The Gospels Matthew

The Message of New Wineskins

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 119 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እንደፈጣን ክለሳ በወንጌላት ዉስጥ ስንሄድ የኢየሱስን የተለያየ አመለካከት እንደምታዩ አስታዉሱ ፤ ከማቴዎስ አመለካከት ኢየሱስን እንደ ንጉስ ነው ፡፡ በማቴዎስ በአሮጌዉ መንገድ እየሰራ ባልነበረው እና ወደ ቦታው ወደ ሚመጣው ለአድሱ መሀከል ያለውን ዉጥረት ማየት እንጀምራለን ፡፡

ትምህርት

ማቴዎስ(9፡ 1-8)፡ ኢየሱስ ወደ ራሱ ከተማ በመግባት መፈወስ ጀመረ ፤ አንዳንድ ጎአደኞቹ በእርሱ ፊት አንድ ሽባ ሰዉ አመጡ ፡፡ ኢየሱስ የጎአደኞቹን እምነት አየ ሽባዉንም ሰዉዬ ኃጢዓት ተሰረየልህ አለው (ቁጥር 2) ፡፡ ይህ ኢየሱስን የታመመውን አገልጋዩን እንዲፈዉስለት እንደጠየቀው መቶ አለቃው ነው ፤ በመቶ አለቃዉ እምነት ምክንያት ኢየሱስ አገልጋዩን እንደፈወሰው አምናለሁ በተጨማሪም ስለ ሽባውም ሰዉ ተመሳሳይ ነገር እንደሆነ አምናለሁ ፤ ኢየሱስ ወደ ኢየሱስ ሰዉየውን ላመጡት ሰዎች እምነት ምላሽ ፈወሰው ፡፡

ማቴዎስ(9፡ 9-13)፡ እነዚህ ቁጥሮች ኢየሱስን ለመከተል የማቴዎስ መጠራት መለየትን ይናገራሉ ፡፡ በግብሩ ስራ ላይ ተቀምጦ እንደነበር ኢየሱስ ማቴዎስን ቀረበው ፤ ኢየሱስ በጠራዉ ጊዜ ወዲያዉኑ ተነሳ ስራዉንም ተወ (ቁጥር 9) ፡፡ የኢየሱስ ቃል አስደናቂ ድርጊት በአገሩ ዙሪያ ተስፋፍቶ ነበርና ማቴዎስም ሰምቶ እንደነበር አምናለሁ ፤ በኢየሱስ መንገድ ተከተለ ይከታተል፣ ይመለከት እና ያዳምጥ በትምህርቱ ስር እንካን ሳይቀመጥ አይቀርም ፡፡

በቁጥር 10 ማቴዎስ ኢየሱስ በገበታው ላይ ከማቴዎስ እንግዶች ጋር እንዴት እንደተቀመጠ ገልፃታል - ከሌሎች ቀረጥ ሰብሳቢዎች እና ኃጢዓተኞች ጋር ፡፡ ፈሪሳዉያን ኢየሱስ ለምን ከእነዚህ ሰዎች ጋር እንደነበር ጠየቁ (ቁጥር 11) ፤ ኢየሱስም መልሶ “ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም “ አላቸው(ቁጥር 12) ፤ በመቀጠል ምህረትንና ርህራሄን እንጂ መስዋዕት አይደለም የሚለውን ምን ማለት እንደሆነ እንደማሩ ነገራቸው ምክንያቱም የመጣዉ ለኃጢዓተኞች ስለሆነ (ቁጥር 13) ፡፡

