The Choice of Life and Death
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ በማቴዎስ 7 ላይ ነን ፡፡ የማቴዎስ 7 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ጥቅሶች ሌሎች ላይ ስለ መፍረድ ጠንቃቃ ስለመሆን ናቸው ፤ ቁጥር 3 በራሳችን አይን ዉስጥ የሆነ ነገር እያለ በሌላ ውስጥ ያለውን ማመልከት እንደሌለብን ይነግረናል ፡፡ ትናትና በኑሮአችን ውስጥ መብራት እንዲችል ስለ ሚፈቅደው ስለ አይን አስፈላጊነት ነገር ግን ከጨለማ መጠበቅን አውርተናል ፡፡
ትምህርት
ስለ ሁሉም ነገር ሁለት ነገሮች ኢየሱስ ያወራውን በእነዚህ ጥቅሶች ዛሬ እናጠናለን፡ ሁለቱ በሮች፣ ሁለቱ መንገዶች፣ ሁለቱ ጥፋቶች(ሞት)፣ የህዝቡ ሁለቱ ቡድኖች፣ ሁለቱ ቤቶች፣ ሁለቱ ግንበኞች፣ ሁለቱ ፍሬዎች፣ ሁለቱ ዛፎች እና ሁለቱ ጥያቄዎች ፡፡ ለእኛ ስላለን ምርጫ ለመረዳት አስፈላጊ እንደሆነ አምናለሁ ፡፡ በቐሚነት በምርጫ ጉዞ ላይ ነን (ዘዳ 30፡ 19; መዝ 1፡ 1-2; ኤር 21፡ 8) ፤ ሁሉንም ቀን የህይወት መንገድ ወይም የሞት መንገድ ምርጫ ስላለን እንንቃ ፡፡ የትኛው መንገድ ልትመረጡት የፈለጋችሁት ንጉሱ ኢየሱስን ያከብረዋል ? የእነዚህ ጥቅሶች መነሻ ያ ነው ፡፡
ማቴዎስ (7፡ 13-16)፡ ኢየሱስ ለመሄድ ቀላል የሆነ ሰፊ መንገድ ብዙዎችም ይሄዱበት የነበር ነገር ግን ወደጥፋት የሚመራ እንደነበር ተናገረ (ቁጥር 13) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚጫነው “ በአለም ላይ በጣም ብዙዉ ህዝብ እንደ ፃፎችና ፈሪሳዊያን ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው ፤ በቀላሉ የዉጫዊ ስራቸው እንደሚቆጠር ያምናሉ ፡፡ “ ከዚያም ኢየሱስ ሌለኝዉን በር እንደ ጠባብ፣ መንገዱ እንደ አስቸጋሪ እና ጥቂት ሰዎች እንደሚፈልጉት አቀረበው (ቁጥር 14) ፤ እነዚህ ፅሁፎች ስለ እያንዳንዳቸው መንገዶቹ ዋጋ/ ሽልማት ነው፡ (ማቴ 25፡ 46; ዮሐ 17፡ 2 እና ሮሜ 9፡ 22) ፡፡ ሰፊው መንገድ ወደ ጥፋት ይመራል ፡፡ ጠባቡ መንገድ ወደ ህይወት ይመራል ፡፡ የሚታወቅ እዉነት የሆነ ንፅፅር ምንድን እንድናደርግ በጠየቀን መሀከል ያለ ነው ፤ ብዙ ሰዎች ቀላሉን መልዕክት እና ሰፊዉን መንገድ ይወዳሉ (ማቴ 10፡ 38-39; 16፡ 24-25; ዮሐ 15፡ 18-19) ፡፡
በጣም ብዙ ሰዎች ከጠባቡ መንገድ ይልቅ የሰፊውን መንገድ መልዕክት መግባባት ነው የሚፈልጉት ፤ ወደ ቁጥር 15 ይመራል፡ “ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡበባችሁ በዉስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ “ (ሐዋ 20፡ 29) ፤ ኢየሱስ ለችግር አይፈልጋችሁም ነገር ግን ለደስታ ብዙ ነገሮችን እንድታገኙ ይፈልጋል የሚሉ ይሆናሉ ፡፡ ማክአርቱር የሚለው “ እነዚህ ራሳቸው እንደ በግ በመደበቅ አይደለም የሚያታልሉት ነገር ግን እዉነተኛ እረኛ በመምሰል እንጂ “ ፤ በእዉነት የጠነከረ መልካምም የሆነ መልዕኮቶች ይኖራቸዋል ፡፡
