Jesus' Instructions For His Apostles
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King Matthew 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለማቴዎስ መፅሀፍ የምንጠቀመው አንድ ቃል ንጉስ ነው ፡፡ በማቴዎስ 10 የንጉሱን አምባሳደሮች ጅማሬ እናያለን ፤ የአምባሳደር ሚና ሄዶ የንጉሱን ስራ መስራት ነው ፡፡ ኢሳ (6፡ 8) የሚለው “ የጌታንም ድምፅ ማንን እልካለሁ ? ማንስ ይሄድልናል ? ሲል ሰማሁ ፡፡ እኔም እነሆኝ እኔን ላከኝ አልጉ ፡፡” ይህ የማቴዎስ 10 መነሻ ነው ፡፡
ትምህርት
ማቴዎስ(10፡ 1-4)፡ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን በአንድ ላይ ሰብስቦ “ በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምን ሁል እንዲፈዉሱ “ስልጣን ሰጣቸው (ቁጥር 1) ፤ ሁሉም 12ቱም ደቀመዛሙርት ነበሩ በተሰጣቸዉ ስልጣናቸዉና አሳይመንት ሐዋሪያት ሆኑ ፡፡ ማክአርቱር የሚለው “ ደቀመዛሙር ማለት በሌላ የተመራ ተማሪ ማለት ነው ፤ ሐዋሪያ በተልዕኮው ለላካዉ የበቃ(የጠራ) ተወካይነትን ይገልፃል ፡፡ “
በቁጥር 10 ኢየሱስ ተግባሩን እንዲሰሩ ደቀመዛሙርቱን ለመላክ እያዘጋጃቸው ነበር ፤ ይህ አገልግሎቱን እንዲሰሩ ለ 12ቱ ደቀመዛሙርት የድርጊት እቅድ ነበር ፡፡ እንዴት አድርገው ደቀመዛሙርቱ ስልጣን ተቀበሉ ? ኢየሱስ ለመስጠት ስልጣን ነበረው ፡፡ እዚህ ጋር ለሌሎች ስልጣን የሰጠ መሪ እስካሁን አልነበረም ፡፡ ማክአርቱር የገለፀው ይህ ስልጣን ተሰጥቶ የነበረው ምክንያት ደቀመዛሙርቱ/ሐዋሪያቱ “ የመሲሁን መድረስ እንዲያሳዉቁና እንዲያረጋግጡት ሲደመር ወንጌሉን የሚሰብኩ ሐዋሪያቶች መሆን እንዲችሉ “ ነበር ፡፡ ሁሉንም ርኩስ መናፍስት እንዲያስወጡና ሁሉንም በሽታና ህመም እንዲፈዉሱ ነገራቸው ፤ ኢየሱስ ለመንግስቱ መጀመር እያዘጋጃቸው ነበር ፡፡
ማቴዎስ የ12ቱን ደቀመዛሙርት ስም ሰጥቶአል ሁልጊዜም በጥንድ ዘርዝሮአቸዋል ፤ የሁል ቀን ሰዎች ነበሩ ፡፡ መጀመሪያ ስምዖንና ወንድሙ እንድሪያስ ፤ ቀጣይ የነበሩት ደግሞ ወንድማማቾች የነበሩት የዘብድዮስ ልጆች ተብለዉ የተጠሩት ያዕቆብና ዮሐንስ ነበሩ ፤ ሁሉም እነዚህ አራቱም የኢየሱስ ቅርብ እና አሳ አጥማጆች ነበሩ ፡፡ ቀጣይ ማቴዎስ ፊሊጶስን እና በርተሎሜዎስን ጠቀሰ ከዚያም በመቀጠል ቶማስና ማቴዎስ ቀረጥ ሰብሳቢዉ( ራሱ ፀሀፊው) ፡፡ አንዳንድ ምሁራን ማቴዎስና የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ ወንድማማቾች እንደነበሩ ይጠቅሳሉ(ያመለክታሉ)፡፡ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ ሌላዉ ስሙ ይሁዳ ከነበረው ከታዴዎስ ጋር ተጠቅሶዓል ፤ ታዲዎስ የሚለውን ስም ለመጠቀም ሳይመርጥ ስላልቀረ ከአስቆርቱ ይሁዳ ጋር ግራ የሚያጋባ አይሆንም ፡፡ በመጨረሻም ቀናተኛው ስምዖንና(ምክንያቱም የቀድሞው ቀነዓኒዊያን ፓለቲካ አባል ዉስጥ ነበረ) አስቆርቱ ይሁዳ ፡፡