ይህ የእብሪትና የጭንቀት መንፈስ የማቴዎስ 9 መነሻ ነው ፤ የኃይማኖት መሪዎች ነገሮችን በሌላ መንገድ ሲያደርጉ ለምን በአንድ መንገድ እንደሚያደርግ ኢየሱስ ይጠየቅ ነበር ፡፡ ኢየሱስ ያደረገዉን እንዳልወደዱት ነገሩት ነገር ግን ማድረጉን ቀጠለ ፤ ንጉሱ ኢየሱስን በምንከተል ጊዜ መቼም የኃይማኖትን መንገድ በፍፁም አይመስል ፡፡ በቤተ ክርስቲያን መነቃቃት ያስፈለገን ምክንያት የኃይማኖተኝነት መንፈስ የተሰበረ እንዲሆን ስለሚያስፈልገን ነው ፡፡ ኢየሱስ ምህረትና ርህራሄ ይፈልጋል ፤ መስዋዕታችንና ቁርባናችን ብቻ አይፈልግም ፡፡ ኢየሱስ ኃጢዓተኞችን እንጂ ፃድቆችን ሊጠራ አልመጣም (ቁጥር 13) ፤ በዚህ ንግግር ነበር ማቴዎስ ኢየሱስን መከተል የጀመረው ፡፡

ማቴዎስ(9፡ 14)፡ ቁጥር 14 የመጥምቁ ዮሐንስ ተከታዮች ኢየሱስን በጠየቁት ጊዜ ወደ ሌላ ጊዜ በመሸጋገር ይጀማራል ፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ መልዕክት የንስሀ ነበር መልዕክቱ ኢየሱስ ላደረገዉ ሁሉ መንገዱን የነፃ እና የተቀየረ ለማድረግ ያስፈለገ ነበር ፡፡ በዚህ ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት የኢየሱስን እና የደቀመዛሙርቱን ተግባራት ጠየቁት ፡፡ በሉቃ (5፡ 29-39) መሰረት ፈሪሳዉያን ከመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት ጋር ነበሩ ፤ ጥያቄአቸዉ ስለ ኃይማኖታዊዉ የፆም ድርጊት እና ሌሎች ብዙ ኃያማኖታዊ ስለነበሩዓቸው ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ከሚያደርጉት በላይ ስለፃሙ ነበር ፡፡

እስራኤላዊያን ለስርየት ቀን እንዲፆሙ ያስፈልጋቸዉ ነበር (ዘሌ 16፡ 29-30) ፤ በእያንዳንዱ ሳምንት ሁለቱ የፆም ቀናቶች በፍቃደኝነት ነበሩ ይሁንና ፈሪሳዉያን ኃይማኖታዊ አድርገዉታል (ሉቃ 18፡ 12) ፡፡ በዚህም ጥያቄው መረዳት እንደቻልነው “ ኢየሱስ ልክ እንደኛ ሁለቱን ቀናት አንተና ደቀመዛሙርትህ ለምን አትፆሙም ? በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር የሚፈልገው የጾም ማስረጃ ባዙ አለ( ዘጸ 34፡ 28; ዘሌ 11፡ 44-47) ፤ ከተለያዩ አይነት እንስሳዎች እና ለናዝራዊነት ልክ እንደ ሳሞሶን ከብዙ ነገሮች እንዲፆሙ ተጠይቀዉ ነበር ፡፡

ፈሪሳዉያኑ እንደ ኃይማኖታዊ አስተሳሰባቸው አካል በሳምንት ሁለት ጊዜ ይፆማሉ ፤ ይህ ባህላቸዉ እና ኃይማኖታቸዉ ነበር ፡፡ ኬንት በርጊሁስ አምስት የጾም ምድቦችን ሰጥቶአል፡ “(1) ጾም እንደ ኃዘን ወይም ለቅሶ ምልክት; 2) ለኃጢዓት እንደ ንስሀ እና ይቅርታን እንደ መፈለግ ምልክት; 3) በጸሎት እንደ እርዳታ; 4) መልዕክተኝቹን በመርዳት ለዉጠየት የእግዚአብሄርን መገኘት እንደ መለማመድ እና 5) እንደ ህዝብ አምልኮ አከባበር ፡፡” ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ለምን እንደማይጾሙ በጠየቁ ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት የነበራቸዉ መነፅር ይህ ነበር ፡፡

