The Gospels Matthew

Earthly Possessions or Heavenly Treasures

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 116 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

አራቱን ወንጌላት በማጥናት ሂደት ላይ ነን - ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ ፡፡ አካታች ወንጌል ናቸው ይህ ማለት ሁሉም ኢየሱስ ተካቶባቸው በነረው ታሪክ ነገር ግን በተለያየ እይታ ይመለከታሉ ማለት ነው ፡፡ ይህን በዚህ መንገድ አስቡት፡ በዳላስ ማብሪክ ቅርጫት ካስ ጫዎታ ላይ ሆናችሁ ከዳኛው እይታ ጥሪ ተደረገላችሁ የማብሪክ ተጨዋቾች ተጨዋቾች የተለየ እይታ ይኖራቸዋል የተጋጣሚ ቡድን ተጨዋቾችም የተለየ እይታ ይኖራቸዋል ፤ ጨዋታዉ አሁንም ሆኖአል ነገር ግን ሁሉም በተለያየ አይቶታል ፡፡

በቀጣዮቹ ብዙ ወራት ላይ ኢየሱስ ማን እንደሆነ የተለያዩ እይታዎች የሚሆኑ ላይ እንመለከታለን ፤ በማቴዎስ ኢየሱስን እንደ ንጉስ እናያለን ፤ በማርቆስ ኢየሱስን እንደ አገልጋይ እናያለን ፤ በሉቃስ እና በዮሐንስ ኢየሱስን ማንነቱን በተለያየ እናያለን ፡፡ ደስታ ስለ ኢየሱስ አድስ ነገር ለመማር የሚቀጥል ነው ፡፡ ትናትና በአንድ ጥቅስ ላይ አትኩረናል ፤ ከዛ ምን እንደተማርን አስቡ ፡፡ ፀሎቴ በወንጌል ዉስጥ ስትሄዱ 100 ጊዜ ብታነቡዓቸውም እንካን እግዚአብሄር ወደ ክርስቶስ የሚያመለክቱ ጥቂት ያልተጣራ ወርቅ መስጠቱን እንዲቀጥልላችሁ ነው ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ(6፡ 1-8)፡ በምዕራፍ 5 መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ በተራራው ስብከት አገልግሎቱን ማሳወቅ ጀመረ ፡፡ ማቴዎስ 6 የኢየሱስ ንግግር ተሰብስቦ ለነበረው ህዝብ እንዴት እንደሚሰጡና በትክክል እንደሚፀልዩ ገለፃ ነው ስለዚህ ህዝብ አያሳስባችሁም ፡፡

ማቴዎስ (6፡ 9-18)፡ በማቴ (6፡ 9-13) ኢየሱስ ለአዳማጮቹ የእግዚአብሄርን ፀሎት በመስጠት አስተማራቸው ፡፡ ኢየሱስ ይህ ሁሉ በምህረት የተመሰረተ እንደሆነ ገለፀ (ቁጥር 14-15) ተከታዮቹም እንዴት መፆም እንደሚገባቸው አወራቸው (ቁጥር 16-18) ፡፡ የመጨረሻው ምሳሌ በምድረበዳ ኢየሱስ የፆመው 40 ቀንና 40 ሌሊት ነው ፡፡

ማቴዎስ (6፡ 19-21)፡ ዋይርስቤ ያመለከተው “ እምነትን በቁስ ላይ ማድረግ ልብን እንደሚገዛ “ ነው ፡፡ በቁጥር 19-21 ኢየሱስ ስለ ንብረት አዉርቶአል ገንዘብ በተፈጥሮው ክፉ እንዳልሆነ እዉቅና ሰጥተአል (ምሳ 6፡ 6-8) ፡፡ በሁሉም ቀን ተግብራችን ለመጎአዝ ገንዘብ ያስፈልገናል ቤተሰባችንንም እንድንከባከብ ያግዘናል (1ጢሞ 6፡ 10) ፤ በተጨማሪም ገንዘብ መደሰትን ይሰጣል መቆጠብ ደግሞ መልካም ነገር ነው (1ጢሞ 4፡ 4) ፡፡ ግባችን ልጆቻችንን እን የልጅ ልጆቻችንን በዉርስ ለመባረክ በቂ ገንዘብ እንዲኖረን ይሆናል (ምሳ 13፡ 22; 2ቆሮ 12፡ 14) ፡፡

