The Gospels Matthew

The Greatest Faith

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 118 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና ሊቀጠቀጥ በማይችል ጠንካራ መሰረት ላይ መመስረት እንዳለብን አጥንተናል በእግዚአብሄር ቃል ጠንካራ መሰረት ያስፈልገናል ፡፡ ሁሉንም ቀን በቃሉ ውስጥ የምትቆፍሩ ከሆነ ይህ ሂደት ወዲያዉኑ ህይወታችሁን እንደሚቀይር እናምናለን ፡፡

ትምህርት

በማቴዎስ 8 ሁሉም አይነት የፈዉስ አይነት ታሪክ አሉ ፤ የመጀመሪያዎቹ አራት ጥቅሶች ኢየሱስ ስለነካዉ ስለ ተፈወሰዉ አንድ ለምፃም ያወራል ፤ ኢየሱስ ከማህበረሰቡ ጋር መስተጋብር ፍጥሮና ተግባብቶአል ፡፡ ወደ አለም እንድንሄድ አዝዞናል ምክንያቱም ስልጣን ሰጥቶናል ፡፡ ኢየሱስ ባህሉን ተግባብቶታል ፡፡

ማቴዎስ(8፡ 5-13)፡ በቁጥር 5 ኢየሱስ ባህሉን አዉቆታል ፡፡ ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም ገባ በዚያ ካሉት ሰዎች ጋር መስተጋብር እያደረገ ነበር በዚያን አንድ መቶ አለቃ ወደ እርሱ መጣ ፤ መቶ አለቃ የሮማዉያን ወታደራዊ ሰራተኝ 100 ወታደሮችን የሚያስተዳድር ነበር ፡፡ ካርሶን የተናገረው እነዚህ ብዙዎቹ ሰራተኞች የሰሜቲካዊያን (በዘመናዉ ጊዜ ሊቢያኖሳዊያ) እና የሶሪያ ዳራ የሚኖራቸዉ ናቸው ፡፡ መቶ አለቃዉ የጦሩ የጀርባ አጥንት የሆነ ነው ፤ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ የመቶ አለቃውን ስታነቡ ሁልጊዜ ጥሩ ንግግር ነው ፡፡ መቶ አለቃው በስሩ የሚቆጣጠረቻው ስልጣን ያለውን የሚወክልና የቅንነትን ስሜት ያደርጋል ፤ ይህ መቶ አለቃ ወደ ኢየሱስ የመጣው “ እርዳታ ያስፈልገኛል” ለማለት ነበር ፤ ከኢየሱስ በመለመን መቶ አለቃው በኢየሱስ ቁጥጥር ሰውር እንደነበር እዉቅና ሰጠ ፡፡

ይህ ፅሁፍ ጥቂት አሰገራሚ ነገሮች አሉት ፤ የመጀመሪያዉ አስገራሚ ከቁጥር አምስት ይመጣል ፤ የጦሩ ሰዉ መቶ አለቃዉ ራሱን ዝቅ ማድረጉና ኢየሱስን መለመኑ አስደንቆኛል ፡፡

ቢያንስ ሁለት አስገራሚዎች ከቁጥር 6 አሉ ፤ መጀመሪያ መቶ አለቃዉ ኢየሱስን እንደ “አምላክ” ገለፀው ፡፡ ብዙ ሀተታ ሰጪዎች መቶ አለቃው በዚህ ርዕስ ትሁት እነነደነበር እና ኢየሱስን እንደ አምልክ ተቅሶት እንዳልነበር ይናገራሉ ፡፡ መቶ አለቃዉ ኢየሱስን ለመለመን ፍቃደኛ እንደነበር ቀድመን ለይተነዋል ፤ ቀጣዩ ምልከታ መቶ አለቃዉ ለአገልጋዩ መለመን ነበር ይህ ማለት ሊረዳው ስልጣን እንደነበረው ኢየሱስን እንደ ባለሰልጣን እዉቅና ሰጠው ፡፡

