈልግም ብለው ለሚያስቡት እና በመዶሻ ሊያስወግዱት እንደሚወረዉሩት ለመግለፅ የአክሮን ቲዎሪ ይጠቀማል ፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር አክሮንን የመረጠው ለማጥፋት አይደለም ነገር ግን “ በመሬት ላይ በመትከል በራሱ በመፈፀም ትልቅ ዝፍ እንዲሆን ይፈቅዳል ፡፡” በትንቢታዊ ንግግር የእስራኤል በረሀ በመጨረሻ ጥብቅ ይሆናል (ኢሳ 35፡ 1) ፤ የእስራኤል ምድር ብዛት ስልሳ ፐርሰንቱ ምድረበዳ ነው ፤ አንድ ቀን ጋርደን ይሆናል ፡፡ ይህን ምድር ካጠፋን ኢሳያስ የሰጠውን ትንቢታዊ ቃል እናጠፋለን ፤ ኢየሱስ የተናገረው ሙሉ ሂደቱን ለመፀም እንደመጣነው ፡፡

ጥቂቶች የያዙት አራት የቀለም(የትምህርት) ሀሳቦች(አመለካከቶች) እነዚህ ናቸው፡

  • አንዱ አመለካከት “ ኢየሱስ የመጣው የስርዕት ህጉን(አስሩን ትዕዛዝ) ለመፈፀም (ለመጠበቅ) ነገር ግን የእስራኤልን ሲቪል እና የወንጀለኛ ህግን አጥፍቶአል “ ነው ፡፡
  • ሌላው አመለካከት “ ኢየሱስ የመጣው ትርጉሙን ለመፈፀም፣ ግልፅ ያልሆኑትን ሙሉ አስፈላጊነታቸውን ለማስፋት “ ነው ፡፡
  • ሰዎስተኛው አመለካከት ኢየሱስ የመጣው የብሉይ ከዳን ህጉን አስፈላጊነት ወደ አድስ ርዝመት ለማስረዘም ነው ፡፡
  • ምናልባት “ ኢየሱስ ሙሉ ብሉይ ኪዳንን ለመመሰረት የስልጣኑን ማረጋገጫ በህጉ ላይ ለመጨመር እንደመጣ ተመለከተ “ ፤ ይህ እዚህ እያረጋገጥን ያለውን የሚመስል ይሆናለል ፡፡

ይህ ፅሁፍ እንዴት መተርጎም እንደሚቻል እነዚህ የተለያዩ እይታዎች ናቸው (ኤፌ 2፡ 11-13; ዕብ 10፡ 19) ፡፡ ወደ እግዚአብሄር የሚወስደው መንገድ በኢየሱስ በኩል ተከፍቶልናል ፤ ብሉይ ኪዳንን ለመፈፀም ኢየሱስ ለእኛ ወደ እግዚአብሄር መንገዱን ከፍቶልናል ፤ በጠጨማሪም አይሁዶችንና አህዛብን የለየውን ግድግዳ አፍርሶታል ስለዚህ ህጉን የመፈፀም አካል እና ትንቢቶቹ እነዚህ መሰናክሎች በእዉነቱ ይሰበራሉ ፡፡ ከግድግዳው አልፈን እንድንመጣ ፈቅዶልናል (ኤፌ 2፡ 11-13) በእጅም የተሰራ መቅደስ የለም ፡፡ ሐዋ( 7፡ 48) የሚለው “ ነገር ግን ነብዩ እንዳለ ልዑል የሰው እጅ በሰራችው አይኖርም ፡፡”

መዝጊያ

ህጉን እና ነብያቱን ለመፈፀም ኢየሱስ ብዙ ነገር አደረገ ፤ እስካሁን ያጠፋቸው ነገሮች አሉ ፤ ወደታች ግድግዳዎችን ቀደደ፣ መጋረጃውን ወደ ታች ቀደደ፣ በሰዎች እጅ የተሰራውን መቅደስ አፈረሰ - ከህንፃዎች አራቀ ፤ ነገር ግን ህጉንና ነብያቱን አልቀደደም ምክንያቱም እነዚያ ነገሮች ወደ ክርስቶስ ክስተት ስላመለከቱ ፡፡ በግል እንዴት ህጉን እንፈፅመዋለን ? ሁለት መንገዶች ፤ ኢየሱስን በመወከል እን በመምሰል፡ እንደ መንፈስ በመጎአዝ (ሮሜ 8፡ 1-4) እና ሌሎችን በመውደድ (ሮሜ 13፡ 10) ፡፡