በሌላ በኩል ገንዘብ መጥፎ ሊሆን ይችላል ፤ በገንዘብ በትንሽ የምትቀየሩ ወይም ሰዎችን በትክክል የማትዙ እንደሆናችሁ እግዚአብሄር ያውቃል (ያዕ 5፡ 2-5) ፤ በዚህም “ ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነውና አንዳንዶችም ይህን ሲመኙ ከኃይማኖት ተሳስተው በብዙ ስቃይ ራሳቸውን ወጉ “ (1ጢሞ 6፡ 10) ፤ ይህ ማለት የተከፈለ ልብ አላቸው ማለት ነው ….ገንዘብን በመውደድ እና እግዚአብሄርን በመውደድ መሀከል ፡፡

በሌላ ወገን ለሰማይ እንዴት ሀብትን መሰብሰብ እንችላለን (ማቴ 6፡ 20) ? የኔልሰን ማብራሪያ የሚያትተው “ የኑሮአችን የመጨረሻ መድረሻችን ምድራዊ ወይ ሰማያዊ ነው እናም የልፋታችን ክምችት ትክክለኛው ሀብታችን በየት እንደሆነ ይገልጣል “ ፤ ይህ ማለት ለእምነት አገልግሎት ሽልማቶች አሉት ማለት ነው …. የእምነት ስራ በእዉነቱ በሰማይ ያከማቻል(ያስቀምጣል) (1ጴጥ 1፡ 14) ፡፡ ስለዚህ ትኩረታችን በንጉሱ በኢየሱስ ላይ በማድረግ በድብቅ ነገሮችን በምንሰራ ጊዜ ሰማያዊ ሽልማቶችን የምንቀበልበት ያ ነው (ማቴ 5፡ 12; 6፡ 6; 10፡ 42) ፡፡

ማቴዎስ (6፡ 22-23)፡ ሶርግ “ ልብ የሰዉነት ዋና እና እዉቀትን፣ ስሜትን እና ፈቃድን የሚቆጣጠር ነው “ እንደሆነ ገልፆታል ፤ ዋይርስቤ በቁስ ላይ ያተኮረ እምነት ከልብ በላይ እንደሚቆጣጠር “አይምሮንም” ሁሉ እንደሚቆጣጠር ጨምሮአል ፡፡ ስለዚህ በቁስ ልብን ከማስገዛት ወደ አዕምሮን ማስገዛት እየሄድን ነው ፡፡ ኢየሱስ አይን አካል መሉ ብርሀን እንዲሆን ወይም ጨለማ እንዲሆን ይፈቅዳል አለ (ቁጥር 22-23) ፡፡ ስለዚህ በዉስጣችሁ ያለው ብርሀን ጨለማ ከሆነ ያጨለማ ምን ያክል ጥልቅ ነው ? የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው “ አይናችሁ ጥሩ ላይ ካልሆነ የሰውነታችሁ ማንኛውም አካል መዝናናት አይችልም ፡፡” አይንችሁ መጥፎ ከሆነ ሁሉም ነገር ላይ ጉዳት አለው ፤ ለሪሞቶአ አይን በስታ ጨለማ እንዲሆን ብትፈቅዱለት የአለም ነገሮች እን የምድር እምነት አይምሮአችሁን ወደ ጨለማ መቀየር ይጀምራል ፡፡ አይናችሁን እና አይምሮአችሁን ከጨለማ ከተከላከላችሁ እይንችሁ እና አይምሮአችሁ ብርሃን ይሆናል ፡፡ በመፅሀፍ አይን ከልብ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ተገንዘቡ (መዝ 119፡ 10, 18, 148) ፤ ህይወታችሁን በጨለማ ወይም በብርሃን ባስገዛችሁ ጊዜ ህይወታችሁ የሚሄድበት ያን ነው ፡፡