በቁጥር 7 ሌላዉ አስገራሚ ኢየሱስ አገልጋዩን ለመፈወስ እንደሚመጣ መለሰለት ፤ መቶ አለቃዉ በቀላሉ እንዲረዳው ጠየቀዉ ኢየሱስም እሺ አለው ፡፡ አባታችን መልካም ነገሮችን ሊሞላን ይፈልጋል ፡፡ ለሌላ በፀሎት ስንማልድ ከዚህ ሽልማቱ የሚመጣበት ነው ፤ ይህ ለኢየሱስ ማውራት እንድትፈልጉ ያደርጋችኃል ፡፡ በትህትና በዙፋኑ ፊት መምጣት እንችላለን ምክንያቱም ኢየሱስ ይረዳናልም ፀሎታችንም ይሰማል ፡፡

የሚያስገርመዉም በቁጥር 8 መቶ አለቃዉ እራሱ ተገቢ እንዳልሆነ በማወጁ ቀጠለ ፡፡ ማክርአርቱር የተናገረው “ የአይሁዶች ባህል በአህዛብ ቤት የገባ አንድ ሰው በአከባበራቸው የረከሰ ነበር ” ፤ መቶ አለቃዉ እንደ አይሁድ ወደ ቤቱ ከበገባ ኢየሱስ እንደሚረክስ ያዉቃል ፡፡ በኢየሩሳሌም በድሮ ከተማ በር ላይ ዉጪ የሚመስል አይነት ነው ፤ ሙስሊሞች በምስራቅ በር ሰፍረዉ እና በሩንም ዘግተዋል ፡፡ ደግሞም ወርቃማው በር በመባል ይታወቃል እናም መሲሁ የእግዚአብሄርን መንግስት እንደገና ለመስራት ይጎአዝበታል ፤ ሙስሊሞች በሩን መምረግ ብቻ አይደለም ያደረጉት ነገር ግን መካነ መቃብርም በፊቱ አስቀመጡ ምክንያቱም ማንኛውም ካህን መካነ መቃብሩን በማለፍ(በማቐረጥ) እራሱን እንደማያረክስ ያውቃሉ ፡፡ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ርኩስ ስለመሆን ትኩረቱ አይደለም ነገር ግን በዚያ ፋንታ የሰዎችን ኑሮ መንካት ፈለገ ፡፡ ለመመለስ ለኢየሱስ ጊዜዉ ስለነበረ በዚያ መካነ መቃብር ይመጣል ፡፡

ከቁጥር 8 አስገራሚው መቶ አለቃዉ ኢየሱስ አገልጋዩን ለመፈወስ ስልጣን እንደነበረው ማመኑ ነው ፤ ሌላዉ አስገራሚው መቶ አለቃዉ ተገቢ እንዳልነበር ማሰቡ ነገር ግን ኢየሱስ ነበር ፡፡ ራሱን ዝቅ በማድረግ ለአገልጋዩ እርዳታ ለማግኘት ፍቃደኛ ነበር ፤ ኢየሱስ በፊቱ ራሳችን ዝግ የማናደርግ ከሆነ ምህረቱን ወይም ፀጋዉን በኑሮአችን ላይ ለማፍሰስ ፍላጎቱ የለውም(አይፈልግም) ፡፡ የመቶ አለቃዉ መልስ በቂ አልነበርኩም የሚለው ልክ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ለኢየሱስ ጠፍሩን መፍታት እንካን ብቁ አልነበርኩም ከሚለው መልሱ ጋር ተመሳሳይ ነበር (ማር 1፡ 7; ዮሐ 1፡ 27) ፤ ለዚያ ነው ኢየሱስ የተመለከተው ፡፡

በቁጥር 9 አስገራሚዉ መቶ አለቃዉ ነው ምክንያቱም ወታደር ነበር በቀላሉ በስልጣኑ መሰረት ይገናኝ ነበር ፤ የኢየሱስ ስልጣን እንደሚበልጥ ያውቃል ፡፡