ማቴዎስ(9፡ 15)፡ የመጥምቁ ዮሐንስ እና የኢየሱስ ደቀመዛሙርት እርስ በእርሳቸው ይደጋገፋሉ ባላችሁ አስባችኃል ፤ በቁጥር 15 ኢየሱስ ያለው “ ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? በሌላ ቃላት የጠየቃቸው “ የሰርጉ እንግዶች፣ የሙሺሪት ልጆች፣ ደቀመዛሙርቱ እኔ ከእነርሱ ጋር እያለሁ ማዘን ይችላሉ ? “ ለፆም አንዱ ምክንያት ሀዘን ወይም ለቅሶ ነበር ፡፡ ቁጥሩ ኢየሱስ በሄደ ጊዜ ከዚያ ይፆማሉ በማለት ቀጠለ (ቁጥር 15) ፤ የኢየሱስ ቃላቶች የዮሐንስን ደቀመዛሙርቶች መረዳት አስደነገጠ ፤ ይሁንና መጥምቁ ዮሐንስ በሚዜነት ተጠቅሶ ነበር (ኢሳ 62፡ 5; ሆሴ 2፡ 20; ዮሐ 3፡ 29) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚለው “ እዚህ የተገለፀዉ መርህ ኢየሱስ ክርስቶስ በአጠቃላይ በአድስ ስርዓት ከቀድሞው ከአይሁዶች ሀብት ጋር ሊገጥም የማይችለውን ለማምጣት የመጣ ነው ፡፡” ከህግ ገዢነት ወደ እግዚአብሄር ፀጋ ጊዜ እንሄዳለን ፡፡

ማቴዎስ(9፡ 16-17)፡ ኢየሱስ በአሮጌ እና አድስ ወይን አቁማዳ ምሳሌ በኩል ይናገር ስለነበረው ጸጋ መጻፍ ጀመረ ፤ ልክ አድሱን ልብስ በአሮጌዉ ላይ በማድረግ በትክክል እንደማይዘው አይሁዶች ለረጅም ጊዜ እንዴት እንደሚጾሙ ትዕዛዙን ይከተሉ ነበር አድስ መንገድ እንዳለ ማየት አልቻሉም ነበር ፤ በቁጥር 17 ትኩረቱ “በአድስ” እና “ በአሮጌ “ ነው ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር ለእነዚህ ማሳያ ገለፃ ሰጥቶአል ፡

“ በመሳሳቡ ምክንያት የእንስሳ ቆዳዎች ለወይን መብላላት ይጠቅም ነበር ፤ ወይኑ እንደተብላላ ግፊት ያመጣል አቁማዳዉን ይወጥረዋል ፡፡ ቀድሞ የተወጠረዉ ቆዳ መሳሳቡን ያጣል ይፈራርሳል ወይኑም አቁማዳዉም ይበላሻል ፡፡ ኢየሱስ እንደ ማሳያ የቀድሞዉ ስርዓት አይነት ምሳሌ በፈሪሳዉያንና በዮሐንስ ደቀመዛሙርቶች የሚተገበረው በዓላዊያን ጾም ከአድሱ ኪዳን ዘመን ወይን ጋር እንደማይገጥም ለማስተማር ይህን ተጠቀመ ፡፡”

ፈሪሳዉያን “ የኦርቶዶክስ ዋና(ሀሳብ)” የሚወክሉና የተለዩ ከአይሁዶች 6000 ያክል የተለዩ ጥቂቶች ነበሩ ፤ በአሮጌዉ ልብስ ወይም አቁማዳ የሚያስቀምጥ ቡድን ከነበር ፈሪሳዊ ይሆናል ፤ ነገር ግን ኤርሚያስ የተናገረው ከምድረባዳ እንካን ሲያወጣቸዉ እግዚአብሄር የሰጣቸዉን ኪዳን እንደሰበሩት ከአያቶቻቸዉ ጋር እንደተደረገዉ ኪዳን የማይሆን አድስ የፀጋ ኪዳን አለ ፡፡ እግዚአብሄር አድስ ኪዳን ያስቀምጣል “ ህጌን በልቦናቸው አኖራለሁ በልባቸዉም እጽፈዋለሁ “ (ኤር 31፡ 33; ሕዝ 36፡ 26-27) ፤ ነገር ግን ያ አድሱ መንፈስ በአሮጌዉ ስርዕት፣ በገበታው፣ በ613 ህጎች በአሮጌዉ መንገድ ነገሮችን አሰራር ዉስጥ መቀመጥ አይችልም ፡፡ አድሱ ኪዳን ያን ይቀይራል በእኛ ዉስጥ ባለዉ በእግዚአብሄር መንፈስ ይጀምራል ፡፡ እናም እዉነታው ለአድሱ አቁማዳ ክፍት ከሆንን ፈጣን ለዉጥ መሆን ይችላል ፡፡