ማቴዎስ(6፡ 24)፡ዋይርስቤ በቁስ ላይ ንግግሩን በዚህ መንገድ ጨረሰ፡ “ በቁስ ላይ ያተኮረ እምነት ልብን፣ አይምሮን እን ፈቃድን ይገዛል ፡፡” ኢየሱስ ያለው “ ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም ወይም አንዱን ይጥላል ሁለተኛውንም ይወዳል ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል ፤ ለእግዚአብሄር እና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም “(ቁጥር 24) ፡፡ ምድራዊ የቁስ ሀብት መፅሀፍት የሚሉት “ ጣዖት ወይም አምላክ ከአንዱትክክለኝ እግዚአብሄር ጋር የሚጋጭ የሰዉ ልብ ጣዖት ወይም የሀሰት አምላክ እንደሚሆን ነው “ ፤ ያ ማለት በምድራዊ ሀብት የጠፋን ስለ መንግስቱ ሀሳብ የረሳን እንሆናለን ማለት ነው ፡፡ የመንግስቱ አይምሮ መኖር ማለት የምናደርገው፣ ያለን መንግሰቱን ለማሻሻል የሚኬድ ነው ፡፡ ታስከር ይህን እንደ ባሪያ አይነት አስተሳሰብ ገልፆአል የተናገረውም “ አንድ ባለቤት መኖር እና የሁል ጊዜ አገልጋይ የባሪያነት ባህሪይ አለው ፡፡“ ከሰዉ ፍቃድ ቦኃላ ለመሄድ ወይም ከእግዚአብሄር ፈቃድ ቦኃላ ለመወሰን አግኝታችኃል ፡፡

ቁጥር 25 ያስከተለው፡ “ ስለዚህ እላችኃለሁ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱበት አትጨነቁ ነፍስ ከመብል ሰዉነትም ከልብስ አይበልጥምንም ? “ የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው “ በቁስ ንብረት ላይ ልብን ማስቀመጥ ወይም በእነርሱ እጥረት መጨነቅ በሚቀጥል አለመረጋጋት የሚያኖር እና የራስን መንፈሳዊ በረከት ከእግዚአብሄር የሚያስቀር ነው ፡፡ “ እግዚአብሄር በልባችሁ ውስጥ ምንድን እንዳለ፣ ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል ስለዚህ “ በጥንቃቄ፣ በማሰብ እና በእምነት” መጎአዝ መጀመር ትችላላችሁ እግዚአብሄር እንደሚያሳያችሁ ታውቃላችሁ ፡፡ ለጭንቀት በተሰጠን ጊዜ እግዚአብሄር እንደማይጠነቀቅልን እንገምታለሁ በራሳችንም ነገሩን እናደርጋለን (ቁጥር 26) ፤ ቁጥር 27 ለምን መጨነቅ እንደማያስፈልገን ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ከተከተሉት ቦኃላ እነዚያን ያደርጋል ፤ በቁጥር 28-29 ኢየሱስ አድማጮቹን እንዴት የእግዚአብሄር ጥንቃቄ ለዕኛ ታላቅ እንደሆነ የእግዚአብሄርን ባለፀግነት ከሰለሞን ጋር በማወዳደር አሳሰባቸው (2ዜና 9፡ 3-4) ፡፡

በቁጥር 31 ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን በእርሱ ላይ እምነት ከነበራቸው ቀጣዩ ምግብ ከየት እንደሚመጣ እንዳይጨነቁ ጠየቃቸው (ማቴ 8፡ 26) ፡፡ ኮንስታብል የሚለው “ ልክ እንደዚህ የሚያወራ ሞኝ ብቻ አይደለም ስለ ህይወት አስፈላጊነት የሚበሳጭ አምላክ የለሽም ነው እንጂ ፤ የሚጨነቁ ደቀመዝሙር እግዚአብሄርን እንደማይመለከቱና እንደማይምኑ እንደ አላማኞች (አህዝብ) ይኖራል ፡፡” በቁስ ነገሮች ላይ ትኩረት በምናደርግ ጊዜ ጣዖተኞች እንሆናለን ፤ ነገር ግን የእግዚአብሄርን መንግስት መፈለግ እርሱን መጀመሪያ ማስቀመጥ ነው (ማቴ 6፡ 33) ፡፡ ዋይርስቤ የተናገረው “ አማካኙ ሰው ራሱን በሁለት ሌቦች መሀከል የሚያሰቃይ ነው፡ በትናት ፀፀት እና ስለ ነገ በመጨነቅ ፡፡” ኮንስታብል የተናገረው እግዚአብሄር በቂ ፀጋ ሰጥቶናል “ ስለዚህ በህይወት አንድ ጊዜ አንድ ቀን መነጋገር እንችላለን ፤ ነገ ለሚገጥመን በቂ(የሚረዳንን) ፀጋ ይሰጠናል ፡፡” በዚያ ንግግር ታግያለሁ ለነገ ፀጋ እንደሚያስፈልገኝ አስባለሁ ፤ ነገር ግን አልሆነም ፤ እግዚአብሄር ለዛሬ በቂ ፃጋ ሰጥቶናል ፡፡