በቁጥር 10 ኢየሱስ ተደነቀ ፤ በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ኢየሱስ ተደነቀ የሚል ፅሁፍ አንብባችኃል ? መቶ አለቃዉ “ና “ሂድ” ወይም “አድርግ” ብሎ ማዘዝ እንደሚችል በነበረው ታላቁ እምነት ኢየሱስ ተደነቀ ፤ አስገራሚ ነው ! መፅሀፍ የሚለው ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ክርስቶስ በእርሱ ከፍ ይላል ከፍም ያደርገዋል ፡፡ ይህ አህዛብ ታላቅ እምነት እንደነበረው ኢየሱስ ጠቀሰው ምክንያቱም ኢየሱስ ማድረግ እንደሚችል እዉቅና ስለሰጠ ፤ ሁሉም መቶ አለቃዉ ያደረጋቸዉ ለአገልጋዩ ለመለመን ነበር ፡፡ በቁጥር 6 ስንመለስ መቶ አለቃዉ ለኢየሱስ እርዳታ አልጠየቀም ፤ በቁጥር 8 ለኢየሱስ ያለው “ቃል ብቻ ተናገር ብላቴናዬም ይፈወሳል ፡፡“ ኢየሱስ በፈዉስ ስራ ላይ ስለሆነ ወደ ልባችንና አሳባችን በመመለስ እንድናስቀምጠው እፈልጋለሁ ፤ ይህ የመንግስቱ ስራ ነው ፡፡ ስልጣኑ አለው የመንግስቱ ተግባር ላይ ነው ስለዚህ የፈለገውን ማድረግ ይችላል ፡፡

በቁጥር 11 ኢየሱስ በሰማይ የእስራኤልን መሰባሰብ ገለፀው ፤ ታላቅ እምነት በመኖሩ ኢየሱስ አህዛቡን አመስግኖት ከነበር ቦኃላ ያለው ሽግግር አስደንጋጭ ነው ፤ ነገር ግን የዚህ ቁጥር ሀሳብ እስራኤል በሰማይ በአንድ ላይ በሚመጣ ጊዜ ግብዛዉ ለአይሁዶች ብቻ የሚሆን ሳይሆን አህዛብም(ከምስራቅ እና ከምዕራብ የሆኑ) በብዙ ግብዣዉ ላይ ይሆናሉ ፡፡ የዚያን ጊዜ ኃይማኖታዊ መሪዎች የእግዚአብሄር መንግስት እና የመሲሁ ግብዣ ለአይሁድ ብቻ እንደነበር ነው የሚያስቡት ፤ በቁጥር 12 ኢየሱስ “ የመንግስት ልጆች ግን በዉጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል “ አለ ፡፡

ኢየሱስ አይሁዶች ስለ ሰማይ በአማራጭ አመለካከት እየሞገታቸው ነበር ፤ አህዛቡን አመስግኖት ነበር አህዝብ ከሁሉም በመንግሰቱ ግብዣ ላይ እንደሚቀላቀሉ ያመለክታል (ኢሳ 59፡ 19; ሚል 1፡ 11) ፡፡ ኢየሱስ ሊፈፅም እንጂ ሊያጠፋ እንዳማይመጣ ተናገረ ፤ “ መፈፀም “ ማለት ወደ ፍፃሜ መምጣት ማለት አይደለም ነገር ግን በቦታው የነበረውን ሂደት ለመጨረስ ነው ፡፡ ብዙዉ የእነዚህ ትንቢታዊ ቃሎች እስካሁን አልተገለጡም (አልታወቁም) ፤ የመሲሁ ግብዣ አሁንም ቦታው ላይ ነው ፡፡ የኢየሱስ ስም በእስራኤል ብቻ ሳይሆን በህዝቦች መሀከል ታላቅ ይሆናል - አሁንም በቦታው ነው ፡፡ አይሁዶች ተቸግረው የነበረው ይህ ግብዣ ለእነርሱ ብቻ እንደሚሆን ማሰባቸው ነበር ፡፡ የቁጥር 12 መጨረሻ የሚለው ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል ፤ በመፅሀፍ ስለዚህ የሚናገር ብዙ ቦታ አለ (ማቴ 22፡ 13) ፡፡