በሐዋ (19፡ 2-5) ጳዉሎስ በኤፌሶን ደቀመዛሙርትን አልፃፈም በመንፈስ ባለመጠመቃቸዉ ምክንያት ነገር ግን በዚህ ፋንታ ወደ እነርሱ አፈሰሰባቸዉ፣ አስተማራቸዉ እና በእነርሱ አገልግሎቱን አደረገ ፤ እጆቹን በእነርሱ ላይ አስቀመጠ መንፈስ ቅዱስም በእነርሱ ላይ መጣ በሌላም ቐንቐ እና ትንቢትን መናገር ጀመሩ (ሐዋ 19፡ 6-7) ፡፡ የጥሪአችን አካል ከእነዚህ ጋር መጎአዝና ኃማኖቱን ነጻ ማድረግ ነው ፤ በዚህ ነገር ጳዉሎስ ጊዜ ኢንቨስት በማድረጉ ምክንያት 12 ሰዎች አድሱን ኪዳን ለመለመድ አገኙት ፡፡

የሪቫይቭ ት/ቤት ለመጀመር የመራን ይህ ክስተት ነበር ይህ ምሳሌ ዉይይት ማድረግ እና ስለ እግዚአብሄር መንግስት በመማር በትይራኑስ ማስተማሪያ አደራሽ ላይ ለሁለት አመት በየቀኑ በማጥናት (ሐዋ 9፡ 10) በዚህ ምክንያት በመላዉ ኤሲያ፣ በአይሁድና በግሪክ በሁለቱም የኢየሱስን መልዕክት መስማት ችለዋል ፡፡

መዝጊያ

ወንጌል ለቀረጥ ሰብሳቢዎች እና ለኃጢዓተኞች የሚያስፈልግ ነው ፤ ወንጌል ለአይሁድና ለአህዛብ የሚያስፈልግ ነው፡፡ ለራሳችን አድሱን አቁማዳ መያዝ የለብንም ነገር ግን በዚህ ምክንያት ሁሉም ስለ እግዚአብሄር የመስማት እና ከኃያማኖት ባርነት ነጻ የመሆን እድል አላቸው ፡፡ በቐሚነት አይነት የእግዚአብሄርን ቃል በምታነቡ ጊዜ መላዉ ማህበረሰባችሁ እንደሚቀየር እናምናለን ፡፡

  1. Kent D. Berghuis, Christian Fasting: A Theological Approach (Dallas: Biblical Studies Press, 2007), p. 4.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 1999), p. 1157.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1139.