ማቴዎስ(10፡ 5-15)፡ ቁጥር 5 የሚለው፡ “ ኢየሱስ ትዕዛዝ ከሰጣቸዉ ቦኃላ እነዚህን 12ቱን ላካቸው “ ፤ ከላይ እንደጠቀስናቸዉ በጥንድ ተላኩ ፡፡ ትዕዛዞቹ(የጨዋታዉ ዕቅዶች) በቀረዉ የማቴዎስ 10 ዉስጥ ቀጥለዋል፡፡
ትዕዛዞቹ ያካተቱት፡
- በአድማጮቹ አይሁዶች ላይ ያተኩራሉ - “ የእስራኤል የጠፋው በግ “ የሌላ ህዝብ ወይም የሰማራዊ አይደለም (ኤር 50፡ 6; ማቴ 15፡ 24; ዮሐ 4፡ 22; ሮሜ 1፡ 16) ፡፡
ሄደው የእግዚአብሄር መንግስት ቅርብ ነዉ የሚለውን ማሳወቅ ማክአርቱር “ የሰማይ መንግስትን” “ የእርሱ በሆኑት ላይ የእግዚአብሄር የበላይነት(አገዛዝ) እንደሚሰራ ፤ መንግስቱ አሁን በአማዮች ልብ ላይ በሰማያዊ መንፈሳዊ መሪነት የተገለጠ ነው አንድ ቀን በግልፅ በምድራዊ መንግስት የሚመሰረት እንደሚሆን “ በመጥቀስ ገልፃታል ፤ ራዕ (20፡ 4-6) ፡፡ ኃላፊነቱ “ መሄድ “ የሚለውን ያካትታል ፤ ፕለመር ይህን ያለው፡
“ ኃላፊነቱ “ ለመስበክ መሄዳችሁ “ የዚህ አቅጣጫዎች ሌላው የጊዜያዊ ባህሪያ ማመላከቻ ነው ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመንቀሳቀስ “ የመስክ ሰባኪዎች “ አሉ ፡፡ ቐሚ ድርጅት የሚሞከር አይደለም ፤ ሁሉም በጎች የተበታተኑ ናቸው የመጀመሪያው ነገር ለእረኛዉ ፍላጎት በእነርሱ ለማንቃት ነው ፡፡ ዝግጁ ከሆኑ መሲሁና መንግስቱ ዝግጁ ናቸው ፡፡ “
አንድ ማብራሪያ ያነበብኩት እነዚህ 12ቱ ሰዎች በእስራኤል መሪዎች እንደሆኑ አመልክቶአል ነገር ግን በዚያ ፈንታ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሆነዋል ፡፡
በማቴዎስ(10፡ 5-6) ለክርስቶስ አምባሳደሮች- ለደቀመዛሙርቱ/ለሐዋሪያቱ በበጎቹ ምላሽ መሰረት የእግዚአብሄር መንግስት ይደርሳል ፡፡በማቴዎስ 10 እና በማቴዎስ 28 ሂደት መሀከል አይሁዶች አቅርቦቱን አልተቀበሉም ፤ በመቀጠል በማቴዎስ 28፡ 18-20 ትኩርቱ ተቀየረ፡
“ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው ስልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኃቸው ያዘዝኃችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኃቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጎአቸው እነሆም እኔ እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ፡፡”
ኢየሱስ የጨዋታውን እቅድ እንደቀየረው ይሰማል ነገር ግን አሁንም ከሁሉም ስልጣን ጋር ነው ፤ የንጉሱ አምባሳደሮች በሰፊዉ ይዘት አሳይመንት ተሰጥቶአቸዋል፡ “ ሁሉንም አህዛብ ደቀመዝሙር እንዲያደርጉ ፡፡“ ዘካ(12፡ 10) የሚለው፡