ጴጥሮስ የፃፈው “ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ ፤ እነርሱም የዋጃቸዉን ጌታ እንካ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፉ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ “ (2ጴጥ 2፡ 1; ኤር 6፡ 13-15) ፡፡ ስለዚህ እንዴት ልዩነቱን እንዳኘዋለን ? ሁለት ዛፎች አሉ ፍሬ የሚያፈሩና የማያፈሩ አሉ (ቁጥር 16) ፡፡ ማክአርቱር የሚለው “ ሀሰተኛ ትምህርት ስጋን መገደብ አይችል ስለዚህ ሀሰተኛ ነቢያቶች እርጉምነትን ያዉጃሉ “ ፤ መጥፎ ዛፎች መልካም ፍሬ ሊያፈራ አይችል ፡፡
ማቴዎስ (7፡ 17-20)፡ መልካም ዛፎች መልካም ፍሬና ህይወት ያፈራል ነገር ግን መጥፎ ዛፎች መጥፎ ፍሬና ሞት ያፈራሉ (ቁጥር 17) ፤ “ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም ፡፡ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል ፡፡ ስለዚህ ከፍሬያቸዉ ታውቐአቸዋላችሁ “ (ቁጥር 18-20) ፡፡ ሁለቱ በሮችና ሁለቱ ዛፎች ተመሳሳይ ዉጤት አላቸው ፤ ሰፊዉ በር እና መጥፎ ፍሬ ዛፍ ሁለቱም ያጠፋሉ ፤ ጠባቡ በር እን መልካሙ ፍሬ ዛፍ ህይወትን ይሰጣል ፡፡ የህይወትን መንገድ ወይም የሞትን መንገድ ለመከተል ምርጫ አላችሁ (ይሁ 3-4) ፡፡ በአሜሪካ ማህበረሰብ ዉስጥ አንዱ ጉዳይ ሀሰተኝ መምህራኖች እንዳሉ እንካን አለማወቃችን ነው ፤ ፊትን በማየት ብቻ የንግግሩን እዉነታ ሳንረጋግጥ ሁሉንም የሰማነውን እንወስዳለን ፤ ያ የማንቂያ አካል ነው ፡፡
ማቴዎስ (21-28)፡ በቁጥር 21ማክአርቱር 2 ጥያቄዎችን ለይቶአል አንዱ ሀሰት አንዱ ደግሞ እዉነት (2ተሰ 2፡ 7-12) ፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመከተል ያላገኙ ከእግዚአብሄር ይለያሉ(ይርቃሉ) ፤ እነዚህ ሁሉ ምርጫዎች ከህይወት አርቀው ይመራሉ ፡፡ ዋይርስቤ የገለፀው “ እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር ለፍርድ በጠራ ጊዜ ሁለቱ መንገዶች(በሮች) የእምነት ህይወት መጀመሪያን ይገልፃል ፤ ሁለቱ ዛፎች እዚህ አሁን የእምነት ህይወትን እድገት ይገልፃል(ያሳያል) ፤ እናም ሁለቱ ቤቶች የእምነት ህይወት መጨረሻን ይገልፃል ፡፡” ለቁጥር (24-25) ሁለቱን ቤቶች እና ሁለቱን ግንበኞች ላይ መመልከት እንችላለን ፤ ቤቱን መልልካም አለት መሰረት ላይ የተሰራ - ያለምንም ጉዳት ጎርፉን ይቐቐማል ፤ እነዚህ ሰዎች ሰምተዋልም እንደ ሰሙትም አድርገዋል ፡፡ ቁጥር 26-27 ሌለኛዉን ቤትና ግንበኛ ሊንቀሳቀስ በሚችል በአስቸጋሪ አሸዋ መሰረት ላይ የተሰራውን ይገልፃል - በጎርፉ ጊዜ ወደቀ ጠፋም ፤ እነዚህ ሰዎች ሰምተዋል ግን አላደረጉትም ፡፡