ህጉ ጊዜጣዊ እን ዘላለማው ነው ፡፡ ኢየሱስ በትክክል ህጉን አክብሮአል በዘፍጥረት እን በሚልክያስ መካከል የተጻፈውን ሁሉንም ነገር ይፈፅማል ፤ ምክንያቱም የድነትን መንገድ ስለሰጠን፣ በእግዚአብሄር እና በእኝ መሀከል ያለውን መሰንክሎች ሰባብሮአል እናም መጋረጃውን ቀድድአል ፡፡ ይህ ግንኙነት በመንፈስ እንድንሄድ እና ሌሎችን እንድንወድ በተጨማሪም ማቴ (5፡ 17) መያዝ እንድንጀምር ይፈቅድልናል ፡፡

  1. 1 Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1148.

  2. 2 Radmacher, Allen, and House, p. 1148.

  3. Radmacher, Allen, and House, p. 1148.

  4. Radmacher, Allen, and House, p. 1148.

  5. William W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 22.

  6. Craig L. Blomberg, Matthew, pp. 103-105; quoted in Dr. Constable’s Expository (Study) Notes, p. 103, available online at http://www.soniclight.com/constable/notes.htm.

  7. Richard C. Lenski, pp. 205-207; quoted in in Dr. Constable’s Expository (Study) Notes, p. 103, available online at http://www.soniclight.com/constable/notes.htm.

  8. Wolfgang Trilling, Das wahre Israel: Studien zur Theologie des Matthaus-Evangeliums, pp. 174-179.

  9. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes, p. 104, available online at http://www.soniclight.com/constable/notes.htm.

ጥያቄዎች

  1. ማቴዎስ (5፡ 1-12) በብዛት ስለ ብፁዕነት የሚገልፅ ነው ፤ “ ብፁዕ “ ማለት ምንድን ነው ? ከማቴዎስ 5 እግዚአብሄር አማኞቹን ለመባረክ ፍቃደኛ ነው የተለያዩ መንገዶቹን ጥቀሱ ፤ እነዚህ በረከቶች ለእናንተ ይተገበራሉ ? እንዴት ?
  2. ሰዎች ሲነቅፉዓችሁ ወይም ስለ እርሱ ሲዋሹዓችሁ ለምን እግዚአብሄር እንደ ሚባርካችሁ ምን ታስባላችሁ (ማቴ 5፡ 11-12) ? መፅሀፍት ስለዚህ እንድንደሰት ወይም ደስተኛ እንድንሆን ለምን ተናገረ ? (1ጴጥ 4፡ 13-14)
  3. በማቴዎስ (5፡ 14) ደቀ መዛሙርቱን ኢየሱስ “ የአለም ብርሀን ናችሁ “ ብሎ ነገራችው ፤ ይሁን እንጂ በዮሐንስ (8፡ 12) ኢየሱስ የአለም ብርሃን እንደሆነ ተናግሮአል ፡፡ ይህ የሚጣረስ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? ለምን ታሳባላችሁ ወይስ ለምንስ አላሳባችሁም ? በእነዚህ በሁለቱ ፅሁፎች ለእኛ ኢየሱስ ምንድን ነዉ ያለው ? ( ማቴ 5፡ 14-16; ዮሐ 9፡ 5; ፊል 2፡ 15)
  4. ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን ህግ ሁል ጊዜ ይሰሙት ከነበረው አንድ እርምጃ ተጨማሪ ለምን ወስዶት እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ (ማለትም, ማመንዘር/ መመኘት, መግደል ) (ምሳ 6፡ 25; ማቴ 5፡ 21-45; ቆላ 3፡ 5; 1ዮሐ 3፡ 15) ? በእነዚህ ንባቦች ኢየሱስ በጣም ያሳሰበው ስለ ምን ነበር ?
  5. ወደ መሰዊያዉ ስጦታ ስታመጡ በእናንተ ላይ የሆነ ሰዉ ያደረገባችሁን ታስታዉሳላችሁ ማቴዎስ(5፡ 23-24) መጀመሪያ እንድታደርጉት ኢየሱስ ምንድን አላችሁ ? ይህ አሁን ለእናንተ ይተገበራል ? አዎ ከሆነ ለዚያ ግንኙነት እርቅ በማምጣት ላይ እንዴት ታቅዳላችሁ ?
  6. በማቴዎስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 5:44-45a