በዚህ ታሪክ መሀከል ላይ ኢየሱስ አይሁዶችን እምነት ካላቸው አህዛቦች በብዙ ወደ ገበታው መምጣት እንደሚችሉ ተናገረ ፤ መጨረሻም ላይ አገልጋዩ በሙሉ ተፈወሰ (ቁጥር 13) ፡፡ የመንግስቱ አስተሳሰበ(ሀሳብ) ሲኖረን እንደ መቶ አለቃዉ እና እንደ ኢየሱስ መጎአዝ እንደምንችል አምናለሁ ፡፡ አንድ ጥቅስ ላይ እንድንመለከት ከዚያም በምልከታው ዉስጥ ወደ ትርጉሙ ሂደት በመንቀሳቀስ መሬት ላይ እንድንተገብረው እፈልጋለሁ፡ “ ሄዳችሁም መንግስተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ “ (ማቴ 10፡ 7) ፡፡

በእግዚአብሄር መገኘት በምተጎአዙ ጊዜ፣ ክርስቶስ ህይወታችሁን እንደቀየረዉ በመትጎአዚ ጊዜ የሰማይ መንግስት ቅርብ ይመጣል ማድረግ የምትችሉት ይህ ነው፡ “ የታመመን መፈወስ፣ የሞተን ማስነሳት፣ የቆዳ በሽተኞችን ማንፃት፣ ክፉዉን ማባረር ፤ ያለ ክፍያ በነፃ ተቀብላችኃል ያለ ክፍያ ስጡ “(ቁጥር 8) ፡፡

በዚህ ትህትና የምንጎአዝ ከሆነ ንጉሱ ኢየሱስ ስልጣን እንደሰጠን እንረዳለን በዉስጣችን ባለው በመንፈስ ቅዱስም ክርስቶስ የሚያደርጋቸዉን በእዉነቱ ማድረግ እንችላለን ……የታመመን መፈወስ፣ የሞተን ማስነሳት፣ የቆዳ በሽተኞችን ማንፃት፣ ክፉዉን ማስወጣት ፡፡ የተሰጣችሁን ልትሰጡት ያስፈልጋችኃል ፡፡

መዝጊያ

በዚህ ክፍል እንድታደርጉት የምፈልገው መፅሀፍ ያለውን ቀስ እንድትሉና እንድታተኩሩት ነው ፤ በመጨረሻም ከዚህ ክፍል የወሰድኩት በኢየሱስ ወደ ገበታዉ ከመጣችሁ ከእርሱ መማር ትችላላችሁ ከዚያም ልክ ኢየሱስ እንዳደረገው “ መምጣት” “መሄድ” እና “ ማድረግን ” ነው ፡፡ ሁሉንም ያለክፍያ ተቀብለናልና ከከፍያ ነፃ መስጠት ምላሻችን ነው፡፡

  1. Donald A. Carson, Matthew, p. 200; Dr. Constable’s Expository (Study) Notes, p. 154; available online.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005). p. 1136