መዝጊያ

ስለዚህ ጭንቀትን እንዴት ነው የምንቐቐመው ?ዋይርስቤ ሰዎስት ቃላቶችን በጭንቀት ላይ አሸናፊነትን የሚሰጡንን አስቀምጦአል ፤ መጀመሪያ ዋይርስቤ የሚለው በእግዚአብሄር ለመታመን በቂ እምነት መኖር (ማቴ 6፡ 30) ፤ ሁለተኛ ያለው ለልጆቹ እንደሚጠነቀቅላቸው በአባቱ መታመን ይገባንል (ማቴ 6፡ 32) ፤ ሰዎስተኛ ያለው በኑሮአችን እንደ ቀዳሚ በእግዚአብሄር ላይ ማተኮር (ማቴ 6፡ 33) ፡፡ ዋይርስቤ በዚህ መንገድ አጠቃለለው፡ “በአባታችን ላይ እምነት ካለን እና መጀመሪያ ካስቀመጠነው የሚያስፈልገንን ያማላል ፡፡”

8 R. V. G. Tasker, The Gospel According to St. Matthew: An Introduction and Commentary (Grand Rapids, MI: Wm. B. Eerdman’s Publishing), p. 76; quoted in Dr. Constable’s Exposi- tory (Study) Notes, p. 136; available online.

  1. William W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 27.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1152.

  3. T. Sorg, The New International Dictionary of New Testament Theology, s.v. “kardia,” pp. 180-184; quoted in Dr. Constable’s Expository (Study) Notes, p. 136; available online.

  4. Wiersbe, p. 27

  5. Radmacher, Allen, and House, p. 1152.

  6. Wiersbe, p. 27.

  7. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005). p. 1311.

  8. Radmacher, Allen, and House, p. 1152.

  9. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes on Matthew, p. 138; available online at soniclight.com.

  10. Constable, p. 138.

  11. Wiersbe, p. 28.

  12. Constable, p. 139.

  13. Wiersbe, p. 28.

ጥያቄዎች

  1. በማቴ (5፡ 16) ኢየሱስ ሁሉም እንዲያዩት መልካም ስራችሁ እንዲያበራ እንደፈቀደ ተናገረ ይሁን እንጂ በማቴ (6፡ 1) መልካም ስራችሁን በህዝብ ፊት እንዳትሰሩ ተናግሮአል ፤ እነዚህን ንግግሮች ኢየሱስ እንዲናገር ምክንያቱ ምንድን ነው ? (ኤፌ 5፡ 8-9; 1ጴጥ 2፡ 12)
  2. ገንዘብ ማስገባት እና ማስወጣት በራሱ ክፉ አይደለም ፤ ማቴ (6፡ 24) ሁለት ጌቶች ማገልገል አትችሉም ይላል ፤ ገንዘብን ለመልካም መጠቀም የሚቻልበት ጥቂት ተግባሪዊ መንገዶች ምንድን ናቸው (ምሳ 6፡ 6-8; 13፡ 22; 2ቆሮ 12፡ 14; 1ጢሞ 4፡ 4; 5፡ 8) ? እንዴት ገንዘብ መጥፎ ሊሆን ይችላል ? (ሉቃ 12፡ 13-21; 1ጢሞ 6፡ 10; ያዕ 5፡ 2-5)
  3. ማቴዎስ 6 በሰማይ ሀብት እንድናከማች ይናገራል በዚያም ለእነዚያ ነገሮች እግዚአብሄር ይሸልማል ፤ ሀብትን ወይም ሽልማትን በሰማይም በተጨባጭነት እንዴት ማከማቸት እንችላለን ? (ማቴ 5፡ 12; 6፡ 6, 15, 20; 10፡ 42; 1ጴጥ 1፡ 14)
  4. በማቴ(6፡ 14) ኢየሱስ ሌሎችን ይቅር ባላችሁ ጊዜ የሰማይ አባታችሁ ይቅር ይላችኋል ለምንድን አለ (ማር 11፡ 25; ኤፌ 4፡ 32; ቆላ 3፡ 13) ? ሌሎችን ይቅር ማለታችን ለእግዚአብሄር ለምን አስፈለገው ? በህይወታችሁ የእናንተ ይቅርታ የሚያስፈልጋችሁ ሰዎች አሉ ?
  5. በማቴ (6፡ 5-13) እያንዳንዳችንን ኢየሱስ ለመፀለይ እንዴት አስተማረን (2ነገ 4፡ 33; መክ 5፡ 2; ሮሜ 8፡ 26-27) ? ኢየሱስ ለፀሎት በራሱ እንደተለየ ጠቅሶዓል ነገር ግን በምኩራብ መፀለይ መልካም ነውን ? ለምን ወይስ ለምን አይሆንም (ሉቃ 18፡ 10-14; ኤፌ 6፡ 18; 1ተሰ 5፡ 17; ያዕ 5፡ 16) ? ሁልጊዜ በፀሎታችን ላይ ካተኮርን የትም ብንፀልይ ችግር የለውም ?
  6. በማቴዎስ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 6:33-34a