አንድ ሀተታ ሰጪ ቤቱ ሀይምኖታዊ ህይወታችሁን ይወክላል ዝናቡ መለኮታዊ ፍርድን እንደሚገልፅ እና ለእግዚአብሄር ቃል በመታዘዝ መሰረቱን የሰራው ብቻ እንደሚም ጠቅሶአል ፡፡ በቁጥር 28 ኢየሱስ ስብከቱን በጨረሰ ጊዜ “ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ እንደ ፃፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸዉ ነበርና ፡፡“ ህዝቡ በስልጣኑ ለምን ነበር በጣም የተደነቁት ? ፃፎችና ፈሪሳዉያን የራሳቸዉን ሀሳብ አያስተምሩም ይልቁንም “ ሁልጊዜ የተለያዩ የአይሁዶች ምሁራንን እና የህግ ሊቆችን ንግግር ይጠቅሳሉ ፤ ኢየሱስ እንደ እግዚአብሄር ልጅ ለመናገር በቃሎቹ ላይ ስልጣን ለመጨመር የሰዉ መምህር አላስፈለገውም ፡፡”
ኢየሱስ የማንንም አስተያየት ሳይጠቅስ በሙሉ ስልጣን ተናገረ (ማር 1፡ 22) ፡፡ ብዙዉን በመንፈስ ቅዱስ ላይ በመደገፍ እጎአዛለሁ ብዙዉን በሰጠኝ ስልጣን እናገራለሁ ፤ ፈተናው ከመንፈስ በመጣ በዚህ ስልጣን እንሄዳለን (ማር 1፡ 22; 11፡ 28) ? ንጉሱ ኢየሱስ ከእኛ ጋር እንዳለ በማንን ጊዜና ስልጣን እንዳለን ስናምን በጠባቡ መንገድ መጎአዝ እንችላለን ፣ መልካም ፍሬ ማፍራት እንጀምራለን መሰረታችንንም በአለት ላይ መገንባት እንችላለን ፡፡ ከዚህ ቦኃላ የሚያስፈራን መንም የለም ፡፡ ሉቃ (6፡ 48) “ ቤት ሲሰራ አጥልቆ የቆፈረ በዓለት ላይም የመሰረተ ሰውን ይመስላል ፤ ጎርፍም በመጣ ጊዜ ወንዙ ያን ቤት ገፋው በዓለት ላይም ስለ ተመሰረተ ሊያናውጠው አልቻለም ፡፡” በኑሮአችን በቃል እና ወደ መዓዘን ድንጋዩ ክርስቶስ በጥልቅ በቆፈርን ጊዜ ምንም ነገር አያነቃንቀንም ፤ ምንም ጥፋት አያጠቃንም ፤ በዚህ ስልጣን እንጎአዛለን ፡፡
መዝጊያ
በዚህ ስልጣን ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ለመጎአዝ የምትጀምርበት ጊዜ ነው….በእዉነቱ በኑሮአቸን ክርስቶስ አለን ያም በፍጥነት ቀይሮናል በዚህም ምክንያት ሰዎች ያለንን ይፈልጋሉ ፡፡ በእግዚአብሄር ቃል በጥልቀት መቆፈር እንቀጥል በዚህም ምክንያት መሰረታችን ሊንቀጠቀጥ(ሊፈርስ) አይችልም ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1153.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005). p. 1135.
MacArthur, p. 1135.
William W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew–Galatians (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 31.
Wiersbe, p. 32.
ጥያቄዎች
-
በእናንተ አይን ዉስጥ ግንድ እንደ ነበር እግዚአብሄር እስካሁን ገልጦላችሁ (ማቴ 7፡ 3-5) ? አዎ ከሆነ ምክንያቱ ለመርዳት ከሌላ አይን ዉስጥ ልታወጡት ትሞክሩት ስለ ነበር ነበር ?
-
በማቴዎስ (7፡ 12) ኢየሱስ ህዝቡን እንዲደርግላቸዉ የሚፈልጉትን በተመሳሳይ መንገድ ለሌሎች እንዲያደርጉ አስተማራቸው ፤ ማቴ (25፡ 31-46) ተመልከቱ ፡፡ ኢየሱስ ስለ በጎች እና ስለ ፍየሎች ባስተማረ ጊዜ ይህን መርህ ታዩታላችሁ ? “ ፍየሎችን “ የተረገሙ ብለዉ የተጠሩት እና ወደ ዘላለም እሳት የተላኩት ለምን ነበር ?