ጥያቄዎች

  1. በማቴዎስ 9 በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ጥቅሶች ዉስጥ ኢየሱስ ኃጢዓትን ይቅር የማለት ስልጣን እንደነበረው እንዴት አድርጎ አሳያ ?
  2. በማቴ (9፡ 9) ኢየሱስ እንዲከተለው ማቴዎስን ጠራው ተከተለውም ፤ ኢየሱስን እንድትከተሉ ጥሪያችሁ መቼ ነበር ? ማቴዎስ እንዳደረገው ወዲያዉኑ በመታዘዝ መለሳችሁ ወይስ ለጊዜው ተቃወማችሁ ?
  3. ኢየሱስ ከቀረጥ ሰብሳቢዎች እና ኃጢዓተኞች ጋር እራት በሚበላበት ጊዜ በማን ነበር የተተቸው ? ለጥያቄአቸው ኢየሱስ እንዴት መለሰላቸው ?
  4. በቁጥር 13 ማቴዎስ ሆሴ (6፡ 6) ጠቀሰ ፤ የእግዚአብሄር ሰዎች በመስዋዕት ህጉ ቀጥለዉ ነበር ነገር ግን የእግዚአብሄር እና የእዉነት እዉቀት ተሰጥቶአቸው ነበር (ሆሴ 4፡ 1) ፡፡ ኃይማኖተኞች የሆኑ በእንቅስቃሴ የሚሄዱ ነገር ግን በእግዚአብሄር ወይም በእዉነት የማይሄዱ ሰዎች ታውቃላችሁ ? (ሮሜ 1፡ 21-25)
  5. ኢየሱስ ስለ ልብሱ እና ስለ አቁማዳው የተጠቀመዉን ማሳያ በእነዚህ ቁጥሮች አድስ ለሆነ ሰው እንዴት ትገልፁለታላችሁ ? (ማቴ 9፡ 16-17; 2ቆሮ 5፡ 17)
  6. ኢየሱስ የፈወሳቸውን ሁለቱን እዉሮች የሆነዉን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው ፤ ለምን ያን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ?
  7. ስለ ሰዎች መሰበር በሰማችሁ ወይም የመጀመሪያ እገዛን በምስክር በሰማችሁ ጊዜ ኢየሱስ እንዳደረገው ርህራሄ ይሰማችኋል (ማቴ 9፡ 36) ? ወደ መኸሩ ሰራተኞችን እንዲልክ ለእግዚአብሄር ስለ መፅለይ አስባችኋል ? እናንተን መለካ እንደሚፈልግ ተረድታችሁታል ?
  8. በማቴዎስ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ መንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ፡፡

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Matthew 9:36

“When He saw the crowds, He felt compassion for them, because they were weary and worn out, like sheep without a shepherd.”

ኢየሱስ የምስራችን እየሰበከ እና በህዝብ ውስጥ ያለውን ሀመም እና ደዌ እየፈወሰ በከተሞች እና በመንደሮች መዞሩን ቀጠለ፡፡ ኢየሱስም ወደ ውጭ ሲወጣ የህዝቡን ብዛት አይቶ አዘነላቸው፡፡

በክርስቶስ እንደሚያምን ሰው፥ በዙሪያችሁ ላሉት ሰዎች የኢየሱስ ፍቅር ናችሁ፡፡ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰዎች እና ፍላጎቶቻቸውን ታያላችሁ? ወይስ በስራ ወደተጠመዳችሁበት ቀጣይ ዝግጅት መንገዳጅሁን በማቅናት በፍጥነት አልፋችሁአቸው ተሄዳላችው? መንፈስ ቅዱስ መንገዳችሁን እንዲመራ እየፀለያችሁ በእውነት ሰዎችን ለማየት አይኖቻችሁን ክፈቱ፡፡ ጌታ አንድን ሰው ወደ ትኩረታችሁ ሲያመጣ ምን ይሰማችሁአል? ኢየሱስ ለደከሙት እና ለዛሉት ርህራሄ ይሰማው ነበር፡፡ እናንተስ ይሰማችኋል ወይስ እራሳቸውን መንከባከብ ይችላሉ ብሎ በማመን አሊያም ሌሎች ይረዱአቸዋል ብሎ ተስፋ በማድረግ አልፋችኋቸው ትሄዳላችሁ?

ሰዎች የተበላሹ ናቸው ነገርግን እንደ ክርስቶስ ተከታይ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰዎች ልታዩ፣ ስለነሱ ሊሰማችሁ እና ልትወዷቸው ይገባል፡፡ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ መከሩ ብዙ ስለሆነ የመከሩ ጌታ ወደ መከሩ ብዙ ሰራተኞችን እንዲልክ እንዲፀልዩ ተናግሯል፡፡ ዛሬ፥ እናንተ ለኢየሱስ ፀሎት መልስ መሆን ትችላላችሁ፡፡ እየተጎዱ ያሉን ሰዎች ላማየት አይኖቻችሁን ክፈቱ፥ ስለነሱ ርህራሄ ተሰምቶአቸሁ የኢየሱን ፍቅር ወደ ተግባር ለውጡ፡፡

“ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።”

— የማቴዎስ ወንጌል 9:36

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ዘካርያስ 7:9-10 — "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፤ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፤"

የማቴዎስ ወንጌል 9:37-38 — “”በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤"

ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:12 — “እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 9