“But seek first the kingdom of God and His righteousness, and all these things will be pro-vided for you. Therefore, don’t worry about tomorrow, because tomorrow will worry about itself.”

ደቀመዛሙርቶቹ ከተራራው ስብከት የኢየሱስን ትህምርት መስማት ቀጠሉ፡፡ ኢየሱስ እንዴት ከእግዚያብሔር ጋር በመስጠት፣ በመፀለይ፣ በመፆም እና ቁሳዊ እቃዎችን በአግባብ በመያዝ መጓዝ እንደሚቻል ተግባራዊ ተምህርቶችን አስተማረ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ለነዚህ ሰዎች እንዲህ አላቸው " ስለ ህይወታችሁ አትጨነቁ"፡፡ እነዚህ ደቀመዛሙርት ኢየሱስን ለመከተል መተዳደሪያቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ትተው ነበር፡፡ በአይምሮአቸው ይመላለስ ስለነበረው ፥ምን እንበላለን፣ ምን እንጠጣለን ወይም ምን እንለብሳለ ጥያቄ መገመት ትችላላችሁ? ሆኖም፥ ኢየሱስ ከመጨነቅ ይልቅ የእግዚያብሔርን መንግስትን አስቀድመው መፈለግ እንዳለባቸው እና እነዚያም ነገሮች አንደሚሰጧቸው ማስተማሩን ቀጠለ፡፡

እንደ ክርስቶስ ተከታይ፥ ከሁሉም የህይወት ጉዳዮች በላይ ጌታን ፈልጉ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ህይወትን ተከተሉ፡፡ አስቀድማችሁ እርሱን ስትፈልጉ፥ የሚያስፈልጓችሁ ነገሮች ሁሉ እንደሚጨመርሏችሁ ኢየሱስ ቃል ገብቷል፡፡ ስለዚህ፥ መጨነቅ አቁሙ እና እግዚሓብሔር ነገሩን እንደያዘው አስታውሱ፡፡ ከመሆኑ በፊት፥ ስለምትበሉት እና ስለምትጠጡትን እርሱ ያውቃል፡፡ ዛሬ እራሳችሁን ስትጨነቁ አግኝታችሁት እንደሆነ ፥ ቆም በሉ እና ስለእግዚያብሄ,ሔር ታማኝነት እና እርሱን ስትፈልጉ ሌላውን እንደሚሰጣችሁ ስለገባው ቃል በፀሎት ሆናችሁ አመስግኑ፡፡

“ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚያብሔርን መንግስት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡”

—ማቴዎስ 6:33-34

ተጨማሪ መፅሀፍት

  • ምሳሌ 3:5-6 — “በፍፁም ልብህ በእግዚያብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱምጎዳናህን ያቀናልሃል፡፡”
  • ፊልጵስዩስ 4:6-7 — “ በነገር ሁሉ በጸሎት እና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚያብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ፡፡ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚያብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል፡፡”
  • ቆላስይስ 3:1-2 — “ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሳችሁ ክርስቶስ በእግዚያብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይያለውን እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም፡፡”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 6