-
በማቴ(7፡ 13-14) ኢየሱስ ስለ ሁለቱ በሮች አወራ ፤ ሁለቱን በሮች ግለፁ ፤ በዮሐ 10፡ 7 እና 9 ኢየሱስ ራሱን እንደ ምንድን ገለፀ ? ዮሐ (14፡ 6) ተመልከቱ ፤ እነዚህ ሁሉም ንባቦች ወደ ተመሳሳይ ሀሳብ እንደሚያመለክቱ ታስባላችሁ ?
-
በማቴዎስ 7 በቁጥር 16 እና 20 ሁለት ጊዜ ኢየሱስ “ በፍሬአቸዉ ታዉቋቸዋላችሁ “ አለ ፤ መልካም ዛፍ ምንድን ፍሬ ይሸከማል ? (ገላ 5፡ 22-23)
-
በማቴ (7፡ 21-23) መሰረት ወደ መንግሰተ ሰማያት የሚገባው ማነው ?
-
ማቴዎስ 7፡ 24 አንድ ጥበበኛ ሰው ቤቱን በአለት ላይ እንደሚሰራ ይናገራል ፤ ይህ አለት ምን እንደሆነ ምን ታስባላችሁ (መዝ 62፡ 2; 1ቆሮ 10፡ 4) ? በዚህ ንባብ ይህን ሰዉ ጥበበኛ ያደረገዉ ምንድን ነው ? (ያዕ 1፡ 22)
-
በማቴዎስ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 7:1-2
“Do not judge, so that you won’t be judged. For with the judgment you use, you will be judged, and with the measure you sue, it will be measured to you.”
በተራራው ስብከት መኻል፥ ኢየሱስ በሌሎች እንዳይፈርዱ ነገራቸው፡፡ በአንድ ጊዜ መውደድ እና መፍረድ አትችሉም፡፡ ለአነድ ደቂቃ ስለዚህ አስቡ፡፡ በሰዎች ላይ ስትፈርዱ በቀኑ ውሎአቸው ፣ በድሮ ህይወታቸው፣ ወይም በአስተዳደጋቸው ሙሉ ፥ ምን ገጥሞአቸው እንደነበር ምንም ሀሳብ የላችሁም፡፡
ስለራሳችሁ ህይወት አስቡ፥ ከዚያም ጌታ እናንተን እና የምትፈርዱበትን ያንን ሰው እኩል እንደሚወድ አስታውሱ፡፡ ኢየሱስ፥ ሌሎችን እንዴት በርህራሄ መውደድ እንዳለባችሁ የሚያሳይ ምሳሌ ነው፡፡ እናንተም ዛሬ የተወደዳችሁት በዚሁ ፍቅር እና ርህራሄ ነው፡፡ ኢየሱስ ያለ ገደብ ይወዳችኋል፥ ሌሎችንም በተመሳሳይ ፍቅር እንድትወዱ ይጠይቃችኋል፡፡ ዛሬ፥ ሌላው ላይ የሚፈርድ ሀሳብ ሲመጣባችሁ፥ ጌታ እርሱ እንደሚያይ የሚያዩ አይኖች እና እርሱ እንደሚወድ የሚወድ ልብ እንዲሰጣችሁ ጠይቁት፡፡
“ እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፡፡”
—የማቴዎስ ወንጌል 7:1-2
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የማርቆስ ወንጌል 12:31 — “ ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ የምትል እርሷን የምትመስል ይህች ናት፡፡”
- ሮሜ 14:10 — “ አንተ በወንድምህ ላይ ስለምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና፡፡”
- የያቆብ መልዕክት 4:11 — “ ወንዲሞች ሆይ እርስ በእርሳችሁ አትተማሙ፡፡ ወንድሙን የሚያማ በወንድሙ የሚፈርድ ሕግን ያማል በሕግም ይፈርዳል፤ በህግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ህግን አድራጊ አይደለህም፡፡”
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 7
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።