“But I tell you, love your enemies and pray for those who persecute you, so that you may be sons of Your Father in heaven.”

ኢየሱስ በተራራ ላይ ተቀምጦ ፥ ደቀመዛሙርቱም በዙሪያው ተሰብስበው ሳሉ፥ እንደ ክርስቶስ ተከታይ እና ደቀመዝሙር የዕለት ተዕለት ኑሮን ለመኖር የሚሆንን ጥበብን ሰጣቸው፡፡ ይሄ ስብከት የተራራው ስብከት በመባል የሚታወቅ ሲሆን በእርሱም ኢየሱስ ስለ ልብ ጉዳዮች ተናግሯል፡፡ ደቀመዛሙርቱ ጌታን መውደድ እንዳለባቸው ያውቃሉ፥ ኢየሱሰ ግነ ከዚህ በማለፍ ጠላቶቻቸውን መውደድ እና ለጠላቶቻቸው መፀለይ እንዳለባቸው አሰተማራቸው፡፡

ይህ የማይቻል ሊመስል ይችላል፡፡ ቢሆንም፥ የክርስቶስ ገደብ የሌለው ፍቅር ሸፍኖአችሁ ፥ እርሱ ራሱ ሌሎችን መውደድ እንድትችሉ እና ትልቁን ፣ የከፋውን እና ራስ ወዳዱን ጠላታችሁን ሳይቀር መውደድን ያስችላችኋል፡፡ ዛሬ፥ ጌታ ርሁሩ ልብ እንዲሰጣችሁ እና የማይወዷችሁን ሰዎች የምትወዱበትን ፍቅር እንዲሰጣችሁ ጠይቁት፡፡ ምናልባት አንዳንድ ሰዎች እናንተን ወይንም ልጆቻችሁን ደግ ያልሆነ ቃል ተናግረው ይሆናል፡፡ ለነዚያ ሰዎች በመፀለይ ጀምሩ፡፡ ከዚያም ጌታ እነዚያን ሰዎች እንዲባርክ እና በከበረ ፍቅሩ ሀይላቸውን እንዲሰብር ጠይቁት፡፡ ለነዚያ ሰዎች በመፀለይ ፥ ጌታ ለህይወታቸው እቅድ እንዳለው እና ይህንን አስቸጋሪ ግንኙነት በመልካም እንደሚለውጠው ታመኑ፡፡ ሰዎች ጠላቶቻችሁን እንደምትወዱ ሲያስተውሉ፥ ለኢየሱስ በተራራ ላይ እንዳለ ከተማ እና በምድር እንዳለ ጨው ትሆኑለታላችሁ፡፡ ሰዎች በእናንተ የተለየ ነገርን ያያሉ—የኢየሱስ ፍቅር፡፡ ምናልባት፥ ፍቅራችሁ አንድን ሰው ወደ ኢየሱስ ይስባል፡፡

“እኔ ግን እላችኋለው በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሙአችሁንም መርቁ”

— የማቴዎስ ወንጌል5:44-45

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ምሳሌ 25:21 — “ ጠላትህ ቢራብ እንጀራ አብላው፥ ቢጠማም ውኃ አጠጣው”
  • ሮሜ 12:9-10— “ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን፡፡ ክፉውን ነገር ተፀየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤ በመንድማማች መዋደድ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ”
  • 1ኛ ዮሐንስ 4:7— “ ወዳጆች ሆይ ፥ፍቅር ከእግዚያብሔር ስለሆነ ፥የሚወደውም ሁሉ ከእግዚያብሔር ስለተወለደ እግዚያብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በእርሳችን እንዋደድ፡፡ ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 5