“ በዳዊትም ቤት ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ ፤ ሰዉም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል ሰዉም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኃዘን ያዝኑለታል ፡፡ “
የኢየሱስ ተልዕኮ ዙሪያዉን ሙሉ እንደሚመጣ እናም ያ የአይሁድ ሰዎች ወንጌልን ቢገፉትም እንካን በመጨረሻ ምን እንደገፉ እንደሚያቁ የእግዚአብሄር ተስፋ ነው ፡፡
በቁጥር 8 ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ያለ ክፍያ የተማመን እንዲፈዉሱ፣ የሞተ እንዲያስነሱ ክፉዉን እንዲያስወጡ ነገራቸው ፤ ስንቲሞችን ወይም ጠገንዘብ ከረጢት እንካን አይሸከሙም ነበር ፡፡ ሉቃ (22፡ 36) ይህ የሚፃረር ይመስላል፡ “ እርሱም አሁን ግን ኮረጆ ያለው ከእርሱ ጋር ይዉሰድ ከረጢትም ያለዉ እንዲሁ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ ፡፡ “ ይህ ልዩነት አድማጭ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ልዩነቱን ገልፆአል፡
“ የደቀመዛሙርቱ ተልዕኮ የአጭር ጊዜ ነበር ፤ ያ ማለት ለኢየሱስ እንደ መሲህ የህዝቡን ምላሽ ለመለየት ሀገራዊ ኃይማኖታዊ ጥናት ያደርጋሉ ፡፡ ለ12 ደቀመዛሙርት በጣም ትልቅ የማይሆን ቢበዛ 75 በ125 ማይል አካባቢ ይሸፍናሉ ፤ ስለሆነም ሰፊ አቅርቦቶች አላስፈለጉዓቸውም ፡፡ “
ለሉቃ (22፡ 36) ኢየሱስ ሰዎቹን ለረጅም ጉዞ ላካቸው ከራሳቸዉ ህዛብ አካባቢ ዉጪ ይሆናል ፤ እንደተጎአዙ በእርዳታ እርግጠኛ መሆን አልቻሉም ፡፡
ማቴዎስ በዚህ ጉዞ ላይ በደህና ላልተቀበሉዓቸው፣ መምጣታቸዉ ጥሩ እንዳልሆነ እንዲሰማቸዉ ያደረጉዓቸው ወይም ለማዳመጥ ተቃዉሞን ላሰሙዓቸው “ የእግራቸዉን አቦአራ አራግፈው “ ከተማዋንና ቤቱን ትተው እንደሚወጡ መዝግቦዓል (ቁጥር 13-14) ፡፡
ዋይርስቤ የሚለው በአሁኑ ጊዜ መልዕክታችን መንግሰተ ሰማይ ቀርባለችና ሳይሆን ከዚያ ይልቅ ኢየሱስ ለኃጢዓታችን ሞቶአል ነው ፤ በማቴዎስ ከምዕራፍ 10 እስከ ምዕራፍ 28 መልዕክቱ “ መንግስተ ሰማይ እጃችን ላይ ናት “ ነበር ፤ ነገር ግን በማቴዎስ 28 ቅያሬ አለ እንደ ትኩረት በሁሉም ህዝብ ወደ ሁሉም ሰው የዞረ ነው ፡፡
መዝጊያ
በማቴዎስ 10 በጣም ብዙ አለ ፤ ላይ ላዩን አክከናል ፤ ነገር ግን ከዚህ ምዕራፍ የወሰድነው እንደ አምባሰደሮቹ ለመስራት ሁላችንም ስራ አለን ፡፡ እናም አንድ ቀን አለ ክርስቲያኖች በፍፁም የሚያስደንቅ ነገር የሚያዩበት ጊዜ - የአይሁድ ሰዎች ወደ መሲሁ ሲመለሱ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1140.