ጥያቄዎች

  1. በህጉ መሰረት ለምፃም ኢየሱስን በሚጠጋበት ጊዜ ሰዉየዉ ምንድን ማድረግ ይበቅበታል (ዘሌ 13፡ 45) ? ለዚህ “ለረከሰ ሰዉ “ኢየሱስ እንዴት መለሰለት (ማቴ 8፡ 3) ? ባህላችን አምኖ ያረከሳቸዉን እንዴት አድርጋችሁ ነው የምትመልሱላቸው ?
  2. በማቴ (8፡ 5) የተጠቀሰዉ መቶ አለቃ ሮማዉ እንጂ እስራኤላዊ አልነበረም ይህ ሊሆን የሚችል ነው ? አገልጋዩን ሊፈዉስለት አብሮት ወዲያዉኑ ለመሄድ ፍቃደኛ መሆኑ አላስደነቃችሁም ? ለምን ?
  3. ኢየሱስ ይህ የመቶ አለቃዉን እምነት እንደ ምሳሌ አዘጋጀልን ከእስራኤላዊያን መካከል እንኳን አልፈለገም ፤ ኢየሱስ እንደ ታላቅ እምነት እዉቅና እንዲሰጠው ይህ ሰዉ ምንድን ስለ ተረዳ ነበር ?
  4. በማቴ (8፡ 19-20) ኢየሱስ ፃፎችን እርሱን ከመከተል ተስፋ ማስቆረጥ ነበር የተከሰተው ፤ ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ?
  5. እርሱን መከተል መፈፀም ከጀመሩ አንስቶ ደቀ መዛሙርቱ በግልፅ ኢየሱስ የተለየ እንሚሆን አምነዋል ፤ ብዙ ሰዎችን ሲፈዉስ አይተዉ ቢሆንም እንኳን ማቴዎስ (8፡ 27) ላይ ነፋሱ እና ባህሩ ሲታዘዙለት ጊዜ ለምን እንደተደነቁ ምን ታስባላችሁ ? (ማቴ 8፡ 16)
  6. በማቴዎስ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 8:10

“Hearing this, Jesus was amazed and said to those following Him, ‘I assure you: I have not found anyone in Israel with so great a faith!’”

አንድ መቶ አለቃ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፥ ሽባ ሆኖ ቤት ወስጥ የተኛውን እና በብዙ ስቃይ ውስጥ የነበረውን አገልጋዩን እንዲፈውሰው ጠየቀው፡፡ ይህ ከአህዛብ ወገን የሆነ የሮማውያን የጦር አዛዣ፥ ኢየሱስን አስገረመው፡፡ ምድራዊ ስልጣኑን እና ደረጃውን ቸል ብሎ፥ ለአገልጋዩ የማይገባ ፍቅርን አሳየ እንዲሁም በኢየሱስ ፊት ትህትናን ገለፀ፡፡ በተጨማሪም ኢየሱስ ቃልን በመናገር ብቻ ተኣምራዊ ፈውስን ማድረግ እንደሚችል የሚገልፅ እምነት ነበረው፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ክርስቶስን እንደሚከተል ሰው ዛሬም ኢየሱስ በእናንተ "እንዲገረም"፥ በፍቅር፣ በትህትና እና በእምነት መራመድ የሚያስችላችሁ ሀይል አላችሁ፡፡ በምንም አይነት ነገር ውስጥ ብትጓዙም፥ ልክ እንደ መቶ አለቃው ሁኔታውን በፍቅር፣ በትህትና እና በእምነት ቅረቡ፡፡ ምናልባት እናንተም እግዚሀብሄር በነገሩ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ ስታዩ ትገረማላችሁ!

“ ኢሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለው በእስራኤል እንኳን እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም፡፡”

— የማቴዎስ ወንጌል 8:10

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የማቴዎስ ወንጌል 8:13 — “ ኢየሱስም ለመቶ አለቃ፦ ሂድና እንዳመንክ ይሁንልህ አለው፡፡ ብላቴናውም በዚያች ሰአት ተፈወሰ፡፡”
  • የዮሐንስ ወንጌል 20:29 — “ ኢየሱስም ፦ስለ አየኸኝ አምነሀል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው፡፡’”
  • ቆላስይስ 1:10-11 — “ በበጎ ስራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚያብሄርም እወቀት እያደጋችሁ፥ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመፅናት እና ለመታገስ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በሀይል ሁሉ እየበረታችሁ ”

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 8