MacArthur, p. 1140.
MacArthur, p. 1124.
Alfred Plummer, An Exegetical Commentary on the Gospel According to S. Matthew (London: Robert Scott Roxburghe House, 1909), p. 149.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 1999), p. 1159.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Matthew––Galatians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 37.
ጥያቄዎች
-
“ በደቀ መዝሙር “ እና “ በሐዋሪያ “ መሀከል ያለዉ ልዩነት ምንድን ነው ? ራሳችሁን አንዱን ወይም ሌላውን ወያንም ደግሞ ሁለቱንም እንደምትሆኑ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
-
12 ደቀ መዛሙርት ወደ ምንድን የሰዎች ቡድን ተላኩ ? ወደ እነማንስ አልተላኩም (ማቴ 10፡ 5-6; 15፡ 24) ? ይህ ከማቴ (28፡ 18-20) እንዴት ነዉ የሚለየው ?
-
በማቴ (10፡ 6-8) እንደ ላካቸው 12ቱን እንዲያደርጉት ኢየሱስ ያዘዛቸው የተለዩ ነገሮች ምንድን ናቸው ? ዛሬስ ለእናንተ እነዚህ ነገሮች አሁንም ተግባራዊ ናቸው ? በእድሜአችሁ ከእነዚህ ነገሮች የሆነን(መሆንን) መስክራችችኋል (ምስክርነት አላችሁ) ?
-
በማቴ (10፡ 34) ኢየሱስ ያለው “ ….ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም “ ፤ ሰይፍ ምንድን ነው ? ይህ መግለጫ በዮሐ(14፡ 27 እና 16፡ 33) ስለ ሰላም ከኢየሱስ መግለጫ እንዴት ይለያል ?
-
በማቴ (10፡ 35-36) ቤተሰብን በቤተስ ላይ ማዞር(ማስነሳት) ማለት ምን ማለት ነው ? (ሚክ 7፡ 6; ማቴ 10፡ 37-39)
-
በማቴዎስ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Matthew 10:30-31
“But even the hairs of your head have all been counted. So, don’t be afraid therefore; you are worth more than many sparrows.”
ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን በስልጣን ካዘዛቸው በኋላ፥ ሶስት ጊዜ አላቸው፥
አትፍሩ፡፡ አትፈሩ፡፡ አትፍሩ፡፡
ዛሬም እናንተ በራሳችሁ ቀን ስትሄዱ ፥ ህይወታችሁን ለክርስቶስ ስትኖሩ ተመሳሳይ ሆኖ የሚቀጥለው ምን ይመስላችኋል? አትፍሩ፡፡ምንም የምትሉት ነገር የሌለ ሲመስላችሁ፥ ኢየሱስ የምትናገሩአቸውን ቃሎች ይሰጣችኋል፡፡ ኢየሱስ ሁሉንም ነገር ያካፍላችኋል ስለዚህ ምንም ነገር ከእናንተ አይደበቅም፡፡ ኢየሱስ ከምንም ከማንም በላይ ሀያል ነው፡፡ ኢየሱስ የፀጉራችሁን ቁጥር ያውቃል ደግሞም ከሚያስብላቸው ድንቢጦች በላይ ዋጋችሁ ታላቅ ነው፡፡ የእግዚያብሔር ልጅ ሆይ እግዚያብሔር ይወድሀል፡፡ ስለዚህ ዛሬ አትፍራ፡፡ በኢየሱስ ሙሉ ስልጣን አለህ፥ ተሰጥቶአልና፡፡ ሂድ፣ አትፍራ፡፡
"የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።"
የማቴዎስ ወንጌል 10:30-31
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ትንቢተ ኢሳይያስ 41:10— “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።"
መዝሙረ ዳዊት 56:3 — “እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ።”
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ1:7 — "እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በወንጌላት፡ ክፍል 10
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።